Masero Addis

Masero Addis በFacebook እና Instagram ላይ ድርጅቶን ስራዎን እና ምርትዎን ያስተዋውቁ📈

07/02/2023

Advertize your services on social media!
ምርትና አገልግሎቶን በሶሺያል ሚዲያ ያስተዋውቁ!

🛒 Online ይሚሸጡት ዕቃ አለ?
🛒 አዲስ Business ጀምረዋል?
🛒 የደንበኞችዎን ቁጥር በየቀኑ መጨመር
ይፈልጋሉ?

ከ 3500 ብር ጀምሮ ሺህ ደንበኞች ጋር ይድረሱ!

💳 Payment arrangements for digital marketers
💳ለዲጂታል ማርኬተሮች የኦንላይን ክፍያ እናመቻቻለን

https://telegra.ph/Furnished-Apartment-for-Sale-01-22🏠1 bedroom furnished apartment👉Area: 80m² 📍Location: sarbet, around...
28/01/2023

https://telegra.ph/Furnished-Apartment-for-Sale-01-22🏠1 bedroom furnished apartment

👉Area: 80m²

📍Location: sarbet, around Bisrat Radio

👉All necessary legal documents up to date

💰Price: 13,500,000

🏠1 bedroom furnished apartment 👉Area: 80m² 📍Location: sarbet, around Bisrat Radio 👉All necessary legal documents up to date 💰Price: 13,500,000 📞 092 081 4632

LAND FOR SALEArea: 30,000m² Location: Debre Birhan, Industrial zoneAsking Price: 13,000,000Legal documents availableFor ...
23/07/2021

LAND FOR SALE
Area: 30,000m²
Location: Debre Birhan, Industrial zone
Asking Price: 13,000,000
Legal documents available

For inquiries
Call 0935205729

Register before the time runs out!!  👩‍🎓 👨‍🎓
13/01/2021

Register before the time runs out!! 👩‍🎓 👨‍🎓

07/06/2020

እየተቸን እናግዛለን።
እያገዝን እንተቻለን!
_____________________

ከዚህ ቀደም "መስቀል አደባባይ ላይ ምን እየተሠራ ነው?" በሚል ርእስ ሰጋቶቼን እና ቅሬታዎቼን አጋርቼ ነበር። በቦታው ላይ ዋንኛ ባለድርሻ የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የከተማ አስተዳደሩን "ምን እየተሠራ እንደሆነ ማብራሪያ መጠየቋ ይታወሳል።

ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ የቤተክርስቲያኒቱን መብት እና ጥቅም የሚጋፋ ፕሮጀክት የመገንባት ፍላጎት እንደሌለው ለቤተክህነቱ በመግለጽ ዝርዝር ዲዛይኖቹን እንዲያስረዱ በባለቤት በኩል ለዲዛይን ክለሳ (Design Review) የተመደቡ አርኪቴክቶች በአካል ጠቅላይ ቤተክህነት በመቅረብ ለቤተክርስቲያኒቱ አባቶች እንዲያስረዱ፤ ከማድረጋቸውም በላይ ቤተክርስቲያኒቱ የዲዛይን እና የግንባታ ሂደቱን በጋራ የሚከታተሉ ባለሙያዎች እንድትመድብ ተደርጓል። (ቤተክርስቲያኒቱ አስፈላጊ እንደሆነ ባመነችበት ጊዜ መግለጫ የምትሰጥበት ይመስለኛል)

ምንድነው የሚሠራው?
````````````````````````````
የፕሮጀክቱ ስያሜ እንደሚገልጸው "ከመስቀል አደባባይ፣ ላጋር መዘጋጃ ቤት" የሚያጠቃልል ምቹ የእግረኛ መንገድ ማስፋት፣ የቅርሶች ጥገና፣ የአጸዶች መትከል፣ የአረንጓዴ ሥፍራዎች ዝግጅት፣ የመኪና ማቆሚያ እና የመስቀል አደባባይን በተሻለ መልክ ማዘጋጀትን (Refurbishment) ያካትታል።

ዲዛይነሩ ማነው?
````````````````````````````
ፕሮጀክቱ የዲዛይን ግንባታ (Design Build) እንደመሆኑ የግንባታ ሥራውን የተረከበው የቻይናው ሥራ ተቋራጭ በሥሩ ሀገር በቀል የሆነ አማካሪ ቀጥሯል። የከተማ አስተዳደሩ ደግሞ የዲዛይን ሥራውን እና የግንባታ አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ በሥራ ተቋራጩ የተቀጠረው አማካሪ ቢሮ ላይ ላለመተው በራሱ የዲዛይን ክለሳ (Design Reviewer) አማካሪ በካቢኔው ይሁንታ ቀጥሯል።

በዲዛይኑ እነማን ተሳትፈዋል?
``````````````````````````````````
የመስክ ጉብኝት ባደረኩበት ወቅት ዋናው ተቆጣጣሪ አርኪቴክት (Chief Project Architect) እንዳብራሩልኝ የአርኪቴክቸር፣ የቅርስ ጥበቃ (Conservation)፣ የከተማ ዲዛይን (Urban design) ባለሙያዎች የሆኑ በርካታ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን አብረው እየሠሩ ይገኛሉ። (አንዳንዶቹ ዲዛይነሮች የእኔም መምህራን የነበሩ ፕሮፌሰሮች ናቸው።)

የመዋቅር ዲዛይኑን (Structural Design) የሚከታተለው አምስት ኪሎ የሚገኘው የምህንድስና ትምህርት ቤት መምህራን ቡድን መሆኑን አረጋግጫለሁ። ዲዛይኑ ከፍተኛ ጭነት እና ፍንዳታ እንዲቋቋም ታስቦበት መወጋጀቱን ታዝቤአለሁ።

የገጸምድር ዲዛይን (Landscape Design) የሚያጠኑ ባለሙያዎች በሥራ ተቋራጩ አማካሪ ሥር ተቀጥረው እየሠሩ ነው። በእኔ ምርመራ ዲዛይኑ የተሰጠበት አካሄድ የመርህ ጉድለት እንደተጠበቀ ሆኖ ፕሮጀክቱ ግን ሀገሪቱ አሉኝ በምትላቸው ምስጉን የዲዛይን እና የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያዎች እጅ ላይ እንዳለ አረጋግጫለሁ።

የሚፈርሱ ቅርሶች አሉን ?
````````````````````````````
ከመዘጋጃ ቤቱ በላጋር እስከ መስቀል አደባባይ ያሉትን ቅርስ የሆኑ ሕንጻዎች (Heritage Buildings) እና ሐውልቶች (Monuments) አንድ በአንድ ለመጎብኘት እና በግንባታው የሚደርስባቸው ተጽእኖ ይኖር እንደሆን ለማጥናት እድል አግኝቻለሁ።

የፕሮጀክቱ አማካሪ አርኪቴክት በዝርዝር እንዳስረዱኝ እና በግሌ የዲዛይን ጥናቶቹን እንዳየኋቸው አንድም የሚነካም ሆነ የሚፈርስ ህንፃ እና ሃውልት የለም። በቅርስ ጥበቃ ኤክስፐርቶች ምክር የሚታደሱ እና ከቅርሶቹ ጋር ወደሚሄዱ አገልግሎቶች (Adaptive Reuse) የሚቀየሩ ግን ይኖራሉ።

የመስቀል ደመራ እጣ ?
````````````````````````````
የዲዛይኑም ሆነ የግንባታው ማዕከል በዩኔስኮ የተመዘገበው የደመራው እና የመስቀል በዓል አከባበር እንደመሆኑ ይህንኑ መንፈሳዊ እሴት ይበልጥ ለማድመቅ እና ምቹ ለማድረግ ብዙ እንደተሠራ ታዝቤአለሁ።

ለምሳሌ ደመራው የሚተከልበት ቦታ እንደ መንፈሳዊ ትውፊቱ ከታች ጀምሮ የመጣ ድንግል መሬት ላይ እንዲተከል የተሠራ ሲሆን በገጸ ምድሩ ላይ የተለየ ማድመቂያ ዲዛይን (Surface Aarticulation) ተዘጅቶለታል።

(ጥንት ንግሥት ዕሌኒ እንደተከለችው ሁሉ ደመራው ከሥሩ በሚገኙ በምድር ቤቶቹ ምክንያት በመጣ ተንሳፋፊ ኮንክሪት ላይ ሳይሆን ተለይቶ በተዘጋጀ መሬት ላይ እንዲተከል ዲዛይኑ ተዘጋጅቷል)

ግንባታው መቼ ይጠናቀቃል?
``````````````````````````````````
የፕሮጀክት ቢሮው ባለሙያዎች እንዳስረዱኝ ለመጪው አዲስ ዓመት የሚደርሰው የደመራው መትከያ እና አካባቢው መቀመጫ ደረጃዎች ይሆናሉ። ቀሪው የመኪና ማቆሚያ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች እስከ ገና (ታህሳስ ወር መጨረሻ) ድረስ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቁ ይጠበቃል።

ማጠቃለያ
````````````````````````````
ከዚህ ቀደም እንዳነሳሁት በዚህ ፕሮጀክት ላይ የነበሩኝ የመርህ (የቅደም ተከተል፣ የአዋጭነት ጥናት፣ የዲዛይን ውድድር ወዘተ) ቅሬታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሥራውን ግን በምንችለው ሁሉ እንደ ዜጋ ማገዝ አለብን ብዬ አምናለሁ። በግሌ በዲዛይኑ ውስጥ ቢካተቱ፣ ትኩረት ቢያገኙ የምላቸውን የባለሙያ ሃሳቦች ለማካፈል እድል አግኝቻለሁ። ለዚህም ነው "እየተቸን እናግዛለን፤ እያገዝን እንተቻለን!" የምለው።

በሀገራችን "አኩራፊ እረኛ ቁርሱ እራት ሆኖ ይጠብቀዋል (ያውም ቀዝቅዞ) እንደሚባለው የሀገርን መልክ እና የዜጎች ሕይወት በእጅጉ የሚቀይሩ እና ተጽእኖ የሚያሳርፉ ፕሮጀክቶችን በአካሄድ ቅሬታ መንግሥትን አኩሩፎ ከዳር ቆሞ በደረቁ ከመተቸት በሀሳብ እየተከራከርን በሥራ ደግሞ እየተጋገዝን መጓዝ አለብን እላለሁ።

መንግሥትም የአካሄድ ችግሮቹን ለማረም የዜጎችን ሙያዊ ትችት ለመቀበል በወቃሽነት ብቻ ሳይሆን በገንቢ ሱታፌ (Constructive engagement) በቀናነት ሊያየው ይገባል እላለሁ። አሁንም ለግልጽነት (Transparency) እና ለአሳታፊነት (Participatory) ትኩረት አይነፈግ እላለሁ።

____________________

- መልእክቱ ጠቃሚ ከመሰላችሁ Share በማድረግ በጨዋነት ተወያዩበት።

- እንደተለመደው ስድብ የሚጽፉትን ከገጼ በblock አሰናብታለሁ!

- በ Telegram ቻናልም ቤተሰብ እንሁን
https://t.me/yohannesmekonnen

Address

Bole
Addis Ababa
1000

Telephone

0929480367

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Masero Addis posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Masero Addis:

Share