Exclusive Ethiopia

Exclusive Ethiopia ለተመረጡ ቃለ መጠይቆች ብቻ ☕️ ☕️

"ሴተኛ አዳሪነት" እዛም አለ ለካ! ይሄ ነገር የሰው ልጅ ባህሪ ብቻ ይመስለኝ ነበር። ዛሬ ናሽናል ጅኦግራፊ ላይ ሳነብ ለካስ በእንስሳቱም አለም አለ። በቺምፓንዚዎች ዘንድ Meat-for-se...
14/04/2026

"ሴተኛ አዳሪነት" እዛም አለ ለካ!

ይሄ ነገር የሰው ልጅ ባህሪ ብቻ ይመስለኝ ነበር። ዛሬ ናሽናል ጅኦግራፊ ላይ ሳነብ ለካስ በእንስሳቱም አለም አለ።
በቺምፓንዚዎች ዘንድ Meat-for-sex የሚባል ልምድ አለ። ተመራማሪዎች እንደታዘቡት፣ አዳኝ የሆኑ ወንድ ቺምፓንዚዎች የገደሉትን ስጋ ይዘው እየተንጎማለሉ "ከዝንጆሮ ቆንጆ" ይመርጡና ቀልባቸው ላረፈባት ይሰጧታል። ሴቷ ስጋውን ከወሰደች በኋላ ቅጠል ይጋፈፋሉ (መቸስ ጫካ አንሶላ የለ)

የሚገርመው እንደሚከፈለው ስጋ አይነትና ብዛት አንዴ ወይም ሁለት ሶስት ቀን በተከታታይ ሊሆን ይችላል ጉዳዩ።
በአንታርክቲካ የሚገኙ የአዴሊ ፔንግዊኖች ደግሞ ሴተኛ አዳሪነትን "በቁም ነገር" ነው የሚጠቀሙበት። በሰውኛ ካየነው ክፍያውን "ለጌጣጌጥና ሱስ" አያውሉትም። ሴቷ ቤት ልትሰራ ስታስብ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ነገር ታዘጋጃለች። ለጎጆ መሥሪያ የሚሆኑ ድንጋዮችን ወንዶቹ ይዘው ይመጣሉ። በአንታርክቲካ ድንጋይ እንደ ወርቅ ውድ ነው። ሴቷ ፔንግዊን ጎጆዋን ሰርታ እንቁላሏን ከበረዶ ለመጠበቅ ድንጋይ የግድ ያስፈልጋታል። ወንዱ ድንጋይ ይዞ ሲመጣ የምታደርገው ስምምነት ለህልውና የሚደረግ ትግል እንጂ ለደስታ ብቻ አይደለም። የሆነ ሆኖ ወንድ ሰው ይሁን እንስሳ ለዛ ነገር የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። እና አሪፍ ድንጋ ይዞ የመጣው ጋር እነሆ በረከት ነው። ቤቱ እስኪያልቅ ድንጋይ ከከፈሉ ወንዶች ጋር ሁሉ ትተኛለች። ድንጋይ በቃ ዶላር በሉት በዚያ ሰዓት። አንዳንዴ ደግሞ ድንጋዩን ለመውሰድ ብቻ ግንኙነት እንደምትፈጽም ቃል ገብታ ድንጋዩን ይዛ የምትሮጥባቸው ጊዜያትም አሉ

በጣም ያሳዘነኝ ግን የንቦች ነው። ለካ እንደቀልድ እየቆረጥን የምንሰለቅጠው ማር በሀላል የመጣ አይደለም ወገኖች
ወንዱ ንብ ሴቷን ለማማለል ምግብ ይዞ ይቀርባል። ሴቷ ስጦታውን እየበላች ባለችበት ወቅት ግንኙነቱ ይፈጸማል። እጅ በጅ ነው። ወይም ወንዱ አሪፍ የሚቀሰም አበባ ያለበትን ያውቃል እንበል፤ በነፃ አድራሻውን አይሰጥም። መጀመሪያ "ፓ ዛሬ ያየሁት የአበባ እርሻ" ይላታል፤ ትንሽ ከአበባው የቆነጠረውን ዱቄት ያቀምሳታል። ከዚያ ጥያቄውን ያቀርባል ከተስማማች ጉዳዩን ፈፅሞ አበባው ያለበትን ይጠቁማታል። አንድ የተረገመ ወዳጀ ማር ለካ የጣፈጠው ወዶ አይደለም ብሎኛል ...ገነት አይገባም!

Alex Abreham-

ሰበርየቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም "ኢትዮሪካ"ን አስመልክቶ ማክሰኞ  ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ ታግዷል። ምንጮች እንዳረጋገጡት፣ ቴዲ ከተለያዩ ጋዜጠኞች...
13/04/2026

ሰበር

የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም "ኢትዮሪካ"ን አስመልክቶ ማክሰኞ ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ ታግዷል። ምንጮች እንዳረጋገጡት፣ ቴዲ ከተለያዩ ጋዜጠኞች ጋር የሚያደርገውን ይህንን መግለጫ በቀጥታ ለማስተላለፍ ከአርትስ ቲቪ (Arts TV) ጋር አስቀድሞ ስምምነት ተፈራርሞ ነበር።

ይሁን እንጂ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የቴሌቭዥን ጣቢያው ይህንን ፕሮግራም እንዳያስተላልፍ ጥብቅ እገዳ በመጣላቸው የቀጥታ ስርጭቱ እንዲቋረጥ ተገዷል። በብዙዎች ዘንድ በናፍቆት የሚጠበቀው የቴዲ አፍሮ "ኢትዮሪካ" አልበም፣ ገና በይፋ ሳይለቀቅ ከወዲሁ በመላው ሀገሪቱ ከፍተኛ ውጥረት እና መነጋገሪያ እየፈጠረ ይገኛል።

ዘገባው ዘሀበሻ ነው

ካሙዙ በቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም ላይ ተሳለቀ!😁ገበየሁ ቢሞት ሲተካ ባልቻየምትቀጥል ሀገሬ ብቻመድፉ ሲያጓራ ጥይት ሲያውካካወታደር ቆሞ ወድቆ ሲተካሀገር ሲዋቀር ፍኖት ሲለካባለብዕሩ ርዕይ ቢያ...
12/04/2026

ካሙዙ በቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም ላይ ተሳለቀ!😁

ገበየሁ ቢሞት ሲተካ ባልቻ
የምትቀጥል ሀገሬ ብቻ
መድፉ ሲያጓራ ጥይት ሲያውካካ
ወታደር ቆሞ ወድቆ ሲተካ
ሀገር ሲዋቀር ፍኖት ሲለካ
ባለብዕሩ ርዕይ ቢያስመካ
መመርመሪያውን ሀኪም ቢሰካ
ቁጥር አዋቂ ብቻ ለብቻ
እየተባለ አንተነህ ባልቻ
እየታመነ ሲይዝ ኮርቻ
ገበየሁ ቢሞት ሲተካ ባልቻ
የምትቀጥል ሀገሬ ብቻ
እየተባለ ሲኖር ባገሬ
ተናገር ሲባል በአፍ ከንፈሬ
ተቀመጥልኝ ከሊቅ ወንበሬ
አዕምሮ ገዢው ከአብራክ የወጣ
ክራሩን ይዞ ኪኔ ቢመጣ
ምነዋ ጡፍ ጣፊ እንዲህ ተንጣጣ
ከያኒ ላገር የለውም እጣ?
ፈርምልኝን የፎቶ ጣጣ
የዝናን ሽቶ ድሎት ቂናጣ
የምሽት ድልቂያ የአውሬውን እጣ
ሀገር የሸሸ ትውልድ የቀጣ
ተስፋ አጨልሞ ተስፋውን ያጣ
ሰዶማዊ ጭቃ ነፍሱን አስይዞ
በጭስ ደምብዞ
በአረቄ ፈዞ
ድምጥ አልማዝ አባቱ ተንጫሮ ለዞ
ከከተፋ አምባ ከሚኖር ናውዞ
የቀን ቀን ጭምብል ፈጤ በላጣ
ጦቢያዬ ማለት ሳንቲም ፈለጣ
ይኽስ ይቅርብኝ ብሎ ቢወጣ
አሽሽ እጢሶ ሰሪ ከመንቀፍ
በቀን ቀን ቅን መንገድ ኪኔ ቢሰለፍ
ምነው ጡፍ ጣፊ እንዲህ ተንጣጣ
ከማላቀስ በቀር ከማልቀስ እጣ
ላገር ቀን በቀን ለተስፋ አይምጣ?

አድርሱለት
ለዛ
በዜማ በቅርብ ቀን .....

“አሰብ ወደብ ላይ የሙዚቃ ስቱዲዮ እንከፍታለን” የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሳ
09/04/2026

“አሰብ ወደብ ላይ የሙዚቃ ስቱዲዮ እንከፍታለን”

የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሳ

ሰበር ኢራን ህዝብ ሀብቱንና ቅርሱን ከአሸባሪ መሪዎች ውድመት ለመጠበቅ እንደምታዩት አደባባይ ላይ መውጣቱ በስፋት እየተዘገበ ነው። የአዕምሮ ጤናውን በተመለከተ ብዙ ጉድለት አለበት ተብሎ በስ...
07/04/2026

ሰበር

ኢራን ህዝብ ሀብቱንና ቅርሱን ከአሸባሪ መሪዎች ውድመት ለመጠበቅ እንደምታዩት አደባባይ ላይ መውጣቱ በስፋት እየተዘገበ ነው።

የአዕምሮ ጤናውን በተመለከተ ብዙ ጉድለት አለበት ተብሎ በስፋት መረጃዎች የወጡበት ዶናለድ ትራምፕ ይህንን ውሳኔ ከወሰነ ዓለም ላይ ልዩ ክስተት ሊከተል ይችላል።

QUESTION: Why did Iran allow the US's helicopter fly within their airspace at a very low altitude? This is the answer.AN...
03/04/2026

QUESTION: Why did Iran allow the US's helicopter fly within their airspace at a very low altitude? This is the answer.

ANSWER: It was another well-calculated war strategy by Iran. The moment the US's F-15 fighter jet was downed by the I'RG'C men, Iran knew America will come to rescue their pilots.

An American UH-60 Black Hawk helicopter was deployed for the rescue operation. Iran waited till the helicopter had fully entered their airspace and flying at a very low altitude.

Immediately that was achieved, Iran s'truck it with another air defense system. The helicopter was badly hit by Iran's AD system. The Americans had to abandon the rescue mission and fled.

If you ask me, "what is really happening in this war", I will tell you that Iran, through their sagacious deployment of asymmetric w'ar tactics, is dealing a d'eath blow to the joint forces of the I'sraelis and the Americans. I won't say more than that. Ire o 👏

"ዲሞክራሲን እርሱት"እርሱ የመንግሥታትና የባለሃብት ማታለያ ገመድ ነው
03/04/2026

"ዲሞክራሲን እርሱት"

እርሱ የመንግሥታትና የባለሃብት ማታለያ ገመድ ነው

ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?😸 ዛሬ በውጩ ዓለም በማህበራዊ ድረገጽ ሲዘዋወር ያገኘነው ምስል ነው።
02/04/2026

ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?😸 ዛሬ በውጩ ዓለም በማህበራዊ ድረገጽ ሲዘዋወር ያገኘነው ምስል ነው።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Exclusive Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share