God Bridge - Arba Minch

God Bridge - Arba Minch We work to promote the beauty and nature of Arba Minch City.

02/04/2025
በአርባምንጭ ለሚገነባው ዓለም አቀፍ ስቴድየም ግንባታ በቅርቡ የገቢ ማሰባሰቢያ ይደረጋልየሲቪል ምህንድስናው 40 በመቶ ለደረሰው የአርባምንጭ አለም አቀፍ ስቴድየም ግንባታ በቅርቡ የገቢ ማሰባ...
02/03/2025

በአርባምንጭ ለሚገነባው ዓለም አቀፍ ስቴድየም ግንባታ በቅርቡ የገቢ ማሰባሰቢያ ይደረጋል

የሲቪል ምህንድስናው 40 በመቶ ለደረሰው የአርባምንጭ አለም አቀፍ ስቴድየም ግንባታ በቅርቡ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀገብር በሸራተን አዲስ ሆቴል ይካሄዳል።

በዚህም የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ የተለያዩ ሚኒስትሮች የክልል መስተዳደሮችና ባለሀብቶችን ጨምሮ ከ350 በላይ እንግዶች እንደሚገኙ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም ለስቴድየሙ ቋሚ ገቢ ለማሰባሰብ የቶምቦላ ሎተሪ እጣ ሽልማት የሚካሄድ ሲሆን ይህም ሎተሪ በአርባምንጭ ከተማ ሰፊ የካሬ ቦታ የኤሌክትሪክ ባጃጅ የሞተር ሳይክል የእንግሊዝ ሀገር ደርሶ መልስ ትኬትና የ5 ቀን የኳስ እይታና ምሽት እንዲሁም ሌሎች ሽልማትን የያዘ ነው።

ስቴድየሙ በአሁን ሰአት አጠቃላይ ምህንድስናው 17 በመቶ የደረሰ ሲሆን በ1 ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

በካፍ ስታንዳርድ እየተገነባ የሚገኘው 3 ቢሊየን ብር ወጪ የተመደበለት የአርባምንጭ አለም አቀፍ ስቴድየም ግንባታ የሲቪል ምህንድስናው 40 በመቶ መድረሱ ዛሬ በአርባምንጭ ከተማ ለመገናኛ ብዙሀን በተካሄደው ጉብኝት ተነግሯል።

ስቴድየሙ ግንባታው ተጠናቆ ሲያልቅ እስከ 30ሺ ሰው የመያዝ አቅም እንዳለው የተገለፀ ሲሆን የፊፋ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ፣ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ፣ የካፍ ልዩ ልዩ ውድድሮች ፣ የቻን ውድድር እንዲሁም የኢትዮጵያ ሊጎችን እንደሚያስተናግድም ተነግሯል።

ይህ በካፍ ስታንዳርድ እየተገነባ እንደሚገኝ የተገለፀው የአርባምንጭ አለም አቀፍ ስቴድየም ባሳለፍነው አመት ሀምሌ ወር ላይ እንደተጀመረ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ አንድ አመት ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።

✍️ ድሬቱይብ

10/12/2024

የሚኖር ሃቅ ያላት ከተማ ....አርባምንጭ
***
አርባምንጭ የሠላም እና የደስታ ከተማ ናት ሲባል ለንጽጽራዊ ስበት ወይም ቃል አሰማምሮ ለማፎካከር ሳይሆን ገኖ የሚሰማ፣ የሚዳሰስ ፣የሚታይ እና የሚኖር ሃቅ ነው።

ይህቺ ከተማ በብዙ ተፈትና በብዙ ሠላማዊነቷን ገልጣለች። አንድ አይነት ሰው ሳይሆን አንድነት ጎልቶ የሚታይበት ፤ለመርዝ አረሞች መድኃኒት ያዘለች ጋሞነት ከኢትዮጵያዊነት ተስፍቶ የቆመባት ሸጋ ምድር ናት።

በበጎ ነገር ተስፋ ከመቁረጣችሁ በፊት አርባምንጭን ተመልከቱ። እነሆ እራሷን ከበጎ ነገር ጋር አስተሳስራ እራሷን አንድ ደረጃ ከፍታ ላይ እየሰቀለች ትገኛለች።

የአ/ምንጭ ሠላም በሁሉም ከተማ ጓዳ ይዝለቅ !!!

የጋሞን ጀግንነት፣የባህል እሴት፣ታሪክ፣የተፈጥሮ መስህብና ሀብት የተንፀባረቁበት የጋሞ አደባባይ *******የጋሞ አደባባይ የታላቁን ሕዝቡ ባህል፣እሴትና የተፈጥሮ ሀብትን እንዲያንፀርቅ ተደርጎ...
10/12/2024

የጋሞን ጀግንነት፣የባህል እሴት፣ታሪክ፣የተፈጥሮ መስህብና ሀብት የተንፀባረቁበት የጋሞ አደባባይ
*******
የጋሞ አደባባይ የታላቁን ሕዝቡ ባህል፣እሴትና የተፈጥሮ ሀብትን እንዲያንፀርቅ ተደርጎ የተሰራ ሲሆን እሳቤዎችን መገለጫዎች ያደረገ በዘመኑ ምህንድስ ሳይንስ፣ የአርክቴክቸራል ንድፈ ሀሳብና በእንቁ ድንጋይ የሞዛይክ ጥበብ ሥራ ተውቦ ተሰርቷል።

የአደባባዩ የላይኛው መገለጫ( በነሀስ ተሰርቶ በቅርቡ የሚገጠም) የጋሞ ጀግና ሰው ባህላዊ ጦርና ጋሻን አንግቦ ከጠንካራው አንበሳ አጠገብ ቆሞ የሚታይ ሲሆን ይህም " ጋሞ " ውርስ መጠሪያ ስም አንበሳ መሆኑንና የጀግነነቱን፣ የአይበገሬነት፣ ጥንካሬውንና ታላቅነትን ያመለክታል።

አርባ ሁለቱን ደሬዎች የሚወክሉ የውኃ መፍሰሻ ( Fountain Nozel ) ቋቶችና የሚፈሰው ውኃ የጋሞ ሕዝብ እሴትና መገለጫ የሆነውን ሠላም በምድሪቱ ላይ እንደሚፈስ የሚያመላክቱ መሆናቸው ተጠቅሷል።

የጋሞ ጀግና የቆመበት ክብ አርማታ ደግፈው የቆሙት 42 ምሰሶዎች፣በቀርከሃ ቀለም የተሠሩ 42 ክብ ቢሞች መገለጫቸውም 42ቱን የጋሞ ደሬዎችን ሲሆን ደሬዎቹ ምሰሶና ማገር ሆነው የጋሞ ህዝብን በጋራ ማቆማቸውን ያሳያል።

የአንድነትና የወንድምነት ምልክት የሆነው ወፍራሙ ክብ ቢም የጋሞ ህዝብን ሁሉን የሰው ዘር በፍቅር የሚሰበስብ አቃፊ መሆኑ የሚያመለክት ሲሆን የጋሞ ህዝብ ጥበብ ሰርቶ የሚያለብስና ጥበበኝነቱን የሚያስረዳ የድንጉዛ ቀለም በዙሪያው እንዲኖርም ተደርጓል።

በተጨማሪም የጋሞ ህዝብ በተፈጥሮ የታደለ መሆኑን በእግዜር ድልድይ፣በአባያና ጫሞ የስምጥ ሸለቆ ሃይቆች የሚያመላክቱ ውሃ ሰማያዊና ቡኒ ቀለም ያሏቸው የውሃ ገንዳዎችና አረንጓዴ የለምላሜ ምልክቶች ተውበው ተቀርፀዋል።

በአባያ ሐይቅ ዙሪያ የጋሞን ባህልና ምርቶች የሚያንፀባርቁ ኩነቶች ገለጭ የሆኑ የሞዛይክ ጥበብ ስራዎች መካከል የሰላምና የእርቅ እሴት የዱቡሻ ስርአትን፣ የሽመናና የፈትል ስራ፣የጋሞ ባህላዊ ቤት፣ የፍቅር መገለጫ በሆነው በጋራ መመገብና መጠጣትን የሚያሳዩ ናቸው።

የአካባቢው የተፈጥሮ ፀጋ የሚያንፀባርቁ፣ የአትክልትና የፍራፍሬ ምርታማነትን የሚገልፁ የሙዝ፣ እንሰት፣ አፕል፣ ማንጎን ጨምሮ የድንቅ ተፈጥሮ ባለቤትም መሆኑን የሚያሳዩ እንደ ሜዳ አህያ፣ አዞ፣አሳና አዕዋፋት የተቀረፁበት ውብ የሞዛይክ ጥበብ ሥራ ተካትውበታል።

✍️ Geta Fekede
Source - GZCTD

አርባ ምንጭ
ህዳር 26/2017 ዓ/ም

 #ታላቁ ሩጫ  በአርባምንጭ በኢትዮጵያ የታላቁ ሩጫ አዘጋጆች ከሳፋሪ ኮም ጋር በመተባበር በደቡቧ ኢትዮጵያ በምትገኘው የውብ ባህልና ቱውፊት ተምሳሌት፤የድንቅ ተፈጥሮ መገኛ ፤ ብዙዎችም ጠርተ...
20/06/2024

#ታላቁ ሩጫ በአርባምንጭ

በኢትዮጵያ የታላቁ ሩጫ አዘጋጆች ከሳፋሪ ኮም ጋር በመተባበር በደቡቧ ኢትዮጵያ በምትገኘው የውብ ባህልና ቱውፊት ተምሳሌት፤የድንቅ ተፈጥሮ መገኛ ፤ ብዙዎችም ጠርተዋት ያልጠገቧት፤ በባይራዎች ምድር፤ የጋሞ መዲና ፤ህብረ ብሔራዊት ከተማ በሆነችው አርባ ምንጭ ከተማ ልዩ ድግስ አሰናድተው ጥሪ እያቀረቡ ይገኛል።

አዘጋጆቹ የ7 ኪሎ ሜትር ሩጫ ድግስ እያወደሱ በሚጠሯት አርባምንጭ ከተማ በወረሃ ሐምሌ በሰባተኛው ቀን ለማሰናዳት ወጥነው ተሳተፉልን ሲሉ ለስፖርቱ አፍቃሪያንና ቤተሰቦች ጥሪ አድርገዋል።
◌◌◌◌◌◌📢🥇🏃‍♂️🥈🏃‍♀️🥉📢◌◌◌◌◌

#በታላቁ ሩጫ 7km Run ||| 2016 ሳፋሪኮም ታላቁ የአርባ ምንጭ ሩጫን እናድምቀው
2024 Safaricom Great Arba minch run ይሳተፉ

📢 አርባ ምንጭን አርባ ጊዜ ቢዞሯት አይጠግቧትም። አብረን እንሩጥባት ያልነው በምክንያት ነው!

📢 አረንጓዴ ቀለም እና አርባ ምንጭ አይለያዩም። ተክሎቿ ሁሉ አርባ ምንጭን አረንጓዴ ቀብተዋታል። እኛም አርባ ምንጭ ስንሮጥ በይበልጥ አረንጓዴ እናድርጋት! (ቆሻሻ እናስወግድ 🗑️ ተክል እንትከል 🌳
ውበቷን እንጠብቅ) ኑ አብረን አረንጓዴ እንሩጥ!

📢 ዓይኖትን ቢጨፍኑ እና አርባ ምንጭን ቢስልዋት ምን ይመጣቦታል? ሲገልጡ ደግሞ እኛ ከሱ በላይ እናሳዮታለን!❤

📢 ከሚጠብቁት በላይ የሚጠብቆት ብዙ ነው! አርባ ምንጭ ይምጡና እንደ አዲስ እናስተዋውቆት 🎊

📢 ፅዱ መሬት🏞 ፣ ንፁህ አየር🌬 ፣ ደስ ሚል ሩጫ🏃🏼 በአርባ ምንጭ🤩 የዚህ ድንቅ ወድድር አካል ይሁኑ!

📢 አርባ ምንጭ የውሃ ምንጭ ብቻ አይደለችም። የብዙ ደስታ ምንጭ ናት! ዙሪያዋን በተፈጥሮ ተከባ እንግዶቿን ትቀበላለች! እናንተም በፈገግታ ተቀበሏት💫

📢 ታላቁ የአርባ ምንጭ ሩጫ 3 ጥቅል እንዳለው ያውቃሉ?

🎒ጥቅል 1
አርባ ምንጭ ሄደው ሩጫውን ብቻ ነው ምሮጠው ካሉ 600ብር ብቻ!🏃🏼

🎒ጥቅል 2
ለምን ሩጫው ብቻ? አርባምንጭ ሄጄ ብዙ የሚወራላትን የዶርዜን መንድር እና የሃይዞ ፏፏቴን ጎብኝቼ፣ በአስደናቂ ገጽታዋ ሃይክ አርጌ፣ ሮጩ ነው የምመለሰው ካሉ 3000ብር ይጠበቅቦታል!🏃🏼🏕🏞

🎒ጥቅል 3
ጥቅል 2 ላይ ያሉት በሙሉ ኖረው ባርቢኪው ለምን ይቅርብኝ ካሉ ደግሞ 3500ብር ይጠበቅቦታል!♨️🏕🏞 ምርጫው የእናንተ ነው!😉

📢 ስለ አርባምንጭ ይህንን ያውቁ ነበር? 🤔

አርባ ምንጭ በኢትዮጵያ ውብ ከሚባሉት ከተሞች መሀል የተመደበች ሲሆን ከባህር ጠለል 1,284 ሜትር ከፍ ብላ ትገኛለች። 🏜

ይህች ውብ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ መሮጥን ከግምት አስገብተው ነበር? 🤩🌄❤️

📢 አርባ ምንጭ እንሩጥ ካላችሁ ከግርምት ሳትነቁ ሮጣችሁ ትጨርሳላችሁ! እስቲ አብረን እንሂድ፣ወደ አርባ ምንጭ እንጓዝ 🚌

📢 አርባ ምንጭን ተቀላቅለን ሩጫችንን ይበልጥ ልናሳምረው ነው! 💫 ዝግጁ? 🎊

📢 በ2016 ሳፋሪኮም ታላቁ የአርባ ምንጭ ሩጫ ምን ምን እናደርጋለን?

✅በወብ ተፈጥሮ ተከበን ሃይክ እናረጋለን🎒🧗
✅የዶርዜ መንደርን ሄደን እንጎበኛለን⛺️
✅ሃይዞን ፏፏቴን እያየን ተፈጥሮን እናደንቃለን🌊
✅ማታ በባርቢኪው ሰዓት እንዝናና♨️

📢 ዝግጁ ነሽ? ዝግጁ ነህ? ዝግጁ ነዎት?

📢2016 ሳፋሪኮም ታላቁ የአርባ ምንጭ ሩጫን እናድምቀው

አዘጋጆቹ ነን!!

📅 እሁድ ጠዋት 07 ሐምሌ 2016
Registration link
https://forms.gle/D77iW6oZGKPdkYiv5
Contact info
+251 116 635 757

እኛም የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ይህንን ታሪካዊ ድግስ አምሮና ደምቆ እንዲሰናዳ መላውን የስፖርቱ ቤተሰቦች፣ ታዳሚዎች፤ ወዳጅና እንግዶቻችንን እንደ ጋሞ ባይራ አባቶች ባህል ለመቀበልና ለማገልገል ዝግጁ በመሆን ዕለቱን በውብ ቀለም ለመፃፍ እድሉን አግኝተናል ◌◌◌ እናመሰግናለን።

ከአካል ጉዳተኞች ማህበራት ጋር በቅርበት የሚሠራው Dires for Development የተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ጋር ለመስራት ውይይት አደረገ*********...
22/04/2024

ከአካል ጉዳተኞች ማህበራት ጋር በቅርበት የሚሠራው Dires for Development የተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ጋር ለመስራት ውይይት አደረገ
*********

መነሻውን በሀገረ ኔዘርላንድ ያደረገ Dires for Development የተሰኘው በጎ አድራጎት ማህበር " The Long Trail " የተባለ ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎትን የሚሰጥ ፕሮጀክቱ የአካል ጉዳተኞችን ማህበረሰባዊ ትስስር ለማጠናከርና የድጋፍ አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ፕሮግራም በአርባ ምንጭ ከተማ ለመስራት ከከተማው አስተዳደር ጋር መክሯል።

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት Mr. Jos Vesemann አካል ጉዳተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በየትኛው መልኩ መርዳትና በማህበረሰቡ ዘንድ የጋራ የሆኑ እሴቶችን በመጠቀም በጋራ እንዲያራምዱ ማስቻል ዋና ዓላማው መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎች ያሏት ባለፀጋ ሀገር ናት የሚሉት Mr. Jos Vesemann በድንቅ ተፈጥሮ ምህዳር፣ በባህላዊ እሴቶች፣አስተማማኝና ሰላማዊ የኑሮ መስተጋብር በደቡብ በተለይም በጋሞ ዞንና በአርባ ምንጭ መኖሩ የፕሮጀክቱ ምርጫ መሆኑን አሳውቀዋል።

አርባ ምንጭ ባላት እምቅ የቱሪዝም ሀብት በተገቢው መልኩ አልታወቀችም የሚሉት አስተባባሪው በርካታ ቱሪስቶችና አዘጋጆች በየዓመቱ የሚሳተፉበት ግዙፍ "ዓመታዊ የባህልና ሙዚቃ ፌስቲቫል" ዝግጅት በማካሄድ የከተማዋን ገፅታና ከፍታ ይበልጥ ለአለም የማስተዋወቅ ሥራ ይሰራልም ብለዋል።

አቶ ገዛኸኝ ጋሞ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ዓላማውን ገልጾ በዕቅድ ደረጃ ይዞ ላቀረበው ጥያቄ በደስታ የሚቀበሉት መሆኑን ገልፀው አስተዳደሩ አካል ጉዳተኛ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በራሱና ከተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ግለሰቦች ጋር በቅንጅት የመደገፍ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝና የትኛውም ማህበረሰብ አቀፍ ድጋፎችን እውቅና በመስጠት እንደሚያበረታታ አስታውቀዋል።

ከተማዋ ይበልጥ እንድትተዋወቅና የአለም የቱሪዝም መዳራሻ እንድትሆን የፕሮግራሙ መዘጋጀት የከተማው የቱሪስት ፍሰትን በመጨመር ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀው በቀጣይ በሚደረጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አስተዳደሩ የሚደግፈው ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ዋና ጸሃፊ አቶ አባይነህ ጎጁ በበኩላቸው ላለፉት በርካታ ዓመታት በማህበረሰብ ድጋፍ ስራዎች ሰፊ ልምድና አቅም ያለው የ Dires for Development በጎ አድራጎት ማህበር የሚመራው ፕሮጀክት አካል ጉዳተኞችን መርዳት ዓላማው አድርጎ ለጀመረው ሰፊና ዘላቂ የሥራ ዕቅድ ምስጋናቸውን አቅርበው ተፈጥሯዊና ወቅታዊ የሆነው የአካል ጉዳተኝነት የሁሉም የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ታሪካዊው "ዓመታዊ የባህልና ሙዚቃ ፌስቲቫል" ዝግጅት ተግባራዊ ሆኖ የመጀመሪያው ዙር በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

Communication ✍️

የደስታ ሁሉ ምንጭ የሆነች ከተማ - አርባ ምንጭ●○◉●○●◉○●◉○●◉○●◉○●◉○●◉○●◉እድሜ ጠገብ በሆኑ እፅዋት የታጨቀው ደኗ ዉሎ ማደር ይቻላል፣ ቁጥር የሌለው ደስታን የሚያላብሱ የ40ዎቹ...
27/02/2024

የደስታ ሁሉ ምንጭ የሆነች ከተማ - አርባ ምንጭ
●○◉●○●◉○●◉○●◉○●◉○●◉○●◉○●◉

እድሜ ጠገብ በሆኑ እፅዋት የታጨቀው ደኗ ዉሎ ማደር ይቻላል፣ ቁጥር የሌለው ደስታን የሚያላብሱ የ40ዎቹ ምንጮች መገኛ የሆነው ደን ልዩ ነው፤

አብሮ የመኖር ተምሳሌት የሆነ ሕዝብ እንግዳ ስለምትሆኑ ቆይታችሁ የደስታ ነው፤ በአባያና ጫሞ ሐይቅ ትዝናናላችሁ፤

አዞ ገበያና አዞ ራንች ስትደርሱ ሌላ ትዕይንት ይጠብቃቹሀል፣ የእግዜር ድልድይ መገኛ፣ ባለ ጥቁርና ነጭ ቀለሙን የዱር እንስሳ እንደልብ የምታዩበት የነጭ ሳር ሥነ ምህዳር ልዩ የተፈጥሮ መስህብ የእናንተ ነው፤

የግብርና ቱሪዝም ቀጠና፣ሁሉን የምታገኙባቸው ቅንጡ ሎጆችና ምቹ መዝናኛዎች ለሁሉም ማረፊያ ናቸው፤

ደግሞ ሌላ በዚህ መንደር ስትደርሱ ከሀገራችሁ ባህል ጋር ትተዋወቃላችሁ፣ ደስታው ልዩ ነው ፦ ይደመጣል፣ ይሳባል፣ ይሰማል፣ የራሳቸው የሆነ ዜማ፣የጥበብና የእውቀት መዳረሻ፤

ኩታን ከቡሉኮ ደርበው በክብር የሚለብሱባት፣ድንጉዛን ከጥበብ ለብሰው የሚደምቁባት፣ ፀብን የሚያርቅ እርጥብ ሳር የተቀደሰባት ምድር - የጋሞዎች መዲና ፤ ትንሿ ኢትዮጵያ - አርባ ምንጭ ○○○ ይጓዙ፣ ይምጡ፣ ይጎብኙ!

✍️ጌታ ፈቀደ
🎨 GetaF.

DINGUZA is a sign of Brave, kindness, Endurance,Hope and Happiness for Gamo people. Peoples are love to wear perfectly. ...
23/01/2024

DINGUZA is a sign of Brave, kindness, Endurance,Hope and Happiness for Gamo people. Peoples are love to wear perfectly. Now Africa likes Dinguza and Yoweri Museveni award the truth.

Dinguza!!!!

✍️ || Geta Fekede



📷 2016 የጥምቀት ቀን || አርባምንጭበምስል  .ephiphany .timket .tourism
20/01/2024

📷
2016 የጥምቀት ቀን || አርባምንጭ
በምስል

.ephiphany
.timket
.tourism

Address

Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when God Bridge - Arba Minch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share