20/02/2023
ኢትዮጵያ- በመሰዋትነት የጸናች ሀገር
የካቲት 12 ሲዘከር እናዛን ብርቱ እና ጀግና አባቶቻችንን ለማስታወስ ፤ ለሕዝብ አንድነትና ክብር የተዋደቅ ጀግኖቻቸንን ከአደዋ ዳግም ከ40 አመታት በኃላ የኢጣሊን ግፍና ወረራ ከታሪክ ማህደር መዘን እናስታዉስ፡፡
ዘመኑ እ.ኤ.ዘ.አ 19 88 ዓ.ም ከዉጫሌ ስምምነት ምክንያት የአፍሪካን የመቀራመትና የኢጣሊያኛዉ ቅጅ ሰነድ በመጻፍ ለሀያላን ሀገራት እውቅና በመቃወም ኢትዮጵያዊያን አንድ በመሆን የመጣዉ የኢጣሊን ጦር በማሸነፍ ነጻነታቸዉን ያወጁበት በኃላም ለአፍሪካ ነጻ መዉጣት ትልቅ መሰረት የጣለ ታሪካዊ ክስተት ነበር፡፡
ይህንን ሽንፈት ተከትሎ የኢጣሊ መንግስት ለ40 አመታት ኢትዮጵዮጵያን በሚሲዮን ፣ በትብብር በሚል ስበብ ሲያጠና ከቆየ በኃላ ለሽንፈት የዳረጋቸዉን የኢትዮጵያን አንድነት በማዳከም (በመጣዉ የህዝቡ አስተሳሰብ የሚሉም የታሪክ ድርሳናት እንዳሉ ልብ ይሏል) በዳግም ወረራ ለ5 አመታት ሀገሪቱን ቢቆጣጠራትም ፣ በዉስጥ አርበኞት እና በተሰራዉ የዲፕሎማሲ ስራ ሀገሪቱን ለአንደየና ለመጨረሻ ለቆ ሊሄድ ችሏል፡፡
ይህ ሲሆን በ19 29 ዓ.ም አብረሃም ደቦጭ ፣ ሞገስ አሰግዶም እና ስምኦን አደፍርስ በግራዛይኒ ላይ የጣሉት ቦንም ክፉኛ ስላቆሰለ አጸፍዉን ከ30 ሽህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ በግፍ ተገለዋል፡፡
የካቲት 12 ኢትዮጵያ ዳግም ሉአላዊኗን ያረጋገጠችበት ፤ ዋጋ የተከፈለላት ነች፡፡ ከዚህ ትዉልድ ከኃላ ቀር ለመዉጣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፣ የዘመነ ፖለቲካ ያስፈልገዋል፡፡
ትዉልዱ በጨቋኝና ተጨቋኝ የታሪክ ፕሮፖጋንዳ ወጥቶ ለስራ ፣ ለትምህርት እና እድገት ሊተጋ ያስፈልጋል፡፡
በታሪክ የብሔር ጭቆና ሳይሆን የ ገዥ መደብ ጭቆና ነዉ፡፡ ሁሉም ሕዝብ በፌዉዳሉ ገዥ መደብ ሲበደል የነበረ ነዉ፡፡
ኢትዮጵያ የነቃ ትዉልድ ያስፈልጋታል!
ለተጨማሪ መረጃ ፡-