Tegulet Media and Promotion

Tegulet Media and Promotion ተጉለት ሚዲያ የባህል የታሪክና የኪነ-ጥበብ ዐምድ ፈር ቀዳጅ፤ የሁነት የገበያ ትስስርና የመገናኛ ብዙኃን ሥራዎች አገልግሎት ማቀናጀትና ዓለም-አቀፍ ገቢ ማሰባሰብ ዘርፍ የካበተ ልምድ ያለው ኩባንያ ነው! ሠላም ፍቅርና ከፍታ ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ!

በ1.9 ቢሊዮን ብር የተገነባው ኃይሌ ሆቴል ደብረ ብርሃን ተመረቀ በታዋቂው አትሌትና ኢንተርፕረነር ኃይሌ ገብረስላሴ ባለቤትነት የሚመራው የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግሩፕ፣ በ1.9 ቢሊዮን ብ...
23/04/2026

በ1.9 ቢሊዮን ብር የተገነባው ኃይሌ ሆቴል ደብረ ብርሃን ተመረቀ

በታዋቂው አትሌትና ኢንተርፕረነር ኃይሌ ገብረስላሴ ባለቤትነት የሚመራው የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግሩፕ፣ በ1.9 ቢሊዮን ብር ወጪ ያስገነባውን ዘመናዊ ሆቴል ዛሬ ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ከተማ በድምቀት አስመረቀ። ሆቴሉ የድርጅቱ 11ኛ መዳረሻ ሆኖ ተመዝግቧል።

​ይህ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት በኢንዱስትሪ ከተማዋ ደብረ ብርሃን ያለውን ከፍተኛ የእንግዳ ማረፊያ ፍላጎት ለመሙላትና የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ ተገልጿል። ሆቴሉ በህንፃ ጥራቱና በውስጡ በያዛቸው ዘመናዊ መገልገያዎች በከተማዋ ቀዳሚ ተጠቃሽ ሆኗል።

​በ1.9 ቢሊዮን ብር የተገነባው ይህ ሆቴል፣ ለታላላቅ እንግዶችና ለቱሪስቶች ምቹ የሆኑ 123 መኝታ ክፍሎችን ይዟል። ከዚህም በተጨማሪ አራት የተለያዩ ሬስቶራንቶች፣ የመጠጥ አገልግሎት የሚሰጡ ባሮች፣ ጂምና የሳውና አገልግሎቶችን ያካተተ ነው። ትላልቅ ስብሰባዎችንና ማህበራዊ ኩነቶችን ለማስተናገድ የሚያስችሉ ስድስት ዘመናዊ አዳራሾችም ተገንብተውለታል።

​የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግሩፕ ባወጣው መረጃ መሰረት፣ ሆቴሉ በአሁኑ ወቅት ለ200 በላይ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፤ በቀጣይ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የሠራተኞቹ ቁጥር ወደ 300 ከፍ እንደሚል ታውቋል።

ሻለቃ ኃይሌ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገረው​በቀጣይ በጎንደር፣ በሐረር እና በድሬዳዋ ከተሞች የሚገነቡ ሆቴሎችን በማጠናቀቅ ለምረቃ እንደሚያበቃ ተጠቁሟል። ይህም ድርጅቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የኢንቨስትመንት አሻራ ይበልጥ እንደሚያሰፋው ታምኖበታል። ከኢትዮጵያ ውጪ ኃይሌ ሆቴል በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ለማስፋት እንቅስቃሴ እንደተጀመረ ተነግሯል።

ሀይሌ ግራንድደብረ ብርሃን
23/04/2026

ሀይሌ ግራንድ
ደብረ ብርሃን

10/04/2026
10/04/2026

እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሠላም አደረሰን አደረሳችሁ።

እነሆ አጅግ ግዙፉና በአሠራሩ ድንቅ የሆነው የአያት ፀበል መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን ግንባታ በአባቶቻቺን ፀሎትና በእናንተ ደጋግ ኦርቶዶክሳዊያን ርብርብ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል።

በሙቅ ፀበሉና በፋዋሽነቱ በሚታወቀው አያት ፀበል መድሀኔዓለም ቤተክርስቲያን በርካቶች ከክፉ ደዌ ተፈውሰው ድህነትን በማግኘት ለአለም መሥክረውበታል።

የዚህን ገናና ደብር ቤተመቅደስ በአጭር ጊዜ ለማስፈፀም በሚደረገው ርብርብ በአለም ዙሪያ ያላችሁ ምዕመናን ሁሉ እንድትሳተፉ የአደራ ጥሪ ቀርቦላችኋል።

ለድጋፋችሁ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሂሳብ ቁጥር

CBE-1000589534337
CBE- አጭር ቁጥር -2627

ለተጨማሪ መረጃ

📞
09-1 1-43- 13-37
09 -79 -41- 74- 09

አያት ፀበል መድሃኔዓለምና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን!

እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!መልካም በዓልተጉለት ሚዲያ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ
10/04/2026

እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል

ተጉለት ሚዲያ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ

26/03/2026

ምኒልክ ያችን ሰዓት
(ጋሻው ደበበ አለሙ )

የካቲት 23/ 1888 ማለዳ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት እምዬ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ አድዋ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ያረጉት ፀሎት

መነሻ ሐሳብ- ማስረሻ ፈጠነ (ፕሮፌሰር)
አርትኦት - አሰግደው ሸመልስ

ዝክረ- አድዋ

የካቲት 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

"ቅዱስ ዑራኤል""የብርሃን ጌታ፣ የአምላክ ብርሃን" ✝️ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በመሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ፣✝️ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር...
24/03/2026

"ቅዱስ ዑራኤል"

"የብርሃን ጌታ፣ የአምላክ ብርሃን"

✝️ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በመሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ፣

✝️ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃን መነሳነስ በዓለም ላይ የረጨ መልአክ፣

✝️ለነቢዩ ዕዝራ ስቱኤል ጽዋ ጥበብን ያጠጣ መልአክ ፣

✝️ሰማያዊውን ዕውቀትና ጥበብ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የገለጠ መልአክ፣

✝️ለነቢዩ ሄኖክ የሰማይን ምሥጢርና ሰማያዊውን ዕውቀት የገለጠ መልአክ፣

✝️የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሠማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ መልአክ፣

ቅዱስ ዑራኤል በምልጃው አይለየን

ካዛንቺስ የሚገኘውን ጥንታዊ ደብር፤ የደብረ ፅጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን መራሔ ብርሃናት ሰንበት ት/ቤት ጅምር ሕንጻ ለማስፈፀም በሚደረገው አለም ዓቀፍዊ የድጋፍ ርብርብ ሁላችንም የበኩላችንን እናድርግ!

የድጋፍ ማድረጊያ ባንክ አካውንቶች

✅ንግድ ባንክ ➖2221
✅አባይ ባንክ ➖2222

✅ቴሌ ብር➖0949098301
(አዲሱ ኢብራሄም-የሰንበት ት/ቤቱ ዋና ፀሀፊ)

የውጭ ሀገር የገንዘብ ማሰባሰቢያ አካውንቶች

✅Cashapp➖ $merahe22
✅Zelle ➖4044726429
(Alazar Tefera)

የማህበራዊ ሚዲያ መገናኛ መረቦች

Facebook- merahe 22
TikTok -merahe 22
YouTube- merahe 22

ለተጨማሪ መረጃ

📞
+251977-25-22-22

18/03/2026

በሱፍቃድ ሪል እስቴት

02/03/2026
ምኒልክ ያችን ሰዓት       (ጋሻው ደበበ አለሙ)▫️መነሻ ሀሳብ -ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ ▫️አርትኦት- አሰግደው ሽመልስ የካቲት 23/ 1888 ማለዳ  ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት  እምዬ ዳግማ...
01/03/2026

ምኒልክ ያችን ሰዓት

(ጋሻው ደበበ አለሙ)

▫️መነሻ ሀሳብ -ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ
▫️አርትኦት- አሰግደው ሽመልስ

የካቲት 23/ 1888 ማለዳ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት እምዬ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ አድዋ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ያረጉት ፀሎት

ስብሐት ለእግዚአብሔር- ኅያው በመንበሩ
ሰላም ለዛቲ -ሃገሪትነ ቅድስት
ወሰላም ለህዝብየ- ዘይሔሉ ለምድሩ
ዘይመውት -ለክብሩ ፡፡

ምስጋና ለሕያው አግዚአብሔር
ሰላም ለዚህች -አንድ ቅድስት አገር
ሰላም ለደጉ ህዝቤ-አፈሬን ብሎ ለሚኖር

ክብር ላንተ-ሰማዕቱ የእናት የአባቴ ታቦት
ጊዮርጊስ መመኪያዬ-እንግዴህ ከፊቴ ዝመት
መንገድ ጥረግ ፈረሰኛው -ቀዳማዊው ሰራዊት

ተማርኩ ያለ አገር ሊዘርፍ-ውል አዛንፎ በለበጣ
የነገር ፈሩን ስንጨብጥ -ለሴራው ብልሐት ሲያጣ
ለጦር ልቡ ሸፍቶ -ዳር ድንበር ጥሶ ከመጣ
ፈርሐ-እግዜር የሌለው ጣሊያን -ህዝቤን በጅምላ ሲወር
በህዝቤ ተደምስሶ -አደዋ አረህ ውስጥ ሲቀር
በሟጥሽ ስር ተበትኖ -በአጋም ስራስር ሲሰባበር
እለቱ በደም ታፍኖ-ሰልስቱን በአሞራ ሲያከብር
ኪደነ-ምህረት ገሰሶ-ምንድብድብ ሸዊቶ ሜዳ
እማርክ ብሎ የመጣ -ሞቱ በአፍታ ቢረዳ
እኔ ክፉ እማይደለሁ -ልቤን ቅር እንዳይለው ነገር
መቼም ነፍሰ-እግዚሃር ነውና…
ክብር ለሃያሉ አምላክ -ቃሌን ቀድሜ ልናገር ፡፡

ቴወድሮስ ይሙት! ቃሌ ነው!!
እኔ ምኒልህ …
አይኑን ለጨፈነ ጠላት -እዝኑን ለደፈነ ጦረኛ
መልህቅ ቢያነሳ ብዬ እንጂ -ይሔ ነጭ ነውረኛ
አወድመው እንደሳት ሰደድ -እመታው እንደመጋኛ፡፡

እንዴት አይነት ጥጋብ ነው ? እንዴት አይነት መወፍነን?
ምኒልክን ለባርነት- ኢትዮጵያን ለቅኝ ግዛት
አሳብ ጠንስሶ መጅመንመን?

እንዴት አይነት ንቀት ነው -ምን የሚሉት ሰማይ ማከክ?
ጣሊያን ሱሪ የለበሰው ሐበሻን ለማንበርከክ?.....

አዬ ያገሬ ጀግና
አንጀተ ፅኑው ገበሬ
በማርያም መማፀኔን -ያገር አዋጄን ሰምቶ
ከመናገሻ እስከ ሀረር በጌምድር ተጠራርቶ
የአራት ማዕዘን -ጀግና ድፍን ኢትዮጵያ ተነስቶ
በሮቹን ባለህ ባይ ሳይኖር -ዝሪቱን ለተባይ ትቶ
ወንጭፉን ከማማ ሰቅሎ -ጦርና ጋሻ አንግቶ
ምኒልህ ጠራኝ ብሎ -በጭብጦ ተሸኝቶ
በእፍኝ ጥሬ-ከቤት ወጥቶ
ላመል ታህል በኮዳ ውሃ-ከምንጭ በቅል ጠጥቶ
ለእግሩ ከለላ ሳይኖረው -አሜኮላውን ጥሶ
ጫካውን በግር በፈረስ -ዥው አርጎት እንደኮሶ
ላገር ሟቹ ቃል ጠባቂው ይሔው አደዋ ከተመ
ለነፃነቱ እልፍ ሆኖ -ለክብሩ በአንድ ተመመ
የአብሮነት ቃልኪዳኑን -በባንዲራው ስም አተመ፡፡

እና ከዚህ በላይ -ምን ደስታ አለ?
ከህዝብና ከክብሩ- ሰው ካገሩ ከዋለ

እምነትና ጀብዱን ታጥቆ -አገሩን ብሎ ለመጣ ሰው
እስከ አፅናፍ የሚነገር -ድል ነው ፀዲቅ የሚቆርሰው፡፡

እንደ ቤተ-መቅደሱ -እንደ ሞገሩ ሽታ
እንደ ነጋሪቱ ድምፅ -መለከትና እምቢልታ
ተመስገን ያባቴ አምላክ -ልቤ ሃሴት ተሞልቷል
ሰማዕቱ በእለተ ቀንህ -ክንዴ እልፍ ጦር አንግቷል
ህዝቤ -አፎቱን ከፍቷል

ብቻ ህልም አየሁ በሰመመን…
አንጎለላ ኪዳነምህረት -ከደጅሽ የወይራ አፀድ
በቀስተዳመና ተከቦ- አንዱ ክንፍ ተቆርጦ ሲወርድ
ይሔ ሃሞተ መራር-ይሔ ልበ ተራራ
የሰው ምክር ግድ የለው-ትንሽ ለነፍሱ አይፈራ
ቀኝ እጄን እንዳላጣው- ክንዴን ገበየሁን አደራ::

ክብር ለአያቶቼ
ኢትዮጵያን ከነ-ስሟ -ከነ ክብሯ ላኖሯት
ጣሊያን ጉድጓዱ ይገባል -ዛሬም ማንም አይደፍራት።

የካሳ እልፍኝ ይታዘበኝ -ጦር ሰልጥኜ ያደኩበት
ልበ-ባህሩ ሸዋ -አባ መቻል-አባ መስጠት
ስም አልጠራም አባባ ብዬ -አይወልደኝም ሀይለመለኮት
እኔ ዳኘው ምኒልህ -ወገኔን ካሳፈርኩት !!

በቀዳማዊ ምኒልክ -በሳህለ ሥላሴ መንፈስ
በአያቴ ወንበር ዘውድ ስጭን -በጥንቶቹ አልጋ ስነግስ
እንዴት ተብሎ ቃል ቢዛነፍ-ጫፏ ይነካል አገሬ
አፍር ይሆናል እንጂ-ጠላት ይገባል መረሬ!!

እውነት ኪዳነ-ምህረት -በቀንሽ ቅጠል ሳልበጥስ
ዳዊት ከደጅሽ ደግሜ -ፀበል ጠጥቼ ሳልሰልስ
ቆመ-ብዕሴሽን ታሽቼ-ገራገራሽን ተሳልሜ
የኖርኩት የከበርኩት -ባንች እማዶለ አለሜ !
ፈገግተዋ የሚያጠግበኝ-የመኖር ውሃ ሙላቴ
እንግዲህ አንቺ ከልያት-ከፊት ቀድማለች ጣይቴ ፡፡

አሔሔ!
ኢትዮጵያዊነት ሥሙ -ሀይሉ ካድማስ የሚርቀው
የወገኔ እንኳን ጦሩ-ድምጡ ጠላት የሚንደው
ከወረይሉ እስከ ሶሎዳ - እየፎከረ የተመመው
እምቢ ብሎ እንደመጣ -የድል ጀንበር ሊያሳልፍ ነው፡፡

እንግዴህ ይህ ነው ፀሎቴ ...

ይህ ቀን -ታላቅ ነውና -
የኢትዮጵያ ሐያልነት በአደባባይ ይወሳ
ወራሪ አጥንቱ ደቆ- ከደሃ ላይ እጁን ያንሳ
አንበሳ አንበሳ ነውና- እንደትላንቱ ዛሬም ያግሳ
ጥቁርና የጥቁር ምድር- አንገቱ ቀና ይበል
የሐበሻን ጠንካራ ክንድ -አውሮጳም አምኖ ይቀበል ።

እኔ ምኒልህ
አይኑን ለጨፈነ ጠላት -እዝኑን ለደፈነ ጦረኛ
ልቦና ቢገዛ ብየ-እንጂ -ይሔ ነጭ ነውረኛ
አወድመው እንደሳት ሰደድ -እመታው እንደመጋኛ፡፡

ብቻ ህልም አየሁ በሰመመን…
አንጎለላ ኪዳነምህረት -ከደጅሽ የወይራ አፀድ
በቀስተዳመና ተከቦ -አንዱ ክንፍ ተቆርጦ ሲወርድ
ይሔ ሃሞተ መራር-ይሔ ልበ ተራራ
የሰው ምክር ግድ የለው-ትንሽ ለነፍሱ አይፈራ
ቀኝ እጄን እንዳላጣው ክንዴን ገበየሁን አደራ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አርባምንጭ ውሃ  ባለቤት  ይሁኑአርባምንጭ ውሃ   #አክሲዮን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ህግ መሠረት ያደረገ እና ዘመናዊ የአክሲዮን ገበያ አሰራር የሚቋቋም ግዙፍ ኢንቬስትመንት ነው።እጅግ አዋ...
26/02/2026

አርባምንጭ ውሃ ባለቤት ይሁኑ
አርባምንጭ ውሃ #አክሲዮን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ህግ መሠረት ያደረገ እና ዘመናዊ የአክሲዮን ገበያ አሰራር የሚቋቋም ግዙፍ ኢንቬስትመንት ነው።

እጅግ አዋጭነት እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ የሚገባው የአርባምንጭ ውሃ ባለድርሻ እንዴት ይሆናሉ?

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉በአጠቃላይ 498 000 አክሲዮን ለሽያጭ የሚቀርብ ይሆናል።

👉የአንዱ አክሲዮን ዋጋ 1000 ብር ነው

👉አንድ ሰው ዝቅተኛ መግዛት የሚችለው 10 ሲሆን ለዚህም የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን 10 000 ብር ነው።

👉 አንድ ሰው መግዛት የሚችለው 5000 አክሲዮን ነው። ስለዚህ አንድ ግለሰብ ከ5000 አክሲዮኖች ወይም ከ5 000 000 ብር በላይ ገንዘብ አውጥቶ መግዛት አይችልም ማለት ነው።

💦 እያንዳንዱ አክሲዮን ገዢ በገዛው የአክሲዮን (ድርሻ) መጠን የገዛውን 5% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላል።

በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ስራ መግባት በሚያስችለው አደረጃጀቱን በሟሟላት ላይ ይገኛል።

ምንጩን ይቅመሱት!
Taste the Source!

አርባምንጭ ውሃ

Address

Bole
Addis Ababa
04

Telephone

+251901001416

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tegulet Media and Promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share