ዌራ ፕረስ ፕሮዳክሽን Wera Press Production

ዌራ ፕረስ ፕሮዳክሽን Wera Press Production Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ዌራ ፕረስ ፕሮዳክሽን Wera Press Production, Advertising/Marketing, Alaba K'ulito.

27/07/2026

#ማስታወቂያ❗
`````````````
ለሰርግ፣ ለእዝን፣ ለስብሰባ እንዲሁም ለተለያዩ ፕሮግራሞች መዋል የሚችል ምቹ የሆነ ድንኳን በኪራይ አቅርበናል።

የሀላባ ዞን ቀይ መስቀል ቅ/ጽ/ቤት የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ የተለያዩ የገቢ አማራጮችን በመፍጠር የአገልግሎት ሽፋኑን ለማስፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡም ተቋሙ ባስገባው አዲስ ድንኳን የኪራይ አግልግሎት መጀመሩን በይፋ አስታውቋል።

በመሆኑም አገልግሎቱን የምትፈልጉ አካላት ወደ ሀላባ ዞን ቀይ መስቀል ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም ስልክ በመደወል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በታላቅ አክብሮት ይገልጻል።

አድራሻችን ፦
ከሀላባ ዞን ፖሊስ መምርያ ጎን እንገኛለን
በስ/ቁጥር +251911546470 ይደውሉ!!

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሀላባ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

27/07/2026
ለሀላባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አባላት በሀላባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር አማካኝነት የተዘጋጀ የእራት ግብዣ መርሃ ግብር  - ሀላባ ቁሊቶ
05/02/2026

ለሀላባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አባላት በሀላባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር አማካኝነት የተዘጋጀ የእራት ግብዣ መርሃ ግብር - ሀላባ ቁሊቶ

10/01/2026

እንኳን ለ2018 የሀላባ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ሴራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! ወ/ሮ ሰብኃ አወል

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሀላባ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰብኃ አወል ለመላው የብሔረስቡ ተወላጆችና ወዳጆች በነገው እለት የሚከበረውን የሀላባ "ሴራ" በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

"ሴራ በአል" የሀላባ ብሔረሰብ የማንነቱ መገለጫ በሆነው ባህሉ ውስጥ ያሉ በርካታ ማራኪ የሆኑ ትውፊታዊ እሴቶችን ለአንድ ወር ያህል በመከወን የሚያሳልፍበትና አዲስ ዓመትን የሚቀበልበት በዓል ሲሆን ይህም ለዘመናት በየአመቱ እየተከበረ የመጣ ክበረ በዓል መሆኑንም ከጠቆሙ በኋላ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙት መላው የብሔረሰቡ ተወላጆች እና የሀላባ ወዳጆች እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በማስከተልም የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዋ ወ/ሮ ሰበኃ በየዓመቱ የመንገሳ ሴራ በዓል የሚከበርበት እለት ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎችና ከመላው የዞኑ ክፍል በርካታ ቁጥር ያለው ሰው የሚገኝበትና ከፍተኛ መጨናነቅ የሚፈጠርበት ቀን መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም በእለቱ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚስተዋለው የተሽከርካሪዎች ብዛትና ፍጥነት እንዲሁም በመገፋፋትና መሰል በሆኑ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት ሳይታሰብ ሊደርስ ከሚችል ጉዳት እራስን ለመጠበቅ ጥንቃቄ የተሞላበት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ወ/ሮ ሰበኃ በዓሉ የደስታና የሀሴት ይሆንልን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ ለሀላባ ብሔረሰብ የአዲሱ ዓመት ዘመን መለወጫ ሴራ በዓል በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
Ethiopian Red Cross Society

Address

Alaba K'ulito

Telephone

+251926992190

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዌራ ፕረስ ፕሮዳክሽን Wera Press Production posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዌራ ፕረስ ፕሮዳክሽን Wera Press Production:

Shortcuts

Share