Oriental Orthodox Tewahido Church

Oriental Orthodox Tewahido Church Be Ewunetu lieul egziabher yimesgen
hulum n***r le bego new...
hulem melkaminetin enisira...

‹‹በዓለ ደብረ ታቦር›› ጌታችን በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ የሚከበር በዓል ነው።የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዓ...
18/08/2026

‹‹በዓለ ደብረ ታቦር›› ጌታችን በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ የሚከበር በዓል ነው።

የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዓበይት በዓላት አንዱ የደብረ ታቦር በዓል ነው። በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን የሚከበረው ይህ በዓል መሠረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ደቀ መዛሙርት (ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስን) ይዞ ወደ ደብረ ታቦር ተራራ በመውጣት ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቶ ልብሱ እንደ ብርሃን ነጭ ሆኖ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ነው (ማቴ. 17÷1-8)። በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር አብ “የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ አሰምቷል።

ከቤተ ክርስቲያን ውጭም ይህ ዕለት “ቡሄ” ተብሎ በልዩ ትውፊት ይከበራል። ሕፃናት ጅራፋቸውን ይዘው እያጮሁና እየዘመሩ በየቤቱ ይዞራሉ፤ ችቦ ይበራል፣ ሙልሙል ዳቦም ይታደላል።

ትርጉሙ፡ "ቡሄ" ማለት ብራ፣ ብርሃን ወይም የተገለጠ ማለት ነው። የክረምቱ ጨለማና ጭጋግ አልፎ ወደ ብሩህ መፀው የምንሸጋገርበት ወቅት መሆኑን ያመለክታል።

ሙልሙል ዳቦና ችቦ፡ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን ሲገልጥ ምሽት በመሆኑ እረኞች ሳይመለሱ ቀርተው፣ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ የመውጣታቸውን ትውፊት ለማስታወስ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ ይሰጣል፤ ችቦም ይበራል።

የጅራፍ ድምፅ፡ ልጆች ጅራፍ ሲያጮሁ የሚያደሉበት ምክንያት አብ “የምወደው ልጄ ይህ ነው” ሲል ሐዋርያት ደንግጠው የወደቁበትን የመለኮት ድምፅ ለማስታወስ ነው።
ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን❤🙏


Oriental Orthodox Tewahido Church

12/07/2026

እግዚአብሔር አምላክ__ በ3 ነገሮች ይፈትንካል.

Oriental Orthodox Tewahido Church

ላም አለኝ በሰማይ___?👍Oriental Orthodox Tewahido Church
11/07/2026

ላም አለኝ በሰማይ___?👍

Oriental Orthodox Tewahido Church

ፀጥታ ያለበት ብቸኛ ቦታ 🙏🙏🙏Oriental Orthodox Tewahido Church
10/07/2026

ፀጥታ ያለበት ብቸኛ ቦታ 🙏🙏🙏

Oriental Orthodox Tewahido Church

❤️❤️❤️❤️Oriental Orthodox Tewahido Church
09/07/2026

❤️❤️❤️❤️

Oriental Orthodox Tewahido Church

Today's my best photo Share ,and follow Oriental Orthodox Tewahido Church
04/07/2026

Today's my best photo
Share ,and follow

Oriental Orthodox Tewahido Church

+++ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) +++❖ ይህ ጾም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ አጽዋማት ውስጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ጾም ነው።❖ የሰኔ ጾም ይህ ጾ...
31/05/2026

+++ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) +++

❖ ይህ ጾም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ አጽዋማት ውስጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ጾም ነው።

❖ የሰኔ ጾም ይህ ጾም የሐዋርያት ጾም በመባል ይታወቃል ስለ ምን የሐዋርያት ጾም ተባለ ቢሉ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ የጾሙት ጾም ስለሆነ ነው።

የሰኔ ጾም የሚጾምበት ጊዜያት

❖ የሰኔ ጾም ቢያንስ 15 ቢበዛ 45 ቀናት ያህል ይጾማል
❖ የሰኔ ጾምን እስከ 9 ሰአት እንድንጾም ቤተክርስቲያን አውጃለች ።
❖ ጾሙ የሚገባበት ቀን በየዓመቱ የተለያየ ቢሆንም የጾሙ ማብቂያ ዕለት ግን ሐምሌ 5 ድረስ ነው ።

❖ ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህራቸውን አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው ማለትም ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን
በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የስራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡

❖ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያ ጾምን አድርገዋል፡፡

❖ ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ ጌታችን አስቀድሞ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡

‹‹ እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው? አሉት

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው
ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ››
ማቴ 9፥15-16

❖ እኛም ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ‹‹መሣሪያ›› አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ ነው፤ አንድ አንዶች እንደሚሉት የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምዕመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡

ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን በሰላም ያስፈፅመን አሜን በእውነት

"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያመልጣል"ምሳ1:33

ርእሰ አድባራት ዱ/ሻ/አ ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ ቤዛ ብዙኋን ሰ/ት/ቤት

✨በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑን✨
https://sites.google.com/view/sealitemhret/home

Çcccc, EOTC

Oriental Orthodox Tewahido Church

😭 የጣና ሐይቅ እምባ... ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ልብ ሰባሪ መርዶ!ከባሕር ዳር የተሰማው ዜና እጅግ ያሳምማል። የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ዓመታዊ የዋዜማ በዓል ለማክበር፣ በደስታ...
22/05/2026

😭 የጣና ሐይቅ እምባ... ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ልብ ሰባሪ መርዶ!

ከባሕር ዳር የተሰማው ዜና እጅግ ያሳምማል። የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ዓመታዊ የዋዜማ በዓል ለማክበር፣ በደስታና በዝማሬ ወደ ገዳሙ ይጓዙ የነበሩ በርካታ ምዕመናን በጣና ሐይቅ ላይ በደረሰ ድንገተኛ የጀልባ መስመጥ አደጋ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ነጭ ነጠላቸውን ለብሰው፣ ለበረከት የተነሱ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሳይደርሱ በሐይቁ ማዕበል ተቀጥፈዋል። እስካሁን ባለው መረጃ በአደጋው የብዙዎች ሕይወት ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን፣ የሟቾች ቁጥር በውል አልታወቀም።

ይህ ድንገተኛ አደጋ መላዋን ቤተክርስቲያን እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማንያንን በከባድ ኀዘን ውስጥ ጥሏል።

ጽናቱን ይስጠን! 🙏
ፈጣሪ በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡትን ነፍሳቸውን በቅዱሳኑ፣ በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍ ያሳርፍልን። ለተጎዱ ቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እግዚአብሔር አምላክ መጽናናትንና ብርታትን ይስጥልን!


Oriental Orthodox Tewahido Church

‹‹ገብርኄር›› ማለት “መልካም አገልጋይ ፣ ቸር አገልጋይ፣ ታማኝ አገልጋይ” ማለት ነው።ስድስተኛው ሳምንት ገብርኄር ተብሎ ይጠራል።በቅድስት ቤተክርስቲያን ቋንቋ ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው። ...
22/03/2026

‹‹ገብርኄር›› ማለት “መልካም አገልጋይ ፣ ቸር አገልጋይ፣ ታማኝ አገልጋይ” ማለት ነው።

ስድስተኛው ሳምንት ገብርኄር ተብሎ ይጠራል።

በቅድስት ቤተክርስቲያን ቋንቋ ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው። ገብርኄር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ታማኝነታቸውን ለማየት የተለያዩ መክሊት ተሰቷቸው ወተው ወርደው አትርፈው እንዲያመጡ ስለተላኩ ታማኝ ባሪያ ገብርሄር የተናገረው ነገር በዚህ ሰንበት ይወሳል።

በንፁሕ የጾመ ወንድሙን በአንደበቱ ያልሸነገለ ደም ያላፈሰሰ ታማኝ አገልጋይ ወደ ጌታው ደስታ ይገባል። አዲሲቷን ምድር ይወርሳል እያለች በስድስተኛው ሳምንት ቅድስት ቤተክርስቲያን ትዘምራለች።
🙏🙏🙏

Çccccc HENOK abebe

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Oriental Orthodox Tewahido Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Oriental Orthodox Tewahido Church:

Shortcuts

Share