Zinu ye kolfe

Zinu ye kolfe Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Zinu ye kolfe, Marketing Agency, Kolfe, Addis Ababa.

የአዲስ አበባ ለውጥ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲና የኮንፍረንስ ማዕከልነቷን ያደሰችበት ጉዞ ነውኢትዮጵያ ታሪካዊ የአፍሪካ መዲናነቷንና ዲፕሎማሲያዊ ገጽታዋን በአዲስ መልክ በመገንባት፣ በዓለም አቀፍ ...
21/07/2026

የአዲስ አበባ ለውጥ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲና የኮንፍረንስ ማዕከልነቷን ያደሰችበት ጉዞ ነው

ኢትዮጵያ ታሪካዊ የአፍሪካ መዲናነቷንና ዲፕሎማሲያዊ ገጽታዋን በአዲስ መልክ በመገንባት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የኮንፍረንስና የኤግዚቢሽን ማዕከል ለመሆን በቃች። ​በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መሪነት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተከናወኑት ግዙፍ ፕሮጀክቶች አዲስ አበባን ለአለም አቀፍ ጉባኤዎች ይበልጥ ማራኪና ዝግጁ አድርገዋታል።

አድዋ ድል መታሰቢያ ግዙፍ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ሁነቶችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዘመናዊ የአዳራሽና ኤግዚቢሽን ማዕከል፣ የአፍሪካ ህብረት አዲስ አዳራሽና አቪዬሽን ከተማ፣ ግዙፍ አየር ማረፊያዎችንና መስተንግዶዎችን ጨምሮ የተከናወኑ የትራንስፖርትና የሎጅስቲክስ ማሻሻያዎች ይበልጥ ተመራጭ አድርጓታል። በተጨማሪም ወዳጅነት ፓርክ፣ የእንጦጦ ፓርክና የዓመታት የሸገር ውበት ፕሮጀክቶች ለአለም አቀፍ እንግዶች ምቹ፣ ጽዱ እና አረንጓዴ አካባቢን በመፍጠር የመዲናዋን ገጽታ ሙሉ በሙሉ ቀይረዋል።

24/06/2026
ዋናው ጤና ፡- የላፍቶ ሆስፒታል ምረቃ እንድምታዋናው ጤና ነው ይላል አገራችን ብሂል ፡፡ ትክክል ነው፡፡ ጤና ሁሉም ነገር ነው፡፡ ለውጡም ይሄን የጤና ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶበት ሲሰራ ቆይ አሁ...
27/05/2026

ዋናው ጤና ፡- የላፍቶ ሆስፒታል ምረቃ እንድምታ

ዋናው ጤና ነው ይላል አገራችን ብሂል ፡፡ ትክክል ነው፡፡ ጤና ሁሉም ነገር ነው፡፡ ለውጡም ይሄን የጤና ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶበት ሲሰራ ቆይ አሁን ላይ ውጤቶቹን ማየት ጀምናል፡፡ ከእነዚህ የለውጥ ውጤቶች መካከል ደግሞ ሰሞኑን የተመረቀው የላፍቶ ሆስፒታል ነው፡፡

ሆስፒታሉ በ5.4 ሄክታር ላይ የተገነባ ሲሆን 17 ህንፃዎችን በውስጡ ያካተተና 500 አልጋዎች ያሉት አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የተገነባ ትልቅ ሆስፒታል ነው፡፡ በውስጡ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የያዘው ይኸው ሆስፒታል መሬቱና ግድግዳዎቹ በራሱ ፀረ-ባክቴሪያ እንዲሆን ታስቦ የተገነባ ሆስፒታል ነው፡፡

በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተደገፈው የሆስፒታሉ መሳሪያዎች ስንሰማቸው እንግዳ የሆኑ ምጡቅ ቴክኖሎጂዎችን በውስጡ አካትቷል፡፡ በዚህም ካንስርና የልብ ህመመን የመሳሰሉ ክፍተኛ ትኩረት የሚጠይቁ በሽታዎችን በከፍተኛ ደረጃ ለማከም የሚያስችል ሆስፒታል ነው፡፡

የዚህን ዘመናዊ ሆስፒታል መመረቅ አስመልክቶ የከተማችን አስተዳር ከንቲባ አዳነች አበቤ እንዳሉት የከተማችን አስተዳደራችን ለህዝቡ ጤና ፣ ደህንነትና ክብር የሰጠውን ትልቅ ትኩረት በተግባር ያሳየንበት አንዱ የጋራ አሻራችን ነው ብለዋል፡፡

ለከተማችንም ላፍቶ ሆስፒታል ፋይዳው ብዙ ነው፡፡ በአፍሪካ በዴፕሎማሲ ማዕከልነት የ3ኛደረጃ የያዘችውን ከተማችንን በጤናውም ዘርፍ የጤና ቱሪዘም መዳረሻ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡ ለህክምና ወደ ውጪ የሚወጣውን የአገር ሀብት በማስቀረት በአገር ውስጥ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ህክምና ለመስጠት ትልቅ ፋይዳ ያለው ነው፡፡

27/05/2026
እራሱ በሶሻል ሚዲያ ታውቆ እየሸቀለበት ሀገር ለምን በሶሻል ሚዲያ ተዋወቀች እያለ ነውያለፈው የመንግስት አገዛዝ ስርዓት የሀገሪቱን አንጀት ሲበላ ኖሮ በለውጥ ላጲስ ተፍቆ እስኪጠፋ ድረስ ኤል...
22/05/2026

እራሱ በሶሻል ሚዲያ ታውቆ እየሸቀለበት ሀገር ለምን በሶሻል ሚዲያ ተዋወቀች እያለ ነው

ያለፈው የመንግስት አገዛዝ ስርዓት የሀገሪቱን አንጀት ሲበላ ኖሮ በለውጥ ላጲስ ተፍቆ እስኪጠፋ ድረስ ኤልያስ መሰረት የሚባል ጋዜጠኛ ድምፅ አልነበረውም ምክንያም የፈሪሃ-ስልጣን ሰለባ ነበረና! ዛሬ ግን ሀገሪቱ በምትሄድበት እያንዳንዷ የለውጥ እርምጃ ላይ እንቅፋት ለመሆን 24 ሰዓት የሚቃወም "ፕሮፌሽናል ተቃዋሚ" ሆኗል።

ሰሞኑን የአለማችን ታዋቂ የሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የኢትዮጵያን መነሳትና ውበት እያደነቁ ሲመላለሱ፣ የነ ኤልያስ የቅናትና የጥላቻ ድባብ ግን ጨፍኗል። የሀገር ስም ሲነሳ የሚቆረቁራቸው ይሄ የኤሊያስ አካሄድ እኮ የጀማሪ ተቃዋሚ ሙድ ነው፤ በተቃውሞ 18 ዓመት ሲሞላው እንደ አሮጌ ወይን ይሰክናል፣ አሁን ግን ገና ነው።

በእወነት ሀገር ከፍ ስትል አብረህ ከፍ ማለት ካቃተህ፣ ውድቀትህ የራስህ እንጂ የሀገር አይደለም። ችግርን ብቻ እየለቀሙ ማውራትና መልካሙን ነገር መደበቅ የጋዜጠኝነት ሳይሆን የባንዳነት ባህሪ ነው!እራሱ በሶሻል ሚዲያ ለመታወቅ እየተጋጋጠ፣ በእሱ እየሸቀለ ሀገር ለምን በሶሻል ሚዲያ ተዋወቀች እያለ ነው። ቢያውቅ ዛሬ እየተዋወቀ ያለው ነገ ይሄ መንግስት ሲያልፍም የሀገራችን ስም ግን በወርቅ ቀለም ተፅፎ የሚቀርበት መንገድ ነበር።

Address

Kolfe
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zinu ye kolfe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share