08/06/2026
4 ሎሚ ገበያ ይዘው የወጡት እናት ( እመትገሎ ኮበሺህ)!
"በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አራት ፍሬ ሎሚ ይዘው ለመሸጥ ገበያ ወጥተው በነበሩበት ምስላቸው የብዙዎችን ልብ የሰበሩትና ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆኑት እናት እመት ገሎ ኮበሺህ፣ ሰይፉ ፋንታሁን አጊንቷቸዋል።
እመት ገሎ (Gelo Kebeshi) ይባላሉ። በአዲስ አበባ ከተማ ከ20 ዓመታት በላይ ኖረዋል። አማርኛ ቋንቋ ብዙም ስለማይችሉ የሚግባቡት በጉራጊኛ ነው።
ህይወታቸውን በጉሊት ንግድ እየደገፉ፣ በዚህ እድሜአቸው ዛሬም ድረስ በላስቲክ በተሰራ ጎጆ (መጠለያ) ውስጥ ነው የሚኖሩት።
እማማ ወደ ገበያ የወጡት 4 ፍሬ ሎሚ ብቻ ይዘው ነበር። የያዟት 4 ሎሚ ተሸጣላቸው፣ ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው የሚሆን አንድ እንጀራ ገዝተው ለመግባት... የቤት ነገር ቢያስጨንቃቸው እንጂ በዚህ በደከመ እድሜአቸው ድጋፍ እንጂ ድካም አይገባቸውም ነበር።
እማማ ሰው እጅ ከመጠባበቅና ከመለመን ይልቅ፣ በወዛቸው ሰርተው ለመኖር የሚያሳዩት ተጋድሎ ለእኛ ለወጣቶቹ ትልቅ የሥራ ፍቅርና የጽናት ትምህርት ነው። ነገር ግን አቅማቸው የደከመ አረጋዊ እናት በመሆናቸው የሁላችንም ሰብአዊ ድጋፍ አሁን ያስፈልጋቸዋል።
የእማማን እንባ ማበስ የሁላችንም ድርሻ ነው።የባንክ አካውንት፦1000769117125 Gelo Kebeshi (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)"