16/04/2026
!
!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው እና ልዩ አማካሪያቸው ንጉሴ አስረስ የሚመራው አምባገናዊነት የሕግ የበላይነት እየተሸረሸረ፣ የዜጎች መሠረታዊ መብት በባለሥልጣናት ፍላጎት ሥር እየወደቀ ይገኛል።
:- በቡታጅራ ከተማ ነዋሪ በሆኑት በአቶ ሐሰን ከድር ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ነው። አቶ ሐሰን ከድር ያላንዳች በቂ ምክንያትና የሕግ አግባብ ታስረው ለረጅም ጊዜ ሲንገላቱ ቆይተዋል።
አቶ ሐሰን ከድር:- ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የታሰሩበት መንገድ ከመነሻው ህገ-ወጥ የሆነ፣ ያለ መከሰስ መብታቸው ያልተነሳ መሆኑ፣ የቀረበባቸው ክስ መነሻ የሌለው መሆኑ ተረጋግጦ፣ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዲሰናበቱ ቢወሰንም፣ የሕግ የበላይነትን የማይቀበሉ አካላት ውሳኔውን ጥሰዋል።
አቶ ሃሰን ከድር:- ከፍርድ ቤት ነፃ ተብለው መውጣት ሲገባቸው፣ የትም ተደርጎ የማያቅ በባለ ሥልጣናት ቀጥተኛ ትዕዛዝ የሃይል እርምጃና እንግልት ዳግም ተይዘው እንዲታሰሩ ተደርጓል።
በሹማምንታት ግፍና ጭቆና እየደረሰባቸው ያለው አቶ ሐሰንን ከድር፣ አቶ ቶፊቅ አወል፣ አቶ ፈይሰል አወል እና አቶ ሸይቾ ኢብራሂም ከመኖሪያቸው ቡታጅራ ተነጥለው ወደ ሆሳና በመጫናቸው ምክንያት ለመጠየቅና ጉዳያቸውን ለመከታተል የሚሄዱ ቤተሰቦችና ወዳጆች ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸውና ላላስፈላጊ ወጪ እየተዳረጉ ይገኛል።
? አንድ ዜጋ በፍርድ ቤት ነፃ ከተባለ በኋላ በፖለቲካ ሹማምንት ትዕዛዝ ታፍኖ መወሰዱ "ከሕግ በላይ ነን" የሚሉ አካላት መኖራቸውን ያሳያል። ሕገ-መንግሥቱ የሚሰጠው መብት በተግባር ካልተከበረ ፍትሕ የት ትገኝ?
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በቡታጅራ ከተማ ነዋሪ በሆኑት በአቶ ሐሰን ከድር፣ በአቶ ቶፊቅ አወል፣ በአቶ ፈይሰል አወል እና ሸይቾ ኢብራሂም ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሕግ መጣስና እንግልት የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለማሳወቅ እንወዳለን።
#ጥሪያችን፦
1➧ የሚመለከታቸው የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አክብረው አቶ ሐሰን ከድርን በአስቸኳይ እንዲፈቱ።
2➧ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይህንን ሕገ-ወጥ ድርጊት እንዲከታተሉትና ድምፅ እንዲሆኑ።
3➧ ፍትሕ ወዳድ ዜጎች ሁሉ ይህንን ግፍ ለዓለም እንዲያሳውቁ ጥሪ እናቀርባለን።
!
!
!
የጭቁኑ የመስቃን ህዝብ ድምፅ!