ጄዚራ አፍሪካ Jazeera Africa

ጄዚራ አፍሪካ Jazeera Africa True Unity for African, Solution Journalism, Professional Journalists, stories worth Africa

27/09/2026

ሰቆጣ ለመከላከያ ምስጋናዋን በድምቀት ገልፃለች
መቻል

ከሕወሓት ጋር ተሰልፈው ሲዋጉ የነበሩ በርካታ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በሀገር መከላከያ እጅ ወደቁከሕወሓት ጋር በመተባበር በተለያዩ የግንባር መስመሮች ሲዋጉ ከነበሩት ከሁለት ሺህ በላይ የኤርትራ ...
27/09/2026

ከሕወሓት ጋር ተሰልፈው ሲዋጉ የነበሩ በርካታ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በሀገር መከላከያ እጅ ወደቁ

ከሕወሓት ጋር በመተባበር በተለያዩ የግንባር መስመሮች ሲዋጉ ከነበሩት ከሁለት ሺህ በላይ የኤርትራ (ሻዕቢያ) ታጣቂዎች መካከል በርካቶቹ መደመሰሳቸው እና መማረካቸው ተገለጸ።

በተካሄደው የፀረ-ጥቃት እርምጃ የተማረኩት እና የተደመሰሱት የሻቢያ ታጣቂዎችን ሙሉ ማንነትና ዝርዝር መረጃ በሚመለከት በቅርቡ ይፋ የሚደረግ መሆኑ ተጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት በሕይወት የተረፉ በርካታ የሻቢያ ታጣቂዎች ወደ ኤርትራ በመሸሽ ላይ እንደሚገኙና በድንበር አካባቢ የነበሩ የኃይል ስብስቦችም ከአካባቢው እያፈገፈጉ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ሰቆጣ - አላማጣ - ኮረምየመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ሰቆጣን ከህውሃት ታጣቂዎች ታድገዋል። ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ የፀጥታ ኃይሉን ሲያመግን እና ደስታውን ሲገልፅ ታይቷል።መከላከያ አላማጣን ለፖ...
27/09/2026

ሰቆጣ - አላማጣ - ኮረም

የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ሰቆጣን ከህውሃት ታጣቂዎች ታድገዋል። ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ የፀጥታ ኃይሉን ሲያመግን እና ደስታውን ሲገልፅ ታይቷል።

መከላከያ አላማጣን ለፖሊስና ሚኒሻ አስረክቦ ወደ መሆኒ እና ኮረም አቅጣጫ አቅንቷል።

አላማጣ ህውሃት በብስጭት ወደ ከተማ መድፍ ተኩሶ ቦሌ ሰፈር ኮንዶምኒየም ጀርባ የ6 ነፁሃን ህይወት መቅጠፉም ተሰምቷል።

የአቶ ጌታቸው ረዳ መልዕክት"የሕወኃት መሪዎች በትግራይ ወጣት ላይ የሚፈፅሙት ወንጀል ወሰን የለውም።”በጀግንነት እና በህዝባዊነት የሚታወቀውን ሰራዊት የወንጀለኞች መጫወቻ ሆኖ ከማየት በላይ ...
26/09/2026

የአቶ ጌታቸው ረዳ መልዕክት

"የሕወኃት መሪዎች በትግራይ ወጣት ላይ የሚፈፅሙት ወንጀል ወሰን የለውም።”

በጀግንነት እና በህዝባዊነት የሚታወቀውን ሰራዊት የወንጀለኞች መጫወቻ ሆኖ ከማየት በላይ እና እንዲዋጋላቸው በፋኖ የሚያታልሉ እና የሚረሽኑ ሓይሎች ሆነ እንደማየት የሚያበሳጭ ነገር የለም።

የትግራይ ሠራዊት ደመ ከልብ ከሚያደርጉህ እና ከሚዋሹህ ጨካኝ መሪዎች ከማገዱህ እሳት ጎትተህ ኣስገብተህ ራሳቸው እንዲሞቁት አድርግ፤ ክቡር መስዋእትነት የሚል የጮሌዎች መፈክር አይመለከተኝም በላቸው።

ለወላጆችህ እና ለህዝብህ ስትል ከሞት ህይወት ምረጥ።
ሁሉም ወንጀለኞች ዋጋቸውን የሚያገኙበት ሥራ ሥራ።
ሞት ይብቃ በል ይላል!"" ብለዋል: አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር

መስከረም16 ቀን2019ዓ.ም

የሀገር መከላከያ ሰራዊት 13 አካባቢዎችን ከህውሃት የጥፋት ኃይሎች ማስለቀቁበራያ አላማጣ ግንባር እየተደረገ ባለው ውጊያ መከላከያ ሰራዊቱ ባደረገው ማጥቃት በዛሬው እለት 13 ስፍራዎችን ሙሉ...
26/09/2026

የሀገር መከላከያ ሰራዊት 13 አካባቢዎችን ከህውሃት የጥፋት ኃይሎች ማስለቀቁ

በራያ አላማጣ ግንባር እየተደረገ ባለው ውጊያ መከላከያ ሰራዊቱ ባደረገው ማጥቃት በዛሬው እለት 13 ስፍራዎችን ሙሉ በሙሉ ማስለቀቁ ተገልጿል:-
— ራያ አላማጣ ወረዳ እና ራያ ጨርጨር ወረዳ
1. ዋጃ
2. ጥሙጋ
3. አየር ማረፊያ
4. ቢትሞ
5. ኩቢ ቀረንሳ
6. ኩቢ ድርባ
7.በደና ለኮ
8. ትግሬ መንደር
9. ጉበና መንደር
10. ራያ መንደር
11. ባይባዎ
12. መሓጎ
13. ቀይ አፈር
በመከላከያ ሰራዊቱ ነፃ የወጡ ሲሆን በአላማጣ የነበሩ የሕወሓት ጦር እና አመራሮች ወደኋላ እየሸሹ፣ መከላከያ ሰራዊቱ ወደ ፊት ቀጥሏል።

የጉሙዝ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉ.ህ.ዲ.ን) ‹‹ትብብር ለህልውና›› ከተባለው አዲስ ጥምረት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው በይፋ አስታውቋል። ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፣ ማንም አ...
25/09/2026

የጉሙዝ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉ.ህ.ዲ.ን) ‹‹ትብብር ለህልውና›› ከተባለው አዲስ ጥምረት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው በይፋ አስታውቋል። ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፣ ማንም አካል ሳያውቅና ስምምነት ላይ ሳይደረስ ስሙን ከሌሎች የታጠቁ ኃይሎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ማካተቱን በጥብቅ አውግዟል። የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ኦግራይን ጉደታ እንደገለጹት፣ ጉ.ህ.ዲ.ን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሙሉ ዕውቅና ያለው ሕጋዊና ሰላማዊ ፓርቲ ነው።

🚩 በተጨማሪም በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ 14 የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን በማሸነፍ ህዝቡን በመወከል ላይ ይገኛል። በመሆኑም ፓርቲው ከማንኛውም ህገ-ወጥ ስብስብ ጋር እንደማይሰራ እና ስሙን ያለአግባብ የተጠቀሙ አካላትን ድርጊት ፈፅሞ እንደማይቀበል አረጋግጧል።

ፈረንሳይ 🇫🇷 እና እንግሊዝ 🇬🇧 የህወሃት የቀሰቀሰውን ጦርነት አወገዙ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ በሰሜን ኢትዮጵያ፣ በአፋር፣ በአማራና በደቡባዊ ትግራይ በህወሃት ታጣቂዎች የተፈጸሙ ጥቃቶችን እ...
24/09/2026

ፈረንሳይ 🇫🇷 እና እንግሊዝ 🇬🇧 የህወሃት የቀሰቀሰውን ጦርነት አወገዙ


ፈረንሳይ እና እንግሊዝ በሰሜን ኢትዮጵያ፣ በአፋር፣ በአማራና በደቡባዊ ትግራይ በህወሃት ታጣቂዎች የተፈጸሙ ጥቃቶችን እንዲሁም የመቐለ፣ አክሱምና ሽረ አውሮፕላን ማረፊያዎች በኃይል መያዛቸውን አውግዘዋል።

የአፍሪካ ህብረት በይፋዊ መግለጫው፤ ህወሃት የመቐሌ፣ የአክሱም እና ሽሬ አየር መንገዶችን በኃይል በመቆጣጠር፣ በጥበቃ ላይ የነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላትን በማሰር፣ እንዲሁም በደቡብ ትግራይ...
23/09/2026

የአፍሪካ ህብረት በይፋዊ መግለጫው፤ ህወሃት የመቐሌ፣ የአክሱም እና ሽሬ አየር መንገዶችን በኃይል በመቆጣጠር፣ በጥበቃ ላይ የነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላትን በማሰር፣ እንዲሁም በደቡብ ትግራይና በአፋር ክልል አዳዲስ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት መጣሱን በመግለፅ ኮንኗል።

አሜሪካ ተጨማሪ ማዕቀብ እንደምትጥል አስጠነቀቀች፤ ጦርነት የጀመረውን ህወሓትን  አወገዘችበኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በአፋር...
23/09/2026

አሜሪካ ተጨማሪ ማዕቀብ እንደምትጥል አስጠነቀቀች፤ ጦርነት የጀመረውን ህወሓትን አወገዘች

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በአፋር እና በአቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ላይ አዲስ ሰፊ የጦርነት እንቅስቃሴ በመክፈቱ አጥብቀው የሚኮንን ጠንካራ መግለጫ አውጥተዋል።

አምባሳደር ማሲንጋ ህወሓት በሰላማዊ መንገድ ከመደራደር ይልቅ ወደ ውጊያ ለመመለስ ባደረገው ውሳኔ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል። የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በዋና ዋና የህወሓት አመራሮች ላይ ማዕቀብ መጣሉን ያስታወሱት አምባሳደሩ፣ የቀጣናውን መረጋጋት የሚያናጉ አካላት ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦች ሊጣሉ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ማሲንጋ እና ሌሎች ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በአካል እስከ መቀሌ ድረስ በመመላለስ አመራሮቹ ከጦርነት እንዲቆጠቡ በርካታ ውይይቶችን ቢያደርጉም፣ ህወሓት ግን ይህንን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እና የተዘረጉ የሰላም እጆችን ሙሉ በሙሉ ባለመቀበል አልፎታል። በተጨማሪም በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አደራዳሪነት በአፍሪካ ሕብረት (AU) ጥላ ስር የተደረገውን ጥረት እና የተቀመጠውን የሰላም አማራጭ በመናቅ ወደ አዲስ ደም አፋሳሽ ግጭት ገብቷል።

አምባሳደር ማሲንጋ ህወሓት ትርጉም ባለው የፖለቲካ ውይይት ምትክ «አሸናፊ የሌለው ጦርነት» መምረጡን አጥብቀው የነቀፉ ሲሆን፣ ኢትዮጵያን ወደ ቀውስ የሚመልሱ አመራሮችን ለመቅጣት ዋሽንግተን ተጨማሪ የማዕቀቦች እንዳሏት አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ሌሎች ታጣቂዎች እና አካባቢያዊ ሚሊሻዎች ከዚህ የህወሓት የተሳሳተ እርምጃ እንዲማሩ፣ ከግጭቱ እንዲቆጠቡና ሁኔታውን ከማባባስ እንዲታቀቡ ግልጽ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።

የአምባሳደሩ አስቸኳይ ጥሪ የመጣው ከ2013 እስከ 2015 ዓ.ም በነበረው የትግራይ ጦርነት ወቅት ደርሶ የነበረውን ከፍተኛ የሰው ሕይወት እልቂት ታሪክ መሠረት በማድረግ ነው። የጦርነቱን ሰለባዎች በተመለከተ በትግራይ የሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎች በጦርነቱ፣ በከባቢ አየር እና በርሃብ ምክንያት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የትግራይ ተዋጊዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጸዋል።

ይህ አስከፊ ታሪክ እንዳይደገም በአፍሪካ ሕብረት የሚመራውን አካታች የፖለቲካ ውይይት እና የፕሪቶሪያውን ስምምነት በተግባር መተርጎም እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መመለስ ለዓለም አቀፍ የባሕር ላይ ንግድ መስመር ደህንነት አስፈላጊ ነው - በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሤ (ዶ/ር)🇪🇹🇮🇱የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕ...
10/09/2026

የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መመለስ ለዓለም አቀፍ የባሕር ላይ ንግድ መስመር ደህንነት አስፈላጊ ነው - በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሤ (ዶ/ር)
🇪🇹🇮🇱

የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መመለስ ለዓለም አቀፍ የባሕር ላይ ንግድ መስመር ደህንነት እና ለቀጣናው ኢኮኖሚ ዕድገት አስፈላጊ መሆኑን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሤ (ዶ/ር) ገለጹ። እስራኤል የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥያቄ የምትደግፈው መሆኑንም አስታውቀዋል።

አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ እና እስራኤል ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ አጋርነት እየተሸጋገረ ነው።

በዚህም የመንግሥት ለመንግሥት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ከፍተኛ ዕድገት እየተመዘገበ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በማደግ ላይ የምትገኝ ሀገር ናት ያሉት አምባሳደሩ፤ ለዚህም የኢትዮጵያን ወጪና ገቢ ንግድ የሚያሳልጥ የባሕር በር ከሌለ ዕድገትን ለማፋጠን አዳጋች ነው ብለዋል።

ለዚህም ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ላቀረበችው ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እስራኤል በሙሉ ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መመለስ የባሕር ላይ ሽብርተኞችንና ወንበዴዎችን በመመከት ለዓለም ሰላም እና የኢኮኖሚ ዕድገት ጥሩ ውጤት የሚያመጣ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት የሁለቱን ሀገራት ጂኦ ስትራቴጂክ ተጠቃሚነትን በማጎልበት ቀጣናዊ የሽብር ስጋቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቀልበስ ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረውም አምባሳደሩ አስረድተዋል።

ሽብርተኞች በቀይ ባሕር ስትራቴጂክ የንግድ መስመር በመርከቦች ላይ በሚፈጽሙት ጥቃት ምክንያት በንግድ ስርዓቱ ላይ ሳንካ እየፈጠሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

የእነዚህ የሽብር ኃይሎች እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ እና እስራኤል ባሻገር ለአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ እስያና ለሌሎች ሀገራትም ጭምር የደህንነት ስጋት መሆኑን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ መልስ ማግኘት መሰል የሽብር ኃይሎች እንቅስቃሴን በመግታት የኢኮኖሚና የደኅንነት ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ነው አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) ያመላከቱት።

በመሆኑም የኢትዮጵያ አስተማማኝ ወደብ የማግኘት ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ተቀባይነት ያለውና እስራኤልም የምትደግፈው መሆኑን ጨምረው አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነትና ወደ ቀይ ባህር የመመለስ ምክንያታዊ ጥያቄ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ብሎም ቀጣናውን በመሰረተ ልማትና በኢኮኖሚ ለማስተሳሰር ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለው አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቀነስ የሚያስችል አቅም እየፈጠረች እንደምትገኝም ገልጸዋል።

እስራኤልም በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ያላትን ልምድና ተሞክሮ በማጋራት ድጋፏን እንደምታጠናክር አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ብዝኅ የተፈጥሮ ሃብት፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትና አምራች የሰው ሃይል ከእስራኤል ቴክኖሎጂና ፈጠራ ትብብር ጋር በማቆራኘት ፈጣን ዕድገት ማስመዝገብ እንደሚያስችላት አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በዓድዋ ድል ለአፍሪካውያን የነፃነት ምልክት እንደሆነችው ሁሉ፤ ድህነትንና ኋላ ቀርነትን በመግታት እንዲሁም በዲጂታል ሥርዓትና ብዝኅ ልማትም ፋና ወጊ መሆኗን ተናግረዋል።
— ኢዜአ

Address

Pyassa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጄዚራ አፍሪካ Jazeera Africa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ጄዚራ አፍሪካ Jazeera Africa:

Shortcuts

Share