Habesha stock exchange

Habesha stock exchange This is a virtual stock exchange in Ethiopia.

17/09/2025

እንደምታውቁት የተለያዩ ድርጅቶች Ethiopian Stock Exchange ላይ ሊስት ተደርገው share መግዛት እና መሸጥ እስክንችል በጉጉት እየጠበቅን ነው።

In the meantime, there are people interested to buy a share of Abyssina, Dashen and Awah Bank, if there is a seller.

‹‹መንግሥት ካፒታል ገበያን በመጠቀም በጀቱን ለመደገፍ ቢጠቀም በጣም ንፁህ መንገድ ነው›› መለሰ ምናለ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ከፍተኛ አማካሪጠንካራ ኢኮኖሚ ያላቸው ያደጉ አገሮችም ሆነ በማደ...
29/05/2022

‹‹መንግሥት ካፒታል ገበያን በመጠቀም በጀቱን ለመደገፍ ቢጠቀም በጣም ንፁህ መንገድ ነው›› መለሰ ምናለ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ከፍተኛ አማካሪ

ጠንካራ ኢኮኖሚ ያላቸው ያደጉ አገሮችም ሆነ በማደግ ላይ የሚገኙ አገሮች ለኢኮኖሚ ዕድገታቸው ቁልፍ የፋይናንስ ምንጭ የሆነው የካፒታል ገበያ (Stock Market) ወይም የገንዘብ ነክ ሰነዶች ገበያ እንደሆነ ይነገራል። ይህ የገበያ ሥርዓት በኢትዮጵያ እንዲቋቋም በርካታ የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ለረዥም ዓመታት ሲወተውቱ መቆየታቸው የሚታወስ ነው። በስተመጨረሻም ይህ ምክረ ሐሳብ ሰሚ አግኝቶ የዛሬ አንድ ዓመት ገደማ የገንዘብ ነክ ሰነዶች ገበያ በኢትዮጵያ እንዲቋቋም የሚያስችል የካፒታል ገበያ ማቋቋሚያ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል። አዋጁ ከፀደቀ በኋላም የአገሪቱን የካፒታል ገበያ ለማቋቋም የባለሙያዎች ቡድን ተመሥርቶ የዝግጅት ሥራዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል። በቅርቡም የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን በመሥራችነት ለማቋቋም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግና የእንግሊዝ መንግሥት ኩባንያ የሆነው FSD የመግባቢያ ስምምነት ፈርመዋል። የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን ለማቋቋም እየደረገ ያለውን የዝግጅት ሒደትና የቀጣይ ምዕራፍ ተግባራት እንዲሁም የገበያው መመሥረት የሚኖረውን ፋይዳ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን ለማቋቋም የተደራጀው የባለሙያዎች ቡድን ሰብሳቢና የብሔራዊ ባንክ ገዥ የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ከሆኑት ከአቶ መለስ ምናለ ጋር አሸናፊ እንዳለ ያደረገውን ቆይታ እንደሚከተለው አቅርበንዋል።

ሪፖርተር፡- እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የካፒታል ገበያ ለማቋቋም በዝግጅት ላይ ነው። የካፒታል ገበያውን የማቋቋሙ ሒደቱ በአሁኑ ወቅት በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

መለሰ ምናለ፡- በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን ለማቋቋም ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን። የካፒታል ገበያውን የሚቆጣጠረውን ባለሥልጣን ለመመሥረት የሚያስፈልገውን ተቋማዊ አደረጃጀትና ኃላፊነት የሚወስን የሕግ ማዕቀፍና የቁጥጥር ማዕቀፉን የተመለከተ የሕግ ማዕቀፍ ለማበጀት ሕጎችን እያረቀቅን ነው። በተጨማሪም የካፒታል ገበያውን ለመምራትና ገበያውን በብቃት ለማንቀሳቀስና ለመቆጣጠር የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል ከወዲሁ ዝግጁ ለማድረግ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን እያከናወንን እንገኛለን።

ሪፖርተር፡- የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን ለማቋቋም የሚያስችል አንድ ስምምነት ከሰሞኑ ተፈርሟል። ስምምነትቱን የተፈራረሙት በቅርቡ የተመሠረተው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግና የብሪታኒያ መንግሥት ተቋም የሆነው FSD ናቸው። ይህንን ስምምነት በተመለከተ የሚነሳ አንድ ጥያቄ አለ ይኸውም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን የማቋቋም ኃላፊነት የተሰጠው ለማነው የሚለው ነው? በዚህ ላይ ምን ይላሉ? አያይዘውም የስምምነቱን ምንነትና ፋይዳ ቢገልጹልን?

መለሰ ምናለ፡- ጥሩ ጥያቄ ነው። ባለፈው ዓመት የካፒታል ገበያ ማቋቋሚያ አዋጅ ከፀደቀ በኋላ ብሔራዊ ባንክ የካፒታል ማርኬት ፕሮጀክት ትግበራ ቡድን አቋቁሟል። ይህ የፕሮጀክት ትግበራ ቡድኑ በዓለም አቀፍ ሕግ፣ በኢትዮጵያ ሕጎች እንዲሁም በማክሮ ኢኮኖሚና ከካፒታል ማርኬት ጋር የተገናኘ ዓለም አቀፍ ልምዶችን ያካበቱ ባለሙያዎች ይዞ በብሔራዊ ባንክ ውስጥ ራሱን የቻለ ቢሮ ተደራጅቶለት የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬትን ለማቋቋም ጠቃሚ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችን ሲያከናውን ቆይቷል። ይህ የፕሮጀክት ትግበራ ቡድን ላለፉት ጊዜያት ሲያከናውናቸው ከነበሩ አበይት ጉዳዮች መካከል አንዱ የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬትን የሚቆጣጠረውን ባለሥልጣን ለማቋቋም የሚያስፈልገውን የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ነው። በዚህም የሚቋቋመውን ባለሥልጣን ተቋማዊ አደረጃጀት፣ ባለሥልጣኑን ለማቋቋም የሚያስፈልገውን ሀብት የተመለከቱ ረቂቆችን አዘጋጅተናል። የሚቋቋመው ባለሥልጣንን የሠራተኞች አስተዳደር የተመለከተ ረቂቅም አዘጋጅተናል። ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች ባለሥልጣኑን ለማቋቋም ቁልፍ የሆኑ ጉዳዮችን የተመለከቱ የሕግ ማዕቀፎችን ረቂቅ አዘጋጅተናል። ይህንን ባለሥልጣን ለማቋቋም ቅድሚያ የተሰጠበት ምክንያት የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬትን የመመሥረት ኃላፊነት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተረክቦ ምሥረታውን የሚያከናውነው ይህ ተቋም በመሆኑ ነው። የፕሮጀክት ትግበራ ቡድኑ እያከናወነ የሚገኘው ሁለተኛው ጉዳይ በሚቋቋመው ካፒታል ማርኬት ላይ ባለሥልጣኑ የሚያደርገውን ቁጥጥር የተመለከተ የቁጥጥር ማዕቀፍ ማዘጋጀት ነው። ምክንያቱም አዋጅ ብቻውን የቁጥጥር ሥራን ለማከናወን በቂ አይደለም። አዋጁን የተሟላ የሚያደርጉ መመርያዎችና ደንቦች ያስፈልጋሉ። በመሆኑም እስካሁን ድረስ አሥር የሚሆኑ ደንቦችን እንዲሁም አሥራ አምስት የሚሆኑ መመርያዎችን አርቀቀናል። በእነዚህ ረቂቅ የሕግ ማዕቀፎች ላይ ግብአት ለመሰብሰብም የባለድርሻ አካላት ውይይት ማድረግ ጀምረናል። ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን እየሠራን ቆይተናል። የፕሮጀክት ትግበራ ቡድኑ ለቀጠራቸው ባለሙያዎች ከካፒታል ማርኬት ጋር የተገናኙ የተለያዩ ሥልጠናዎችን ስንሰጥ ቆይተናል። በፕሮጀክት ትግበራ ቡድኑ ለቀጠራቸው ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በካፒታል ማርኬት ዓውድ ውስጥ ተሳትፎ ለሚያደርጉ አካላት ሥልጠናዎችን እንዲሁም የውጭ የትምህርት ዕድሎችን በመስጠት እንዲሠለጥኑ አድርገናል አሁንም እያደረግን እንገኛለን። በተጨማሪም ከተለያዩ የልማት አጋሮችን በማነጋገር የካፒታል ማርኬት ሥልጠናዎችን፣ ከካፒታል ማርኬት ጋር የተገናኘ የጋዜጠኝነት ኮርስ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ጭምር ጥረት እያደረግን እንገኛለን። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የካፒታል ማርኬት ባለፈው ዓመት በጸደቀው አዋጅ በሕግ ደረጃ ተቋቁሟል። ይህ ተቋም የገንዘብ ነክ ሰነዶች ግብይት አገልግሎትን የሚሰጥ ነው። በአዋጁ እንደተደነገገው ይህ ካፒታል ማርኬት በመንግሥትና የግል አጋርነት (Public Private Partnership) አግባብ የሚቋቋም ሲሆን፣ መንግሥት በዚህ ውስጥ ዝቅተኛ ድርሻ እስከ 25 በመቶ የሚሆን ድርሻ በመያዝ የሚቋቋም ይሆናል። የተቀረው 75 በመቶ ድርሻ ለግሉ ዘርፍ የሚተው ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተቋም እንደመሆኑ መጠን መንግሥት በካፒታል ማርኬት ውስጥ የሚኖረውን ድርሻ ወክሎ አክሲዮን ሊይዝ አይችልም። ከዚህ አኳያ መንግሥት ወክሎ ባለድርሻ መሆን የሚችለው ትክክለኛ ተቋም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆሊዲንግ ነው። ይህንን ተቋም ያቋቋመው አዋጅም የመንግሥትን ሀብት የማስተዳደርና መንግሥትን ወክሎ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ላይ መሳተፍ እንደሚችል ይደነግጋል። ቀደም ሲል እንደገለጽከውም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬትን ለመመሥረት የሚደረገውን ጥረት አንድ ዕርምጃ ወደፊት የሚወስድ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል። በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና FSD Africa ወይም Financial Sector Deepening Africa የተባለው መቀመጫውን ኬንያ ካደረገው የእንግሊዝ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። በሁለቱ መካከል በተደረገው ስምምነት FSD የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬትን ለመመሥረት የሚያስፈልገውን ዝግጅት የማከናወን ኃላፊነት የተሰጠው የፕሮጀክት ትግበራ ቡድን ወጪዎች ለመሸፈን ተስማምቷል። ይህ ማለት ግን የካፒታል ገበያውን ለመመሥረት እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል። በመሆኑም የፕሮጀክት ትግበራ ቡድኑ የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬትን ለማቋቋም የሚያስፈለገውን ሁሉንም ነገር የሚከውን ይሆናል ማለት ነው። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት አክሲዮን ኩባንያ ሆኖ በንግድ ሚኒስቴር እንዲመዘገብ ማድረግ፣ ቢዝነስ ፕላኑን መቅረፅ፣ አክሲዮኖችን መሸጥ፣ ከሚቋቋመው የካፒታል ማርኬት ባለሥልጣን ፈቃድ ማውጣት፣ ለገበያው ጠቃሚ የሆኑ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን ግዥ መፈጸምና መሰል ጉዳዮችን ማሟላት ናቸው።

ሪፖርተር ፡- ትክክለኛውን የስቶክ ገበያ ሥነ ምኅዳር ለመፍጠር እንደ ኢንቨስትመንት አማካሪዎች ፣ ክሬዲት ኤጀንሲዎች (ደረጃ ሰጪ ኤጀንሲዎች) ፣ አገናኞችና ሌሎች መሰል ተቋማትን መፍጠር ያስፈልጋል። እነዚህ ደግሞ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሉም። አሁን ስኮላርሺፕ እያገኙ ያሉት ባለሙያዎች እንደዚህ ያሉ ኩባንያዎችን እንዲፈጥሩ ታስቦ ነው?

መለሰ ምናለ፡- በትክክል። የካፒታል ገበያ በጣም የተወሳሰበ ሥነ ምኅዳር ነው። ከገበያው ጋር በቁርኝት የሚሠሩ የተለያዩ ቁልፍ ተቋማት ለምሳሌ አገናኞች (Intermediaries) የኢንቨስትመንት ባንኮች፣ የክሬዲት (ብድር) ደረጃ ሰጪ ኤጀንሲዎች፣ አዘዋዋሪዎች፣ ደላሎች፣ የገበያ ልውውጥ አቅራቢዎችና የመሳሰሉት ያስፈልጋሉ። እነዚህ ደግሞ የየራሳቸውን ክህሎትና ዕውቀትን ይጠይቃሉ። በአሁኑ ወቅት ይህንን ሊሠሩ የሚችሉ ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የሉም ምክንያቱም የካፒታል ገበያ ስለሌለን። በተጨማሪም የካፒታል ገበያን ስንመሠርት ራሱን የቻለ የሰው ኃይል ያስፈልጋል። ችሎታን በተመለከተ ደግሞ ወደፊት ራሳችንን መቻል አለብን።

እስካሁን ከ600 በላይ ባለሙያዎችን አሠልጥነናል። ያስቀመጥነውን መሠረታዊ የክህሎት ደረጃ ያሟሉ በመረጡት የአገልግሎት ዘርፍ የተሻለ ሥልጠና እንዲያገኙ እያደረግን ነው። የሚቋቋመው የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ደግሞ ለካፒታል ገበያው አገልግሎት ሰጪዎች የራሱ የሆኑ አነስተኛ የብቃት መመዘኛ ደረጃን የሚያወጣ ይሆናል። ለምሳሌ ፈንድ አስተዳዳሪዎች የተራቀቀ ክህሎት ያስፈልጋቸዋል፣ በገበያው የሚሳተፉ ደላሎች (Brokers) ግን መሠረታዊ መመዘኛዎችን ብቻ አሟልተው ሊሳተፉ ይችላሉ። አስፈላጊው ብቃት ያለው የሰው ኃይል በአገር ውስጥ እስኪፈጠር ድረስ እንደ ኬንያ ያሉ የውጭ አገር ባለሙያዎች መጥተው እነዚያን አገልግሎቶች ሊሰጡ ይችላሉ። በእነዚህ አገልግሎቶች ሥልጠና የወሰዱና የተመሰከረላቸው የአገር ውስጥ ባለሙያዎች ደግሞ ከውጭ ባለሙያዎች ጋር በመሥራት በመጨረሻም የውጭ ዜጎችን በመተካት የራሳቸውን የአገር ውስጥ ድርጅቶች በማቋቋም ዕውቀቱን ወደ አገር ውስጥ እንዲያስተላልፉ ነው የታቀደው።

ሪፖርተር፡- በአሁኑ ወቅት የተረቀቁት አሥር ደንቦችና አሥራ አምስት መመርያዎች የውጭ አገር ባለሙያዎችና ኩባንያዎች ፈቃድ አውጥተው በስቶክ ገበያ አገልግሎት አቅራቢነት በኢትዮጵያ እንዲሰማሩ የሚያስችሉ ናቸው?

መለሰ ምናለ፡- በትክክል። የካፒታል ገበያ አዋጁ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶችን፣ ባለሙያዎችን፣ የኢንቨስትመንት ባንኮችን፣ ደረጃ ሰጪ ኤጀንሲዎችን፣ አከፋፋዮችን፣ ደላላዎችን፣ አሳዳጊዎችንና ሌሎችንም አይለይም። አሁን እያረቀቅነው ያለው የፈቃድ አሰጣጥ መመርያ የትኛውንም መሥፈርት የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች ፈቃድ አግኝተው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪ ሆነው እንዲሠሩ ያስችላቸዋል።

ሪፖርተር፡- የሚቋቋመው የአክሲዮን (ካፒታል) ገበያ መጠን ወይም የገበያው ካፒታል ምን ያህል ይሆናል?

መለሰ ምናለ፡- ብሔራዊ ባንክ የባንኮች የተከፈለ የካፒታል ምን ያህል ሊሆን እንደሚገባ የሚወስነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደሆነው ሁሉ፣ ለሚቋቋመው አክሲዮን ገበያ የካፒታል መጠን የሚወሰነው በሚቋቋመው የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ነው። ባለሥልጣኑ ከተመሠረተ በኋላ ከሚያወጣቸው መሥፈርቶች አንዱ ይህ ነው።



ሪፖርተር፡- የአክሲዮን ገበያው የካፒታል መጠንን የሚወስኑት ጉዳዮች ምን ምን ናቸው?

መለሰ ምናለ፡- መሠረታዊ መለኪያው የአደጋ ተጋላጭነት ነው። ከአደጋ ተጋላጭነት አንፃር ተመዝኖ ይህንን አደጋ ለመመቋቋም እንደ ቋት ሆኖ የሚያገልግለው ካፒታል ነው። ይህንንም ለመወሰን የሚገበያዩት የኩባንያዎች ድርሻ፣ የባለሀብቶች ብዛት፣ ከግምት ይገባሉ። የአክሲዮን ገበያ አገልግሎትን ለመስጠትና ገበያውን ለመቆጣጠር ጥቅም ላይ የሚውለው ቴክኖሎጂም የካፒታሉ አካል ይሆናል። ኤፍኤስዲ (FSD) ለሚቋቋመው የኢትዮጵያ የአክሲዮን ገበያ በጣም አዋጭ የሆነ ቢዝነስ ሞዴል በመንደፍና የውጭ ባለሀብቶችን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሀብቶችን መሳብ ከቻለ፣ የአክሲዮን ገበያው በትልቅ ካፒታል የሚቋቋም ይሆናል። እስካሁን ባለው ሒደት ከውጭ ባለሀብቶች ወይም ኩባንያዎች ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን አይተናል። በተለይም ኤፍኤስዲ በሌሎች አገሮች የአክሲዮን ገበያዎችን ያቋቋሙ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን በአጋርነት ካመጣ፣ በጣም ትልቅ ካፒታልና ከፍተኛ የገበያ ልውውጥ የሚካሄድበት ይሆናል።

ሪፖርተር፡- መንግሥትን ወክሎ እስከ 25 በመቶ ድርሻ የሚይዘው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ድርሻውን በብር ነው የሚከፍለው?

መለሰ ምናለ፡- መንግሥት የሚይዘው የ25 በመቶ ድርሻ የካፒታሉ አካል ነው የሚሆነው። ግን መንግሥት ይህንን ድርሻ እንዴት ለመክፈል እንዳሰበ አላውቅም። በጥሬ ገንዘብ ማስገባት ወይም ንብረት ሊያቀርብ ይችላል። ዞሮ ዞሮ ግን መንግሥት ድርሻውን ለመክፈል የሚያቀርበው ማንኛውም ነገር እንደ ካፒታል ነው የሚቆጠረው።

ሪፖርተር፡- የኤፍኤስዲ አፍሪካ ባለሥልጣናት ካፒታል ገበያውን ለማቋቋም ለተዋቀረው የፕሮጀክት ቡድን ወጪ መሸፈኛ የሚያቀርቡት ገንዘብ በሒደት ኤፍሲዲ በአክሲዮን ገበያው ውስጥ የሚኖረው ድርሻ ሆኖ እንደሚቀየር ነግረውኛል። የአክሲዮን ገበያውን ለማቋቋም የሚወጣው ወጪ ምን ያህል ነው?

መለሰ ምናለ፡- የመጀመሪያው የፕሮጀክት ወጪ ትልቅ አይደለም። እውነት ነው ይህ ወጪ የሚሸፈነው በኤፍኤስዲ አፍሪካ ነው። ሕጋዊ ሒደቶችን ለመፈጸም፣ የካፒታል ገበያውን በንግድ ሚኒስቴር ለማስመዝገብ፣ ለአክሲዮን ልውውጥ ፈቃድ ለማግኘት፣ ለባለሙያዎች ቅጥር፣ ለባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወጪዎች፣ አክሲዮኖችን ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ለመሸጥ፣ ዓለም አቀፍ ጉዞዎችን ጨምሮ የመንገድ ትዕይንት ወጪዎችንና ሌሎች ወጪዎችን የሚሸፍነው በኤፍኤስዲ አፍሪካ ነው። እነዚህ ወጪዎች ሊመለሱ የሚችሉ ናቸው ወይም በአክሲዮን ልውውጥ ወቅት ወደ አክሲዮንነት ሊቀየሩ ይችላሉ። ይህንን የሚወስነው ኤፍኤስዲ አፍሪካ ቦርድ ነው።

ሪፖርተር፡- የአክሲዮን ባለቤትነት ማረጋገጥ ተግባር በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ተቋም ነው የሚከናወነው ወይስ በራሱ በካፒል ገበያው ነው የሚረጋገጠው?

መለሰ ምናለ፡- አይደለም። በይፋ ግብይት የሚካሄድባቸው ሁሉም አክሲዮኖች በወረቀት ቅርፅ ሊቀመጡ እንደማይችል የካፒታል ገበያ አዋጁ ይደነግጋል። ይህ ማለት ሁሉም አክሲዮኖች ወደ ዲጂታል ፎርማት መቀየር አለባቸው ማለት ነው። በተጨማሪም በማዕከል የተመዘገቡና ፈቃድ ባለው የአክሲዮን አስቀማጭና አስወጋጅ ኩባንያ መያዝ አለባቸው። ለምሳሌ የዘመን ባንክ ባለአክሲዮኖችን ማወቅ ከፈለግክ ወደ ዘመን ባንክ በመሄድ ሁሉም ባለአክሲዮኖች በእጅ የተመዘገቡበት ትልቅ ማኑዋል ደብተር ይሰጡሃል። ያ መቀየር አለበት ምክንያቱም ለባለቤቶቹ ደኅንነቱ የተጠበቀ አይደለም። ወደ ካፒታል ገበያው ስንመጣ ግን ይህ አሠራር አይኖርም። የእያንዳንዱን አክሲዮን ደኅንነት በተመለከተ ኃላፊነት የሚወስድ ፈቃድ ያለው የአክሲኖች ጠባቂ ኩባንያ ይኖራል። እያንዳንዱ አክሲዮን የራሱ የሆነ መለያ ቁጥር ይኖረዋልና ባለቤቶች በልዩ ሁኔታ ተለይተው የሚታወቁበት ሥርዓት ይኖራል። የአክሲዮኖች ልውውጥ ወይም ግብይት በተፈጸመ ቁጥር ወዲያውኑ የአክሲዮን ባለቤትነቱ በኤሌክትሮኒክ መንገድ ከሻጩ ወደ ገዢው ይተላለፋል። ይህ የሚከናወንበት ቴክኖሎጂ መልካም ጎኖች ዋነኛው ለባለሀብቶች አስተማማኝና በጣም የተጠበቀ መሆኑ ነው።

ሪፖርተር፡- የካፒታል ገበያ አዋጁ የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ ካፒታል ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ይፈቅዳል። እነዚህ የውጭ ኩባንያዎች በቢትኮይን (Bitcoin) ወይም በሌሎች ዲጂታል ምንዛሬዎች ኢንቨስት ለማድረግ ቢጠይቁስ?

መለሰ ምናለ፡- እንደ ቢትኮይን ያሉ ዲጂታል ምንዛሬዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ለግብይት አይቀርቡም። አሁን ባለው ሁኔታ የውጭ ባለሀብቶች የፋይናንስ ተቋማትን አክሲዮን እንዲገዙ አይፈቀድላቸውም። የባንክ አክሲዮኖችን መያዝ ለውጭ አገር ዜጎች የተከለከለ በመሆኑ። ስለዚህ በኢትዮጵያ አክሲዮን ገበያ ውስጥ የውጭ ባለሀብቶች በመሳተፍ እንዲገዙ የተፈቀደላቸው አክሲዮኖች ለውጭ ዜጎች በተፈቀዱ መስኮች ማለትም ከንግድ ሥራዎች ወይም ዘርፎች የሚመነጩ አክሲዮኖችን ብቻ ነው። የውጭ ባለሀብቶች በአክሲዮን ገበያው መሳተፍ የሚችሉት አሁን ባለው የኢንቨስትመንት ሕግ ለእነሱ በተፈቀደው ዘርፍ ላይ ብቻ ይሆናል።

ሪፖርተር፡- በካፒታል ገበያው የሚሳተፉ የውጭ ባለሀብቶች ካፒታላቸውን በተደጋጋሚ ወደ አገራቸው ለመመለስ ቢጠይቁስ? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያለማቋረጥ የውጭ ምንዛሪ ማቅረብ ይችላል?

መለሰ ምናለ፡- በአሁኑ ጊዜ ከፊል ክፍት የሆነ የካፒታል ፍሰት ሥርዓት አለን። የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት አድርጎ መሸጥና በፈለገው ጊዜ መሄድ ይችላል። የማይቻል ነገር የፖርትፎሊዮ ፍሰቶች ማለትም (የአክሲዮን ገበያ ኢንቨስትመንትን የማስወጣት ተግባር) ነው። አሁን ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት እንደ አንድ የቱሪስት ባለሀብት ነው። ትኩስ ገንዘብ ተብሎም ይጠራል። እዚህ መጥተህ ኢንቨስት ታደርጋለህና በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ስትሆን ትሄዳለህ። የፖርትፎሊዮ ኢንቨስትመንትን የማስወጣት ጉዳይ በፖሊሲ ይወሰናል። በብሔራዊ ባንክና በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚወሰን ይሆናል። ሁለቱንም የሚያጣምር ውሳኔ መስጠትም ይችላል። ለምሳሌ መንግሥት የውጭ ባለሀብቶች ከስድስት ወራት በፊት ዋስትና እንዳይሸጡ የሚያዝ ፖሊሲ ሊያወጣ ይችላል። በጣም ተለዋዋጭ ገበያን ለማስወገድ እንደዚህ ያሉ ፖሊሲዎችን መተግበር ይቻላል።

ሪፖርተር፡- የአክሲዮን ገበያው የካፒታል አካውንት ሊበራላይዜሽን (ነፃ ማድረግን) ይፈቅዳል?

መለሰ ምናለ፡- የካፒታል አካውንት ሊበራላይዜሽን በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ብቻ ሊወሰን የሚችል የፖሊሲ ጉዳይ ነው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ያስፈልገዋል። በአሁኑ ጊዜ ከፊል የተከፈተ የካፒታል አካውንት አስተዳደር ሥርዓት ነው ያለን። የውጭ ዜጎች ካፒታላቸውን ወደ አገራቸው መመለስ እንደሚችሉ ሲፈቀድላቸው የገዙትን አክሲዮን በመሸጥ መመለስ ይችላሉ። የካፒታል አካውንት ሊበራላይዜሽን ግን የፖሊሲ ጉዳይ በመሆኑ ወደፊት ታይቶ የሚወሰን ነው የሚሆነው።

ሪፖርተር፡- በአክሲዮን ገበያው የሚሳተፉ ኩባንያዎች እንዴት ነው የሚለዩት? አንዳንዶች ገበያው ሥራ የሚጀምረው በ50 ኩባንያዎችን በመለየት ነው ይላሉ?

መለሰ ምናለ፡- ገበያዎች በመንግሥት የሚታዘዙ አይደሉም፡፡ ነገር ግን በመንግሥት ማበረታቻዎች ያድጋሉ። በአክሲዮን ገበያው የሚሳተፉትን ወይም የሚዘረዘሩትን ኩባንያዎች ብዛት መንግሥት የሚወስንበት መንገድ የለም። በማበረታቻዎች ላይ በመመሥረት ግን ገበያውን መገንባት ይቻላል። ለዚህ መንግሥት ማበረታቻ መስጠት አለበት። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ብዙ ኩባንያዎች ይፋዊ ወደ ሆነው የአክሲዮን ግብይት እንዲመጡ ካሮትና ልምጭ ሊያስፈልግ ይችላል። ቀድሞውኑ የሕዝብ ኩባንያዎች የሆኑት በአክሲዮን ገበያው ለመሳተፍ ሰፊ ዕድል ያላቸው። በተለይ አክሲዮን ለሕዝብ የሚሸጡ የአክሲዮን ኩባንያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ። ምክንያቱም ቀድሞውኑም ለሕዝብ የተሸጡ አክሲዮኖች አሏቸው። በዚህ ሒደት የሚፈጠረው መገበያየት ብቻ ነው። ምን አልባት ድርሻቸውን ለመገበያየት አነስተኛ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ ይጠየቁ ይሆናል እንጂ የተለየ ነገር አይኖርም። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የአክሲዮን ገበያ የለም። የዋጋ ግኝት፣ ግልጽነት፣ ወዘተ የለም። ዋጋ በአቅርቦትና በፍላጎት መወሰን አለበት። ስለዚህ ባለአክሲዮኖች ኩባንያዎቻቸውን ዝቅተኛውን መስፈርቶች አሟልተው በይፋ ወደ አክሲዮን ገበያው እንዲገቡ ግፊት ማድረጋቸው አይቀርም። ስለዚህ ሁሉም ኩባንያዎች፣ ባንኮች፣ ኢንሹራንስ፣ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች፣ የቢራ ፋብሪካዎችና ሌሎችም በአክሲዮን ኩባንያ የተደራጁ ኩባንያዎች በአክሲዮን ገበያው የሚሳተፋ ይሆናል። ነገር ግን በዚህ ገበያ ለመሳተፍ ዝቀተኛውን መስፈርት ማሟላት አለባቸው። ለዚህም ከኩባንያዎች ጋር በአቅም ግንባታ ላይ እየሠራን ነው።

ሪፖርተር፡- የመንግሥት ልማት ድርጅቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ሥር ናቸው። ሆልዲንግ ኩባንያው ደግሞ በአክሲዮን ገበያው ላይ የ25 በመቶ ድርሻ እንደሚኖረው ተገልጿል። የመንግሥት ልማት ድርጅቶች በአክሲዮን ገበያው ውስጥ የሚሳተፉ ከሆነ የውስጥ ለውስጥ ግብይት ሊከሰት አይችልም። ይህንን እንዴት ማስቀረት ይቻላል?

መለሰ ምናለ፡- የውስጥ ለውስጥ ንግድ ጉዳይ የሚፈጠር አይመስለኝም። አዎ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ኩባንያው የበርካታ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ባለቤት ነው። የመንግሥት ልማት ድርጅቶች በአክሲዮን ገበያው ከሚኖራቸው የንግድ ልውውጥ አንፃር ሁለት ውሳኔ የሚሹ ጥያቄዎች አሉ። የመጀመሪያው የፖሊሲ ውሳኔ የሚሻ ጥያቄ ነው። አንደኛው የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ሊበራላይዝ ማድረግ ወይም አለማድረግ የሚለው የፖሊሲ ጥያቄ ነው። ይህ በመንግሥት ደረጃ የሚወሰን ጉዳይ ነው። ለምሳሌ መንግሥት አሥር በመቶውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመሸጥ ከወሰነ እያንዳንዱ ዜጋ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ድርሻ እንዲያገኝ ማድረግ የሚቻለው በአክሲዮን ገበያው ነው። ይህ አካሄድ የፕራይቬታይዜሽን ሒደቱን ዴሞክራሲያዊ ያደርገዋል። ከዚህ ቀድም ግን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ወደ ግል ሲያዛውረው ገዥው የአገር ውስጥ ወይም የውጭ አገር ትልቅ ሀብታም ባለሀብት ይሆናል። ትልልቅ ኢንተርፕራይዞችን በሀብታሞች መዳፍ ውስጥ ማስገባት ደግሞ የፖለቲካ ችግር ይፈጥራል። አሁን እየተፈጠረ ባለው ዕድል ግን ሀብታምም ሆንክ ደሃ አንድ ድርሻ መግዛት ትችላለህ። ሁሉም ሰው በመንግሥት ልማት ድርጅቶች ውስጥ ወይም በግል ኩባንያዎች ላይ ድርሻ እንዲኖረው ማድረግ ይቻላል። ይህም ግልጽነትን፣ እኩልነትን ያረጋግጣል። በአክሲዮን ገበያው የሚዘረዘሩ የመንግሥት ልማት ድርጅቶችንም ግልጽና ለሕዝብ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል። እነዚህ ድርጅቶች በመንግሥት የተያዙናና በሙስና የተተበተቡ ብቻ ናቸው። ስለዚህ የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ለተወሰኑ ባለሀብቶች ከመሸጥ ይልቅ ወደ ግል ማዞር በጣም የተሻለ ነው።

የውስጥ ለውስጥ ግብይት የሚፈጠረው አንድ ሰው ስለ አክሲዮን ገበያ ውስጥ ስለተዘረዘረ አንድ ኩባንያ የውስጥ አዋቂ መረጃ ሲኖረው ነው። የውስጥ አዋቂው መረጃን ከሕዝብ ቀድሞ ያገኛልና መረጃውን ተጠቅሞ አክሲዮኑን ለመገበያየት ይጠቀምበታል። በዚህ ሁኔታ የውስጥ ለውስጥ ንግድ ሊፈጠር አይችልም። የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ኩባንያው በአክሲዮን ገበያው ላይ ድርሻ ይኑረው እንጂ የአክሲዮን ገበያው ራሱን የቻለ ኩባንያ ነው። በእርግጥ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ኩባንያው በሥሩ ስላሉት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች መረጃ ሊኖረው ይችላል። ነገር ግን ይህ መሆኑ የውስጥ ለውስጥ ንግድ እንዲፈጠር ያደርጋል የሚለው አይታየኝም።

ሪፖርተር፡- አንዳንዶች የአክሲዮን ገበያው የመንግሥት የበጀት ጉድለቶችን ለመሙላት የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ እንዳያገለግል ይሠጋሉ። ሌሎች ደግሞ መንግሥት የውጭ ባለሀብቶችን በመሳብ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመፍታት ነው የአሲዮን ገበያውን እያቋቋመ ያለው ይላሉ። በዚህ ላይ ምን ይላሉ?

መለሰ ምናለ፡- እውነት ነው። ከዓላማዎቹ አንዱ የበጀት ጉድለትን ለመሸፈን ነው። መንግሥት ካፒታል ገበያን በመጠቀም በጀቱን ለመደገፍ ቢጠቀም በጣም ንጹህ መንገድ ነው። ዛሬ መንግሥት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ድልድይ ወይም መንገድ መገንባት ከፈለገ ወይ ከውጭ መበደር አለበት አልያም ከብሔራዊ ባንክ መበደር አለበት። ይህ ደግሞ የውጭ ምንዛሪ ቀውስና የብድር ዘላቂነት ችግር፣ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባትን እየፈጠረ ነው። ከብሔራዊ ባንክ መበደርም የዋጋ ንረት ፈተናን ያስከትላል። ነገር ግን መንግሥት ወደ ካፒታል ገበያ ሄዶ የአሥር ወይም የሃያ ወይም የሰላሳ ዓመት ቦንድ በመሸጥ የሚፈልገውን ካፒታል ማግኘት ይችላል። ይህ ካፒታል ቀድሞውኑም በኢኮኖሚው ውስጥ የነበረ በመሆኑ ምንም ማክሮ ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ አይኖረውም። አዲስ ገንዘብ አይደለም ፈሰስ የተደረገው ወይም የገንዘብ ማተም የተገኘ አዲስ ገንዘብ አይደለም። ስለዚህ አንዱ ማሳካት የተፈለገው ዓላማ ይህ ነው።

ሪፖርተር፡- በዚህ መንገድ ብዙ ገንዘብ ከባንክ ወደ አክሲዮን ገበያው ይሸጋገራል ማለት ነው። ይህ በባንኮች የገንዘብ ልውውጥና በብሔራዊ ባንክ የገንዘብ አቅርቦት ላይ ተፅዕኖ አያሳድርም?

መለሰ ምናለ፡- በባንኮችና በአክሲዮን ገበያ ውስጥ የሚኖረው የገንዘብ ሁኔታ የተለያየ ነው። ባንኮች የአጭር ጊዜ ጥቅም የሚሰጥ ገንዘብ ይይዛሉ። በባንኮች የሚቆጥቡ ሰዎች ከተወሰነ ጊዜ በኋላ፣ አብዛኛውን ጊዜ ከወራት በኋላ የቆጠቡትን ገንዘብ ያወጣሉ። በካፒታል ገበያ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለው ገንዘብ የረዥም ጊዜ ተቀማጭ ነው። በአሁኑ ወቅት ሰዎች ከባንክ ይልቅ በሪል እስቴት ላይ ገንዘባቸውን እያወጡ ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ከባንክ የሚያገኙት ትርፍ አነስተኛ በመሆኑ ነው። ስለዚህ የአክሲዮን ገበያው በባንኮች ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል። ባንኮች የ20 ዓመታት ዕድሜ ያለው ፕሮጀክት ፋይናንስ ማበደር ቢፈልጉ ዛሬ ማድረግ አይችሉም። ምክንያቱም ባንክ ያለው ሀብት የደንበኞቹ ተቀማጭ ገንዘብ ነው። ይህ ገንዘብ የአጭር ጊዜ ተቀማጭ ነው። ባንኮች የአጭር ጊዜ ተቀማጭ ገንዘብ ሰብስበው ለረዥም ጊዜ ፋይናንስ ማበደር አይችሉም። በባንኮች ላይ ችግር ይፈጥራል።

ሪፖርተር፡- የአክሲዮን ገበያው መቼ ወደ ሥራ ይገባል ባለሥልጣኑስ መቼ ይቋቋማል?

መለሰ ምናለ፡- ቴክኒካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እየሠራን ነው፡፡ ነገር ግን ባለሥልጣኑን ለማቋቋም አንዳንድ ፎርማሊቲዎች ይቀራሉ። ለባለሥልጣኑ ዳይሬክተሮችና የቦርድ አባላትን መልምለን በዕጩነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ልከናል፣ ውሳኔያቸውን እየጠበቅን ነው። የአክሲዮን ገበያው መቼ ወደ ሥራ ይገባል የሚለውን በተመለከተ ማለት የሚቻለው፣ የአክሲዮን ገበያን የመመሥረት የሚጠይቀው ዝግጅት ብዙ ጊዜ የሚወስድ ነው። የአክሲዮን ገበያን ለማቋቋም የሚወስደው ጊዜ አንድን ባንክ ለማቋቋም ከሚጠይቀው የዝገግጅት ጊዜ በላይ ይሆናል እንጂ አያንስም። እንደዚያ ማሰቡ ይሻላል። አንደ ባንክ በሩን እስኪከፍት ድረስ ከሁለት እስከ ሦስት ዓመታት ይወስዳል። የአክስሲዮን ገበያው ከአሥራ ስምንት ወር እስከ ሁለት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተስፋ እናደርጋለን። ይህ የእኛ ዕቅድ ነው ነገር ግን በተግባር እንዴት እንደሚሆንና ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ አናውቅም።

ጠንካራ ኢኮኖሚ ያላቸው ያደጉ አገሮችም ሆነ በማደግ ላይ የሚገኙ አገሮች ለኢኮኖሚ ዕድገታቸው ቁልፍ የፋይናንስ ምንጭ የሆነው የካፒታል ገበያ (Stock Market) ወይም የገንዘብ ነክ ሰነዶች ገበ.....

24/01/2021

I will be answering any question regarding the coming stock exchange in Ethiopia.
Ask anything in the comment section.

24/01/2021

When the stock Exchange becomes operational, probably within one year, stock brokerage, share dealing and financial planning will be an attractive profession with large compensation.

If you are planning to be one of these people, we are offering a training which makes you ready for the job.

Insightful Interview about the coming stock exchange in Ethiopia.
21/01/2021

Insightful Interview about the coming stock exchange in Ethiopia.

02/01/2021

The future is bright with an Ethiopian stock market

By Elias Tsegaye

If you have been confused by the talk of stock markets in Ethiopia, you are not alone. Most people in our country are clueless about the stock markets in general, and an Ethiopian stock market in particular. So we will make it easy and start from the basics.

What is a stock?

A stock (also referred to as a share) is a guarantee that represents ownership of a fraction of a corporation. This gives the owner a claim over the corporation’s profits and assets. If you buy a stock/share in a bank, you are entitled to a fraction of its profits and you can also sell the share for a higher price in a future time. For example, if you buy a 1000 birr share in an Ethiopian bank, you will get a yearly dividend that ranges from 200 to 300 birr on average.

What is the stock market?

A stock market is a market where financial items such as stocks and bonds are sold. There can be multiple stock trading venues in a country or a region that allows transactions in stocks and other forms of guarantee.

What are the advantages of a stock market?

A stock market shows the performance of companies through their stock’s price. The higher the share prices, the more the company is perceived to be performing well. This creates completion among businesses, as it rewards the best companies and punishes those that don’t perform well.

The public can see which companies are performing well before investing their hard-earned money. The best companies get more investment and grow larger, making the country more efficient as a whole. Everyone is better off.

Does a stock market exist in Ethiopia?

Ethiopia had a share dealing group called the “Addis Ababa Share Dealing Group” during the imperial era. However, after the communist government replaced the monarchy, a command economy was put into place and the stock market was abolished. Since then an Ethiopian stock market has not been allowed to exist a

A Stock Market Will Be A Big Leap Forward For The Financial Sector In EthiopiaThe Council of Ministers, on December 22nd...
31/12/2020

A Stock Market Will Be A Big Leap Forward For The Financial Sector In Ethiopia

The Council of Ministers, on December 22nd, approved a draft law prepared by the National Bank of Ethiopia that allows Ethiopia to introduce a capital market. The bill is now under review by the House of People’s Representatives for approval. This milestone paves the way for the formation of an Ethiopian stock exchange and conveys promise that the country’s financial sector keeps upholding positive changes.

Given the government’s effort to foster a private sector-led economy, accentuated in the Homegrown Economic Reform Agenda, the 10-Year National Perspective Plan, and large privatization initiatives, the need for a capital market has become unquestionable. With the introduction of a stock exchange, there is high probability for sizable share companies to emerge and for established enterprises to be listed for new capital sourcing opportunities. Iterated by the renowned entrepreneur, Ermias Amelga, the formation of a stock market enables the pooling of new funds from the Diaspora community, creates opportunities for portfolio investors (rather than only for foreign direct investors), and reduces information asymmetries as listing requirements are usually stringent where transparency is a permanent obligation.

In a modern economy, publicly shared enterprises are at the heart of national development as they empower robust and forward-looking organizations with strong prospects for much needed employment creation. For shared companies to flourish, a stock exchange platform plays a critical role by opening investment possibilities not only for high-net worth and institutional investors, but also for ordinary individuals with small savings. Large size fund pools otherwise not mobilized, such as pension and insurance funds, will now have a vehicle to funnel capital for long-term value creation.

Importantly, a stock market provides alternative sources of capital apart from what the country is singularly used to: banks. Bank loans in Ethiopia are expensive, collateralized, and inaccessible for the majority of the business community. With the instigation of a capital market, this exclusive dependency on the banking sector will decrease and open much needed room for small & medium enterprises to access bank loans with competitive interest rates as the loan seeking crowed dwindles over time. Additionally, capital markets encourage ordinary citizens to become business owners, allows company ownership transfers to be seamless, help the government finance its fiscal deficit by borrowing from local markets with a low cost, creates a venue where investors meet fund-seekers, thereby facilitating better returns for investors, help the country regenerate the existing fragmented and uncoordinated share market to a higher level of organization. Crucial to note that Ethiopia is among the very last countries to establish a capital market even if efforts for formation have been exerted for more than two decades but to no avail. In the days of the Emperor Haile Selassie I, a stock market in Ethiopia had been established, a basic undertaking at the time. The exchange was administered by the National Bank of Ethiopia, department of Share Exchange, and later on by other financial institutions and few private share dealers labelled as the “Share Dealing Group”, engaged in facilitation of transaction of shares and other services in the stock market. The group ceased to exist in 1975 when financial institutions and large companies were nationalized and transferred into government ownership by the Derg regime.

It is recommended that the stock market should be carefully managed so as to avoid malpractices witnessed in the region with undesirable consequences (i.e. low levels of liquidity, weak institutional capacity, lack of transparency and accountability, etc.), while taking initiatives to share indispensable experiences alongside successful stock exchanges in the region and beyond.

ETHIOPIA APPROVES LAW TO INTRODUCE CAPITAL MARKETThe Council of Ministers of Ethiopia today approves a draft law prepare...
23/12/2020

ETHIOPIA APPROVES LAW TO INTRODUCE CAPITAL MARKET

The Council of Ministers of Ethiopia today approves a draft law prepared by the National Bank of Ethiopia that allows Ethiopia to introduce capital market.

After discussing the benefits of capital market and adding inputs, the Council of Minister has passed the draft law. The law is now sent to the House of Peoples Representatives of Ethiopia to be approved as law of the land that paves the way for introduction of stock market in Ethiopia. After the law is approved by the House, Ethiopia is planning to start trading of companies’ shares and stocks at a stock exchange yet to be named by next year.



Introducing capital market in Ethiopia is found to be important for economic development of the country and prosperity, according to press statement from the Office of the Prime Minister. It is indicated that companies will be able to raise funds by selling shares, stocks and bill to finance promising investment projects.

Capital market also serves citizens as an alternative saving mechanism facilitating investments in stocks. Such increase in the investments coming from domestic saving, will reduce Ethiopia’s dependent in foreign direct investment, according to the statement. It also stated that capital market plays critical role in stabilizing the macro-economy by fixing balance of payment of the country.

Including the neighboring Kenya’s Nairobi Stock Exchange, currently around 30 African countries have capital markets / stock exchanges. Ethiopia is expected to start listing of public companies, which are being regulated by the National Bank of Ethiopia such as, shares of bank and insurance companies. The introduction of stock exchange is expected to allow shareholders of the banks and insurances in Ethiopia to sell their stock any time and get their money or invest in other stocks, among others.

source; Newsbusinessethiopia

29/06/2020

እውን የአክስዮን ገበያ መጀመር ይቻላል?

የአክስዮን ገበያ ‹ስቶክ ማርኬት‹፣ ‹የድርሻ ገበያ›፣ ‹የካፒታል ገበያ› የሚሉ አቻ ትርጓሜዎችን ይሰጠዋል፡፡ የአክስዮን ገበያ ግለሰቦች በተቋማት፣ በኩባንያዎች ያላቸውን የሀብት ድርሻ የሚሸጡበት ቦታ ነው፡፡ በኳስ ሜዳ ኳስ ለመጫወት ሕጎች እንዳሉት ሁሉ፣ ገበያውን ለማከናወን የሚደረግ እንቅስቃሴም የራሱ ሕጎች አሉት፡፡

ራሱን የቻለ በመንግሥት ቁጥጥር የሚደረግባቸው ሕጋዊ ተቋማት ይኖሩታል፡፡ ተቋማቱ ግብይቶች ሕግን ተከትለው መፈፀማቸውን ይቆጣጠራሉ፤ ያሳልጣሉም፡፡

የአክስዮን ገበያ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የኢንዱስትሪዎችን መቋቋም ተከትሎ እንደተጀመረ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡
የአክስዮን ገበያ ሁለት ዓይነት አካሄድ አለው፡፡ እንደኛው ኩባንያዎች የሀብት ድርሻቸውን አቅም ላላቸው ግለሰቦች የሚሸጡበት ሂደት ነው፡፡ ይህም ዛሬ ላይ በእኛ አገር ባንኮች፣ የመድህን ድርጅቶች፣ ሪል እስቴቶች ለመቋቋም የሚሸጡት የአክስዮን ድርሻ እንደ ማለት ነው፡፡ ይህ ቡዙውን ጊዜ አዲስ ኩባንያ፣ ፋብሪካ፣ የንግድ ተቋም ለመመሥረት የሚደረግ የገንዘብ አቅም ማሰባሰቢያ መንገድ ነው፡፡ ሽያጩ በዋናነት የሚከናወነው በካንፓኒው ነው፡፡

ሁለተኛው ግለሰቦች በኩባንያዎች ያላቸውን የሀብት ድርሻ ለሌላ ሁለተኛ ወገን የሚሸጡበት መንገድ ነው፡፡ ይህም በካንፓኒው ላይ ያለን የባለቤትነት መብት የሚያስተላልፉበት መንገድ ነው፡፡ በዚህኛው የአክስዮን ገበያ፣ ሽያጩ የሚከናወነው በግለሰቦች መካከል ነው፡፡

ዛሬ በዓለም ላይ ከ200 ባለይ አገራት ግዙፍ የአክስዮን ገበያዎች በመመሥረት ከፍተኛ ገንዘብ በማንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዓመት ከ19 ትሪሊዮን በላይ ዶላር በአክስዮን ገበያ ላይ የሚንቀሳቀስ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በዓለማችን በአሁን ጊዜ ፈጣን የገንዘብ እንቅስቃሴ ከሚደረግባቸው ቦታዎች መካከል የጃፓኑ ቶክዮ የአክስዮን ገበያ የቻይናው ሻንጋይ አክስዮን ገበያ፣ በአፍሪካም ከ29 በላይ የአክስዮን ገበያ ያለ ሲሆን፣ በደቡብ አፍሪካ (እ.ኤ.አ) 1883 የተቋቋመው ጁሐንስበርግ የአክስዮን ገበያ፣ በሞሮኮ (እ.ኤ.አ.) 1929 የተቋቋመው ካዛብላንካ የአክስዮን ገበያዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ፋይዳ

የአክስዮን ገበያ ግለሰቦች ባላቸው ውስን ጥሪት የድርጅት ባለቤትነት መብትን የሚያገኙበት የተቋማት የትርፍ ተጋሪ የሚሆኑበት ሂደት ነው፡፡ አልያም በጥቂት ገንዘብ የገዙትን የሀብት ድርሻ አቆይተው አትርፈው በመሸጥ የተሻለ ገንዘብ የሚያገኙበትን ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡

በመሆኑም በግለሰቦች እጅ ያለ ሥራ የተቀመጠን ገንዘብ ወደ ገበያ በማስገባት ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡ በተለይ አሁን አሁን የኑሮ ግሽበቱ ምጣኔ ከባንኮች ዓመታዊ ወለድ መጠን ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ በሆነበት ጊዜ የአክስዮን ገበያ ለባለሀብቶች ኹነኛ አማራጭ መሆን ይችላል፡፡

በሌላ በኩል ተቋማት ለግለሰቦች ድርሻ መሸጣቸው ተጨማሪ የገንዘብ አቅም የሚፈጥርላቸው በመሆኑ ለሥራቸው መስፋፊያ እና ሥራ ማስኬጃ ተጨማሪ የገንዘብ አቅም መፍጠር ይችላሉ፡፡ ማስፋፍያዎች ሲደረጉ ደግሞ ምርት ይጨምራል፡፡ ምርት ሲጨምር የትርፍ መጠንም የዛን ያህል ያድጋል፡፡ ምርት ሲበዛ በአነስተኛ ዋጋ ለተጠቃሚዎች ምርት ማድረስ ይችላል፡፡ ማስፋፋፊያውን ተከትሎ ተጨማሪ የሰው ኀይል ይቀጠራል ሠራተኛ ሲቀጥሩም ሆነ፡፡ ዓመታዊ ትርፍ መጠናቸው ሲጨምር መንግሥት የሚያገኘው የታክስ መጠን የዚያን ያህል ይጨምራል፡፡ የሥራ አጥ ቁጥር ይቀንሳል፡፡ ዜጎች በቅናሽ ዋጋ ምርቶችን በቀላሉ የሚያገኙበት ዕድል ይፈጠራል፡፡ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ምርት የመተካት ዕድልም ይሰጣል፡፡ የአክስዮን ገበያ ሁልጊዜም ትርፋማ ያደርጋል ማለት ግን አይቻልም፡፡ ተቋማት በጠንካራ አስተዳደር እጦት የሚከስሩበት ሁኔታም ሊኖር ይችላል፡፡ የአክስዮን የድርሻ ባለቤቶች መካከል በሚፈጠሩ ግጭቶችም ተቋማት የመፍረስ ዕድል ሊገጥማቸው ይችላል፡፡

የአክስዮን ገበያ በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ አክስዮን ቀድመው ከጀመሩ አገራት መሀል ተጠቃሽ ነች፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ዛሬ ላይ አገሪቷ ሕጋዊ ማዕቀፍ ያለው የአክስዮን ገበያ ከሌላቸው ጥቂት አገራት አንዷ ናት፡፡ በኢትዮጵያ የአክስዮን ገበያ የተጀመረው በቀዳማዊ አፄ ኀይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በ1930ዎቹ የመጨረሻዎቹ ዓመታት እንደነበር ጽሑፎች ያስረዳሉ፡፡

ከአርባ አምስት ዓመት በፊት ደርግ ሥልጣን እስኪይዝ የአክስዮን ግብይት ለ15 ዓመታት ገደማ ይደረግ እንደ ነበረ የሚናገሩት በሰዓቱ የአክስዮን ገበያው ተሳታፊ አቶ ኀይሉ ገብረ እግዚአብሔር ናቸው፡፡ “በቀዳማዊ አፄ ኀይለ ሥላሴ ዘመን 21 ኩባንያዎችን ማክሰኞ ተሰብስበን እንሻሻጥ ነበር፡፡ ሐሙስ ገንዘቡን እንቀያየር ነበር፤” ይላሉ፡፡

አቶ ኀይሉ በኋላ የእዝ ምጣኔ ሀብታዊ አመራርን የሚከተለው ደረግ ሥልጣን ሲይዝ ሁሉም ነገር እንደቀረ በማስታወስ ይናገራሉ፡፡

ከደርግ ቀጥሎ ወደ ሥልጣን የመጣው ኢሕአዴግም ቢሆን የነጻ ገበያን እከተላለሁ ቢልም የአክስዮን ገበያን ሕጋዊ ማዕቀፍ ባለው መልኩ ለማቋቋም እስካሁን አልደፈረም፡፡ ከቅርብ ወራት ወዲህ የአክስዮን ገበያን በአገሪቷ ለመጀመር የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረገ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. እስከ 2020 ድረስ ገበያውን በኢትዮጵያ ለማስጀመር ውጥን ተይዟል፡፡

የአክስዮን ገበያው ምን ይፈልጋል?

የአክስዮን ገበያ ከፍተኛ ቢሊዮን ብሮች የሚንቀሳቀሱበት ገበያ እንደመሆኑ መጠን ጥንቃቄን የሚሻ ገበያ ነው፡፡ በመሆኑም እንቅስቃሴውን የሚቆጣጠሩ ጠንካራ መንግሥታዊ ተቋማት መኖራቸው የግድ ይላል፡፡ የተቋማቱ ግንኙነትም በጠንካራ መሠረት ላይ መመሥረት አለበት፡፡
የገበያው በርካታ እንቅስቀቃሴ በኤሌክትሮኒክ መሣሪያ የሚታገዝ በመሆኑ ቀላጣፋ የኢንትርኔት አገልግሎት እንደሚፈልግ የሰርብሩስ ካምፓኒ ፕሬዝዳንት እና የዘርፉ ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ኀይለ ሚካኤል ይገልጻሉ፡፡

ባለሀብቱ ስለሚገዛው ካምፓኒ፣ ስለዋጋው፣ የወደፊት ዕቅድ መረጃዎችን በድረ-ገጾች አማካኝነት የሚያገኝ መሆኑን የገለፁት ባለሞያው አስተማማኝ ኢንተርኔት፣ የማይቆራረጥ ኀይል፣ ጠንካራ የመረጃ ቋት፣ የሰለጠኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሞያዎች፣ ለዘርፉ የግድ አስፈላጊ መሆናቸውን ያነሳሉ፡፡

ከሁሉም አስቀድሞ ግን የአክስዮን ገበያ በሕግ እና በሥርዓት መመራት እንዳለበት የሚገልፁት አቶ ተስፋዬ ገበያውን የሚያውቅና የሚያግዝ ተቋም መገንባት እንዳለበት ያነሳሉ፡፡ ከመንግሥት ተቋማት አቅም አንጻር ስለ አክስዮን ገበያ የሕግ አውጭው አካል (የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት) ቅድሚያ ግንዛቤው ሊኖረው ይገባል የሚሉት ባለሙያው፣ የሚወጣው ሕግ በደንብ የተጠናና ሊያሠራ የሚችል ልምድ ባላቸው ሰዎች መዘጋጀት እንዳለበት ይገልጻሉ፡፡

በገበያው ውስጥ የሚደረገውን የንግድ ልውውጥ ካላይ ሆኖ የሚቆጣጠር የስቶክ ልውውጥ ኤጀንሲ መኖር አለበት የሚሉት አቶ ተስፋዬ ኤጀንሲው ማን ከማን አክስዮን ገዛ? በስንት ተሸጠ? ምን ያህል ትርፍ ተገኘ? የሚለውን የመቆጣጠር ኀላፊነት እንደ ሚኖረውም ያብራራሉ፡፡ በካንፓኒዎች የሚሠሩ የኦዲት ሪፖርቶችን ትክክለኝነት የሚያረጋግጥ፤ የኦዲተሮችን ብቃት ደረጃ የሚያወጣ እና የሚለካ፤ ራሱን የቻለ መንግሥታዊ የኦዲት ተቋጣጣሪ ተቋም መኖር እንዳለበት ያነሳሉ፡፡

ሕጎች ተጥሰው ሲገኙ ሕግ የሚያስከብር፣ አጥፊዎችን ሊቀጣ የሚችል ሌላ ተቋም ሊኖር ይገባል ሲሉ በአሜራካን ሀገር ከሰሩበት ልምዳቸው ተነስተው ይመክራሉ፡፡ ሌላው የአገሪቱ

Tesfaye Boru, [28.06.20 20:17]
ን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚቃኝ እና ፖሊሲን የሚያዘጋጅ ፍቃድ የሚሰጠው የብሔራዊ ባንክ ከተጠቀሱት ተቋማት ጋር በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው አቶ ተስፋዬ ያብራራሉ፡፡

የአክስዮን ገበያ ፈተናዎች

ኢትዮጵያ የአክስዮን ገበያን ቀድመው ከጀመሩት ሀገራት መካከል ብትሆነም ዛሬ ግን ሕጋዊ ማዕቀፍን የተከተለ የአክስዮን ገበያ የላትም፡፡

በሀገሪቱ የተደረገውን የፖለቲካ ሽግሽግን ተከትሎ ወደ ሥልጣን የመጣው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተዳደር የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት ከገባበት ቀውስ ለማውጣት በርካታ አማራጭ ውጥኖችን አውጥቶ ሲንቀሳቀስ ይስተዋላል፡፡
ከቅርብ ወራት ወዲህ በሀገሪቱ የአክስዮን ገበያን ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑን ከመንግሥት በኩል ሲገለፅ እየተደመጠ ነው፡፡

በ2020 የአክስዮን ገበያን ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ገልፀው ለዚህም አንድ ቡድን ተቋቁሞ እየሠራ እንደሚገኝ አክለው ተናግረዋል፡፡ ዛሬ ላይ የቡድኑ የጥናት ውጤት ምን ላይ እንደ ደረሰ ባይታወቅም በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት ግን ገበያውን ለማስጀመር ውጥን ተይዞ ነበር፡፡

አክስዮን ገበያ በአገሪቱ መጀመር አለበት በሚለው ላይ ልዩነት እንደሌላቸው የሚናገሩት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች አሁን ሀገሪቷ ባላት የመሠረተ ልማት እና የተቋማት አቅም ላይ ግን እምነት እንደሌላቸው ሲገልፁ ይደመጣል፡፡
አቶ ተስፋዬ እንደሚሉት ከሆነ የአክስዮን ገበያ ጠንካራ የሆነ የኢንተኔት ፍጥነትን በቴክኖሎጂ የዳበረ ልምድ ያለው ባለሞያና የማይቆራረጥ ኀይል መኖር እንዳለበት ያነሳሉ፡፡ በአገሪቱ ያለው የኢንተርኔት እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደከማ በመሆኑ የአክስዮን ገበያን በኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ማስጀመር አዳጋች እንደሚሆንም ይገልጻሉ፡፡ የ‹አይ ኮ የቴክኖሎጂ ካንፓኒ› ተወካይ አቶ ታጋይ ሞላ ግን በዚህ ሐሳብ አይስማሙም፡፡ በሀገሪቷ ያሉት ባንኮች ከከተማ እስከ ገጠር ያላቸው እንቅሥቃሴ ቴክኖሎጂን ማዕከል ያደረገ ስለመሆኑ ይገልጻሉ፡፡

አብዛኛዎቹ የፋይናንስ ተቋማት በኢንተርኔት የታገዘ ሥራዎችን የሚሠሩ መሆኑን የሚያነሱት አቶ ታጋይ አብዛኛዎቹ የራሳቸውን የመረጃ ቋት ገንብተው እየሠሩ ነው፡፡ በዚያም ትርፋማ ናቸው ይላሉ፡፡ አሁን ያለውን የቴክኖሎጂ አቅምን አዳዲስ ከሚመጡ የቴክኖሎጂ ግኝቶች ጋር ተደማምሮ የአክስዮን ገበያ የሚፈልገውን የቴክኖሎጂ አቅም መፍጠር እንደሚቻል ያብራራሉ፡፡

የአክስዮን ገበያ ከሁሉ አስቀድሞ ሕጋዊ መሠረት እንዲኖረው ያስፈልጋል የሚሉት አቶ ተስፋዬ፣ የአክስዮን ድርሻ ሸጠው ወደ ሥራ ሳይገቡ ዓመታትን ያሳለፉ ካንፓኒዎች በርካታ መሆናቸውን በማንሳት፣ ይህ ክፍተት የመጣው ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ነው ይላሉ፡፡
ሰዎች ለሚያወጡት ገንዘብ ሕጋዊ መተማመኛ እንደሚፈልጉ ገልፀው፣ ገበያን ሊመራ የሚችል ሕግ እና መመሪያ በጥንቃቄ መሠራት እንዳለበት ያብራራሉ፡፡

የአክስዮን ገበያ̎ በጨበጣ̎ የሚጀመር አይደለም የሚሉት ባለሙያው ̎በአገሪቱ ስንት ፕሮጀክቶች ተጀምረው ለፍሬ ሳይበቁ ዓመታት ተቆጥረዋል? ይህን ደካማ የተቋማት የማስፈፀም አቅም ይዘን የአክስዮን ገበያን መቀላቀል አስቸጋሪ እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡

አሁን ያሉት ተቋማት የሚታመሰውን የማክሮ ምጣኔ ሀብት ማረጋጋት ባልቻሉበት፤ በተቋማት ፍትሐዊ አሠራር ባልሰፈነበት፣ ሕገ ወጥ ደላላን መቆጣጠር ያቃተው የመንግሥት ተቋም ባለበት፣ የአክስዮን ገበያን መጀመር፣ ‹ሲሮጡ የታጠቁት› እንዳይሆን ቅድሚያ የተረጋጋ ጥናት ማድረግና የተቋማትን አቅም ማሻሻል ይፈልጋል፡፡

ገበያውን መምራት የሚችል ልምድ ያለው ተቋማት ግንባታ መቅደም እንዳለበት የሚያነሱት አቶ ተስፋዬ ጠንካራ አሠሪ ሕግና ተቆጣጣሪ አካላት በሌለበት ሁኔታ የአክስዮን ገበያ መመሥረት እንደማይቻል ይገልጻሉ፡፡ ‹ወጡ ከእንጀራው ቀደመ› እንዳይሆንም ለአክስዮን ገበያ ሊውሉ የሚችሉ በቂ ኩባንያዎች አሉን ወይ? የሚለውም ጥያቄ መመለስ ያለበት ጉዳይ እንደሆነም ይናገራሉ፡፡ የኀይል አቅርቦት አስተማማኝ ባልሆነበት፣ ኢንተርኔት በተደራሽነትም በፍጥነትም አዝጋሚ በሆነበት እና የተቋማት ሕግ የማስፈፀም አቅም ደካማ በሆነበት ሁኔታ እነዚህን ፈተናዎችን ተቋቁሞ በ2020 የአክስዮን ገበያ በኢትዮጵያ እውን ሊሆን ይችላልን? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡

(ይስሐቅ አበበ)
https://www.facebook.com/109685953824694/posts/189348065858482/

It will be a game-changer for the investment practices of the country.
26/05/2020

It will be a game-changer for the investment practices of the country.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ለማቋቋም የሚያስፈልጉትን የሕግ ማዕቀፎች አዘጋጅቶ ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ሰሞኑን እንደ....

Address

Addis Ababa
1212

Telephone

+251991215483

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habesha stock exchange posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share