Dallol Marketing & Communication

Dallol Marketing & Communication We offer state of the art media & communication Services(Media Production,Consultancy, Advertisment & Event Organizing).

Dallol Media & Communications PLC is a privately held media production company; based in Addis Ababa,Ethiopia. Dallol was established in 2016 with the intention of making a difference on the media industry, and committed to ensure inspiring media out put that can meet the need of its potential consumers. With a team of highly skilled experts in the media industry for about two decades; Dallol Prov

ides a holistic range of media Production & Communications services for Digital, Print & online media outlets; Among many :- Event Management,Advertisement,Media production,Marketing,Consultancy and lots more. For further information; you may visit our website using this link http://dallolmedia.com/

  እድል ለትግርኛ እና እንግሊዘኛ ተናጋሪዎች!   #ትግርኛ እና  #እንግሊዘኛ ተናጋሪ የሆናችሁ እና ከድርጅቱ ጋር ለመስራት የምትፈልጉ ብትሞክሩት መልካም ነው።
10/08/2019

እድል ለትግርኛ እና እንግሊዘኛ ተናጋሪዎች!

#ትግርኛ እና #እንግሊዘኛ ተናጋሪ የሆናችሁ እና ከድርጅቱ ጋር ለመስራት የምትፈልጉ ብትሞክሩት መልካም ነው።


Facebooks uppdrag är att göra det möjligt för människor att skapa en community och föra världen närmare samman. Tillsammans kan vi hjälpa människor att skapa starkare communities - gå med.

ሀያ ሁለት አካባቢ(አዲስ አበባ) ዛሬ ቀትር ላይ ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥቷል!በስፍራው ተገኝቼ እንዳየሁት ፖሊስ ሁለት የሰው ህይወት ያለፈባቸው ስፍራዎችን ከቦ መረጃ እየወሰደ ነው። ፖሊ...
07/08/2019

ሀያ ሁለት አካባቢ(አዲስ አበባ) ዛሬ ቀትር ላይ ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥቷል!

በስፍራው ተገኝቼ እንዳየሁት ፖሊስ ሁለት የሰው ህይወት ያለፈባቸው ስፍራዎችን ከቦ መረጃ እየወሰደ ነው። ፖሊሶች "እያጣራን ስለሆነ መረጃ አሁን የለንም" ያሉኝ ሲሆን የአካባቢው እማኞች ግን አንድ ግለሰብ "ሞባይል ሊሰርቀኝ ነበር" በማለት የሌላ ሰው ጭንቅላት ላይ ተኩሶ ገድሏል። ከዛም ተኳሹ በሰዎች ተይዞ አካባቢው ወዳለ ፖሊስ ጣብያ ቢወሰድም የገዳዩን ሽጉጥ ይዞ የነበረው ፖሊስ "ባርቆበት" በአካባቢው የሱቅ ባለቤት የነበረን ግለሰብ መትቶ እሱም ህይወቱ አልፏል።

ማሳሰብያ: የዛሬው ግድያ ትናንት እዛው ሀያ ሁለት ተፈፅሞ ነበር ተብሎ በሀሰት ከተናፈሰው የግድያ ወሬ ጋር ግንኙነት እንደሌለው አረጋግጫለሁ።

ኤልያስ መሰረት

የኬንያ መንግስት "እየሱስ ነኝ" እያለ ገንዘብ ሲሰበስብ የነበረውን ነጭ ግለሰብ ከሀገሩ አባሯል!ግለሰቡ ሰሞኑን በወጡ ቪድዮዎች ላይ እንደታየው በኬንያ መንገዶች ላይ እየተዘዋወረ ተአምር እሰ...
07/08/2019

የኬንያ መንግስት "እየሱስ ነኝ" እያለ ገንዘብ ሲሰበስብ የነበረውን ነጭ ግለሰብ ከሀገሩ አባሯል!

ግለሰቡ ሰሞኑን በወጡ ቪድዮዎች ላይ እንደታየው በኬንያ መንገዶች ላይ እየተዘዋወረ ተአምር እሰራለሁ፣ ገነትንም ትወርሱ ዘንድ እረዳለሁ እያለ ገንዘብ ሲሰበስብ ነበር። ከግለሰቡ መባረር በተጨማሪ እሱን ወደ ኬንያ እንዲመጣ ያረጉ የኬንያ ፓስተሮችን መንግስት አስሯል ብሎ ዴይሊ አፍሪካ ዘግቧል።

 #እርጅናን  የሚያጠፋ   ==========================ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ ፊታችንን ጨምሮ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችን ላይ የሚታይ የቆዳ መሸብሸብን በማጥፋት የወጣትነ...
11/01/2019

#እርጅናን የሚያጠፋ
==========================
ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ ፊታችንን ጨምሮ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችን ላይ የሚታይ የቆዳ መሸብሸብን በማጥፋት የወጣትነት ገፅታ እንድንላበስ የሚያስችል የቆዳ ማተምያ ቁስ ተሰራ።

ይህ “ #አፕቴ” የተሰኘ አዲስ በሰውነታችን ላይ የሚታዩ የቆዳ ሽብሽብ መስመሮችን የመሸፈን ስራ ያከናውናል።በሰከንድም እስከ 200 የሽብሽብ ፍሬሞችን የመሸፈን አቅም እንዳለው ተገልፆዋል።

ቴክኖሎጂው በውስጡ በተገጠመለት የረቀቀ ካሜራ አማካኝነት የቆዳችንን ቀለም እና አይነት በመለየት ወደ ማይክሮ ፕሮሰሰር መረጃ የሚልክ ሲሆን ይህንን ተከትሎም በላዩ ላይ የተገጠሙት 120 የሚሆኑ የማተምያ ቀዳዳዎች ለቆዳችን የሚስማማውን ንጥረ ነገር በቆዳችን ላይ ያትማሉ።

ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ግኝት በአሁኑ ሰዓት በላስቬጋስ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ለእይታ ቀርቧል ።

ምንጭ: ቢቢሲ

የቦሌ ዓለምአቀፍ ኤርፖርት አዲሱ ተርሚናል መንገደኞችን ማስተናገድ ጀመረ=========================================አዲሱ ተርሚናል ወደ ስራ መግባቱ   በዓመት 22 ሚልዮ...
11/01/2019

የቦሌ ዓለምአቀፍ ኤርፖርት አዲሱ ተርሚናል መንገደኞችን ማስተናገድ ጀመረ
=========================================
አዲሱ ተርሚናል ወደ ስራ መግባቱ በዓመት 22 ሚልዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንዲኖረው የሚያስችል ሲሆን ይህም ከአፍሪካ ትልቁ የኤርፖርት ድርጅት እንዲሆን ያደርጓል።

New terminal starts servicing passengers!!! Now, Bole has a capacity to serve 22 million a year. That would make it the largest airport facility in Africa. Flyethiopian

የኢትዮጵያውያንን የፈጠራ ሃሳቦችንና ስራዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ በነፃ ለመመዝገብና ለመጠበቅ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡=========================================...
09/01/2019

የኢትዮጵያውያንን የፈጠራ ሃሳቦችንና ስራዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ በነፃ ለመመዝገብና ለመጠበቅ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡
=========================================

‹‹ ›› ( ) የተሰኘው ድርጅት የኢትዮጵያ የፈጠራ ስራዎችን ለመመዝገብና ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችለውን ስምምነት ከ ጋር ተፈራርሟል፡፡
ሰምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) እና ‹‹የሴቭ አይዲያ›› መስራችና ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሃዝቦ ሾኮ ፈርመውታል፡፡

ሴቭ አይዲያ የተሰኘው ድርጅት በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የፈጠራ ስራዎችን በነፃ የሚመዘግብ፤ የሚጠብቅ፤ ሃሳቦቹ ወደ ስራ እንዲገቡ ከባለሃብቶች ጋር የማገናኘት ስራ የሚሰራና ራሱም የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት ነው፡፡

ስራዎቹን ኦንላይን ለህዝብ ክፍት በማድረግ እንዲተዋወቁ የማድረግ ስራ የሚሰራው ድርጅቱ በአፍሪካ ውስጥ ደቡብ አፍሪካ፤ ታንዛኒያ፤ ኬንያ፤ አይቮሪኮስትና ቦትስዋና ይሰራል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) ሚኒስቴሩ ‹‹በዲዛይን ኢትዮጵያ›› ውድድር ወቅት የቀረቡ የኢትዮጵያውን የፈጠራ ሃሳቦች አለም አቀፍ እውቅና ኖሯቸው እንዲጠበቁና ወደ ስራ እንዲገቡ ፍላጎት አለው ብለዋል፡፡

‹‹ሴቭ አይዲያ›› የአፍሪካ ቢሮውን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚከፍት ፕሬዝዳንቱ ፕሮፌሰር ሃዝቦ ሾኮ ተናግረዋል፡፡

ቤል ካሽ ሁለት   ገፆችን ሊያስጀምር ነው===================================================  ተጠቃሚዎች በበይነመረብ አማካኝነት ግብይት መፈም የሚችሉባቸው ሁለ...
09/01/2019

ቤል ካሽ ሁለት ገፆችን ሊያስጀምር ነው
===================================================
ተጠቃሚዎች በበይነመረብ አማካኝነት ግብይት መፈም የሚችሉባቸው ሁለት የኤሌክትሮኒክ መገበያያ ገፆችን በቅርቡ እንደሚያስጀምር አስታወቀ።
የተሰኘው ገፅ በዋነኛነት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ተገልጋዮቹ ብቻ ካሉበት ቦታ ሆነው ቁሳቁሶችን የሚሸምቱበት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በበይነመረብ አማካኝነት የግዥ ትእዛዝ እና ክፍያ የተፈፀመባቸው ቁሳቁሶቹን ወደ ደምበኞች ለማጓጓዝም ከ #ዲኤችኤል ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።

ተቋሙ በመጀመርያው ምዕራፍ ወደ 2,500 የሚጠጉ ሴት ኢትዮጵያውያን በባለቤትነት በሚያስተዳድሩዋቸው የተለያዩ ድርጅቶች የተመረቱ ምርቶችን ለማሻሻጥ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል።
በተመሳሰይ ቤልካሽ ከኢትዮጵያ ውጭ ሆነው የኤሌክትሮኒክ ግብይት መፈፀም ለሚፈልጉ ደንበኞቹ አገልግሎት የሚሰጥ የተሰኘ ሌላ ገፅ ያዘጋጀ ሲሆን የክፍያ ስርዓቱም በማስተር ካርድ አማካኝነት አንደሚከወን ለማወቅ ተችሏል።

ቤልካሽ ኢትዮጵያ ፤ መቀመጫውን ኔዘርላንድ ባደረገው እና የተሰኘ በኤሌክትሮኒክ ክፍያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ድርጅት እህት ኩባንያ ሲሆን እ.ኤ.አ ከ2011 ጀምሮ በኢትዮጵያ በተለይም በሞባይል ክፍያ አና የገንዘብ ማስተላለፍ ዘርፎች ላይ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ከኩባንያው ድረገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኤሌክትሮኒክ ክፍያ ስርዓት በተገቢው አለመስፋፋት እና በዚህ ዘርፍ ላይ ግልፅ የሆኑ ፖሊሲዎችን አለመኖራቸው በኢትዮጵያ መሰል የኤሌክተሮኒክ ግብይት ተቋማት እንዳይስፋፉ እንቅፋት መሆኑን ባለሞያተኞች ይገልፃሉ።

ምንጭ፡ #አዲስፎርቹን

ኬንያ ከቱሪዝም ዘርፏ  1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር  አገኘች=======================ኬንያ በፈረንጆቹ  2018 የቱሪዝም ሀብቷን ከጎበኙ ቱሪስቶች 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ማግኘቷ...
09/01/2019

ኬንያ ከቱሪዝም ዘርፏ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር አገኘች
=======================
ኬንያ በፈረንጆቹ 2018 የቱሪዝም ሀብቷን ከጎበኙ ቱሪስቶች 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ማግኘቷ ተገለፀ፡፡

ሀገሪቷ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ጎብኝዎችን በማስተናገድ ነው ይህን ገቢ ማግኘት የቻለችው፡፡

ይህ ውጤት የተመዘገበው መንግስት የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ በያዘው ዕቅድ እና በአዳጊ ገበያዎች ላይ በተሰራ ከፍተኛ የማስተዋወቅ ስራ መሆኑን የሀገሪቱ ቱሪዝም ካቢኔ ፀሃፊ ናጅብ ባላላ ተናግረዋል፡፡

225 ሺህ 157 አሜሪካዊያን ኬንያን በመጎብኘት አሁንም በቀዳሚነት በመቀመጥ የሀገሪቱ የቱሪዝም ቁልፍ የገቢ ምንጭ ሆነዋል፡፡

ቻይናዊያን ጎብኝዎች ኬንያን ለጉብኝት መዳረሻ በማድረግ ቁልፍ ቦታ መያዝ የቻሉ ሲሆን፥81 ሺህ 709 ቻይናዊያን በ2018 ኬንያን ጎብኝተዋል፡፡

ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ የምታገኘበት ዘርፍ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን አፍሪካ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና በበረራ ቁጥር ET 338 የተመዘገበው ቦይንግ B-737-800 የመንገደኞች አውሮፕላን በኡጋንዳ ኢንተቤ በማረፍ ላይ እንዳለ ከመንደርደሪያው በጥቂት ...
03/01/2019

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና በበረራ ቁጥር ET 338 የተመዘገበው ቦይንግ B-737-800 የመንገደኞች አውሮፕላን በኡጋንዳ ኢንተቤ በማረፍ ላይ እንዳለ ከመንደርደሪያው በጥቂት ሜትሮች በመውጣት የመንሸራተት ችግር እንዳጋጠመው ተሰማ፡፡አውሮፕላኑ ከመሰመሩ የመውጣት ችግር ያጋጠመው ዛሬ ጠዋት መንገደኞችን ከአዲስ አበባ አሳፍሮ ወደ ኡጋንዳ ርዕሰ ከተማ ኢንተቤ መደበኛ በረራ አድርጎ በማረፍ ላይ በነበረበት ወቅት መሆኑን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ ገፅ ሚዲያ ከተሰራጨው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

መንገደኞቹም ሆነ የበረራ ሰራተኞቹ ምንም ጉዳት አልደረሰባቸውም፤በአውሮፕላኑ ላይም የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል፡፡ከኢንተቤ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ተመዝግበው የነበሩ መንደኞችን ለማጓጓዝ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና ፤ ለተፈጠረው መጉላላት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል፡፡የአደጋው መንስኤም እየተመረመረ ነው ተብሏል፡፡

02/01/2019

በቅርቡ በ #ኢትዮጵያ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለለትን ( ) ምንነት ለማወቅ ቪድዮውን ይመልከቱ

የበይነመረብ ጠንሳሹ ዶ/ር   በ81 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ========================================= #በይነመረብ አሁን ከምንጠቀምበት የረቀቀ ደረጃ ላይ ከመድ...
02/01/2019

የበይነመረብ ጠንሳሹ ዶ/ር በ81 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
=========================================
#በይነመረብ አሁን ከምንጠቀምበት የረቀቀ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት በመሰረታዊ ንድፈ ሃሳብ እንዲጠነሰስ እና ተግባር ላይ እንዲውል ትልቅ አስተዋፅኦ ካደረጉ ግንባር ቀደም ተመራማሪዎች መካከል አንዱ የሆነው አሜሪካዊው ተመራማሪ ዶ/ር ላሪ ሮቤርትስ በ81 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ዶ/ር ላሪ በአሜሪ የጦር ሃይል ምርምር ማዕከል አማካኝነት የተመሰረተው እና " #አርፓኔት- " የተሰኘውን የ እንዲገነባ ተልዕኮ የተሰጠውን የተመራማሪዎች ቡዱን እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ መረሻ ከተቀላቀለበት ግዜ አንስቶ አሁን ድረስ እየተገለገልንበት ለሚገኘው በይነመረብ እውን እንዲሆን አስፈላጊ የተባሉትን የሶፍትዌር እና ሃርድዌር ግብኣቶችን በማበልፀጉ ሂደት ላይ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል።

ዶ/ር ላሪ_ሮቤርትስን ጨምሮ በዚህ ታሪካዊ ፕሮጀክት ሂደት ውስጥ ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፣ #ቪንትሰርፍ እና የተባሉ እውቅ ተመራማሪዎች እና የቀድሞ የስራ ባልደረቦች ለበይነመረብ እውን መሆን ባበረከቱት ታላቅ አስተዋፅኦ ምክንያት “ ” የሚል መጠርያ ማግኘታቸው ይታወቃል።

ዶ/ር ላሪ ሮቤርተስ በደረሰበት ድንገተኛ የልብ ህመም ምክንያት እ.ኤ.አ ዲሰምበር 26/2018 ፤ በ81 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ምንጭ: #ቢቢሲ

የእስራኤል ተመራማሪዎች በሳምንቱ ውስጥ አንድ ያልተለመደ ነገርን ይዘው መጥተዋል እርሱም አበቦች የነፍሳትን ድምጽ መስማት እንደሚችሉ ይፋ ማድረጋቸው ነው፡፡አበቦቹ የአበባ ቀሳሚዎቹን ነፍሳት ...
31/12/2018

የእስራኤል ተመራማሪዎች በሳምንቱ ውስጥ አንድ ያልተለመደ ነገርን ይዘው መጥተዋል እርሱም አበቦች የነፍሳትን ድምጽ መስማት እንደሚችሉ ይፋ ማድረጋቸው ነው፡፡

አበቦቹ የአበባ ቀሳሚዎቹን ነፍሳት ድምጽ በሚሰሙበት ወቅት በሦስት ደቂቃ ውስጥ በውስጣቸው ያለውን የስኳር መጠን ይጨምራሉ ብለዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ጥናቱን ያካሄዱት ፕሪምሮስ በተሰኘው የዱር አበባ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተክሎች ከመስማት ባሻገር የማሽተት፣ የንክኪ እና የብርሃን ስሜቶችን ስለመያዛቸውና ምላሽ እንደሚሰጡም በቅርብ የተካሄዱ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dallol Marketing & Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Dallol Marketing & Communication:

Share