KOO KEET

KOO KEET Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from KOO KEET, Marketing Agency, Addis Ababa.

09/06/2026

ከእርሻ እስከ ፍርድ ቤት፣ ከመንገዶች እስከ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ኢትዮጵያ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ዜጎችን ማዕከል ያደረጉ አገልግሎቶችን የሚሰጥ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር እየገነባች ነው።



ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

09/06/2026
09/06/2026
09/06/2026
አዲስ የጤና ቴክኖሎጂ ለአዲስለአዲስ አበባ አዲስ የሆነ እና በአይነቱ የመጀመሪያው ነው የተባለለት የጤና አገልግሎት ተጀምሯል፡፡አግልገሎቱ የከተማችንን ህዝብ የጤና አገልግሎት በአዲስ ከፍታ ላ...
06/06/2026

አዲስ የጤና ቴክኖሎጂ ለአዲስ

ለአዲስ አበባ አዲስ የሆነ እና በአይነቱ የመጀመሪያው ነው የተባለለት የጤና አገልግሎት ተጀምሯል፡፡አግልገሎቱ የከተማችንን ህዝብ የጤና አገልግሎት በአዲስ ከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ ነው፡፡ ይህ ብዙ የተባለለት የጤና አገልግሎት የዲ.ኤን፣ኤ (DNA) የፎረንሲንክ እና የስነ-ምረዛ ምርመራ ልህቀት ማዕከል ሲሆን ማዕከሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቋል፡፡

የማዕከሉ አገልግሎት ስራ ሲጀመር አገራችን ከፍተኛ ወጪ የምታወጣባቸው የጤና ምርመራ አግልገሎቶች በአገር ውስጥ እንዲሰጡ ያስችላል፡፡ በዚህም ውጪ አገር በመላክ ረጅም ጊዜ ይወስድ የነበረው ምርመራ በአገር ውስጥ ፈጣን በሆነ መንገድ ማግኘትን ያስችላል፡፡ በዚህም በከፍተኛ ደረጃ ጊዜንም ወጪንም ይቆጥባል ተብሎለታል፡፡

ማዕከሉ ለአዲስ አዲስ የሚያሰኘው ሌላው ጉዳይ ዘመናዊ ምርመራ መስጠቱ ብቻ ሳይሆን የጤና መረጃ ማዕክል የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህም ማዕከሉ የDNA መረጃ ማካመቻና ማነፃፀሪያ ሲስተም (CODIS)፣ በወንጀል የተጠረጠሩ ፣ ወላጅነትን ለማረጋገጥ የሚቀርቡ የማስረጃ ጥያቄዎችን እና ተመሳሳይ የዘር መለያ ፣ የቤተሰብ ግንኙነት የዘር ሀረግ መለይትንና ማረጋገጥን የመሳሰሉ ዘመናዊ አግልግሎቶችን የሚሰጥ ዘመናዊ ማእክል ነው፡፡

ማዕከሉ ከጤና ባሻገር የአገራችንን የፍትህ ስርዓት በማገዝም እጥፍ ድርብ ጠቀሜታ እንዳለው ነው ከንቲባዋ የተናገሩት፡፡ ምክንያቱም ደግሞ የፍትህ ስርዓቱ ማስረጃዎች መካከል አንዱ በዚህ ማዕክል የሚሰጡ የDNAን አይነትና ተዛማጅ የጤና ምርመራ ማስረጃዎች ናቸው፡፡

በዚህም እነዚህ አግልግሎቶች ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ማግኘት ከተቻለ ቀልጣፋ ፍትህም ማግኘት ይቻላል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የህብረተሰቡ የመብት ጥያቄዎችን በብቃት ለመመለስ ማዕከሉ ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡ በእነዚህና በመሳሰሉት የማእከሉ አዳዲስ አግልግሎቶች የተነሳ አዲስ የጤና ቴክኖሎጂ በአዲስ ተጀመረ ተብሎሎታል፡፡

06/06/2026

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KOO KEET posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share