ethio 24

ethio 24 በ ኢትዮ 24 ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከታማኝ ምንጮቻችን እምናገ

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 4 ደርሷል!የ75 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት በተጓዳኝ ህመም በሆስፒታል ውስጥ ተኝተው ሲታከሙ የነበሩ ሲሆን በገጠማቸው የመተንፈስ ችግር ምክንያት በኮሮና ቫይረስ በሽታ...
05/05/2020

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 4 ደርሷል!

የ75 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት በተጓዳኝ ህመም በሆስፒታል ውስጥ ተኝተው ሲታከሙ የነበሩ ሲሆን በገጠማቸው የመተንፈስ ችግር ምክንያት በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተጠርጥረው ምርመራ ናሙና ከተወሰደ በኃላ በምርመራ ውጤቱ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከመረጋገጡ በፊት ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።

05/05/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,047 ላቦራቶሪ ምርመራ አምስት (5) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ አርባ አምስት (145) ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ75 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት በመጣራት ላይ ያለ (በጤና ተቋም ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን ከተወሰደ ናሙና የተገኘ)

ታማሚ 2 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ የመኖሪያ ቦታ አፋር ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 3 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ የመኖሪያ ቦታ አፋር ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 4 - የ8 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #ያላት።

ታማሚ 5 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊት የመኖሪያ ቦታ ኦሮሚያ፣ ባቱ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #ያላት።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት 16 ሰዎች (15 ከአዲስ አበባ እና 1 ከአማራ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና አንድ (91) ደርሷል።

05/05/2020

አጫጭር መረጃዎች ፦

- በኒውዚላንድ ለሁለተኛ ቀን በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ዜጋ አልተገኘም ተብሏል። ኒው ዚላንድ ጥላ የነበረውን ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብም እያላላች ትገኛለች -

- በቻይና ባለፉት 24 ሰዓት 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙን ሪፖርት አድርጋለች። በሌላ በኩል በሀገሪቱ ለስምንተኛ ተከታታይ ቀን ሞት አልተመዘገበም።

- በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዘ ዝቅተኛው የሞት መጠን ተመዝግቧል፤ የሟቾች ቁጥር 1015 ሲሆን ይህም ከአንድ ወር በኋላ ዝቅተኛው ነው -

- ባለፉት 24 ሰዓት በደቡብ ኮሪያ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ሁሉም ከውጭ ሀገር የገቡ ናቸው (በሀገር ውስጥ ቫይረሱ ሳይገኝ ሁለት ቀን ሆኖታል)

- ካምቦዲያ ባለፉት 3 ሳምንታት በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው ስለመኖሩ ሪፖርት አላደረገችም። ካምቦዲያ በቫይረሱ ከተያዙ 122 ሰዎች 120ዎቹ በፍጥነት እንዲያገግሙ በመርዳት አመርቂ ውጤት አስመዝግባለች-

- ደቡብ አፍሪካ በትላንትናው ዕለት ብቻ 437 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጋለች። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 7,220 ደርሷል።

- ናይጄሪያ በአንድ ቀን ከፍተኛ ነው የተባለለትን በኮቪድ-19 የተያዘ የሰው ቁጥር ሪፖርት አድርጋለች፤ ባለፉት 24 ሰዓት 245 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 2,802 ደርሰዋል።

05/05/2020

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 24,088
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 1,758
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 5
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 60
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 0
• አጠቃላይ ያገገሙ - 75
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 140

የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ወሰነ!የህወሓት  ስራ  አስፈፃሚ  ኮሚቴ  ዛሬ  ምሽት ባወጣው  መግለጫ ከትግራይ ህዝብና ለትግራይ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር...
05/05/2020

የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ወሰነ!

የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ከትግራይ ህዝብና ለትግራይ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ሙሉ እውቅና ከሚሰጡ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በመሆን ክልላዊ ምርጫን ጨምሮ የህዝቡን መብት ከትርምስ ለመታደግ የሚያስችሉ ሥራዎችን በክልል ደረጃ ለማድረግ ዝግጅት እንዲደረግ መወሰኑን አሳውቋል፡፡

የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይህ እንቅስቃሴ የፀረ ኮረና (ኮቪድ-19) ዘመቻዎችን እንዲሁም ተቀባይነት ያላቸውን ህገ-መንግስታዊ መርሆዎችን ባሟላ መልኩ የሚፈፀም ይሆናልም ብሏል።

ከላይ ያለውን ውሳኔ ጨምሮ ሌሎች በህወሓት የማእከላይ ኮሚቴ የተላለፉ ውሳኔዎችን ይህን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ https://telegra.ph/TPLF-05-04

04/05/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,758 ላቦራቶሪ ምርመራ አምስት (5) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ አርባ (140) ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከፑንትላንድ የተመለሰና በጅግጅጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 2 - የ23 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከፑንትላንድ የተመለሰና በጅግጅጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 3 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከፑንትላንድ የተመለሰና በጅግጅጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 4 - የ17 ዓመት ኢትዮጵያዊ የባህር ዳር ነዋሪ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #ያለው።

ታማሚ 5 - የ19 ዓመት ስዊድናዊ (ትውልደ ኢትዮጵያዊ) ፤ ከስዊድን የተመለሰና በአዲስ አበባ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,560 ላቦራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን...
03/05/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,560 ላቦራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 135 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ49 ዓመት ኢትዮጵያዊ የባቱ /ዝዋይ/ ነዋሪ አዲስ አበባ ህክምና በመከታተል ላይ ያለ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የለውም (በጤና ተቋም ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን ከተወሰደ ናሙና የተገኘ)

ታማሚ 2 - የ45 ዓመት ኢትዮጵያዊት የስልጢ ወረዳ፣ ስልጤ ዞን ነዋሪ (ደቡብ ክልል) ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የላትም (በቤት ለቤት ቅኝት እና አሰሳ የተለየች)

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ስድስት (6) ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ሰባ አምስት (75) ደርሷል።

የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,112፣ ሞት 2፣ ያገገሙ 686- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 435፣ ሞት 22፣ ያገገሙ...
03/05/2020

የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,112፣ ሞት 2፣ ያገገሙ 686

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 435፣ ሞት 22፣ ያገገሙ 152

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 671፣ ሞት 31፣ ያገገሙ 34

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 533፣ ሞት 36፣ ያገገሙ 46

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 133፣ ሞት 3፣ ያገገሙ 69

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 45፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 0

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 26

አጫጭር መረጃዎች ፦- በዩናይትድ ኪንግደም የሟቾች ቁጥር 28,131 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ621 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። በሌላ በኩል በአንድ ቀን 4,806 ሰዎች በቫይረሱ መያዛ...
03/05/2020

አጫጭር መረጃዎች ፦

- በዩናይትድ ኪንግደም የሟቾች ቁጥር 28,131 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ621 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። በሌላ በኩል በአንድ ቀን 4,806 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት በኳታር 776 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 14,872 ደርሰዋል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 474 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። በሌላ በኩል 1,900 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በቱርክ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 124,375 ደርሰዋል፤ በአንድ ቀን 1,983 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የሟቾች ቁጥር በ78 ጨምሮ በአጠቃላይ 3,336 ሆኖ ተመዝግቧል።

- ግብፅ በዛሬው ዕለት 298 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 6,193 ደርሷል።

- በጋና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 2,169 ደርሰዋል፤ ባለፉት 24 ሰዓት 95 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 88% በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ግልፅ የሆነ የጉዞ ታሪክ የላቸውም ብሏል።

- በAfricaCDC መረጃ መሰረት በአፍሪካ 1,701 ሰዎች ሞተዋል፤ 41,330 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 13,621 አገግመዋል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ የሟቾች ቁጥር ከ243,024 ደርሷል፤ 1,102,551 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 3,456,207 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ሳቢያ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ዕርዳታ ጠባቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ የፋይናንስ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ መናገራቸው DW ዘግቧል።ሚኒስትሩ እንዳሉት በዚህ ሳቢ...
03/05/2020

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ሳቢያ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ዕርዳታ ጠባቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ የፋይናንስ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ መናገራቸው DW ዘግቧል።

ሚኒስትሩ እንዳሉት በዚህ ሳቢያ በአገሪቱ ዕርዳታ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በአጠቃላይ ወደ 30 ሚሊዮን ያሻቅባል።

መንግስት የኮሮና ወረሽኝን ለመከላከል ያቋቋመው የምኒስትሮች ኮሚቴ በትናንትናው ዕለት ባደረገው እና ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በመሩት ውይይት ለዚህ ብቻ ኢትዮጵያ 1.4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ገልጸዋል።

የኮሮና ወረርሽኝን ለመቋቋም ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት፣ ከአውሮፓ ኅብረት፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታኒያ እና ቻይና 2.1 ቢሊዮን ዶላር ዕገዛ መጠየቋን አቶ አሕመድ ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር በቅርቡ ለኢትዮጵያ ሊሰጥ እንደሚችል ጠቁመዋል።

በትናንትናው ዕለት የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ጫና ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የ411 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ አጽድቋል። የዓለም ባንክ በበኩሉ 750 ሚሊዮን ዶላር የበጀት ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚችል የፋይናንስ ሚኒስትሩ አስረድተዋል -
ምንጭ-DW

በአሁኑ ወቅት አገሪቱ 27 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የለይቶ ማቆያ ማዕከል ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ሲሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያም ገልጸዋል፡፡...
03/05/2020

በአሁኑ ወቅት አገሪቱ 27 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የለይቶ ማቆያ ማዕከል ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ሲሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያም ገልጸዋል፡፡ በእነዚህም ከ9ሺህ በላይ ዜጎችን በማቆያው ውስጥ መሆናቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

በቀጣይ ሁኔታዎች እየታዩ ዩኒቨርሲቲዎቹ 90 ሺህ ሰዎችን በለይቶ ማቆያነት እንዲይዙ ለማስቻል የማዘጋጀት ሥራ መሰራቱንና ከማቆያነት ባሻገርም ጊዜያዊ የመመርመሪያ ጣቢያ ሆነው እንዲያገለግሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል
ምንጭ-ENA

በግብፅ  በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ ምርመራ በ358 ሰዎች በኮሮና COVID-19 መያዛቸውን   ዘግቧል፡፡ ይህም በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 5 ሺህ 895 አድርሶታል፡፡...
02/05/2020

በግብፅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ ምርመራ በ358 ሰዎች በኮሮና COVID-19 መያዛቸውን ዘግቧል፡፡ ይህም በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 5 ሺህ 895 አድርሶታል፡፡

የጤና ሚንስቴር ቃል አቀባይ ካሊድ መጋህድ እንደገለጹት በ24 ሰዓታቱ 14 ታማሚዎች ሕይወት አልፏል ፤ ይህም በግብፅ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 406 አድርሶታል ብለዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ 79 ሰዎች ማገገማቸውና ከሆስፒታል መውጣታቸው ነው የተነገረው፡፡

Address

Ethiopia, Addis Abeba
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ethio 24 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ethio 24:

Share