MaBizplus

MaBizplus https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-94lOqkY2SM0 The goal is to give simple, timely insights that help people stay informed through social media.
(1)

​🏦 Banking | Economy | Entrepreneurship on the Ethiopian , African & global markets.
💡 Building a digital mindset for leaders.
👇 Follow for the latest financial news and growth strategies. MaBizPlus shares quick and reliable updates on global, African, and Ethiopian finance, banking, the economy, digital finance, and investment trends.

25/05/2026

በአንድ ሚሊየን ብር ምን መስራት ይቻላል?
በአንድ ሚሊየን ብር ምን መስራት ይቻላል?

ብዙ ጊዜ ብር ሞተ ሲባል እሰማለሁ በትክክል የሞተው ብሩ ነው ወይስ የገበያው መዋቅር፣ የማምረት አቅም እና የፋይናንስ ሲስተሙ ነው? መቸስ ብር ምንዛሬው ምንም ይሁን ምን የትም ዓለም ያለን ምርትም ሆነ አገልግሎት የመግዛት አቅሙ እኩል የሚሆንበት ነጥብ አለ Purchasing Power Parity (PPP) የሚሉት። ለምሳሌ አንድ ግራም ወርቅ ኢትዮጵያ ውስጥ 25,000 ቢሆን አሜሪካ በዚሁ መጠን በሚመነዘር ዶላር ይሸጣል። በዚህ ስሌት ሄደን ስለስራ እናውራ።

ተመልከቱ አንድ ቻይናዊ 43,000 የቻይና ዮዋን ቢኖረውና ቻይና ስራ ልጀምር ቢል ከ 9,000 በላይ የተመዘገቡ ጥቃቅን ግን አትራፊ ስራወች መስራት ይችላል። ኬንያ በዚህ ብር ከጥቃቅን እስከመካከለኛ ስራወች መጀመር ይቻላል።

ይሄንኑ ብር ወደአሜሪካ ውሰዱት ከስድስት እስከ ሰባት ሺዶላር ይሆናል። ምን ይሰራል? የሆነ ስራ አላችሁ እንበል በዚህ ብር ዳውን ፔይመንት(ቅድሚያ ክፍያ) አይናችሁ ያረፈበትን አዲስ መኪና ማውጣትና ኡበርም ስሩበት ሌላ ዘና ብላችሁ ከ5-7 ዓመት ቀሪውን ትከፍላላችሁ። ሌሎች በርካታ ሰራወችን መስራትም ትችላላችሁ። በተለይ የምግብ ዝግጅት፣ ወይም የእጅ ሙያ ካላችሁ ጥሩ መነሻ ነው። በእርግጥ አሁን የዓለም ኢኮኖሚው መሳከር ነገሩን እንደወሬው ቀላል ላያደርገው ይችላል።

ይሄንኑ ገንዘብ ወደኢትዮጵያ መንዝሩት አንድ ሚሊየን ብር ማለት ነው። ምን ትሰሩበታላችሁ? ለምን ሌላ አገር ያውም ግዙፍ የሚባሉ አገራት ጥሩ ስራ ሊያስጀምር የሚችል ገንዘብ አገራችን ላይ ጉልበት አነሰው?

ቻይና ውስጥ በ43,000 ዩዋን (1 ሚሊየን ብር ገደማ) በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቅን ስራዎች የሚገኙት አምራች ማሽኖች፣ ጥሬ ዕቃ እና የሎጂስቲክስ ሲስተሙ እጅግ ስለረከሰና ስለቀለጠፈ ነው። አሜሪካም ውስጥ በ6,000 ዶላር መኪና በዱቤ አውጥቶ በኡበር መስራት የሚቻለው ጠንካራ የብድር (Credit) ሲስተም ስላለ ነው። ኬንያ ክፍት እና ፈጣን የንግድ እንቅስቃሴ ስላላት ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ከብሩ በላይ የፋይናንስ ሲስተሙ ነው ያቀነጨረን። አስተያየት አላችሁ?
MaBizplus

የዕቃ አስተላላፊነት ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ሙሉ በሙሉ ክፍት ሆነ‼MaBizplus ​የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ፣ የዕቃ አስተላላፊነት (F...
25/05/2026

የዕቃ አስተላላፊነት ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ሙሉ በሙሉ ክፍት ሆነ‼
MaBizplus
​የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ፣ የዕቃ አስተላላፊነት (Freight Forwarding) የኢንቨስትመንት ዘርፍን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ለማድረግ ወሰነ።

​ቀደም ሲል በደንብ ቁጥር 474/2012 መሠረት ዘርፉ ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች በቅንጅት ብቻ የተከለለ የነበረ ሲሆን፣ የውጭ ባለሀብቶች ድርሻም ከ49% እንዳይበልጥ ተገድቦ ቆይቷል። ይህ አሰራር በዘርፉ ላይ የሚፈለገውን የአዲስ ኢንቨስትመንት ፍሰት ገድቦት መቆየቱ ተገልጿል።

​ይህ አዲሱ የቦርዱ ውሳኔ፡-

📌​ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት፣

📌​አገራዊ የሎጂስቲክስ ወጪን ለመቀነስ፣
​የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማምጣት፣

📌 እንዲሁም ​የአገር ውስጥ ተዋናዮች አቅማቸውን አሳድገው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።

በአንድ ሚሊየን ብር ምን መስራት ይቻላል?ብዙ ጊዜ ብር ሞተ ሲባል እሰማለሁ በትክክል የሞተው ብሩ ነው ወይስ የገበያው መዋቅር፣ የማምረት አቅም እና የፋይናንስ ሲስተሙ ነው? መቸስ ብር ምንዛ...
25/05/2026

በአንድ ሚሊየን ብር ምን መስራት ይቻላል?

ብዙ ጊዜ ብር ሞተ ሲባል እሰማለሁ በትክክል የሞተው ብሩ ነው ወይስ የገበያው መዋቅር፣ የማምረት አቅም እና የፋይናንስ ሲስተሙ ነው? መቸስ ብር ምንዛሬው ምንም ይሁን ምን የትም ዓለም ያለን ምርትም ሆነ አገልግሎት የመግዛት አቅሙ እኩል የሚሆንበት ነጥብ አለ Purchasing Power Parity (PPP) የሚሉት። ለምሳሌ አንድ ግራም ወርቅ ኢትዮጵያ ውስጥ 25,000 ቢሆን አሜሪካ በዚሁ መጠን በሚመነዘር ዶላር ይሸጣል። በዚህ ስሌት ሄደን ስለስራ እናውራ።

ተመልከቱ አንድ ቻይናዊ 43,000 የቻይና ዮዋን ቢኖረውና ቻይና ስራ ልጀምር ቢል ከ 9,000 በላይ የተመዘገቡ ጥቃቅን ግን አትራፊ ስራወች መስራት ይችላል። ኬንያ በዚህ ብር ከጥቃቅን እስከመካከለኛ ስራወች መጀመር ይቻላል።

ይሄንኑ ብር ወደአሜሪካ ውሰዱት ከስድስት እስከ ሰባት ሺዶላር ይሆናል። ምን ይሰራል? የሆነ ስራ አላችሁ እንበል በዚህ ብር ዳውን ፔይመንት(ቅድሚያ ክፍያ) አይናችሁ ያረፈበትን አዲስ መኪና ማውጣትና ኡበርም ስሩበት ሌላ ዘና ብላችሁ ከ5-7 ዓመት ቀሪውን ትከፍላላችሁ። ሌሎች በርካታ ሰራወችን መስራትም ትችላላችሁ። በተለይ የምግብ ዝግጅት፣ ወይም የእጅ ሙያ ካላችሁ ጥሩ መነሻ ነው። በእርግጥ አሁን የዓለም ኢኮኖሚው መሳከር ነገሩን እንደወሬው ቀላል ላያደርገው ይችላል።

ይሄንኑ ገንዘብ ወደኢትዮጵያ መንዝሩት አንድ ሚሊየን ብር ማለት ነው። ምን ትሰሩበታላችሁ? ለምን ሌላ አገር ያውም ግዙፍ የሚባሉ አገራት ጥሩ ስራ ሊያስጀምር የሚችል ገንዘብ አገራችን ላይ ጉልበት አነሰው?

ቻይና ውስጥ በ43,000 ዩዋን (1 ሚሊየን ብር ገደማ) በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቅን ስራዎች የሚገኙት አምራች ማሽኖች፣ ጥሬ ዕቃ እና የሎጂስቲክስ ሲስተሙ እጅግ ስለረከሰና ስለቀለጠፈ ነው። አሜሪካም ውስጥ በ6,000 ዶላር መኪና በዱቤ አውጥቶ በኡበር መስራት የሚቻለው ጠንካራ የብድር (Credit) ሲስተም ስላለ ነው። ኬንያ ክፍት እና ፈጣን የንግድ እንቅስቃሴ ስላላት ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ከብሩ በላይ የፋይናንስ ሲስተሙ ነው ያቀነጨረን። አስተያየት አላችሁ?
MaBizplus

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ እና የሌተር ኦፍ ክሬዲት (LC) መመሪያዎችን አሻሻለ MaBizplus የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር እና የፈቃድ አሰጣጥ ማነቆዎችን በማቃለል ...
25/05/2026

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ እና የሌተር ኦፍ ክሬዲት (LC) መመሪያዎችን አሻሻለ
MaBizplus
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር እና የፈቃድ አሰጣጥ ማነቆዎችን በማቃለል የንግድ ሥራን ለማሳለጥ የሚያስችል አዲስ መመሪያ ይፋ አድርጓል።

ባንኩ ይህ ማሻሻያ የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ውጤታማነት፣ ግልጽነት እና ተወዳዳሪነት ይበልጥ እንደሚያሳድገው አስታውቋል።

በአዲሱ ማሻሻያ መሠረት የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ሒሳብ ላላቸው ተቋማት እና የገቢ ማቆያ (ሪቴንሽን) ሒሳብ ባለቤቶች ከብሔራዊ ባንክ ምንም ዓይነት ቅድመ ፈቃድ ሳይጠብቁ፣ በተቀባይነት ላይ የተመሠረቱ የሌተር ኦፍ ክሬዲት (LC on acceptance) እና ሰነድ በባንክ በኩል የሚከፈልበትን (CAD) የክፍያ ሥርዓቶች እንዲያጸድቁ ሙሉ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል።

በተጨማሪም የውጭ ምንዛሬ ሒሳብ ያላቸው ተቋማት ከባንኮች ቅድመ ፈቃድ ውጭ በሰነዶች (CAD) አሠራር ሥር የዕቃዎች ጭነት እንዲታዘዝ ወይም እንዲጀመር ማድረግ ይችላሉ። ክፍያው የሚፈጸመው ግን አስፈላጊ ሰነዶች ቀርበው በባንኮች ሲረጋገጡ ብቻ ይሆናል።

የአገልግሎት ተመኖች ሥርዓት መያዝ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ብሔራዊ ባንኩ በንግድ ባንኮች የሚጣሉ የሌተር ኦፍ ክሬዲት (LC) ክፍያዎች እና የአገልግሎት ተመኖች ከዓለም አቀፍ አሠራር ጋር እንዲጣጣሙ የቁጥጥር እርምጃ ወስዷል።

በሒሳብ ባለቤቶች ላይ የሚጣሉት የኮሚሽን ክፍያዎች በዓመታዊ መሠረት የሚወሰኑ እና እንደየአገልግሎት ዘመኑ ተመጣጣኝ ተካፍለው (pro-rata) እንዲተገበሩ ታዝዟል።

እነዚህ ተመኖች ከዚህ ቀደም ብሔራዊ ባንኩ ካስቀመጠው ከፍተኛ ገደብ ማለፍ እንደሌለባቸውም በጥብቅ አሳስቧል።

ይህ እርምጃ ለአስመጪዎች እና ላኪዎች የግብይት ወጪን በመቀነስ የኢትዮጵያን የንግድ ፋይናንስ ተወዳዳሪነት በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በተለይም ወደ አምራች ኢንዱስትሪው ለሚገቡ የግብዓት አቅርቦቶች ፈጣን የባንክ አገልግሎት ለማግኘት በማስቻል፣ ሀገራችን ወደ ማኑፋክቸሪንግ መር ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር እና አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ዕድገቱን በጽኑ እንደሚደግፍ ታምኖበታል።

ብሔራዊ ባንክ የተረጋጋ እና ቀልጣፋ የውጭ ምንዛሬ ገበያን ለመገንባት ሒደቱን በቅርበት መከታተሉን እና አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ተጨማሪ እርምጃዎችን መውሰዱን እንደሚቀጥል አስታውቋል።

በለሚ ታደሰ

PUBLIC NOTICE | NOTICE ON FX DIRECTIVE AMENDEMENT AND RATIONALIZATION OF FEES AND CHARGES ON LETTERS OF CREDITMaBizplus ...
25/05/2026

PUBLIC NOTICE | NOTICE ON FX DIRECTIVE AMENDEMENT AND RATIONALIZATION OF FEES AND CHARGES ON LETTERS OF CREDIT
MaBizplus
https://t.me/Mabizpluse

      #ሰሞኑን ጣና ሃይቅ ላይ በተከሰተው የጀልባ መስመጥ አደጋ ብዙዎቻችን አዝነን ስሜታችንን ስንገልፅ ሰንበተናልብዙ ሰውም የተጎዳ መስሎን አንብተናል አልቅሰናል።   #የአደጋው መንስኤም...
24/05/2026



#ሰሞኑን ጣና ሃይቅ ላይ በተከሰተው የጀልባ መስመጥ አደጋ ብዙዎቻችን አዝነን ስሜታችንን ስንገልፅ ሰንበተናል
ብዙ ሰውም የተጎዳ መስሎን አንብተናል አልቅሰናል።

#የአደጋው መንስኤም ሁለት የአሳ ማስገሪያ ጀልባዎች በሞገድ ምክንያት መጋጨት ነበረ
ነገር ግን የተጋጩት ከኃይቁ ዳር ከደረሱ በኋላ ስለነበረ አብዛኛው ሰው በህይዎት ተርፈው ባዕሉን የተካፈሉ ሲሆን።
#የአንድ ሰው ህይት አተናል ነፍስ ይማር።

✅ሌላ ጀልባው ላይ የነበሩ አራት ሰዎች ደግሞ ተፈልገው ያልተገኙ ሲሆን የአብዛኛው ግምት ግን አደጋው የደረሰብት የሀይቁ ዳር አካባቢ በዓሉን ሚያክብር ብዙ የተሰበሰበ ሰው ስለነበረ ወተው ከህዝቡ ጋር ተቀላቅለው ሊሆን ይችላል የሚል ነው።

✅በአዳጋው የአንድ አባት ህይወት ነው ያጣነው 🙏
የሚጠብቀን አምላክ አያንቀላፋም🙏
Mihret Takele ✍️

ግንቦት 15/2018  #10 ብር ሲሸጥ የነበረው  #ዳቦ 12 ፣ 15 ብር ገብቷል፡፡15 ብር ይሸጥ የነበረው ደግሞ 20 ፣ 25 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ይህም የሸማቹን ኪሱ ይብሱኑ እየተፈታተነው...
23/05/2026

ግንቦት 15/2018 #10 ብር ሲሸጥ የነበረው #ዳቦ 12 ፣ 15 ብር ገብቷል፡፡

15 ብር ይሸጥ የነበረው ደግሞ 20 ፣ 25 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

ይህም የሸማቹን ኪሱ ይብሱኑ እየተፈታተነው ነው፡፡

ዳቦ እንዲህ ዋጋው እየተወደደ የመጣው በምን ምክንያት ነው?

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. https://youtu.be/-6kpILhNsv0

ንጋት መኮንን

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የናፍጣ ዋጋ እንዲቀንስ ትዕዛዝ አስተላለፉ​  I የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በአሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር እያደረጉት ባለው ጦርነት ምክንያት የነ...
23/05/2026

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የናፍጣ ዋጋ እንዲቀንስ ትዕዛዝ አስተላለፉ
​ I የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በአሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር እያደረጉት ባለው ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በመናሩ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞና የትራንስፖርት አድማ ተከትሎ፣ የናፍጣ ዋጋ እንዲቀንስ መንግስታቸው መወሰኑን አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ከሀገሪቱ የትራንስፖርት ዘርፍ ተዋናዮች ጋር ከተወያዩ በኋላ በሰጡት መግለጫ፣ በቅርቡ በሚወጣው የሰኔ እና ሐምሌ ወራት የዋጋ ክለሳ ላይ በአንድ ሊትር ናፍጣ ላይ የ10 የኬንያ ሺሊንግ ቅናሽ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

​በመካከለኛው ምስራቅ በተቀሰቀሰው ጦርነት እና የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋትን ተከትሎ በኬንያ የናፍጣ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ የነበረ ሲሆን፣ ይህም በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በሀገሪቱ የተቀሰቀሰ ከፍተኛ የትራንስፖርት መዘጋት እና የሰዎች ህይወት የጠፋበት ተቃውሞ አስከትሏል። መንግስት የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ ከ28 ቢሊዮን ሺሊንግ በላይ በድጎማ እና በታክስ ቅናሽ መልክ ወጪ ማድረጉን ፕሬዝዳንት ሩቶ ገልጸዋል። ይህ አዲሱ የዋጋ ቅናሽ ውሳኔ በሀገሪቱ ተፈጥሮ የነበረውን የትራንስፖርት አድማ ለማርገብ የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል።

በስህተት የገባለትን 200 ሺህ ብር  የመለሰው ዘመኑ አታላይ ​  I በ“ዜና 24” ዲጂታል ሚዲያ የካሜራ ባለሙያ የሆነው ወጣት ዘመኑ አታላይ፣ በስህተት ወደ ባንክ አካውንቱ የገባለትን 200...
23/05/2026

በስህተት የገባለትን 200 ሺህ ብር የመለሰው ዘመኑ አታላይ

​ I በ“ዜና 24” ዲጂታል ሚዲያ የካሜራ ባለሙያ የሆነው ወጣት ዘመኑ አታላይ፣ በስህተት ወደ ባንክ አካውንቱ የገባለትን 200 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ለባለቤቱ በታማኝነት መለሰ። ወጣቱ ብሩን ለመመለስ በቅድሚያ ብሄራዊ የዲጂታል (ፋይዳ) መታወቂያ ማውጣት ነበረበት።

​የካሜራ ባለሙያው ዘመኑ አታላይ በስህተት ወደ ሂሳብ ቁጥሩ የገባውን ይህንን ከፍተኛ ገንዘብ ለባለቤቱ ለማስረከብ በፈለገበት ወቅት፣ የወቅቱን የባንክ አሰራርና መመሪያ ተከትሎ ለመንቀሳቀስ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ማቅረብ ግድ ሆኖበታል። ወጣቱ መታወቂያው ያልነበረው ቢሆንም፣ የሌላውን ሰው ገንዘብ በአስቸኳይ ለመመለስ ሲል የፋይዳ መታወቂያ የመውሰድ ሂደቱን በፈጣን ሁኔታ አጠናቋል።

​አስፈላጊውን ህጋዊና የባንክ ፕሮሰስ በሙሉ ካጠናቀቀ በኋላ፣ በአካውንቱ ላይ ተቀምጦ የነበረውን ሙሉ 215 ሺህ ብር ለትክክለኛው የገንዘቡ ባለቤት በዛሬው ዕለት በሰላም አስረክቧል። ድርጊቱ በዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎችና በታዘቡት የባንክ ደንበኞች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል።

23/05/2026

ነጻ ሕክምና ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ!!

ከግንቦት 23-27/2018 ዓ.ም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባሉን ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት ሀኪሞችና ከእስራኤል ሐገር በሚመጡ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት ይሰጣል::

አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች
------------------------------------------
1. የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy)

2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery)

3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery)

4. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና

5. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ናቸው::

የጋራ ጥረት ለማኅበረሰብ ጤንነት!

ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Address

Sudan Street
Debra Markos

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MaBizplus posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to MaBizplus:

Share