አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7

አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7 ሰላም ፣ ፍቅር ፣ ጤና ለአለማችን !

የአእምሮ ህመም እክል ያለባትን ግለሰብ  መፀዳጃ ቤት ውስጥ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ !🤔 #አሪፍመዝናኛ ◆ በቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የአእምሮ ሕመም እክል ...
22/05/2026

የአእምሮ ህመም እክል ያለባትን ግለሰብ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ !🤔

#አሪፍመዝናኛ ◆ በቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የአእምሮ ሕመም እክል ያለባትን ግለሰብ በመፀዳጃ ቤት አስገብቶ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታወቀ።የቦረና ፖሊስ ዋና መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዲባባ ዲዳ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት ተከሳሽ አብረሃም ጭርቆ ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ረፋድ አራት ሰዓት ላይ በያቤሎ ከተማ ውስጥ ድርጊቱን መፈጸሙ ተገልጿል።

ተከሳሹ የአዕምሮ ህመም እክል ያለባትን እና በተከሰተባት ሕመም ምንም አይነት የማገናዘብ እና የመረዳት ችሎታ የሌላትን በመፀዳጃ ቤት አስገብቶ እጅግ አስነዋሪ በሆነ መንገድ የመድፈር ጥቃቱን መፈፀሙን የተመለከቱ የአካባቢ ሰዋች ለፖሊስ በሰጡት መረጃ ከመፀዳጃ ቤቱ ሳይወጣ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።ፖሊስም ተከሳሹን በቁጥጥር ስር በማዋል የአእምሮ ህመም እክል ያለባትን ሴት በጥንቃቄ በማስመርመር የመደፈር ጥቃት እንደተፈፀመባት ከጤና ተቋም በአገኘው ማስረጃ፣ ማረጋገጡን ገልፀዋል። የምርመራ መዝገቡም በተለያዩ ማስረጃዎች በማጠናከር ለአቃቢ ህግ ተልኳል።

አቃቢ ህግም አእምሮአቸውን በሳቱ እና ድርጊቱን መቃወም በማይችሉ ላይ የሚፈፀም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ክስ የመሰረተ መሆኑን ገልፀዋል።ክሱን የተመለከተው የቦረና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት ተከሳሹ ለመልካም ጸባይ ተቃራኒ የሆነ ተግባር በመፈጸሙ 12 ዓመት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ዲባባ ዲዳ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።

አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7 📻✨

22/05/2026

አረጌ እዚህ ላይ ደሞ ይለያል !!🤔🎼

አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7 📻✨

😮 "የስደት ህይወት እንደታሰበው አልጋ በአልጋ አልሆነም!" — በ GH₵210,000 ( ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጎ ) ወደ UK የተሰደደው ጋናዊ ወደ ሀገሩ ለመመለስ እየጠየቀ ነው! ...
22/05/2026

😮 "የስደት ህይወት እንደታሰበው አልጋ በአልጋ አልሆነም!" —

በ GH₵210,000 ( ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጎ ) ወደ UK የተሰደደው ጋናዊ ወደ ሀገሩ ለመመለስ እየጠየቀ ነው! 🇬🇭✈️🇬🇧

#አሪፍመዝናኛ ◆ ​በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ትልቅ መነጋገሪያ በሆነው አዲስ መረጃ መሰረት፣ አብዱል የተባለ ጋናዊ ወጣት የተሻለ ህይወት ፍለጋ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥቶ ወደ እንግሊዝ (UK) ቢያቀናም፣ አሁን ግን ህይወት ፈታኝ ሆናብኛለች ሲል በምሬት ተናግሯል ።

​📌 ስለ ሁኔታው ዋና ዋና ነጥቦች፦
​ያወጣው ወጪ፦ ወደ UK ለመጓዝ GH₵210,000 (ከፍተኛ የገንዘብ መጠን) አውጥቷል።

​የቀድሞ ስራው፦ በጋና አክራ (Greater Accra Region) ውስጥ በብስክሌት ጥገና ስራ (Bicycle Repairer) ይተዳደር ነበር።

​የገጠመው ችግር፦ እንግሊዝ ከገባ ሁለት ዓመታት ቢያልፉትም፣ ራሱንም ሆነ በሀገር ቤት ያለውን ቤተሰቡን ማስተዳደር የሚያስችለው ምንም አይነት ትርጉም ያለውና ቋሚ ስራ ሊያገኝ አልቻለም።

​ምኞቱ፦ መጀመሪያ ላይ የመሰደድ ከፍተኛ ፍላጎት የነበረው ቢሆንም፣ ምርጫው ግን ስፔን ወይም ጃፓን መሄድ ነበር።
​"የስደት ህይወት ፈታኝ ሆኖብኛል፤ እራሴንና ቤተሰቤን መርዳት አልቻልኩም፤ አሁን ወደ ሀገሬ ጋና መመለስ እፈልጋለሁ!" — አብዱል (ከSVTV Africa ጋር ባደረገው ቃለ-ምልልስ)
​ይህ ጉዳይ በሶሻል ሚዲያ ላይ ሰፊ አስተያየቶችን እና ክርክሮችን እያስነሳ ይገኛል።

ብዙዎች የስደት ህይወት ከሩቅ እንደሚታየው ቀላል እንዳልሆነ ማሳያ ነው ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ የተሻለ አማራጭ መፈለግ አለበት እያሉ ነው።

​🤔 እናንተስ ምን ትላላችሁ? ይህንን ያህል ከፍተኛ ገንዘብ አውጥቶ ስደት ከመሄድ፣ በሀገር ውስጥ በዚያ ገንዘብ ትልቅ ስራ መፍጠር ይሻል ነበር? ወይስ የደረሰበት ችግር ጊዜያዊ ነውና መታገስ አለበት?

​ሀሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇👇

​ #ስደት

አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7 📻✨

22/05/2026

የኔ ቆንጆ ባለጌ ?🙄😂

አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7 📻✨
#አሪፍመዝናኛ

https://www.youtube.com/live/pmVWxUmz4t0?si=hOmzl4drxd2qVsgt
22/05/2026

https://www.youtube.com/live/pmVWxUmz4t0?si=hOmzl4drxd2qVsgt

ኤፍሬም አበበ — — ከፍ ከፍ ከፍ ፣ ቤተሰብ ፣ ቤተሰብ ፕላስና ሌሎችም በርካታ የራሱ መለያዎች ያሉት ወጣትና ዝነኛ የሬዲዮ እና የመዝናኛው ዘርፍ ባለሙያ ሲሆን በጣም ተወዳጅና አዝናኝ ዝ.....

እንደዚህ ይቻላል 🤔 እንዴ ?!ወይኔ ቡናችን 🙆‍♂️አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7 📻✨
22/05/2026

እንደዚህ ይቻላል 🤔 እንዴ ?!
ወይኔ ቡናችን 🙆‍♂️

አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7 📻✨

የሰው ልጅ ኩላሊት በቀን እስከ 200 ሊትር ደም ያጣራል። አሁን ደግሞ ሳይንቲስቶች በቤተ ሙከራ ውስጥ በትክክል ተመሳሳይ ስራ የሚሰራ ኩላሊት ማሳደግ ችለዋል ።🤔 #አሪፍመዝናኛ ◆ በኤደንብራ...
21/05/2026

የሰው ልጅ ኩላሊት በቀን እስከ 200 ሊትር ደም ያጣራል። አሁን ደግሞ ሳይንቲስቶች በቤተ ሙከራ ውስጥ በትክክል ተመሳሳይ ስራ የሚሰራ ኩላሊት ማሳደግ ችለዋል ።🤔

#አሪፍመዝናኛ ◆ በኤደንብራ ዩኒቨርስቲ (University of Edinburgh) ተመራማሪዎች የስቴም ሴሎችን (stem cells) በመጠቀም ደም ማጣራትና ሽንት ማስወገድ የሚችሉ የኩላሊት ክፍሎችን (organoids) ፈጥረዋል ።

ይህ በኮምፒውተር የተሰራ ሞዴል ሳይሆን፣ ልክ እንደ እውነተኛ ኩላሊት ተግባርማከናወን የሚችል ሕያው ቲሹ ነው ።

የግኝቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

1. ተግባራዊ ስራ፦ እነዚህ በቤተ ሙከራ የበቀሉ የኩላሊት ክፍሎች ልክእንደ ተፈጥሮአዊው ኩላሊት ደምን የማጣራትና ሽንት የማመንጨት አቅም አሳይተዋል።

2. ተስፋ ለሚሊዮኖች፦ በዓለም ዙሪያ ከ8ዐዐ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በከባድ የኩላሊት በሽታ ይሰቃያሉ ። አብዛኛዎቹ ደግሞ የኩላሊት ንቅለ ተከላ (transplant) የማግኘት ዕድል የላቸውም፡፡

የወደፊት ግብ፦ ይህ ግኝት ወደፊት የአካል ክፍሎችን የመጠበቅን ስቃይሙሉ በሙሉ ሊያስቀርና የተጎዱ የሰውነት ክፍሎችን የመጠገን ስልትን ሊቀይር ይችላል ።

ይህ አስደናቂ ግኝት ለኩላሊት ታካሚዎች አዲስ የሕይወት ተስፋን የሰነቀ ነው ፡፡





አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7 📻✨

21/05/2026

#ዲያስፖራው !🤔 ትላክለት እንዴ 😂

አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7 📻✨

 #አርሰናል ከበርካታ አመታት ተደጋጋሚ ሙከራ እና ጥረት በኋላ፦ #አሪፍመዝናኛ ◆  በዘንድሮው አመት የውድድር ዘመን  የፕሪምየር ሊጉ የዋንጫ ባለቤት ለመሆን የቻለበት ምስጢር በርካቶች ሲሉ ...
19/05/2026

#አርሰናል ከበርካታ አመታት ተደጋጋሚ ሙከራ እና ጥረት በኋላ፦

#አሪፍመዝናኛ ◆ በዘንድሮው አመት የውድድር ዘመን የፕሪምየር ሊጉ የዋንጫ ባለቤት ለመሆን የቻለበት ምስጢር በርካቶች ሲሉ እንደሚደመጠው በእድል ምክንያት ? ወይስ በፍፁም የጨዋታ ብቃት ?🤔

👉 በእርስዎ እይታ በየትኛው ነው ብለው ያምናሉ ???🙄
👉 ሀሳብዎን በኮሜንት ያጋሩን !!🙏

አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7 🏆✨
#አርሴናል

Address

Addis Ababa
46350

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አሪፍ መዝናኛ j fm 106.7:

Share