ECNTV

ECNTV አዳዲስ ሰበር ዜናዎችና መረጃዎችን፣ የመዝናኛ፣ የኪነጥበብ፣ የስፖርት እና ሌሎች አዝናኝ ፕሮግራሞች ይቀርቡበታል። የyoutube ቻናላችንን subscribe ያድርጉ http://www.youtube.com/

12/02/2026

አቶ አማን ፍስሐፅዮን የEBS TV መስራች ከዚህ ዓልም በሞት ተለዩ፣ ነፍስ ይማርልን።

የኢትዮጵያ ሚዲያ ታላቅ ባለውለታ ተለዩን! 🕊️የኢቢኤስ (EBS TV) መስራችና የብዙዎች መነሳሳት የሆኑት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል። አቶ አማን ኢትዮጵያ ...
11/02/2026

የኢትዮጵያ ሚዲያ ታላቅ ባለውለታ ተለዩን! 🕊️

የኢቢኤስ (EBS TV) መስራችና የብዙዎች መነሳሳት የሆኑት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል። አቶ አማን ኢትዮጵያ ውስጥ የግል የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት ፈር ቀዳጅ ከመሆናቸውም በላይ፣ ለሀገራችን የሚዲያ እድገትና ለባለሙያዎች መፍለቂያ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የኢንዱስትሪው ምሰሶ ነበሩ።

ባበረከቱት የማይተካ ስራ ሁልጊዜም በክብር ሲታወሱ ይኖራሉ። ለቤተሰቦቻቸውና ለሚዲያ ቤተሰቡ መጽናናትን እንመኛለን።
ECN - TV ©

ℹ️ ለበለጠ መረጃ
▤▤▤▤▤▤▤▤
Youtube ገፃችንን subscribe ያድርጉ
👉 https://www.youtube.com/
Facebook ገፃችንን follow ያድርጉ
👉https://www.facebook.com/ecntv

‎   ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት የንቅናቄ ፎረም  በምንጃር ሸንኮራ ወረዳና በአረርቲ ከተማ በድምቀት ተካሄደ።‎‎ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ዞናዊ የንቅናቄ ፎረም  በምንጃር ሸንኮ...
11/02/2026

‎ ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት የንቅናቄ ፎረም በምንጃር ሸንኮራ ወረዳና በአረርቲ ከተማ በድምቀት ተካሄደ።

‎ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ዞናዊ የንቅናቄ ፎረም በምንጃር ሸንኮራ ወረዳና በአረርቲ ከተማ አሰተዳደር በአማረና በደመቀ ዝግጅት በበሱፍቃድ ሪልስቴት ፕሮጀክት ሳይት ግቢ እሁድ የካቲት 1/2018 ዓ.ም. ተካሔደ ።

‎ በአረርቲ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ አቶ ተሻለ ጥላሁን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት በማስተላለፍ አንገብጋቢ የህዝብ ጥያቄና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ማለትም የመንገድ፣የውሀ ፣የመብራትና ሌሎችንም አንስተዋል ።

‎ "ድንቅ የስራ ባህል ወዳለባት ምንጃር ሸንኮራ ወረዳና አረርቲ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብ በሰላም መጣችሁ በማለት በጥቅሉ ሰሜን ሸዋ ለኢንቨስትመንት የተመቸ ሰላም ወዳድና ታታሪ ማህበረሰብ ያለበት ዞን ሲሆን ለኢንቨስትመንት በቂ ግብአት ያለው በመሆኑ ከ23 በላይ ማእድናት መኖሩን በጥናት የተረጋገጠ ሲሆን ለአልሚዎች ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥረም የተናገሩት የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ናቸዉ፤ዋና አስተዳዳሪዉ አክለዉም"ልብለልብ ተገናኝተን ሸዋን እናልማ "ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

‎ምንጃር ለኢንቨስትመንት ጥያቄ ፈጥኖ ምላሽ የሚሰጥና ባለፍት አመታት እንደዞን ከ250 በላይ አልሚዎችም ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረላቸውም ጠቅሰዋል ።ምንጃር ለአዲስ አበባ ቅርብ መሆኑ ባለሀብቶች እንክብካቤ ስለሚፈልጉ ልማታቸው ተጠብቆ ምርታማ እንዲሆኑ ሰላም ወዳድ የሆነው ማህበረሰብ ሰላምንና ደህንነትን መጠበቅ እንደሚኖርበትም ገልጸዋል ።
‎ በሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ በአቶ ደምሰ ዞናዊ የመወያያ ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት በማድረግ ከማህበረሰቡ የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የፌደራል የክልልና የዞን አካላት በተገኙበት ምላሽ በመስጠት መግባባት ላይ በመድረስ የእለቱን የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ዞናዊ የንቅናቄ ፎረም በልዩ ልዩ ሁነቶች ታጅቦ ማጠናቀቅ ተችሏል ።

በኢንቨስመንት ፎረሙም የተለያዩ የፌዴራል ፣የክልል ፣የዞንና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ወረዳዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የአካባቢው ተወላጆች ፣ ባለሀብቶች የተገኙ ሲሆን አቶ ዝናቡ ይርጋ የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ፣ዶ/ር ደመቀ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ፕላን ቢሮ ሀላፊ ፣አቶ እንድሪስ አብዱ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ፣የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁና ሌሎችም በየዘርፍ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች የጸጥታ አካላት የሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

እንደሚታወቀው ምንጃር አረርቲ ከተማ
👉ከአዲስ አበባ ምንጃር አረርቲ ከተማ አስተዳደር 133ኪ ሜትር
👉ከደብረ ብርሀን 263ኪ ሜትር
👉ከባህር ዳር 695 ኪ ሜትር
👉ከሞጆ 56ኪ ሜትር
👉ከደብረ ብርሀን በሀገረ ማርያም 178 ኪ/ሜትር ሲሆን በወረዳውና በከተማው የሚገኙ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ና ምቹ ሁኔታዎችም የሚገኙ ናቸዉ።

‎ℹ️ ለበለጠ መረጃ
▤▤▤▤▤▤▤▤
Youtube ገፃችንን subscribe ያድርጉ
👉 https://www.youtube.com/
Facebook ገፃችንን follow ያድርጉ
👉https://www.facebook.com/ecntv

ማስተር አብነት ከበደ እንኳን ለሀገርህ አበቃህ!❤️🙏 ኢትዮጵያውያን የምስራች! የሁላችንም ወንድም ደጎ ማስተር አብነት ከበደ በሰላም ሀገሩ ገብቷል ።  ለኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አላ...
07/02/2026

ማስተር አብነት ከበደ እንኳን ለሀገርህ አበቃህ!❤️🙏

ኢትዮጵያውያን የምስራች! የሁላችንም ወንድም ደጎ ማስተር አብነት ከበደ በሰላም ሀገሩ ገብቷል ። ለኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ።

በታይላንድ ባንኮክ የህክምና ክትትሉን ሲያደርግ የቆየው ተወዳጁ ወንድማችን ደጉ ሰዉ ማስተር አብነት ከበደ ህክምናውን በድል አጠናቆ ዛሬ ጥር 30/2018 ዓ.ም.አዲስ አበባ ገብቷል።

አሁን ላይ ሙሉ ጤንነት እንደሚሰማው ገልጿል። "የደጋግ ኢትዮጵያውያን ጸሎት ለሀገሬ አብቅቶኛል" በማለት ለጸለያችሁለትና ከጎኑ ለቆማችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል።

ፈጣሪ አምላክ ለተደረገለት መልካም ነገር ሁሉ ክብር ይግባው ። ፈጣሪ ጨርሶ ይማርህ ወንድማችን !!❤️🙏❤️

በ1.2 ቢሊየን ብር የተገነባውና በ32 ታዋቂ ባለሙያዎች የተመሰረተው "ዶክተርስ አሊያንስ አጠቃላይ ሆስፒታል" በዛሬው ዕለት ተመረቀ​በኢትዮጵያ የጤናውን ዘርፍ አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግና ጥ...
07/02/2026

በ1.2 ቢሊየን ብር የተገነባውና በ32 ታዋቂ ባለሙያዎች የተመሰረተው "ዶክተርስ አሊያንስ አጠቃላይ ሆስፒታል" በዛሬው ዕለት ተመረቀ

​በኢትዮጵያ የጤናውን ዘርፍ አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግና ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ለማቅረብ በከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የተገነባው ዶክተርስ አሊያንስ አጠቃላይ ሆስፒታል የምርቃ ስነ-ስርዓቱን በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ አካሂዷል።

​ተቋሙን ልዩ የሚያደርጉት ዋና ዋና ነጥቦች፡
​💰 የመዋዕለ ንዋይ አቅም፦ ሆስፒታሉ በ 1.2 ቢሊየን ብር ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን፣ ይህም መስራቾቹ ትልቅ ሕልምን ሰንቀው ወደ ተግባር መግባታቸውን ያሳያል።

​👨‍⚕️ የባለሙያዎች ጥርቅም፦ ከ25 ዓመታት በላይ የካበተ ልምድ ባላቸው ከ 32 በላይ ሰብ-ስፔሻሊስት ሐኪሞች የተመሰረተ ነው።

ይህም ታካሚዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና ምክርና ክትትል በሀገራቸው እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

​🏥 የመኝታና የመሠረተ ልማት አቅም፦
​ከ 100 በላይ የተኝቶ ማከሚያ አልጋዎች።
​በዘመናዊ መሣሪያዎች የተደራጁ 5 የቀዶ ጥገና ክፍሎች።

​የ24 ሰዓት የድንገተኛ ክፍልና የፅኑ ሕሙማን (ICU) ሕክምና።

​💼 የሥራ ዕድል ፈጠራ፦ በአሁኑ ወቅት ከ120 በላይ ሠራተኞችን የያዘ ሲሆን፣ በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር ከ 300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዷል።

​ምን ምን አገልግሎቶች ይሰጣሉ?

ሆስፒታሉ ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ጣራ ሥር በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባል። ከእነዚህም መካከል፦
👉​የእናቶችና ሕፃናት ሕክምና
👉​የልብ፣ የኩላሊትና የስኳር ሕመም ክትትል
👉​አጠቃላይና የውስጥ ደዌ ቀዶ ጥገናዎች
​ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሕክምና

​🌍 የሕክምና ቱሪዝምና የወደፊት ዕቅድ፦

ቀደም ሲል ዜጎች ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ውጭ አገር የሚጓዙበትን ወጪና እንግልት ለማስቀረት ሆስፒታሉ ትልቅ ግብ ሰንቋል። በተጨማሪም ከአጎራባች አገራት ታካሚዎችን በመቀበል የሆስፒታል ቱሪዝምን (Medical Tourism) የማሳደግና የውጭ ምንዛሬን የማዳን ዕቅድ ይዟል።

​📍 አድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ ራስ ደስታ አካባቢ፣ ከአርበኞች ትምህርት ቤት ጎን፣ ሰናይ ሕንፃ ላይ።

​ሆስፒታሉ ከጥር 1 ጀምሮ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ ዛሬ በተደረገው የምርቃ ስነ-ስርዓት ላይ የጤና ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ስፔሻሊስት ሐኪሞችና የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

07/02/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Master Kasahun Kebede, Jafare Kebatu, Mesele Abegzare, Mohammed Abdljelil, Tsehay Chukamo Minota, Selam Biranu

ዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ጉባዔ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ኤሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡የማዕድን ሚኒስትሩ  ሀብታሙ ተገኘ (ኢ/ር) የዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመን...
05/02/2026

ዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ጉባዔ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ኤሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ ሀብታሙ ተገኘ (ኢ/ር) የዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ፕሬዚዳንት ፖል በትማንና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ አበበ ተክሉ ተግኝተዋል።

በጉባዔዉ ላይ ከ14 የተለያዩ የዓለም ሀገራት የተወጣጡ አካላትከወርቅ ማዕድን ስራ ጋር ግንኙነት ያላቸው አለም አቀፍ ኩባንያዎች፣ ወርቅ አምራቾችና ሲያናይድ ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አምራቾች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።

ይህ ጉባዔ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሲያናይድ ትራንስፖርት እና ሲያናይድ አጠቃቀም ደህንነት ባስመዘገበው ውጤት ነው።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ - የሀገር ሀብት


ℹ️ ለበለጠ መረጃ
▤▤▤▤▤▤▤▤
Youtube ገፃችንን subscribe ያድርጉ
👉 https://www.youtube.com/
Facebook ገፃችንን follow ያድርጉ
👉https://www.facebook.com/ecntv

04/02/2026

🌟 Witness the Heartwarming Journey of Dr. Biniyam and his life-changing work in Mekedoniya! 🌟 In this inspiring video, immerse yourself in the incredible e...

የክብረት ሽልማት፦ አርቲስት ሱራፌል ተካ መኪናውን ተረክቧል!ለሳምንታት ሲጠበቅ የነበረው ታላቅ ቀን ዛሬ ጥር 24/2018 ዓ.ም.እውን ሆኗል! ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ(Popular Electron...
01/02/2026

የክብረት ሽልማት፦ አርቲስት ሱራፌል ተካ መኪናውን ተረክቧል!

ለሳምንታት ሲጠበቅ የነበረው ታላቅ ቀን ዛሬ ጥር 24/2018 ዓ.ም.እውን ሆኗል!
ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ
(Popular Electronics) ለአርቲስት ሱራፌል ተካ ቃል የገባውን ዘመናዊ መኪና ዛሬ እሁድ ጥር 24/2018 ዓ.ም.በደመቀ ስነ-ስርዓት አስረክቧል።

ይህ ሽልማት እንዲሳካና ውጤታማ እንዲሆን የቲክቶክ ቻሌንጁን (Challenge) ተቀብሎ በብቃት የተወጣው ቲክቶከር አዶናይ ሊመሰገን የሚገባው ትልቅ ስራ ሰርቷል። አዶናይ ላሳየው ቁርጠኝነት እና ለፈጠረው መነቃቃት አድናቆት እየተቸረው ይገኛል።

አርቲስት ሱራፌል ተካ የመኪናውን ቁልፍ ሲረከብ በቦታው የነበሩ እንግዶች በታላቅ ጭብጨባ አጅበውታል።

በዝግጅቱ ላይ በርካታ ቲክቶከሮች ጋዜጠኞች የአርቲስት ሱራፌል ተካ ወዳጆች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ታዋቂ ግለሰቦች በመገኘት ለዝግጅቱ ድምቀት ሰጥተዋል።

ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ የገባውን ቃል በተግባር በማሳየቱ እና አርቲስቱን በመሸለሙ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አትርፏል። አርቲስት ሱራፌልም ለዚህ ስኬት በመብቃቱ እንኳን ደስ አለህ እንላለን!

እንኳን ደስ አለህ ሱራፌል ተካ!
ትልቅ ምስጋና ለቲክቶከር አዶናይ!
ክብር ለPopular Electronics!

ፎቶግራፍ Naomi 📸 studio
ጋዘጤኛ : ሲሳይ መንግስቴ
ℹ️ ለበለጠ መረጃ
▤▤▤▤▤▤▤▤
Youtube ገፃችንን subscribe ያድርጉ
👉 https://www.youtube.com/
Facebook ገፃችንን follow ያድርጉ
👉https://www.facebook.com/ecntv

01/02/2026

የሁለቱ ባለሐብቶች ልጆች በመቄዶንያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ተዳሩ!!ኢትዮጵያዊቷ የሴት ባለሀብት ወ/ሮ ትልቅሰው ገዳሙ ወንድ ልጃቸውን አቶ ሁንልኝ አምደወርቅን መኪና በማስመጣት ከ....

17ኛዉ ከተማ አቀፍ የባህል ሳምንት በኢግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ ነዉ።        የአ.አ ባህልና ኪነ ጥበብ ቢሮ ከጥር 23/5/18_24/5/18 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘዉ ኢግዚቢሽን ማ...
01/02/2026

17ኛዉ ከተማ አቀፍ የባህል ሳምንት በኢግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ ነዉ።

የአ.አ ባህልና ኪነ ጥበብ ቢሮ ከጥር 23/5/18_24/5/18 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘዉ ኢግዚቢሽን ማዕከል ሞቅ ደመቅ ባለ ዝግጅት እየተዘጋጀ ይገኛል።ይህን ፌስቲቫል የተለያዩ ግለሰቦች እየጎበኙ ሲሆን የባህል ሳምንት ከ11 አንዱም ክፍለ ከተሞች የተዉጣጡ ዲዛይነሮች ፣ሸክላ ሰሪዎች የተለያዪ የባህል አልባሳት የሚያዘጋጁ ፣የዕደ ጥበብ ስራዎች ባለሞያዎች እንዲሁም ከአሁን ቀደም ለየት የሚለዉ የባህለ ምግቦች ማለትም ጤፍ ፣ሽንኩርት ፣ቴማቲም፣በርበሬ፣ጥራጥሬ፣እንቁላል በተጨማሪም ማየት የተሳናቸዉ የቤት ዕቃዎች ማለትም መወልወያ፣መጥረጊያ ፣የፅዳት ዕቃዎች ለታዳሚያን አቅርበዋል።
ፕርሮግራሙ ለሁለት ቀን የሚቆይ ሲሆን ከትናንት ከ23/5/18_24/5/18 ዓ.ም የሚቆይ በመሆኑ በክብር እንድትጎበኙ ECN TV & Radio ጥሪዉን ያስተላልፋል።
ሪፓርተር ብርሃኑ ደጀኔ
24/5/18 ዓ.ም

ℹ️ ለበለጠ መረጃ
▤▤▤▤▤▤▤▤
Youtube ገፃችንን subscribe ያድርጉ
👉 https://www.youtube.com/
Facebook ገፃችንን follow ያድርጉ
👉https://www.facebook.com/ecntv

በ3 ድንቁ ቅፅበት ለወመዘክር ተበረከተደራሲ(አጋዝ) ገብረየሱስ ኃይለማሪያም ያነሷቸው ''የሚሊኒየሙ መሸኛና መቀበያ'' ፎቶግራፎችን ጨምሮ ጥንታዊ መፅሐፍቶቻቸውን ለወመዘክር አበረከቱ።'ድንቁን...
31/01/2026

በ3 ድንቁ ቅፅበት ለወመዘክር ተበረከተ

ደራሲ(አጋዝ) ገብረየሱስ ኃይለማሪያም ያነሷቸው ''የሚሊኒየሙ መሸኛና መቀበያ'' ፎቶግራፎችን ጨምሮ ጥንታዊ መፅሐፍቶቻቸውን ለወመዘክር አበረከቱ።

'ድንቁን ቅፅበት' በሚል የደራሲ ገብረየሱስ ኃይለማርያም በፈረንጆቹ ሚሊኒየም መባቻ እስከ ወጨጫ ተራራ በመጓዝ ያነሷቸው የሚሊኒየሙ ጀንበር መሸኛና መቀበያ ፎቶግራፎችን ጨምሮ የጫሙት ሽካ፣ ተኬትነት አጂነት/አገኪ፣ ነሁቸርና The Gurage and their Culture የተሰኙ የድርሰት ሥራዎቻቸውን ለብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አስረክበዋል።

በቋንቋ፣ በባህልና በማኅበረሰብ ልማት ዘርፎች ያበረከቷቸው የሕይወት ዘመን አገልግሎቶች "አጋዝ" የሚል ባህላዊ ስያሜ የተሰጣቸው አጋዝ ገብረኢየሱስ ኃይለማርያም በጉራግኛ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ 16 መጽሐፍትን ጽፈዋል። ለጉራጌ ባህልና ቋንቋ ልማት ካበረከቱት አስተዋጽኦ ባሻገር የጉራጌ ሕዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅትን (ጉህራልድ) መሥርተዋል፤ አገልግለዋልም። በሌሎች ሀገራዊና ዓለምአቀፍ ተቋማትም አሻራቸውን አኑረዋል።

ተወዳጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ከሶዶ ለማ ሚድያ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ በወመዘክር ኅሩይ አዳራሽ ነው የተካሄደው።

በዚህም ታላላቅ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበትም የደራሲው ተወዳጅ መጻሕፍትና ያነሷቸው ታሪካዊ ፎቷግራፎች ለታሪካዊው ወመዘክር ተበርክቷል።

''ድንቁ ቅፅበት'' መርሀ ግብር በምርቃት የተጀመረ ሲሆን ደራሲ በብርሃነ ዓለሙ በአጋዝ ገብረየሱሰ መፅሀፍና የአፃፃፍ ስልት ላይ እንዲሁም ገጣሚ ክፍሌ ተመስገን ከጫሙት ሽካ መፅሐፍ የተቀነጨበ ታሪክ አቅርበዋል።

የብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተ መፅሀፍት አገልግሎት ፅህፈት ቤት ኅላፊ አቶ አባተ ካሣው ሰነዶቹን ሲረከቡ ባደረጉት ንግግር ባለ ታሪኩ አጋዝ ገብረየሱስ ታሪካዊ ሰነዶችን በማስረከባቸው የተሰማንን ልባዊ ደስታ እንገልፃለን ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሠረት አመርጋ በበኩላቸው እንዲህ አይነት ታሪካዊ ስራዎች በሰነድነት ታስበው የርክክብ ሥነ ሥርዓቱ መዘጋጀቱ ለሀገር ትልቅ ነገር ነው ብለዋል። ባህል፣ ቋንቋና ስነ-ፅሑፍን ለትውልድ ከማሸጋገር አንፃር ሚናቸው ትልቅ ነው ያሉት ሀላፊዋ ደራሲው እንደ ሀገር ላበረከቷቸው ታሪካዊ ሰነዶችም ምስጋና አቅርበዋል።

ደራሲ አጋዝ ገብረየሱስ ሀይለማርያም በበኩላቸው ስራዎቹን ሳከናውን እዚህ ይደርሳል ብዬ ባይሆንም የበርካታ ታሪክና ባለታሪኮች ሰነድ መገኛ የሆነው ወመዘክ ፎቶግራፎቼንና የድርሰት ስራዎቼን በአሻራነት መሰነድ በመቻሉ ደስታ ተሰምቶኛል፤ አመሰግናለሁ''ም ብለዋል። ወደፊትም የታሪካዊ ሰነድ ባለቤቶች ስራዎቻቸው ለትውልድ ተደራሽ እንዲሆኑ ለወመዘክር ማስረከብ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ደራሲው ''ድንቁ ቅፅበት'' በሚል መርሃ-ግብሩን ላዘጋጁት ተወዳጅ ሚዲያና ሶዶ ለማ ሚዲያም ልዩ ምስጋና አቅርበዋል።

ℹ️ ለበለጠ መረጃ
▤▤▤▤▤▤▤▤
Youtube ገፃችንን subscribe ያድርጉ
👉 https://www.youtube.com/
Facebook ገፃችንን follow ያድርጉ
ECN TVtv

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ECNTV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ECNTV:

Share