Bad boy

Bad boy Sᴘᴏʀᴛ,ғᴀsɪᴏɴ,ᴀʀᴛ,ɴᴇᴡs,...............
ሁሉንም መረጃ 💁 ባንድ ቦታ

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ አዲስ ታሪክ ተጻፈ! የቴዲ አፍሮ  "ኢቶሪካ" አልበም ቀድሞ የተለቀቀው 18ኛው ትራክ ጀምበር" በዩቲዩብ ብቻ በተለቀቀ በ 2 ሰዓታት ውስጥ 1 ሚሊዮን እይታዎችን (V...
16/04/2026

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ አዲስ ታሪክ ተጻፈ!

የቴዲ አፍሮ "ኢቶሪካ" አልበም ቀድሞ የተለቀቀው 18ኛው ትራክ ጀምበር" በዩቲዩብ ብቻ በተለቀቀ በ 2 ሰዓታት ውስጥ 1 ሚሊዮን እይታዎችን (Views) በማግኘት ክብረ ወሰን ሰብሯል!

ይህ ድንቅ ስኬት የኢትዮጵያ ሙዚቃ የደረሰበትን የዲጂታል ከፍታ የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ፣ ጥራት ያለው ስራና ጠንካራ ጥረት ሁልጊዜም ውጤቱ ታላቅ መሆኑን የሚያረጋግጥ አነቃቂ ክስተት ነው። ለጥበብ ከሰጠህ፣ ጥበብ በክብር ትመልስልሃለች!

ለቴዲ አፍሮ ለመላው የጥበብ ቤተሰቦች
እንኳን ደስ አላችሁ!

ለሁላችንም ብርታት የሚሆን ታላቅ ኩራት ነው!

🇪🇹🔥

በምስሉ ላይ እምትመለከቱት ተወዳጅ ሰው ማንነው ?
04/04/2026

በምስሉ ላይ እምትመለከቱት ተወዳጅ ሰው ማንነው ?

አስቸኳይ ወቅታዊ መረጃ፦ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠ መግለጫበመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የአየር ክልል መዘጋት ምክንያት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ተለያዩ ከተሞች የሚያደርጋቸውን በ...
02/03/2026

አስቸኳይ ወቅታዊ መረጃ፦ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠ መግለጫ

በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የአየር ክልል መዘጋት ምክንያት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ተለያዩ ከተሞች የሚያደርጋቸውን በረራዎች እስከ ሌላ ማስታወቂያ ድረስ መሰረዙን አስታውቋል።

በረራ የተሰረዘባቸው መዳረሻዎች፦

1. አማን፣
2. ቤይሩት፣
3. ባህሬን፣
4. ቴል አቪቭ፣
5. ዶሃ፣
6. ኩዌት፣
7. ዱባይ፣
8. ሻርጃህ፣
9. አቡ ዳቢ እና
10. ዳማም ናቸው::

* በረራዎች ሲጀምሩ ለሌላ ቀን በነፃ መቀየር (Rebooking)

* ወደ አቅራቢያ መዳረሻዎች በረራን ማዛወር (Rerouting)

* ያልተጠቀሙበትን ትኬት ሙሉ ክፍያ ማስመለስ (Full Refund)

ተጓዦች አላስፈላጊ እንግልት እንዳይገጥማቸው በረራቸውን ከታች ባለው ሊንክ እንዲያረጋግጡ በጥብቅ ይመከራል፦

https: www. ethiopianairlines com/et/book/booking/flight-status

በቀጥታ ከአየር መንገዱ ትኬት የቆረጣችሁ በ reservation@ethiopianairlines. com መጠየቅ የምትችሉ ሲሆን፣ በወኪል (Agent) የቆረጣችሁ ደግሞ ወኪሎቻችሁን እንድታነጋግሩ ተገልጿል።

አየር መንገዱ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ እየጠየቀ፣ የደህንነት ሁኔታዎችን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታወቋል

አርሰናል 2_1 በሀሆነ ውጤት ቼልሲን አሸነፈ
01/03/2026

አርሰናል 2_1 በሀ
ሆነ ውጤት ቼልሲን አሸነፈ

ትክክለኛ የማን.ዩናይትድ ደጋፊዎች ይህን ፎቶ ዝም ብለውት አያልፉም።
01/03/2026

ትክክለኛ የማን.ዩናይትድ ደጋፊዎች ይህን ፎቶ ዝም ብለውት አያልፉም።

Addis Ababa Ethiopia 🇪🇹🇪🇹
01/03/2026

Addis Ababa Ethiopia 🇪🇹🇪🇹

እንሠማለን ግን አንፈርድም🤐
01/03/2026

እንሠማለን ግን አንፈርድም🤐

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬምን ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ335 ሚሊዮን በላይ ብር ገቢ ተገኘ +++++++++++++++++   | የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬም ባለፉት 18 ወራት ውስጥ የሀገር ውስጥ...
01/03/2026

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬምን ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ335 ሚሊዮን በላይ ብር ገቢ ተገኘ
+++++++++++++++++

| የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬም ባለፉት 18 ወራት ውስጥ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን በማስተናገድ ከ335 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የሙዚዬሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ናዚፍ ጀማል ገለጹ።

የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ናዚፍ ጀማል ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ መታሰቢያ ሙዚዬሙ ተገንብቶ ክፍት ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የጎብኝዎች ፍሰት እያስተናገደ ይገኛል።

ከየካቲት 2016 እስከ የካቲት 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ 335 ሚሊዮን 840 ሺህ 395 ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ከጠቅላላ ጎብኝዎች ተማሪዎች እንደሚገኙበትና ይህም የዓድዋን ታሪክ ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ እየተከናወነ ያለውን ስኬታማ ሥራ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ሙዚዬሙ የኢትዮጵያን ታሪክ ከማሳየት ባለፈ ለስብሰባዎችና ለዲፕሎማሲያዊ መድረኮች ዋነኛ መዳረሻ እየሆነ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ 108 የሀገር ውስጥና 13 ዓለም አቀፍ መድረኮች የተካሄዱ ሲሆን፣ ከ101 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን አስተናግዷል።

በተጨማሪም 11 ሀገራት መሪዎች በሙዚዬሙ የአበባ ጉንጉን ማስቀመጣቸው የቦታውን ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ የሚያጎላ መሆኑን ናዚፍ አብራርተዋል።

በዳግም ከበደ
++++++++++++++++++++++++++++++

@ጋዜጣ-ፕላስ
#ዓድዋ #ቱሪዝም #ኢትዮጵያ

የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላሕ አሊ ኻሚኒ መገደላቸው ተነገረ።በኢስላማዊት የኢራን ሪፐብሊክ ማንኛውንም የሕዝብ ፖሊሲ ጉዳይ ውድቅ ማድረግ እንዲሁም ባለስልጣናትን መሾም እና የመሻር ውሳኔን ጨ...
28/02/2026

የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላሕ አሊ ኻሚኒ መገደላቸው ተነገረ።

በኢስላማዊት የኢራን ሪፐብሊክ ማንኛውንም የሕዝብ ፖሊሲ ጉዳይ ውድቅ ማድረግ እንዲሁም ባለስልጣናትን መሾም እና የመሻር ውሳኔን ጨምሮ የኢራን አብዮታዊ ዘብን የማዘዝ ሥልጣን የነበራቸው ፤ ወጣት ኢራናውያን ያለእርሳቸው አመራር ሕይወትን አያውቋትም የሚባልላቸው ፤ የሪፐብሊኳ ኃያል ሰው በእስራኤል በተፈጸመ ጥቃት መገደላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን ጨምሮ የእስራኤል ባለስልጣናት እየገለጹ ነው።

አያቶላህ አሊ ኻሜኒ እንደ ግሪጎርያኑ አቆጣጠር በ1979 ከተካሄደው የኢራን አብዮት በኋላ ከአያቶላሕ ሩሆላሕ ኻሚኒ በመቀጠል ሁለተኛው የአገሪቱ የበላይ መሪ ሲሆኑ ከ1989 ጀምሮ ደግሞ መንበሩን በበላይነት በመቆጣጠር ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ኢራንን እንደ ሰም አቅልጠው ፤ እንደ ገል ቀጥቅጠው መግዛታቸው ይነገርላቸዋል።

በስፋት እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎችን ተከትሎ ምንም እንኳን ኢራን መሪዋ ስለመገደል አለመገደላቸው እስካሁን በግልጽ ያለችው ነገር ባይኖርም ፤ በሚዲናይቱ ቴህራን በሚገኘው የኻሚኒ መኖሪያ ቤት ላይ ጉዳት መድረሱን የሚያሳዩ የሳተላይት ምስሎች ግን ቀደም ሲል ወጥተው ነበር።

ዛሬ የእግርኳስ ንጉሱ የክርስቲያኖ ሮናልዶ 41ኛ አመት የልደት ቀን ነው!🎂በእግርኳስ ፍቅር እንድንወድቅ ካደረጉን ከዋክብት አንዱ!!🐐
05/02/2026

ዛሬ የእግርኳስ ንጉሱ የክርስቲያኖ ሮናልዶ 41ኛ አመት የልደት ቀን ነው!🎂

በእግርኳስ ፍቅር እንድንወድቅ ካደረጉን ከዋክብት አንዱ!!🐐

13/10/2025

በኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው ለDV 2027 ሎተሪ ለመመዝገብ የሚያስፈልጉዎትን ዝግጅቶች፣ የደረጃ በደረጃ የምዝገባ ሂደት እና ሊጠብቁት የሚገባውን ወሳኝ መረጃ ከዚህ በታች በሰፊው ቀርቧል።

✅1️⃣ ክፍል አንድ፡ የምዝገባ ጊዜ እና ቅድመ ዝግጅት
የDV 2027 ሎተሪ ምዝገባ የሚከናወነው በ2027 ዓ.ም ሳይሆን በጥቅምትና በህዳር ወራት 2025 ዓ.ም. ነው።
1️⃣ የምዝገባ ጊዜ (DV 2027)
✅ መጀመርያ ቀን: በጥቅምት 2025 መጀመሪያ አካባቢ (ትክክለኛው ቀን በየዓመቱ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ ይደረጋል)።
✅ መዝጊያ ቀን: በህዳር 2025 መጀመሪያ አካባቢ።
✅ ጠቃሚ ምክር: ምዝገባው በሚከፈትበት ጊዜ ባለው የኢንተርኔት መጨናነቅ ምክንያት፣ በአልያም በስህተት እንዳይዘጋ ከመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ጀምሮ መሙላት ይመከራል።

2️⃣ ወሳኝ የሆኑ የመረጃ ዝግጅቶች
የምዝገባ ቅጹን መሙላት ከመጀመርዎ በፊት የሚከተሉትን መረጃዎች በትክክል ማዘጋጀት እና ማረጋገጥ አለብዎት።

✅ ፎቶግራፍ እጅግ በጣም ወሳኝ! ፎቶዎ በቅርብ ጊዜ (ባለፉት 6 ወራት) የተነሳ መሆን አለበት። ጀርባው ነጭ መሆን አለበት፣ ጆሮዎች እና አይኖች በግልጽ መታየት አለባቸው፣ እና መነፅር በፍጹም ማድረግ አይፈቀድም። (600x600 ፒክሰል መጠን ያለው ዲጂታል ፎቶ።

✅ ሙሉ ስም በልደት የምስክር ወረቀትዎ ወይም በመታወቂያዎ ላይ እንደተፃፈው በትክክል መመዝገብ አለበት።

✅ የትውልድ ቦታ/ቀን በትክክል ከተወለዱበት ቦታ (ከተማ፣ ሀገር) እና ቀን ጋር መዛመድ አለበት።

✅ የትዳር ሁኔታ በትኩረት! ያገቡ ከሆነ ባለቤትዎን መመዝገብ ግዴታ ነው። ባይሄዱም እንኳ መመዝገብ አለበት። የፍቺ ሂደት ላይ ያለ ግን ገና ያልተፈታ ትዳርም እንደ 'Married' መመዝገን አለበት።

✅ የልጆች መረጃ ዕድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ያላገቡ ልጆችን በሙሉ መመዝገብ ግዴታ ነው። እነዚህ ልጆች ከቀድሞ ትዳር የመጡ፣ የማደጎ ወይም አብረዋችሁ የማይኖሩ ቢሆኑም መመዝገብ አለባቸው።

✅ የትምህርት ደረጃ ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን (12ኛ ክፍል) ማጠናቀቅ አለብዎት። ካልሆነ ደግሞ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ባለው ሙያ ላይ መሥራት።

✅2️⃣ ክፍል ሁለት፡ የDV 2027 ምዝገባ የደረጃ በደረጃ ሂደት
✅ የምዝገባው ሂደት በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ብቻ የሚከናወን ሲሆን፣ ቅጹን ለመሙላት የሚፈጀው ጊዜ አጭር ነው። ስህተት ላለመሥራት ግን መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

1️⃣ ወደ ይፋዊው ድረ-ገጽ ይግቡ
✅ ብቸኛው ትክክለኛ አድራሻ: dvprogram.state.gov
✅ ማስጠንቀቂያ: ይህ ብቸኛው ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ ነው። ሌላ ማንኛውም ...dvlottery.org ወይም ...green-card-register.com የሚል ድረ-ገጽ አታላይ (Scam) ነው።

2️⃣ ቅጹን መሙላት (Entrant Status Check)
የምዝገባ ቅጹን (DS-5501) ሲሞሉ የሚከተሉትን ቁልፍ መረጃዎች በትክክል ያቅርቡ፡

✅ ክፍል 1፡ ስም | ስምዎን በእንግሊዝኛ ፊደላት (ላቲን) ብቻ ይጻፉ። የላቲን ፊደል ያልሆኑ (ለምሳሌ አረብኛ ወይም አማርኛ ፊደላት) መጠቀም አይችሉም።

✅ ክፍል 6፡ ሀገር ኢትዮጵያ (Ethiopia)።
✅ ክፍል 7፡ ፎቶግራፍ ከላይ በተገለጸው መስፈርት የተዘጋጀውን ዲጂታል ፎቶ ይጫኑ።
✅ ክፍል 8፡ ፖስታ አድራሻ አሁን የሚኖሩበትን ሙሉ አድራሻ (ለምሳሌ ክልል፣ ከተማ፣ ቀበሌ/ንዑስ ከተማ) በግልጽ ይጻፉ። የፖስታ ሣጥን (P.O. Box) ግዴታ አይደለም።
✅ ክፍል 9፡ ሀገር የሚኖሩባት ኢትዮጵያ (Ethiopia)።
✅ ክፍል 10፡

The entry period for the DV-2026 Diversity Visa Program was between October 2, 2024 and November 7, 2024. Entries are not being accepted at this time.

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bad boy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share