14/05/2026
መረጃ፥ ይህንን ያውቁ ኖሯል?
ኢትዮጵያ ለሀገር በቀል ማኑፋክቸሪንግ (ማምረቻ) ኢንዱስትሪዎች እስከ 5 ዓመት የሚቆይ የሀገር ውስጥ ገበያ ውል (Procurement Contract) በመስጠት ከአለም የመጀመሪያዋ ሀገር መሆንዋን ያውቁ ኖሯል?
በቅርቡ በተጠናቀቀው የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ላይ ይፋ የተደረገው ይህ አዲስ አሰራር የሀገር ውስጥ ምርትን ለመደገፍ ትልቅ እመርታ ነው!
አስገራሚ እውነታዎች፦
💰 የገንዘብ መጠኑ፦ ከ 57 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገበያ ትስስር ውል ተፈርሟል።
🏢 የመንግስት ተሳትፎ፦ ውሉ አምራቾችን ከ 16 ትላልቅ የመንግስት ተቋማት ጋር በቀጥታ ያገናኛል።
📦 የምርት አይነቶች፦ ምግብ፣ ጨርቃጨርቅ፣ ሲሚንቶ፣ መድኃኒት እና የሶላር ፓነሎችን ጨምሮ 96 ስትራቴጂካዊ ምርቶች ላይ ያተኩራል።
📈 የተመዘገበ ውጤት፦ የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከ46% ወደ 66.3% አድጓል።
🚫 የገቢ ምርት ቅነሳ፦ በ“ኢትዮጵያ ታምርት” ዘመቻ ባለፉት 4 ዓመታት ውስጥ ከ 14.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የወጪ ምርትን በሀገር ውስጥ መተካት ተችሏል።
#ኢትዮጵያታምርት #የማኑፋክቸሪንግኢንዱስትሪ