Abdulmejid Abdi

Abdulmejid Abdi Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abdulmejid Abdi, Advertising/Marketing, Addis Ababa.

09/11/2020

የጃዋር መሀመድ የእስር ቤት ውሎ!****
ሁሌም ጠዋት ላይ ከፀሐይ በላይ ፈክቶ በፈገግታ ቀኑን ይጀምራል! በዙሪያው ያሉ የመንግስት ጠባቂዎች ትንሽ ፈገግ የሚሉት ጃዋርን ካዩ በኋላ ነው!! በጣም ያቀርባቸዋል እነርሱም በጣም ይወዱታል! ሁሌም ይመክራቸዋል! በማንም ላይ ክፉ እንዳትሆኑ! ማንንም እንዳትበድሉ! ይህ ስራችሁ ነው ስራችሁን በታማኝነት ስሩ! ከማንም ጋር ግን በወገናዊነት አትቁሙ!!
****
አንዳንዶቹ ጃዋር መናገር ሲጀምር ይፈዛሉ! በጣም በጣም ይወዱታል! ጃዋር በየቀኑ ብዙ መፀሀፍት ስለሚያነብ ካነበበው ያካፍላቸዋል! ስለ ህግ ፤ ስለ ህብረ ብሄራዊነት ስለ ሀላፊነትን መወጣት ፤ ህብረ ብሄራዊ እና ዲሞክራሲን እንዴት አንድ ላይ ስለማስኬድ በቀን በቀን ይነግራቸዋል!
****
ጠባቂዎቹ ነግቶ አዲስ ነገር እስከሚያወራቸው ይጓጓሉ!! ውጪ ላይ ስላለው የፖለቲካ ሙቀት ብዙም አትገረሙ ይላቸዋል! ለሚመጣው ዘመን እራሳችሁን አዘጋጁ! ይህ እኔ የማልፍበት መንገድ የግድ ነው! ያልጨረስኳቸው ብዙ የማነባቸው የምፅፋቸው ብዙ መፀሐፎች ነበሩ!! እነሱን የምጨርስበት ጊዜ ነው! እያለ ይመክራቸዋል!
****
የጠባቂው እረጅሙ ጥያቄ ****
ከጠባቂዎቹ መካከል አንዱ ቆይ በዚህን ያህል ተስፋኛ እና ህልመኛ የሆንከው እንዴት ነው? ይሄስ ቀን እንደሚያልፍ እንዴት አውቀህ ነው? ገና አልተፈረደብህም! ከዚህ በኋላ ፍርድ አለ! ከዚያም በኋላ የተፈረደብህን መጨረስ አለ! ምናልባት ከየትኛውም የፖለቲካ መድረክ ልትታገት ሁሉ ትችላለህ ታዲያ ይህ ሁሉ እየጠበቀህ እንዴት እርግጠኛ ሆነህ ስለ ነገ ታስባለህ? ብሎ ጠየቀው!
***
የጃዋር እረጅሙ መልስ****
ጃዋርም አየህ ሽንፈት የሚጀምረው ተስፋ ከመቁረጥ ነው! እኔ ወጣትነቴን ፤ እድሜዪን ሁሉ የጨረስኩት በትግል ነው! ትግል የጀመርኩት ገና ህፃን እያለሁ ነው! በአካባቢዬ ከማየው በደል፤ ጭቆና ፤ ግፍ ተነስቼ ነው ትግል ውስጥ የገባሁት!! በእድሜ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበሰልኩኝ ስመጣ ግን ለምን መታገል እንዳለብኝ ገባኝ!!
****
የመጀመሪያው ትግሌ ለጭቁኑ የኦሮሞ ህዝብ ነው!! የኦሮሞ ህዝብ በገዛ ሀገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሮ ለዘመናት ኖሯል! አንድ ሰው ኦሮሞ ነኝ ብሎ መናገር እስኪሸማቀቅ ደረስ በኦሮሞነቱ አፍሯል! አስታውሳለሁ እኔ የ ኢለመንተሪ ተማሪ ሆኜ ቀልቤቻ መገርሳ የሚባል ተማሪ ነበር በስሙ ሲያሾፉበት ትምህርት አቆመ! አንድ ልጨምርልህ አያንቱ ጉታ የምትባል ተማሪ ነበረች በስሟ ብቻ ሲያሸማቅቋት ነበር! ሌላውን በደል እና ግፍ አላነሳውም ምክንያቱም አይጠቅምም!! አሁን የኋላችንን እየጣልን የፊታችንን ማንሳት ነው!! ቂም እና በቀል ውጤቱን አይተነዋል ይሄ የትም አያደርሰንም!!
****
ወደ ጫወታዬ ስመለስልህ ይሄንን እያየሁ እየሰማሁ ነው ያደኩት! ከዛን ጊዜ ጀምሮ ነበር ትግል ውስጤ የገባው ታዲያ እንዴት መታገል እንዳለብኝ አላውቅም ነበር! ወደ ውጪ ሀገር ከወጣሁ በኋላ እየታገልኩኝ በጣም እማር ነበር አንድም ቀን ተስፋ ቆርጬ አላውቅም ይህ ቀን ግን እደሚመጣ አውቅ ነበር! ከትግሌ ሁሉ ትልቁ ትግል ግን መለስ ዜናዊን የታገልኩት እና ኢህያዲግን ያሸነፍክበት ትግል ትልቁ ትግሌ ነው!!
****
ሌላውን ወደፊት በምፅፈው መፀሀፊ ላይ እተርከዋለሁ አሁን ግን ስለ ቄሮ ትግል ልንገርህ የቄሮ ትግል በ 21ኛ ክፍለዘመን በ 1 ላብቶፕ ብቻ ሚሳኤልን መትረየስን ተዋጊ ጀቶችን ሁሉ የማረክንበት አንዱ ታንኬ ነበር!! ታዲያ ማንም አልሞተም አልልህም ከ 5000 በላይ ቄሮ የተሰዋበት ትግል ነው!
****
ይህ ትግል ዛሬ ላይ ሙሉ በሙሉ ቢቀለበስም ለመቀልበሱ ደግሞ ትልቁን ሀላፊነት የምወስደው እኔ ነኝ! ተጠያቂውም እኔ ነኝ እኔ በባህሪዬ ገራገር እና ሰው አማኝ ነኝ ታዲያ በቄሮ ትግል ጊዜ ያመንኳቸው ሁሉ ዛሬ ላይ ከዱኝ! ግማሹ ከእኔ ጋር እስር ቤት ነው ግማሹ በቤቱ እስር ላይ ነው ግማሹ በጥቅም ባሪያ ሆኗል! ለዚህም ጥፋቱ የእኔ ነው የምለው ማንንም ማመን አልነበረብኝም!!
****
ያመናቸው ሰዎች ትግሉን ከቄሮ ቀልብሰው የራሳቸው አደረጉት! እኛንም አታለሉን እኛም መታለላችን ገባን ታዲያ ያታለሉን ሰዎች ቄሮን ብቻ ሳይሆን መላው ሀገሪቱን ሙሉ በሙሉ እንዳታለሉ ገባኝ! በዚህ ጊዜ ነበር ከ አክቲቪስትነት ወደ ፖለቲካኛነት የገባሁት!! ወደ ፖለቲካው ግን ስገባ ሙሉ በሙሉ ስለ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለመላው ጭቁን ፤ ለተታለለው ፤ ለተጭበረበረው ፤ ለተሰረቀው ፤ ኢትዮጵያዎ ሁሉ መቆም እንዳለብኝ ተሰማኝ!!
****
ይሄኔ ብዙ ተቀባይነት አኘሁ የብዙ ሰው ልብ ውስጥ መግባት ጀመርኩኝ ማንም ፖለቲከኛ ያልገባበት ቀበሌ ገጠር እየሄድኩኝ የህዝቡን ኑሮ ስመለከት የባሰ ልቤ ተነካ የባሰ አዘንኩኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈጣሪ ለዚህ ህዝብ መፍትሄ አድርጎ የጠረኝ መስሎ ተሰማኝ!! ለራሴው ቃል ገባሁ ለዚህ ድሀ ህዝብ ድምፅ እንደምሆነው አመንኩኝ!!
****
በዚህ ጉዞ ላይ ነው እንግዲህ ከሀዲያን ድራማቸውን መስራት የጀመሩት! እኔ እድሜዪን ሙሉ ስታገል ቀጥታ እንጂ ድራማ ሰርቼ አላውቅም የፖለቲካ ድራማ እንደ ህፃናት እቃ እቃ ነው!! መጀመሪያ ሁሉ ነገር እውነት ይመስልሀል ልክ ሲመሽ ሁሉም ወደቤቱ ሲገባ እቃቃነቱ እንደሚፈርስ የፖለቲካም እቃቃ ነገሮች ሲለወጡ ቀን ሲመሽብህ ድራማው ይገባሀል!!
****
የድራማው ተዋኒያን አሁን ስልጣን ላይ ያሉት የብልፅግና መሪዎች እና በጥቅም የተደለሉ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች ቄሮዎች ፤ እንዲሁም ከፍተኛ የአማራ ባለስልጣናት ናቸው ሁሉም ድራማውን እየተወኑ በዚህ ድራማ ንፁሐን እያለቁ ለታሪክ የሚቀር ትልቅ ጠባሳ እየጣሉ ነው!! ህዝብ አሁን ላይ ላይነቃ ይችላል! መንቃቱ ግን አይቀርም ያኔ መግቢያ ቀዳዳ እስከሚጠፋ ጭንቅ ይሆናል!
****
ይቅርታ ጫወታህ ስለማረከኝ ነው አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ? አለው ጠባቁው ፖሊስ?****
ምን መሄዳ አለኝ ጠይቀኝ አለ ጃዋር!*****
እንደው የሚፀፅትህ የሚቆጭህ ይሄ ባይሆን ኖሮ ብለክ የምትብሰለሰልበት ሁሌም ልብህ ውስጥ ገብቶ ከልብህ የማይወጣ ነገር አለ? ካለ ምንድነው?****
ጃዋር ሲመልስ!****
ልታስለቅሰኝ ነው? እ እ እ አዎ ብዙ የምፀፀትበት ነገሮች ያን ያህል የሉም ምክንያቱም በትግል ውስጥ ጥሩንም መጥፎንም ነገር የሚቀበል ጫናቃ ይዘህ ነው መግባት ያለብህ ቢሆንም ግን ያላሰብከው ነገር ያልገመትከው ነገር ጭራሽ ይሆናል ብለህ ለሰከንድ ያላሰብከው ነገር ሲሆን እና ሲፈጠር ግን ከልብህ የማይወጣ ቁጭት ከልብ የማይወጣ ሀዘን ሁሌም ባሰብከው ቁጥር የሚቆጭ ነገር አለ ይሄ መቼም ከልቤ አይጠፋም!!
****
እሱም ምን መሰለህ የ ሀጫሉ ሁንዴሳ መገደል! ትዝ ባለኝ ቁጥር ይቆጨኛል! ሀጩ ኪያ ይሄ አይገባውም ሀጩ እንደኛ አይደለም! ሀጩ የእውነት ታጋይ ነው! በዘፈኑ ብቻ ሚሊዮኖችን የማረከ ሚሊዮኖችን ያፈራ በሚሊዮኖች የሚወደድ ከአልማዝ ውስጥ ያለ ሌላ አልማዝ ከእንቁ ውስጥ ያለ እንቁ በምንም አይነት ዋጋ የማትተምነው ልዩ ሰው ነበር! ልዩ በምንም የማትገልፅው ልዩ ሰው!!
****
ይሄንን ነው እንግዲህ በተራ ድራማ ውስጥ ያጣነው!! ይሄን ትልቁን እንቁ ትልቁን ብርሀን ያጠነው!! ይሄን ሳስብ ይቆጨኛል ይሄን ሳስብ እንገበገባለሁ! ከዚህ በፊት የኦሮሞን ትግል ለማጥፋት ብዙዎች ተገለዋል! አሁንም እጠብቅ ነበር ግን ሀጩ ይሆናል ብዬ አንዴም አስቤ አላውቅም!! እንዲሁ ግን ፍርሀት ነበረኝ!! እንደነገርኩህ ብዙ ነገር አሁን ላይ ማለት አልፈልግም በመፀሀፊ ላይ ሁሉንም ስለምፅፈው ያኔ አንባቢያን ከዚህ የበለጠ ብዙ ነገር ስለሚረዱ ለአሁኑ ይብቃን!!
****
የመጨረሻ ጥያቄ? እስር ላይ ሆነህ የናፈቀህ?
****
ብዙ ነገር ይናፍቅሀል? ከምን ልጀምርልህ? ግን ልጄ በጣም ይናፍቀኛል! በጣም በጣም ጣፋጭ በሆነው እድሜው ላይ ነው የተለየሁት እየተንተባተበ በሚያወራበት እድሜ እሱ ትዝ ሲለኝ በጣም እረበሻለሁ! ይሄ ደግሞ ሰዋዊ ስሜት ነው ማንም ልጅ ያለው ይሄ ስሜት ይሰማዋል!! ከዚህ ውጪ ግን የሚናፍቀኝ የኢትዮጵያ ሰላም መረጋጋት የቄሮ ትግል ውጤት ይናፍቀኛል!!!
****
እድል አግኝቶ ጠያቂው ቢጠይቀው ጃዋር እንዲህ ብሎ የሚመልስ ይመስለኛል ለዛሬ አበቃሁ ተስፍሽ ነኝ ከቶሮንቶ!

05/11/2020
31/10/2020

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abdulmejid Abdi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share