Sirgafa

Sirgafa ለሁሉም ነገር አልሃምዱሊላህ

19/08/2026
14/08/2026
ታሪካዊ ክስተት፡ ኢሎን ማስክ የአለማችን የመጀመሪያው ትሪሊየነር (Trillionaire) ሆነ!ይህ ሰው በቃ ሊቆም አልቻለም! የቴስላ እና ስፔስ ኤክስ ባለቤት የሆነው ቢሊየነሩ ኢሎን ማስክ (...
13/06/2026

ታሪካዊ ክስተት፡ ኢሎን ማስክ የአለማችን የመጀመሪያው ትሪሊየነር (Trillionaire) ሆነ!

ይህ ሰው በቃ ሊቆም አልቻለም!

የቴስላ እና ስፔስ ኤክስ ባለቤት የሆነው ቢሊየነሩ ኢሎን ማስክ (Elon Musk) የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊየን ዶላር በማለፍ በሰው ልጅ ታሪክ የመጀመሪያው ትሪሊየነር መሆን መቻሉ ተሰማ።

ይህ ሊሆን የቻለው የጠፈር ምርምር ኩባንያው SpaceX ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አክሲዮን ገበያ (IPO) በይፋ መግባቱን ተከትሎ የኩባንያው የአክሲዮን ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመናሩ ነው። ይህም የኩባንያውን አጠቃላይ ዋጋ ከ2 ትሪሊየን ዶላር በላይ አድርሶታል።

ስፔስ ኤክስ "SPCX" በሚል መለያ ስም ወደ አክሲዮን ገበያ የገባ ሲሆን፥ የቀረበው የአክሲዮን ፍላጎት ከተጠበቀው በላይ እስከ 3 እጥፍ በመጨመሩ በታሪክ ትልቁ የገበያ መግቢያ (IPO) መሆን ችሏል።

ኢሎን ማስክ በኩባንያው ውስጥ ያለው የ38% ድርሻ ብቻ አሁን ላይ 800 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፥ ይህ ስኬት ከቴስላ ካለው ሀብት ጋር ሲደመር የፎርብስ መጽሔት ማስክን የአለማችን የመጀመሪያው ትሪሊየነር አድርጎ እንዲመዘግበው አስችሎታል።

ኢሎን ማስክ ኩባንያው ወደ አክሲዮን ገበያ የገባው ለቀጣይ ትልልቅ ፕሮጀክቶች የሚሆን የፋይናንስ አቅም ለመገንባት መሆኑን ገልጿል።

ከነዚህም መካከል የስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት አውታረ መረብን በከፍተኛ ደረጃ ማስፋፋት፣ በጠፈር ላይ የሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) ዳታ ማዕከላትን መገንባት እና በወደፊት የጠፈር ቴክኖሎጂዎች ላይ በሰፊው ኢንቨስት ማድረግ ይገኙበታል።

Via The National

ለመሆኑ 1 ትሪሊየን ዶላር (1,000,000,000,000) በኢትዮጵያ ብር ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል መገመት ትችላላችሁ?

በአንድ ወቅት ማስክ ገንዘብ ደስታን አይገዛም ማለቱ ይታወሳል እውነት ግን ገንዘብ ደስታን ይገዛል ወይንስ አይገዛም ? ሃሳባችሁን በኮመንት አጋሩን!

🎙 #ለእናቱ ዳቦ በመስረቁ የታሰረው የ15 ዓመት ታዳጊ... የዳኛው ያልተጠበቀ ውሳኔ![ ] [ ] በፎቶው ላይ የምታዩት የ15 ዓመት ታዳጊ ነው። ጥፋቱ ምን ይመስላችኋል? በጠና ለታመመችው እ...
13/06/2026

🎙 #ለእናቱ ዳቦ በመስረቁ የታሰረው የ15 ዓመት ታዳጊ... የዳኛው ያልተጠበቀ ውሳኔ!
[ ]
[ ] በፎቶው ላይ የምታዩት የ15 ዓመት ታዳጊ ነው። ጥፋቱ ምን ይመስላችኋል? በጠና ለታመመችው እናቱ የሚሆን ዳቦ እና አይብ ከሱቅ በመስረቁ ነበር በፖሊስ የተያዘው።
[ ]
[ ] ​ጉዳዩ ፍርድ ቤት ቀረበ ዳኛው የልጁን ሁኔታ ሲሰሙ ግን ያልተጠበቀ ውሳኔ አስተላለፉ ህግን መጣስ ስህተት ቢሆንም፣ የልጁን ሁኔታ እና የማህበረሰቡን ኃላፊነት ለመጠቆም ፈለጉ።
[ ] ​ዳኛው እንዲህ አሉ።
[ ] “በዚህ ከተማ ውስጥ አንድ ታዳጊ እናቱ እንዳትራብ ዳቦ ለመስረቅ ከተገደደ፣ ሁላችንም ጥፋተኞች ነን።”
[ ] ​ከዚያም ዳኛው የሚከተለውን አደረጉ፡
[ ] ​ራሳቸውን ጨምሮ በፍርድ ቤቱ ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ሁሉ እያንዳንዳቸውን $5 (አምስት ዶላር) ቅጣት ቀጡ።
[ ] ​ፖሊስ የጠራውን የሱቅ ባለቤት ደግሞ $1000 (አንድ ሺህ ዶላር) ቀጡ።
[ ] ​የተሰበሰበውን ገንዘብ ሁሉ ለታዳጊው አስረክበው በነፃ እንዲለቀቅ አዘዙ። ከእስር ቤት ይልቅ፣ ገንዘቡን ይዞ ለእናቱ ምግብ እና መድሃኒት እንዲገዛ።
[ ] ​ይህ ታሪክ የሚያስተምረን ፍትህ ያለ ርህራሄ ባዶ መሆኑን ነው። አንዳንድ ጊዜ ከህግ ደብዳቤ ይልቅ የሰው ልጅ ስቃይ ቀድሞ መታየት አለበት።
[ ] ​
[ ] 👉 የዚህ ዳኛ ውሳኔ እንዴት ይታያችኋል? ፍትሃዊ ነው ወይስ ህግን ማላላት?
[ ] 👉 በእኛ ሀገር እንዲህ ያለ ሁኔታ ቢፈጠር ምን መደረግ አለበት ብለው ያስባሉ? share ላይክ አርጉት ✌️

Address

Halaba Kulito
Alaba K'ulito

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sirgafa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share