ETHIO SAT DISH TEC

ETHIO SAT DISH TEC Et

አስቸኳይ የፍለጋ ጥሪ ሙባረክ ሰይድ እንድሪስ ⭐️⭐️⭐️ ሼር ሼር ሼር***ለሰው ልጅ በሙሉ ይድረስ! አንድን እናት ከጭንቅ፣ አንድን ህፃን ከጥፋት ለመታደግ ሰከንዶችን እንጠቀም። ከአቃቂ ቃሊ...
04/03/2026

አስቸኳይ የፍለጋ ጥሪ ሙባረክ ሰይድ እንድሪስ ⭐️⭐️⭐️ ሼር ሼር ሼር
***
ለሰው ልጅ በሙሉ ይድረስ! አንድን እናት ከጭንቅ፣ አንድን ህፃን ከጥፋት ለመታደግ ሰከንዶችን እንጠቀም።

ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው መብራት ሀይል አካባቢ የጠፋው ህፃን ሙባረክ ሰይድ እንድሪስ ይባላል በቀን 23/06/2018ዓ/ም ከቀኑ 11:0 ሰዓት አካባቢ ከመኖሪያ አካባቢው የጠፋው እድሜው 6 ዓመት ቀይ በእለቱ ጥቁር ትሸርት እና ነጭ ሱሪ ለብሷል

* ስም ሙባረክ ሰይድ እንድሪስ
* እድሜ 6 ዓመት

* ይህ መረጃ ለብዙ ሰው እንዲደርስ በማድረግ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን። የእርስዎ አንድ ሼር የህፃኑን ህይወት ሊታደግ ይችላል።

* ይህን ህፃን ያያችሁ ወይም ያለበትን የምታውቁ በነዚህ ስልኮች በአስቸኳይ ደውሉልን፦

* 0921635499
* 0912714945
* 0912268653

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ሞት ሀዘናቸዉን እንደገለጹ ተደርጎ የተሰራጨው ስክሪን ቅጂ ሀሰተኛ ነው ሲል ኢትዮጵያ ቼክ አጋርቷል።ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በኢራ...
04/03/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ሞት ሀዘናቸዉን እንደገለጹ ተደርጎ የተሰራጨው ስክሪን ቅጂ ሀሰተኛ ነው ሲል ኢትዮጵያ ቼክ አጋርቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ሞት ሀዘናቸዉን እንደገለጹ የሚያሳይ ስክሪን ቅጂ (screenshot) በተለያዩ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ ይገኛል።

ይህ ስክሪን ቅጂ “በወንድሜ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ ሞት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልጻለሁ። ኻሚኒ ላለፉት 40 አመታት ኢራንን በለዉጥ ጎዳና የመሩ ብርቱ ሰው ናቸዉ” የሚል መልዕክት ይዟል። በተጨማሪም “ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላ ኢራናዊያን መጽናናትን እመኛለሁ” ይላል።

ኢትዮጵያ ቼክ በብዙዎች ጥቆማ መሰረት የዚህን ስክሪን ቅጂ ትክክለኛነት ለማጣራት በመጀመርያ መልዕክቱ የጠ/ሚሩ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች ላይ እንዳለ ቅኝት አድርጎ እንደዚህ አይነት መልዕክት እንደሌለ ተመልክቻለሁ ብሏል።

በሁለተኛነት ይዘታቸው የተቀየሩ ፎቶዎችን ለመመርመር የሚረዳውን ‘Fotoforensics’ ድረ-ገጽን መጠቀሙን ኢትዮጵያ ቼክ ገልጿል።

ይህ ድረ-ገጽ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌስቡክ ስም የሚገኝበት የስክሪን ቅጂዉ ክፍል የተነካካ ወይም በኮፒ ፔስት (Copy and Paste) ይዘቱ የተቀየረ እንደሆነ አሳይቷልም ብሏል።

በሌላ በኩል በስክሪን ቅጂዉ ላይ የሚገኘው ይዘቱ የተለጠፈበትን ጊዜ የሚያሳይ መግለጫ (Time Stamp) የፊደላት ቅርጽ (Font) ስህተት እንዲሁም ከበስተቀኙ የሚገኘው የግላዊነት ቅንብር የአለም ምስል (Public Privacy Setting Globe Icon) ደግሞ የአቀማመጥ ግድፈት (Misalignment) ያለበት መሆኑንም መመልከቱን ኢትዮጵያ ቼክ ገልጿል።

በተጨማሪም የስክሪን ቅጂዉ ዋና ይዘት ጽሁፍም በተመሳሳይ መልኩ የተለያዩ ግድፈቶች ያሉበት ሲሆን ይህም በቅንብር የተሰራ እንደሆነ የሚጠቁም ነው ብሏል።

በመጨረሻም፣ መረጃው በተለጠፈ በ14 ደቂቃ ውስጥ 44,500 ግዜ ሪአክሽን እንዳገኘ ማሳየቱ በጠ/ሚሩ የፌስቡክ ገፅ ላይ ያለውን መስተጋብር እንደማያሳይ አይተናል ሲል ኢትዮጵያ ቼክ ጨምሮ ገልጿል።

በሌላ በኩል ግን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ኢራን በኩዌት ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ ከኩዌት ልዑል አልጋ ወራሽ ጋር በስልክ መወያየታቸው እንዲሁም በአገሪቱ ላይ የሚፈጸም ጥቃትን በጽኑ ማውገዛቸውን የኩዌት የዜና ወኪል መዘገቡም ተገልጿል።

ምንጭ- ኢትዮጵያ ቼክ

የእስራኤል ጦር የሄዝቦላህ የስለላ አዛዥን መግደሉን አስታወቀ***የእስራኤል ጦር የሄዝቦላህ የስለላ ዋና መሥሪያ ቤት ኃላፊ ሆኖ ያገለገለውን ሁሴን ማክሌድን በአንድ ሌሊት መግደሉን አስታውቋል...
03/03/2026

የእስራኤል ጦር የሄዝቦላህ የስለላ አዛዥን መግደሉን አስታወቀ
***
የእስራኤል ጦር የሄዝቦላህ የስለላ ዋና መሥሪያ ቤት ኃላፊ ሆኖ ያገለገለውን ሁሴን ማክሌድን በአንድ ሌሊት መግደሉን አስታውቋል።

በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት መገደሉን ወታደሮቹ አስታውቀዋል።

የሄዝቦላህ ታጣቂ ቡድን የኢራኑን ሉዓላዊ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒን ግድያ "ለመበቀል" በሚል በእስራኤል የጦር ሰፈር ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ይታወቃል።

​የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ በኢራን ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ለመመከት ወደ ጦርነቱ መግባቱንና የመጀመሪያዎቹን ሮኬቶች ወደ ሰሜን እስራኤል መተኮሱን አረጋግጧል።

የቡድኑ መሪ ናይም ቃሲም "ወረራውን የመመከት ግዴታችንን እንወጣለን፤ የክብርና የጥንካሬ ሜዳውንም አንለቅም" ሲሉ ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል።

ሄዝቦላህ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሱን ተከትሎ፥ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ከ50 በላይ ከሚሆኑ የሊባኖስ መንደሮች ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ አዟል።

እስካሁን በስለላ አዛዡ ግድያ ዙሪያ ከቡድኑ የተሰጠ ምንም አይነት አስተያየት የለም።

Address

Asco
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ETHIO SAT DISH TEC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ETHIO SAT DISH TEC:

Share