Firtuna

Firtuna Firtuna is an Ethiopian-based entertainment news company

Firtuna is a media and production company that provides Art Related news Daily which has a vision of Transforming the Ethiopian art industry to the next level.

15/02/2026

14/02/2026

11/02/2026

በኢትዮጵያ የሳተላይት ቴሌቪዥን ታሪክ ውስጥ ቀዳሚና ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑት የግል ሚዲያዎች አንዱ የሆነው የኢቢኤስ (EBS TV) መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አማን ፍስሃጽዮን ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማኔጅመንት ባወጣው መደበኛ መግለጫ፣ የአቶ አማንን ሕልፈት በከፍተኛ ሐዘን አረጋግጧል። ተቋሙ በመግለጫው ላይ "ለኢትዮጵያ ሚዲያ ዕድገትና ለጣቢያችን ኢቢኤስ ስኬት የማይተካ ሚና የተጫወቱት፣ የታላቅ ራዕይ ባለቤት የሆኑት ብርቱ ሰው ዛሬ እንደ ቤተሰብም እንደ ጣቢያ ብናጣም፣ የአቶ አማን ፍስሃጽዮን ራዕይ ይቀጥላል" ሲል ገልጿል።

አቶ አማን ፍስሃጽዮን በኢትዮጵያ የሚዲያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ዘመናዊና አዝናኝ የሆኑ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን በማስተዋወቅ ረገድ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው። በተለይም እ.ኤ.አ. በ2008 በዩናይትድ ስቴትስ ሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ ውስጥ የኢቢኤስ ቴሌቪዥንን በመመሥረት፣ በውጭ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከአገሩ ባህልና ዜና ጋር ለማገናኘት ትልቅ ድልድይ ሆነዋል።

ጣቢያው ወደ ኢትዮጵያ በስፋት በመግባት በርካታ ወጣት የሚዲያ ባለሙያዎችን፣ አቅራቢዎችንና የኪነ-ጥበብ ሰዎችን ወደ አደባባይ አውጥቷል። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የይዘት አቀራረብ ላይ የከፍተኛ ጥራት (High Definition - HD) ስርጭትንና ዘመናዊ የቶክ ሾው ስልቶችን በማስተዋወቅ ረገድ አሻራቸው የጎላ ነው።

አቶ አማን "ለኢትዮጵያ የሚዲያ ነፃነትና ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ፣ በሥራቸው ደግሞ ለብዙዎች አርአያና አበረታች የነበሩ ሰው ናቸው" በሚል በሥራ ባልደረቦቻቸውና በአድናቂዎቻቸው ዘንድ ሲገለጹ ቆይተዋል።

የአቶ አማን ፍስሃጽዮን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዝርዝር መረጃ ወደፊት እንደሚገለጽ ይጠበቃል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Firtuna posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Firtuna:

Share