The Dove

The Dove ማንኛዉንም ማስታወቂያ በነጻ ለአድማጭ እናደርሳለን፡፡

ሴዶ ማርሻል እስከ 1 ዓመት እስራት ሊቀጣ ይችላል» — ጠበቃ ሰብለ አሰፋ::በETFC 2 Cage ውድድር ውዝግብ ዙሪያ ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ሕጋዊ ማብራሪያ ሰጡአዲስ አበባ — በETFC 2 Cag...
25/08/2026

ሴዶ ማርሻል እስከ 1 ዓመት እስራት ሊቀጣ ይችላል» — ጠበቃ ሰብለ አሰፋ::

በETFC 2 Cage ውድድር ውዝግብ ዙሪያ ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ሕጋዊ ማብራሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ — በETFC 2 Cage ውድድር ዝግጅት ወቅት ተወዳዳሪው ሴዶ ማርሻል "በተቃዋሚዬ ጆኒ ድግምትና መተት ተሰርቶብኛል" በሚል ምክንያት ከውድድሩ ራሱን ማግለሉን አስመልክቶ ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ሕጋዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠበቃ ሰብለ አሰፋ በቪዲዮ በሰጡት መግለጫ፣ ሴዶ ያቀረበው "በእንቁላል መተት ተሰርቶብኛል" የሚለው አቤቱታ በህግ ፊት ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ካልቀረበበት በስተቀር በጆኒ ላይ የተፈጸመ የሐሰት ስም ማጥፋት ወንጀል እንደሆነ ገልጸዋል።

እንደ ጠበቃ ሰብለ ገለጻ፣ በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 613 መሠረት፣ አንድ ሰው ያለበቂ ማስረጃ በሌላው ሰው ላይ የሐሰት ክስና ውንጀላ በማቅረብ መልካም ስሙንና ክብሩን ካደፈረሰ ወይም በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን አመኔታ እንዲያጣ ካደረገ፣ በተጎጂው አቤቱታ አቅራቢነት እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ሊቀጣ ይችላል።

በተጨማሪም ውድድሩ መሰረዙ ከተረጋገጠ ወይም የተወደዱ ተወዳዳሪዎች ባለመሰለፋቸው ምክንያት ቅሬታ ያላቸው የትኬት ገዢዎችና ተመልካቾች የውድድሩን አዘጋጆች ካሳ የመጠየቅ ሙሉ ሕጋዊ መብት እንዳላቸው ጠበቃ ሰብለ አብራርተዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የውድድሩ አዘጋጆች (ETFC) ሴዶ ማርሻል በገባው ውል መሠረት ባለመወዳደሩ ምክንያት ለደረሰባቸው የወጪና የገቢ ኪሳራ እንዲሁም ለተመልካቾች ለሚከፍሉት ካሳ በፍትሐብሔር ሕግ መሠረት ከሴዶ ላይ የጉዳት ካሳ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ገልጸዋል።

📷ጠበቃ ሰብለ አሰፋ

5ኛ ወጥቶ 1ኛ የሆነው ያሲኖ !★ ያሲኖ የማለዳ ኮከቦች የትወና ውድድር የሆነ     ዙር ላይ ከውድድሩ ያሰናብቱታል።★ በችሎታው የሚተማመነው ተመልካቾች      ያሲኖ ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ ይ...
24/08/2026

5ኛ ወጥቶ 1ኛ የሆነው ያሲኖ !

★ ያሲኖ የማለዳ ኮከቦች የትወና ውድድር የሆነ
ዙር ላይ ከውድድሩ ያሰናብቱታል።

★ በችሎታው የሚተማመነው ተመልካቾች
ያሲኖ ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ ይገባዋል
ብለን ጠየቅን።

★ የማለዳ ኮከብ የትወና ውድድር አዘጋጆች
ተመካከሩና አንድ ዕድል ሰጥተው
ወደ ውድድሩ መለሱት።

★ ከበርካታ ሺህ ተወዳዳሪዎችም እስከመጨረሻው
ታግሎ ደረጃ ወስጥ በመግባት 5ኛ ደረጃን
በመያዝ አጠናቀቀ።

★ ዛሬ ያሲኖ የሕብረተሰቡን ችግር እየነቀሰ በማውጣት
ትዝታዎቻችንን እየመዘዘ በድንቅ ትወናው
ማዝናናትና ማስተማሩን ተያይዞታል።

★ የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራምን ለመምራት ሞክሮ
አሳክቶታል።

★ ያሲኖ በማለዳ ኮከቦች የትወና ውድድር
5ኛ ደረጃን ይዞ ቢያጠናቅቅም ስራዎቹ
ግን ሁልጊዜም 1ኛ ናቸው።

★ በኪነጥበብ ስራዎቹ እያስደመመን ጉዞውን
ቀጥሏል።

★ ያሲኖ ብቻውን ተቋም ነው።

★ 5ኛ ወጥቶ በኪነጥበባዊ ስራዎቹ 1ኛ የሆነ
አድናቆት የሚገባው የሚችል አርቲስት ነው።

ያሲኖ ትችላለህ ! በርታ ! ወደፊት !

አክባሪህና አድናቂህ
ዘሪሁን ተዝናኑ
ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!

በETFC 2 Cage ውስጥ የተፈጠረው «የእንቁላል እና የመተት» አወዛጋቢ ውዝግብአዲስ አበባ — በነሐሴ 21 ቀን ሊካሄድ አራት ቀናት ብቻ በሚቀሩበት በአሁኑ ወቅት፣ ታዋቂው የኢትዮጵያ ሚክስ...
23/08/2026

በETFC 2 Cage ውስጥ የተፈጠረው «የእንቁላል እና የመተት» አወዛጋቢ ውዝግብ

አዲስ አበባ — በነሐሴ 21 ቀን ሊካሄድ አራት ቀናት ብቻ በሚቀሩበት በአሁኑ ወቅት፣ ታዋቂው የኢትዮጵያ ሚክስድ ማርሻል አርትስ (MMA) ተወዳዳሪ ሴዶ ማርሻል ከሚጠበቀው የETFC 2 ግጥሚያ ራሱን ማግለሉን በይፋ አስታወቀ።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰራጨው የቪዲዮ መግለጫ፣ ሴዶ የለበሰውን የETFC ስፖንሰርሺፕ ማሊያ አውልቆ በመጣል ከባላጋራው ጋር Cage (ኬጅ) ውስጥ እንደማይገባ ገልጿል።

ሴዶ ለውሳኔው እንደ ምክንያት ያቀረበው ተቃዋሚው «በእንቁላል አማካኝነት ድግምት እና መተት» ፈጽሞብኛል የሚል ሲሆን፣

"ውድድሩ የቀረው 4 ቀን ነው የቀረው፤ ነገር ግን እኔ አልወዳደርም። እንቁላሉን አስጠይቄበታለሁ—ድግምት እና መተት ተሰርቶበታል። ከዚህ በኋላ ከዚህ ሰው ጋር አልጫወትም። ትኬት የገዛችሁ ወይም ስፖንሰር ያደረጋችሁ ከፈለጋችሁ ሌላ ተደባዳቢ ከውጭ አምጡልኝ፤ ከእሱ ጋር ግን በፍጹም አልገባም!"

የውድድሩ አዘጋጆች በጉዳዩ ላይ ያሉት ነገር ባይኖርም፣
የስፖርቱ አፍቃሪዎች ግን አቋሙን አልተቀበሉትም።

ብዙዎች "ሴዶ እምቢ ቢልም፣ ተጎትቶ Cage ውስጥ መግባት አለበት"

እንዲሁም "እንቁላሉን በልተህም ቢሆን Cage ውስጥ ትገባለህ!"በማለት አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ"

እንርዳት
23/08/2026

እንርዳት

🏆🇪🇹 ኢትዮጵያዊው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ አቤል ብርሀኑ ተሸለመ‼️ትላንት በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደው PALCA 2026 መድረክ ላይ አቤል ብርሀኑ የዓመቱ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ (Tra...
23/08/2026

🏆🇪🇹 ኢትዮጵያዊው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ አቤል ብርሀኑ ተሸለመ‼️

ትላንት በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደው PALCA 2026 መድረክ ላይ አቤል ብርሀኑ የዓመቱ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ (Travel Influencer of the Year) በመባል ተሸልሟል። 🌍🏆

አቤል በYouTube የተለያዩ ሀገራትን ለተከታዮቹ በማስጎብኘት የሚያጋራው የጉዞ ይዘት ለዚህ ስኬት እንዳበቃው ገልጿል። ለስኬቱም እግዚአብሔርን፣ ቤተሰቦቹን፣ የስራ አጋሮቹንና ተከታዮቹን አመስግኗል። 🙏

እንኳን ደስ አለህ‼️ 🇪🇹🏆

22/08/2026

ከፍተኛ ውጤት!
በተፈጥሮ ሳይንስ በወንድ 591.6 ከ600 ተመዝግቧል። ተማሪው የኦዳ ስፔሻል ቦርዲንግ - አዳማ ተማሪ ነው። ከሴት ደግሞ 583 ከ600 ሲሆን ከእንጅባራ አገው ምድር ትምህርት ቤት ነው።

የስራ ማስታወቂያ
22/08/2026

የስራ ማስታወቂያ

ዲግሪዋን ጥላ ወደ ገጠር የተመለሰችው "የንብ እመቤት" — አስደናቂ የስኬት ታሪክ! 🐝✨ብዙዎቻችን ዲግሪ ስናገኝ የምናስበው ከተማ ላይ ቢሮ ተቀጥሮ መሥራትን ነው። ይህች ወጣት ግን የተለየ መ...
22/08/2026

ዲግሪዋን ጥላ ወደ ገጠር የተመለሰችው "የንብ እመቤት" — አስደናቂ የስኬት ታሪክ! 🐝✨

ብዙዎቻችን ዲግሪ ስናገኝ የምናስበው ከተማ ላይ ቢሮ ተቀጥሮ መሥራትን ነው። ይህች ወጣት ግን የተለየ መንገድ መረጠች። ስሟ ሩታ ይባላል። በአካውንቲንግ የተመረቀች ቢሆንም፣ ከተማ ላይ ለአመታት በዝቅተኛ ደሞዝ ከመሰቃየት፣ ወደ ትውልድ መንደሯ ተመልሳ የራሷን የፈጠራ ሥራ ለመጀመር ወሰነች።

የጀመረችው ግን በትንሽ ካፒታልና በ2 የባህላዊ ንብ ቀፎዎች ብቻ ነበር።

ምስጢሯ ምን ነበር?

ሩታ ባህላዊውን አሠራር ወደ ዘመናዊ የንብ ማርባት ዘዴ (Modern Beekeeping) ቀየረችው። ስለ ንቦች አያያዝ፣ ስለ ንግሥት ንብ ማርባትና ንጽሕናው ስለጠበቀ የማር አወጣጥ ሥልጠናዎችን ወሰደች።

የመጀመሪያው ዓመት፦ ካገኘችው ጥቂት ማር ሽያጭ ሙሉ በሙሉ ወደ ዘመናዊ ቀፎዎች ተሸጋገረች።

ሁለተኛው ዓመት፦ ጥራቱን የጠበቀ ነጭ ማር (White Honey) ማምረት በመጀመሯ፣ በቀጥታ ለከተማ ትላልቅ ሆቴሎችና ላኪዎች ማቅረብ ጀመረች።

ዛሬ ላይ፦ ከ150 በላይ ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች አሏት። በዓመት በሚሊዮን የሚቆጠር ገቢ የምታገኝ ስኬታማ ነጋዴ ሆናለች! ለአካባቢው ወጣቶችም የሥራ ዕድል ፈጥራለች።

💡 መልእክቱ፦ ስኬት ያለው ከተማ ላይ ወይም ቢሮ መቀመጥ ውስጥ አይደለም። ስኬት ያለው መሬታችንን ተጠቅመን እሴት መፍጠር ውስጥ ነው ።

"ሚሊዮኖቼ ቤተሰቤን ሊመልሱልኝ አልቻሉም!”   | የቀድሞው የኤን.ቢ.ኤ ዝነኛ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ሻኪል ኦኒል በስፖርቱ ዓለም ሊገኝ የሚችለውን ሁሉ ታላቅ ስኬት ዝና እና ከፍተኛ ሀብት ማ...
22/08/2026

"ሚሊዮኖቼ ቤተሰቤን ሊመልሱልኝ አልቻሉም!”

| የቀድሞው የኤን.ቢ.ኤ ዝነኛ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ሻኪል ኦኒል በስፖርቱ ዓለም ሊገኝ የሚችለውን ሁሉ ታላቅ ስኬት ዝና እና ከፍተኛ ሀብት ማግኘት የቻለ ሰው ነው።

አራት ጊዜ የኤን.ቢ.ኤ ሻምፒዮን ሲሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ማከማቸቱ የቅንጦት መኪኖች እና የ30 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ግዙፍ መኖሪያ ቤት ባለቤት መሆኑ የስኬቱ ማረጋገጫዎች ነበሩ።

ነገር ግን ከነዚህ ሁሉ ቁሳዊ ሀብቶች በስተጀርባ ሻኪል በራሱ ስህተቶች ምክንያት የተበተነውን የቤተሰብ ህይወቱን በፀፀት ያነሳል።

በጋብቻው ወቅት ለፈጸማቸው ስህተቶች እና ታማኝ ባለመሆኑ ምክንያት ትዳሩ በመፍረሱ ሙሉ ሀላፊነቱን እንደሚወስድ በግልጽ ተናግሯል።

ትዳሩ ካበቃ በኋላ ያ ግዙፍ መኖሪያ ቤቱ አዲስ መልክ ያዘ።

ሻኪል ይህንን አስመልካቶ ሲናገር፡

"በ30,000 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው ቤት ውስጥ ብቻዬን ነው የምኖረው።

በወቅቱ ስህተት መስራቴ አልገባኝም ነበር ብሏል።

ይህ የሻኪል ገጠመኝ በዓለም ላይ ያሉ ማናቸውም ቁሳዊ ነገሮች ዝና እና ሀብት የቤተሰብ ፍቅር እና ሰላም ሊተኩ እንደማይችሉ ትልቅ ትምህርት የሰጠ ሆኗል።

ገንዘብ ምቾትን እንጂ እውነተኛ ደስታን እና የቅርብ ሰዎችን ፍቅር መግዛት አይችልም።

ስኬት ማለት በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር የምናሳልፈው ሰላም እና ፍቅር የሰፈነበት ህይወት መሆኑን የሻኪል ታሪክ ህያው ምስክር ነው።

በህይወት የምንወስዳቸው የተሳሳቱ ውሳኔዎች እስከመጨረሻው የሚከተል የፀፀት ጠጠሮችን ሊጥሉብን ይችላሉ ሲል ልምዱን አጋርቷል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Dove



በሐዋሳ ከተማ የቤት ኪራይ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ነዋሪዎች ለከፋ የኑሮ ጫና መዳረጋቸው ተገለጸ።በሐዋሳ ከተማ በኮሪደር ልማት ምክንያት የቤት ኪራይ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ነዋሪ...
22/08/2026

በሐዋሳ ከተማ የቤት ኪራይ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ነዋሪዎች ለከፋ የኑሮ ጫና መዳረጋቸው ተገለጸ።

በሐዋሳ ከተማ በኮሪደር ልማት ምክንያት የቤት ኪራይ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ነዋሪዎች ለከፋ የኑሮ ጫና መዳረጋቸው ተገለጸ። በርካታ አከራዮች ዋጋውን በእጥፍና ከዚያ በላይ የሰቀሉት የመኖሪያ ቤት እጥረቱን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ሲሆን፣ በተለይም በወርሃዊ ደመወዝ የሚተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለከፍተኛ ችግር ዳርጓቸዋል። የከተማው አስተዳደር ከመንግሥት ቤት ለተነሱ ነዋሪዎች በቂ ምትክ ሳይዘጋጅ ሰዎችን ማስወጣቱ እና ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ምትክ ቤቶችን ሰርቶ አለማስረከቡ ለእንግልቱ ዋና ምክንያት እንደሆነ ተመልክቷል።

በተጨማሪም ለተፈናቃዮች የሚሰጠው የኪራይ ድጎማ ከ4,000 እስከ 7,000 ብር ብቻ በመሆኑ የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ያላገናዘበ መሆኑ ተገልጿል። በመሆኑም ነዋሪዎቹ ችግሩን ለመቅረፍ የመንግሥት አካላት በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገቡና እንደ አዲስ አበባ ሁሉ አከራይና ተከራይን በሕጋዊ ውል የሚያስተዳድር መመሪያ እንዲዘረጋ ጠይቀዋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Dove posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share