Ethio Dail Mirorr/ኢትዮ ዴሊይ ሚረር

Ethio Dail Mirorr/ኢትዮ ዴሊይ ሚረር news on time

13/07/2023

#ተዋህዶ ሰበር ዜና

04/06/2023

➢ የጎሊያድ ሣቅ.3

👉"እግዜር ስንፈጠር ያዘጋጀልን ነገር ስላለ የሰው ልጅ ቢፈራገጥም የሚያመጣው ለውጥ የለም!! ሕይወት አጭር ናት በዚያ ላይ እዚህ ክፍል ያሉት ሁሉ ዓላማ ካላቸው እኔ የለኝም ብል ለየት ለማለት ጥሩ ነው።
👉"ንፅፅር ያስፈልጋል ብርሃን ያለው ጨለማ ስላለ ነው!ሐዘን ያለው ደስታ ስላለ ነው!ስኬት ያለው ውድቀት... ጨዋ ያለው ባለጌ...ደፋር ያለው ፈሪ... ስላለ ነው!! ሕይወት ላይ ሁሉም ጎበዝ ሁሉም ሐብታም ሁሉም አዋቂ ሁሉም ፀባየኛ ሁሉም ዓላማ ያለው ከሆነ የሕይወት ፍቺ ተራ ይሆናል።"
ገፅ፡97 /ነፃነት ተከስተ/
👉...ምክንያት ውጤት አይለውጥም አባትህ ሞተ ማለት አንተ ሞትክ ማለት አይደለም አባትህ በምድር ላይ የተሰጠው ድርሻ ጨርሶ ተሰናብቷል። አንተም በምድር ላይ የማንም ተራ ውዳቂ ሰካራም ግራ የገባው ህልመኛ ሆነህ ለመኖር አልተፈጠርክም! አንተ በምድር ላይ ታላቅ ድርጊት እንድትፈፅም ነው! በመጠጥ ውስጥ እና ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ራስህን ለመሸፈን ብትሞክር ራስህን ከመደለል ውጪ ያደረከው ነገር የለም!
👉ትላንት ያንተ አይደለችም!ያንተ ጊዜ ዛሬ ናት!ነገም አይደለችም!አሁን ናት። መዝረክረክህን፣ሰበብ መደርደርህን ተውና ተነሳ!እርግጥ በምድር ላይ ማንም የለህም!ጓደኛ!አባት!እናት!ዘመድ ...ወዘተ የለህም!ብቸኛ ግን አይደለህም!የሁሉ ታላቅ እና ፈጣሪ እግዜር ካንተ ጋር ነው!
👉ከራስህ በላይ የምትወዳት ፍቅረኛህ ድንገት ልትክድህ ትችላለች!ለዘመናት በስንት ጥረት ያጠራቀምከው ብር እና ንብረት በድንገት በእሳት ሆነ በሌባ... ሊወድም ይችላል!አሉኝ የምትላቸው ሰዎች ሊርቁህ ይችላሉ። ከሌለህ የለህም ጥላሁን ገሠሠ እንዳለው...
👉ብዙ አስገራሚናየማይታመን ነገር ሊፈጠር ይችላል...ትልቁ ቁምነገር ግን ምንም ይፈጠር ምንም ራስህን ማሸነፍ ነው!በምድር ላይ ያለው ትልቁ እና ጠቢብ የሚባለው ሰው ራሱን ያሸነፈ ነው!እርሱ ባጋጠመው ነገር ተስፋ ቆርጦ በጨለማ የተቀመጠ ሰው ግን እነሆ በቁሙ ሞተ።የቁም በድንሆነ! ለዚህ ነው በዓሉ ግርማ "በሕይወት ላይ ያለው ቋሚ ነገር ለውጥ ብቻ ነው!" ያለው።
👉እግዜርን ማማረር ትተህ ለለውጥ ተነሳ ግሪኮች ትልቅ አባባል አላቸው "ሰይጣን ተስፋ የለውም ግን ተስፋ አይቆርጥ፤ክርስቲያን ተስፋ አለው ግን ተስፋ ይቆርጣል"ይላሉ...ሰበብ መደርደርህን ትተህ ተነሳ...እንዲህ ቢሆን ኖሮ...ይህ ባይሆን ኖሮ...አትበል
ገፅ፡107 /ታደሰ ለማ/

በዓለ ጰራቅሊጦስጲራቅሊጦስ ማለት በልሳነ ጽርዕ “መጸናንዒ” ማለት ነው። ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዝዝ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው፡፡ ...
04/06/2023

በዓለ ጰራቅሊጦስ

ጲራቅሊጦስ ማለት በልሳነ ጽርዕ “መጸናንዒ” ማለት ነው። ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዝዝ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው፡፡ ከሦስቱ አካላት አንዱ ለሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም ነው፡፡ በዓለ ጰራቅሊጦስ ‘በዓለ ጰንጠቆስጤም’ እየተባለ ይጠራል፡፡ ይኸውም በግሪክ ቋንቋ ‘በዓለ ኀምሳ፣ የፋሲካ ኀምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት፣የመከር በዓል’) ማለት ነው፡፡ (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፱፻፮- ፱፻፯)፡፡ በዓለ ጰራቅሊጦስ ወይም በዓለ ጰንጠቆስጤ ከዘጠኙ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደበትን ቀን የምናስብበት በዓል ነው።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ፲፪ቱ ደቀ መዛሙርት፣ ፸፪ቱ አርድእት፣ ፭፻ው ባልንጀሮችና ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ በሚያርግበት ጊዜም “እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ” ሲል ለሐዋርያቱ በገባላቸው ቃል መሠረት ባረገ በ፲ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡ (ሉቃ.፳፬፥፵፱)

በሐዋርያት ሥራ እንደ ተጻፈው በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማለዳ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ መጥቶ የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ በመቀጠልም እንደ እሳት የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በሁሉም ላይ ሞላባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሁላቸውም መንፈስ ቅዱስን ከተሞሉ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መናገር ጀመሩ፡፡ (ሐዋ.፪፥፩-፬) ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ጰራቅሊጦስ ይባላል፡፡

03/06/2023

#ዜና

02/06/2023

ቆይ ግን አንተ ማን ነህ?

የማንነት ጥያቄው እየተመላለሰ ሲያቃጭልበት ለፌ ወለፌ ወመሆኑን ለመንገር በግድ ጆሮው ላይ ተለጥፈው ሲያንሾካሹን ግንርታቸው እያስተጋባ ሲሰማው ያስጨንቀዋል።

ወደዚች በከቻ አለም ፈልጎ እንዳልመጣ ሁሉ ተፈልጎ እንደሚሄድ ለማሳበቅ አፋቸውን ያሾሉ እልፍ የኢብሊስ ወዳጆች አሉ የሁካታቸው ማፍገምገም
የሲቃቸው ሲርሲርታ ለሱ ጥዑም የነፍስ ምግብ ሆኖታል

ነፍሳት ሲቃጠሉና ግግር በረዶ ሰርተው በቁማቸው ጋንድያ ሲሆኑ የሚደሰተው
ሰይጣን ሁሉንም ነፍሳት ተራ በተራ መቅጣቱን ተያይዞታል

እሱም ተራው ደርሶት ግግር በረዶ ውስጥ ነፍሱን ተጣለች

የሲኦልን ሙቀትና ቅዝቃዜ ጠንቅቆ ያውቅ ነበርና ስቃዩ ሲበዛበት ከሲኦል ለማምለጥ መላ ይዘይድ ጀመር

ከብዙ ጥረትና ልፋት በኃላ ልጁ ከሲኦል ታወጣኛለች ያላትን ሻማ ሰራ
በድቅድቁ ጨለማ በሻማይቱ ብርሀንነት ሶስት እርምጃዎችን ወደፊት ተራመደ
ነገር ግን ጨለማውን ተገን አድርገው የከበቡት ብዙ ነፍሳቶች አሰፍስፈው ነበር ሻማይቷን ሊቀሙት

የተጨነቀች ነፍስ .....

ሻማይቱን ለቀቃት...

ሻማዋንም ለመያዝ እልፍ ነፍሶች ተራኮቱ
ተሻሙባት

እሱግን ሊሻማባት ሊሻቀጥባት አልፈቅድምና አፈገፈገ...
ወደ መጨረሻው ጨለማ ወደሚባለው የሲኦል ክፍል ራሱን አሽቀንጥሮ ጣለ

ከወደቀበት ሲነሳም ሰይጣኑ ለእግዜር ፀሎት የሚያደርስበት የገነት መስኮት ታየችው ወደ መስኮቷ ተጠጋ

"እግዚአብሄር እረኛዬ ነው
በለመለመች መስክ ያሳድረኛል"

የሚለው ፀሎት እውነት መሆኑን አመነ
ያመነውም ሲኦል ውስጥ ሆኖ ነው ያውም ሰይጣኑና እግዜሩ በሚገናኙበት በመስኮታቸው ቀዳዳ ተመልክቶ

ወቅቱ ፀደይ ነበርና የገነት ደጃፎች በአደይ አበባ ተንቆጥቁጠዋል

ወደ አበቦቹ አማተር
ከአበቦቹ መሀል ግን አይኑ ውስጥ የገቡት ስራቸው አንድ ቅርንጫፋቸው ለየቅል የሆኑትን ዕቡጦች ላይ አይኑ ተተክሎ ቀረ

ያለመታደል እጣ ፈንታዋ ሆነና አንድኛዋ መንታይቱ አበባ ከሰመች

በመክሰሟ ልጁ አዘነ

አንዷ አበባ አበበች
አንድኛዋ ከሰመች

እነሆ ርግብም በአክናፏ አየሩን ቀዝፋ መታ የቆረችጠውን አበባ በማንቁሯ ቀጠፈቻት ቀጥፋትም እሱ ሲኦል ውስጥ ሆኖ በሚያያት መስኮት በኩል በራ አረፈች። በማንቁሯ የያዘችውን አበባ እንዲቀበላት አንገቷን ወሱ ስክክ አድርጋ በተቀመለኝ አይነት ልምምጥ አይን አይኑን ታየዋለች

ይቀበላት ይሆን?

የኑሮን ውትፍትፍ ቀዳዳ መሙላት ባይችል እንኳን ሊሞላ የሚችል ደንዳና ጫንቃ እንዳለው ያወቀችው

ግን እሷ ማን ናት?

ሻማይቱ?
መንትያ አበቦቹ?
ወይስ ርግቢቱ?

✍️ቅዱስ አርዮስ✍️

የሀገሯ ~  ገመገምከጥርሶቿ ~ ግርግም፣ሳቋ ~ ሲያፍገመግምሳልፍና ~ ሳገድም።አማትሬ ~ ባየው:ተሰትረው ~ ኑረውየቅርብ ሩቅ ~ ሆነው።ኩንስንስ  አመሏጵስጡቂስ ጠረኗ ኑረት   አኳኃኗ፣    ...
02/06/2023

የሀገሯ ~ ገመገም
ከጥርሶቿ ~ ግርግም፣
ሳቋ ~ ሲያፍገመግም
ሳልፍና ~ ሳገድም።

አማትሬ ~ ባየው:
ተሰትረው ~ ኑረው
የቅርብ ሩቅ ~ ሆነው።

ኩንስንስ አመሏ
ጵስጡቂስ ጠረኗ
ኑረት አኳኃኗ፣

ዘንጠፍጠፍ እያለ
ቀልብ እያዋለለ፣

የገዛ ጥላዋ
ብርቅርቅ ገላዋ፣

ውልብ ይልብኛል.....
የድምጿ ሲርሲርታ
ያቃጭልብኛል።

እናማ......

ምናብ ሀሳብ ሲምስ
ሲያወጣ ሲመልስ፣

ጣዕሙን ሊያጣጥም
ምላስ ሲፈረጥም፣

እፀበሉ ግርጌ
ነጠላ አደግድጌ፣

ስለቴን ላስገባ
በእግዜሩ ሙሀባ፣

መጣሁ ከአድባርሽ
እቤተስኪያን ቅጥርሽ፣

የኔ እንዲያ መዋተት
ደርሶ መንከራተት፣

የኔ እንዲያ መውተረተር
ካንቺ ለመሰተር።


እነሆ አካሏን ጎብኝቶ ጠረኗን በምናቡ ምጎ ካጣጣመ በኃላ በዕውኑ አለም ፍለጋውን ማነፍነፉን ቀጠለ።


አንቺ ሆዬ ወዴት አለሽ?

✍ቅዱስ አርዮስ✍
🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Dail Mirorr/ኢትዮ ዴሊይ ሚረር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share