SORA Market

SORA Market ሶራ ለሁሉም

27/02/2026
 ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በመከላከያ እና በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ የመግባቢያ ሰነዶችን ፈረሙ።ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ባደረጉት የመጀመሪያው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ከፕሬዝዳንት ...
27/02/2026



ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በመከላከያ እና በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ የመግባቢያ ሰነዶችን ፈረሙ።

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ባደረጉት የመጀመሪያው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ከፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ለተደረገላቸው የክብር አቀባበል አመስግነው " ‎ባለፉት ጥቂት ዓመታት ፦
- በአቪዬሽን ዘርፍ፣
- በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በነፃ የንግድ ቀጣናዎች፣
- በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በአዘርባጃን አቻው መካከል በተደረጉ የኢኮኖሚ ትብብሮች ላይ በመመስረት አጋርነታችን በየጊዜው እያደገ መጥቷል " ብለዋል።

" እነዚህ የትብብር ዘርፎች ለሁለትዮሽ ግንኙነታችን መጠናከር መሠረት የጣሉ ናቸው ፤ ዛሬ ባደረግነው ጥልቅ ውይይትም ግንኙነታችንን እና ትብብራችንን ይበልጥ ለማጠናከር እና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ተስማምተናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

ዛሬ በመከላከያ እና በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ የመግባቢያ ሰነዶች ተፈርመዋል።

ሶራ ማርኬት ኢትዮጵያ
የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ/ም

ማብራሪያ ..." ምርጫ ቦርድ የክሱ አካል መሆኑ ግልጽ አይደለም። ተከሳሽ መሆን ከነበረት እንኳ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነበር " - የህግ ባለሙያ ጥጋቡ ደሳለኝ➡️ " ፍርድ ቤቱ ማገድ ይችላል...
27/02/2026

ማብራሪያ ...

" ምርጫ ቦርድ የክሱ አካል መሆኑ ግልጽ አይደለም። ተከሳሽ መሆን ከነበረት እንኳ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነበር " - የህግ ባለሙያ ጥጋቡ ደሳለኝ

➡️ " ፍርድ ቤቱ ማገድ ይችላል። ግን ምርጫ ቦርድን ስምረት ከሶ የሚሄደው የፍሬ ነገር ክርክር በአንድ ቀጠሮ ውድቅ የሚሆን ነው" - የህግ ባለሙያ አበራ ንጉስ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት " በአወዛጋቢ " የምርጫ ቦታዎች የወሰነውን ውሳኔ በተመለከተ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እግድ መስጠቱ አቶ ጌታቸው ረዳ አሳውቀዋል።

ይህን ተከትሎም በርካቶች፣ " የፌዴራል ምክር ቤትን ውሳኔ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የማገድ ስልጣን አለው ወይ ? እነ አቶ ጌታቸው መክሰስ የነበረባቸው የፌዴሬሽን ምክር ቤትን እንጂ ውሳኔ አስፈጻሚ የሆነውን ምርጫ ቦርድን ነበርን ? " የሚሉ ጥያቄዎች እያነሱ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ለዚህ ጥያቄ ህጉ አንፃር ምን ይላል ? የሚለውን የህግ ባለሙያዎች ምላሽ ይዟል።

በህጉ መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ውሳኔ ማገድ ይችላል? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሙያዊ ማብራሪያ የጠየቃቸው የህግ ባለሙያው ጥጋቡ ደሳለኝ፣ " አዎ " የሚል ምላሽ አላቸው።

ምክንያቱም ሲያስረዱ፣ " በህገ መንግስቱ አንቀጽ 78 እና ተከታዮቹ ስለዳኝነት አካል መዋቀር፣ የአሰራር ነፃነት እና ገለልተኛነት በሚደነግገው ክፍል በፍርድ ቤቶች ላይ አስፈጻሚው አካል ጣልቃ ገብነት እንዲኖር አይፈቅድም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ምርጫ ቦርድ በፌዴሬሽን ም/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ መሰረት አስፈጻሚ ነው " ያሉት ጠበቃው፣ " የፌዴሬሸን ምክር ቤትን ውሳኔ ተከትሎም ቢሆን የሚደረገው ምርጫ ማስፈጸም ጉዳይ በሆነ አካል ለፍርድ ቤት ስለቀረበ ፍርድ ቤቱ ምርጫ ቦርድን " ጉዳዩን መርምሬ ጊዜያዊ ውሳኔ እስክሰጥ ድረስ ጊዜያዊ እግድ ሰጥቻለሁ " ማለቱ አግባብ ነው።

የእነ ጌታቸው ረዳ አቤቱታ በፌደሬሽን ምክር ቤት በተሰጠው ውሳኔ መሰረት " የአወዛጋቢ " አካባቢዎች የምርጫ ጉዳይ " ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀጥታ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምርጫ እንዲረግ " ተብሎ ለምርጫ ቦርድ የተሰጠው አቅጣጫ ተገቢነት የለውም የሚል መሰረት ያለው ነው።

የህግ ባለሙያ ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ በሰጡት አስተያየት፣ " ምርጫ ቦርድ ውሳኔ አስፈጻሚ ነው። በክሱ የሚካተትበት መንገድ አልታየኝም። ምናልበት ውሳኔ ሰጭ የሆነውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የክሱ አካል ማድረግ ይቻል ነበር እንጂ ቦርዱ አስፈጻሚ ተቋም ነው " ይላሉ።

" ቦርዱ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 102 መሰረት በየአምስት አመቱ ሀገር አቀፍ፣ የአካባቢ እና የማሟያ ምርጫ እንደሚያደርግ ህገ መንግስታዊ ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም ነው። ከነ ችግሩም ቢሆን በአቅሙ ምርጫ ለማድረግ ጥረት እያደረገ ነው " ያሉት ባለሙያው፣ " የክሱ አካል መሆኑ ግልጽ አይደለም። ተከሳሽ መሆን ከነበረት እንኳ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነበር " ብለዋል።

የምርጫ ቦርድ ፍርድ ቤት ምላሽ " ግልጽ ነው " ብለው፣ " እኔ ምን ላድርግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሰጠውን ውሳኔ ነው የማስፈጽመው፤ ፍርድ ቤት አታስፈጽም ካለኝ አከብራለሁ' የሚል ነው ምላሹ " ሲሉም ሙያዊ አስተያነታቸውን ሰጥተዋል።

ስለዚህ የፌደሬሽን ምክር ቤት ነበር " እስካሁን ለምን ዘገየህ ? አሁን ለምን ወሰንክ ? ህዝበ ውሳኔ ማሰጠት ለምን አልቻልክም ? " ተብሎ መጠየቅ የነበረበት ሲሉም ይመከራሉ።

ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የህግ ባለሙያው አቶ አበራ ንጉስ፣ " የተከሰሰው ምርጫ ቦርድ ነው። ወደ ፍርድ ቤት ሳይገባ ፍሬ ነገር የሚወስነው ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ በቀረበለት ክስ መሰ

በመስኮት በመግባት ከ6 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ ንብረቶችን ሰርቋል ተብሎ የተጠረጠረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስ...
27/02/2026

በመስኮት በመግባት ከ6 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ ንብረቶችን ሰርቋል ተብሎ የተጠረጠረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
***
አዲስ አበባ፤ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፡- ጌቱ ተስፋዬ የተባለው ተጠርጣሪ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመው የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሳፋየር አዲስ ሆቴል አካባቢ ከሚገኝ አንድ አፓርትመንት 8ኛ ፎቅ ከምሽቱ 5፡00 ገደማ ነው።

ተጠርጣሪው በአፓርታማው ከሚገኝ አንድ ሬስቶራንት በአስተናጋጅነት የሚሰራ ሲሆን የግል ተበዳይ ወይዘሪት እልፍነሽ አሰፋ የመኝታ ክፍል መስኮት አለመዘጋቱን በማረጋገጥ ከወርቅና ከዳይመንድ የተሰሩ ልዩ ልዩ የአንገት ሀብል፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ ብራስሌትና የጆሮ ጌጣጌጦች፣ 2800 የአሜሪካ ዶላር፣ 2 ሞባይል ስልኮችና የተለያዩ ጌጣጌጦችን በመኝታ በኩል በሚገኝ መስኮት ዘሎ በመግባት የስርቆት ወንጀሉን ፈፅሞ ከአካባቢው ይሰወራል፡፡

የየግል ተበዳይ ወይዘሪት እልፍነሽ አሰፋን አቤቱታ የተቀበለው የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ፖሊስ ጣቢያም የወንጀል ፈፃሚውን ማንነት ለማረጋገጥ ህንፃው ላይ በተገጠመው የደህንነት ካሜራ (CC TV) አማካኝነት በማረጋገጥና ክትትል በማድረግ ግለሰቡ ለጊዜው ተሰውሮ ከነበረበት ሜክስኮ አካባቢ ከሚገኝ አልጋ ቤት ከነ ንብረቶቹ በቁጥጥር ስር መዋሉን ከአደይ አበባ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ማንም ሰው ወንጀል ፈፅሞ ከህግ ማምለጥ እንዳማይችል የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ህብረተሰቡ በመኖሪያ ቤቱም ሆነ የሚያርፍባቸው ቦታዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን በሚገባ ማረጋገጥ እንደሚገባም ጭምር መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
*
ዘገባ፦ ዋ/ሳጅን ደጀኔ ኡልፋታ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ:- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!"

ሁለቱ ወጣት ፖለቲከኞች በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ የምርጫ ክርክር እንዲያደርጉ ተጠየቀ።ወጣት ፈዲላ ቢያ ብልፅግናን ወክላ ወጣት ምስጢረስላሴ ታምራት ደግሞ ኢህአፓን ወክላ የምርጫ የምረጡኝ ቅ...
27/02/2026

ሁለቱ ወጣት ፖለቲከኞች በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ የምርጫ ክርክር እንዲያደርጉ ተጠየቀ።

ወጣት ፈዲላ ቢያ ብልፅግናን ወክላ ወጣት ምስጢረስላሴ ታምራት ደግሞ ኢህአፓን ወክላ የምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳና ክርክር እንዲያደርጉ፡ ክርክሩም በቀጥታ እንዲተላለፍ ብዙዎች እየጠየቁ ነው። ሁለቱም ፖለቲከኞ በማህበራዊ ሚድያ በሚያደርጉት መመላለስ የወጣቱ ትኩረት መሳብ ችለዋል።

ይህንን ሀላፊነት ወስዶ ወደ ተግባር የሚቀይር ጋዜጠኛ እና ሚድያ #ማን ቢሆን ይሻላል?

የእንስቶቹ ፍጥጫ እና ግልምጫ
27/02/2026

የእንስቶቹ ፍጥጫ እና ግልምጫ

🕊️ የሩጫ ንግሥት፤ የመሠረት ደፋር እናት​ እናመሰግናለን🕯️  | ይህ ዜና ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፣ የሩጫ ንግሥቷ መሠረት ደፋር እና ለመላው ቤተሰቦቿ እንዲሁም ለአድናቂዎቿ እጅግ አሳዛ...
27/02/2026

🕊️ የሩጫ ንግሥት፤ የመሠረት ደፋር እናት​ እናመሰግናለን🕯️

| ይህ ዜና ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፣ የሩጫ ንግሥቷ መሠረት ደፋር እና ለመላው ቤተሰቦቿ እንዲሁም ለአድናቂዎቿ እጅግ አሳዛኝ ነው።

ወይዘሮ አስቴር መንገሻ ለሀገር ኩራት የሆነችውን መሰረት ደፋርን ብቻ ሳይሆን፣ ስድስት ልጆችንና 18 የልጅ ልጆችን አፍርተውና ለቁም ነገር አብቅተው ያለፉ ማኅፀነ ለምለም እናት ነበሩ።

​ሀገርን የሚያስጠሩ ጀግኖችን ያፈሩትና ለ54 ዓመታት በፍቅርና በሰላም ትዳራቸውን የመሩት ማኅፀነ ለምለሟ እናት ወይዘሮ አስቴር መንገሻ በተወለዱ በ71 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

​📜 አጭር የሕይወት ታሪክ፦

​ልደት፦
በ1947 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል፣ ኢጄሬ ወረዳ (አዲስ ዓለም) ተወለዱ።

​ትዳርና ቤተሰብ፦
በ1964 ዓ.ም ከአቶ ደፋር ቶላ ጋር ትዳር መስርተው ለ54 ዓመታት በጽኑ ፍቅር ዘልቀዋል። የ6 ልጆች እናትና የ18 የልጅ ልጆች አያት ለመሆን በቅተዋል።

​የጀግኖች እናት፦
የዓለምን የሩጫ መድረክ የገዛችውንና በኦሎምፒክና በዓለም ሻምፒዮና ወርቅ ለሀገሯ ያስገኘችውን የሩጫ ንግሥት አትሌት መሰረት ደፋርን ለኢትዮጵያ ያበረከቱ ታላቅ እናት ነበሩ። ሌሎች ልጆቻቸውም በሙሉ በሕክምናው ዘርፍ ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ አሳድገዋል።

መሰረት ደፋር እ.ኤ.አ በ2007 የአለም ምርጥ አትሌት ተብላ እንድትመረጥና ስሟ በታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ እንዲሰፍር ያደረጉትን ዋና ዋና ስኬቶች እንዲህ ማጠቃለል ይቻላል፦

​ የአትሌት መሰረት ደፋር ታሪካዊ ስኬቶች በአጭሩ
​የአለም ክብረ ወሰኖች (World Records):
​5,000 ሜትር፦ በኦስሎ (ኖርዌይ) 14:16.63 በመግባት ቀዳሚ ሆናለች።

​2 ማይል፦ በካሊፎርኒያ እና በቤልጅየም (8:58.58) በመግባት በአለም ለመጀመሪያ ጊዜ ከ9 ደቂቃ በታች የሮጠች የኢትዮጵያ ጀግና ሴት ናት።

​3,000 ሜትር (የቤት ውስጥ/Indoor): በጀርመን ስቱትጋርት 8:23.72 በመግባት ክብረ ወሰን አስመዝግባለች።

​የኦሎምፒክ ድሎች:
​እ.ኤ.አ በ2004 በአቴንስ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ።
​እ.ኤ.አ በ2012 በለንደን ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ።

​ታሪካዊ እውቅና:
​እ.ኤ.አ በ2007 የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (IAAF) የአመቱ ምርጥ ሴት አትሌት ሽልማት ባለቤት።

​አንዲት እናት ለሀገር የምታበረክተው ከሁሉ የላቀ ስጦታ፣ ሀገሩን የሚወድና ስሟን ከፍ የሚያደርግ ጀግና ትውልድ መፍጠር ነው፤ ወይዘሮ አስቴር ይህንን በተግባር አሳይተዋል።

​ሀገራዊ አገልግሎት፦
ወይዘሮ አስቴር ራሳቸውም ሰላም አስከባሪ በመሆን ሀገራቸውን ያገለገሉ ጀግና ነበሩ።

​መንፈሳዊ ሕይወት፦
ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላቸው፣ በቤተክርስቲያን ሥርዓት የተጉና የሰማይ መንገዳቸውን በቅዱስ ቁርባን የጠረጉ እናት ነበሩ።

​🥀 የስንብት ሥነ-ሥርዓት፦

ወይዘሮ አስቴር ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሀገር ውስጥና በውጭ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው፣ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም አርፈዋል።

የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸውም (የካቲት 15/2018 ዓ.ም) በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

​ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen) ለጀግናዋ አትሌት መሰረት ደፋርና ለመላው ቤተሰቦቿ፣ ወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን ይመኛል።

​ፈጣሪ የነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን! 🙏🇪🇹

​ #መሰረትደፋር #ወይዘሮአስቴርመንገሻ #የሐዘንመግለጫ

ለዘመኑ ሴቶች እሚሆን መልእክትእባካችሁ ሴቶች ከመሞቴ በፊት ስሙኝ ብላ የጻፈችው፣ የዚህችን ልጅ አጭር የህይወት ታሪክ ላጋራችሁ ። ለራሴ ስነግረው ፣ ጊዜ ያለኝ ይመስለኝ ነበር።ስሜ ኤሚሊ ይ...
27/02/2026

ለዘመኑ ሴቶች እሚሆን መልእክት
እባካችሁ ሴቶች ከመሞቴ በፊት ስሙኝ ብላ የጻፈችው፣
የዚህችን ልጅ አጭር የህይወት ታሪክ ላጋራችሁ ።
ለራሴ ስነግረው ፣ ጊዜ ያለኝ ይመስለኝ ነበር።
ስሜ ኤሚሊ ይባላል። ከመሞቴ በፊት የህይወቴን ታሪክ ልነግራችሁ ወደድኩ።

የሆነ ጊዜ አፍላ እድሜ ላይ ነበርኩ ፣ህይወት ለኔ ሙሉ ነበረች።
የወጣትነት ጉልበትና ሀይል ጭምር ተደምሮበት ።
ብዙ ሰዎች ሁሌ እንደሚነገሩኝ ፣በጣም የማምር ውብ ሴት ነበርኩ።
ሁል ጊዜ ቅዳሜና እሁድ በመጣ ቁጥር፣
ከጓደኞቼ ጋር ለመዝናናት እወጣ ነበር።
ታዲያ ስወጣ እይታን የሚስብ አይነት አለባበስ በመልበስ ወደ መሸታ ቤት መሄድ፣ ሌሊት ሙሉ ስጨፍር ማደር ፣ በቃ አብሮኝ የማይተኛ ወንድ የለም
መሳቅ ፣ መጠጣት ፣መጫወት የዘወትር ስራዬ ነበር ።
ያ ህይወቴም፣ ፍጹም በሆነ የነጻነት ዓለምና ህይወት ውስጥ የኖርኩ
ይመስለኝ ስለነበር ያንን ህይወት በጣም እወደው ነበር።

ልክ በ19 አመት እድሜዬ ፣ ሲጋራን ማጨስ ጀመርኩትኝ።
ስጀምረው ሳይገባኝና ስሜቱን ሳላውቀው ለደስታ ብዬ
አንድ እዚህ አንድ እዚያ እያልኩ ማጨስን ጀመርኩ።
በኋላም የዘወትር ልማድ ሆነብኝ።
ሁሌም ሳዝንና ስጨነቅ ሲከፋኝ ሲጋራ እለኩሳለሁ።
የትም ናይት ክለብ ስገባ ፣ ምንም አይነት መጠጥ ስጠጣ
ባዶ እጄን ሳይሆን ከሲጋራ ጋር አለሁኝ ።
የሚገርማችሁ ጊዜው እንኳን የሚሄድ አይመስለኝም ነበር።
እስካሁንም ድረስ ገና ወጣት የሆንኩ ያህል ይሰማኝ ነበር።
ገና ደግሞ በጣ..........ም ጊዜ ያለኝ ሁላ ፣
አይነት ስሜት ነበር የሚሰማኝ።
ነገር ግን ትልቅ ስህተት ነበር። 😭

እድሜዬም ልክ 28 ላይ ሲደርስ፣ የሆነ ህመም ይሰማኝ ጀመር።
ከእንብርቴ በታች የሆነ ስሜት። ኤጭ በማለት
እንደ ኖርማል ነገር አድርጌው ችላ ብዬ ተውኩት።
የሆነ ሰዓት ላይ በወር አበባዬ መምጫ መሀል
ቀናት ላይ ከባድ የሆነ ደም ይፈሰኝ ጀመረ።
የሰውነቴም ክብደት በጣም ይቀንስ ጀመር፣
እኔም ምናልባት ጭንቀት ሊሆን ይችላል የፈጠረው ብዬ ተውኩት።

የሆነ ግዜ የህክምና ባለሞያው ዶክተር ጋር ፣ መሄድ ባለብኝ ሰዓት ስሄድ
ውይ በጣም አረፈድሽ እኮ አለኝ።
ዶክተሩም :-ኤሚሊ የማህጸን ካንሰር አለብሽ አለኝ።
ይህን ሁሉ ነግሮኝ መጀመሪያ ላይ ብዙም ልረዳ አልቻልኩኝም።
በኋላም ለቀናት ያህል ፣ፊቴ በእምባ እስኪታጠብ ድረስ ማልቀስ ጀመርኩ።
እግዚአብሔርንም ሌላ እድል እንዲሰጠኝ ለመንኩት በጣም ተማጸንኩት።
ነገር ግን ካንሰሩ በመላው ሰውነቴ ተሰራጭቷል።
ዶክተሩም ስለካንሰሩ አመጣጥ መንስኤ በዝርዝር
ሲያስረዳኝ ይሄ ሁሉ የማጨስሽ ውጤት ነው አለኝ ።
ሲጋራ ውስጥ ያሉት ኬሚካሎች ማህጸንሽን ቀስ በቀስ
በጊዜ ሂደት ጎድቶ ጨርሶታል ብሎ ነገረኝ።
የሚገርመው ሲጋራ ይሄ ሁሉ መዘዝ እንዳለው ሁሉ፣
አላውቅም። የነገረኝ አንድ ሰው እንኳ አልነበረም ።

ዛሬ ላይ በትክክል መራመድ እንኳን አቅቶኛል
እንደምታዪኝ በጣም ከመክሳቴ የተነሳ ቀጭን ሆኛለው።
አጥንቶቼም ወጥተው ይታያሉ።
ከዚህም በኋላ የድሮዋ እኔ መቼም አልሆንም።
💧ሁሉም ትቶኝ ሄዷል።
እነኛ የምሽት ቤቶቼ ፣
እነኛ መጠጦቼ ፣
እነኛ ሲጋራዎቼ ጉዳያቸው አይደለውም፣ የኔ እንዲህ መሆን አላስጨነቃቸውም ።
ጓደኞቼ አብረውኝ የተኙ ወንዶች ሁሉም ትተውኝ ሄደዋል።
#እናቴ ብቻ ከአጠገቤ ሆና ፣ አይኖቼ ላይ ሞትን የሚጠባበቁ
እንባዎቼን እየጠረገች አብራኝ አለች።

በስተመጨረሻም ይህን ጽሁፍ ለምታነቡልኝ ወጣት ሴቶች
ላስተላለፈው የፈለኩት መልእክት
ገና ወጣት ነኝ ምንም አልሆንም በማለት አትዘናጉ ከእኔ ተማሩ:-
እኔ አሁን ልሞት ነው።

💥እባካችሁ ሲጋራ ማጨስ አቁሙ።
💥ሰውነታችሁን ተጠን

27/02/2026

ድሪል የማይበሳው ቦርጭ😂

በኪሱ ውስጥ የፈነዳ ስልክ ከሞት የታደገው ብራዚላዊበብራዚል ካስካቬል ከተማ የሚኖር አንድ ግለሰብ፣ በሁለት አደገኛ ውሾች ተከቦ ለሕይወቱ በሚታገልበት ወቅት በድንገት በኪሱ ውስጥ የፈነዳ ስል...
27/02/2026

በኪሱ ውስጥ የፈነዳ ስልክ ከሞት የታደገው ብራዚላዊ

በብራዚል ካስካቬል ከተማ የሚኖር አንድ ግለሰብ፣ በሁለት አደገኛ ውሾች ተከቦ ለሕይወቱ በሚታገልበት ወቅት በድንገት በኪሱ ውስጥ የፈነዳ ስልክ ሕይወቱን እንደታደገው ገለጸ።

ሬይናልዶ የተባለው ይህ ወጣት መካኒክ ወደ ሥራው እያመራ ሳለ ነበር ሁለት ግዙፍ ውሾች አድፍጠው ድንገተኛ ጥቃት የሰነዘሩበት።

ሁኔታው እጅግ አስፈሪ የነበረ ሲሆን፣ ውሾቹ ሬይናልዶን መሬት ላይ ጥለው በጭካኔ ይነክሱት ነበር።

ከመካከላቸው አንደኛው ውሻ ጉሮሮውን ለመንከስ ቢሞክርም ሬይናልዶ በከፍተኛ ተጋድሎ ራሱን መከላከል ችሏል።

ይሁን እንጂ ውሻው በድጋሚ እግሩን ለመንከስ ጥረት ሲያደርግ፣ በሬይናልዶ ኪስ ውስጥ የነበረውን ስልክ አብሮ ነከሰ።

በዚህ አጋጣሚ ከገዛው 20 ቀን ብቻ የሆነው የስልኩ ባትሪ በከፍተኛ ሁኔታ በመፈንዳቱ፣ ፍንዳታው የሬይናልዶን ቁምጣ አቃጥሎ በእግሩ ላይ መጠነኛ ጉዳት አድርሷል።

ይህ ያልተጠበቀ ድንገተኛ ፍንዳታና ጭስ ውሾቹን በእጅጉ ስላስደነገጣቸው ሬይናልዶን ለቀው እንዲሸሹ ምክንያት ሆኗል።

ሬይናልዶም በደረሰበት ፍንዳታ ቢደናገጥም፣ ውሾቹ በራቁበት ቅጽበት ተጠቅሞ ከአካባቢው በማምለጥ ለፖሊስ ለመደወል በቅቷል።

በአብዛኛው የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች መፈንዳት እንደ አደገኛ አደጋ ቢታይም፣ ለዚህ ብራዚላዊ ግን ስልኩ የሕይወት አዳኝ ሆኖለታል።

ሐመረ ፍሬው
FM 107.8

የካቲት 20/2018 ዓ.ም
market

27/05/2024

Address

Lideta
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SORA Market posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share