Amater TV

Amater TV ነፃ መረጃ ተጨባጭ ዕውነተኛ የሆኑ ብቻ ማስተላለፍ በማንኛውም መንገድ ተጨባጭ መረጃ ካሎት ማካፈል ይችላሉ።

ልብ ይበሉ በምድራችን ላይ ብዙ አጭበርባሪዎች አሉ የዚህኛው ግን የባሰ ነው።ይሔንን የቴሌግራም ቻናል ተመልከቱት ብዙ ማጭበርበር የሰራ ቻናል ነው።ቻናሉን የተቀላቀላችሁ ከቻናሉ በመውጣት እና ...
01/01/2023

ልብ ይበሉ በምድራችን ላይ ብዙ አጭበርባሪዎች አሉ የዚህኛው ግን የባሰ ነው።
ይሔንን የቴሌግራም ቻናል ተመልከቱት ብዙ ማጭበርበር የሰራ ቻናል ነው።
ቻናሉን የተቀላቀላችሁ ከቻናሉ በመውጣት እና ሚስጥራቸውን በማጋለጥ ወገኖቻችሁን ከመጭበርበር ታደጓቸው።

አይ ወለጋ አይ ብልፅግና
04/12/2022

አይ ወለጋ አይ ብልፅግና

አጉትን ከተማ እና በአጎራባች ቀበሌዎች ያሉ ነዋሪዎች  የኦሮሚያ ልዩ ሃይልን በመፍራት ብቻ፣ህጻናት፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ሁሉ በምሽት እየተሰደዱ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውኛል። መከላከያ ሰ...
04/12/2022

አጉትን ከተማ እና በአጎራባች ቀበሌዎች ያሉ ነዋሪዎች የኦሮሚያ ልዩ ሃይልን በመፍራት ብቻ፣ህጻናት፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ሁሉ በምሽት እየተሰደዱ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውኛል። መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ገብቶ ዜጎችን ካልታደገ፣ ለሚፈሰው ደምና ለሚደርሰው ስቃይ ሁሉ መንግሥት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው።

ዶ/ር አብይ አህመድ:-

👉የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስትር ነው
👉የብልጽግና ፕሬዝዳንት ነው
👉የኦሮምያ ብልጽግና ሊ/መንበር ነው
👉የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ ነው

በየትኛውም የስልጣን አቅጣጫ ቢኬድ፣ ዶ/ር አብይ በኦሮምያ የሚካሄደውን የንጹሃ ሞት ጣልቃ ገብቶ የማስቆም ሙሉ መብትና ስልጣን አለው።

አሁን እንደ ዜጋ የምጠይቀው ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ብቻ ነው። የዜጎችን ደህንነት ከመጠበቅ በላይ ተቀዳሚ ግዴታና ሃላፊነት ደግሞ የለም።

ከአቅሙ በላይ ከሆነ ደግሞ ይህንን በአደባባይ
መናገር ነው።

እንደ ሃገር ከፍተኛ የመከላከያ አቅም በገነባንበት በዚህ ጊዜ የሚፈጽም የንጹሃን ሞት፣ በየትኛውም አመክንዮ ተቀባይነት የለውም። ይህ የግፍ ሞት እንዲቆም ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በአንድነት ድምጻችን ልናሰማ ይገባል።

Via: Fasil yenealem

04/12/2022

ተለማማጅን የተቀላቀለ ተጠቀመ

31/12/2021

አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ።

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሐገራችን በጠና ታማለች አሁን የምትፈልገው መድሐኒት የተግባር ሰው ነው።
ሐብት ያለው በሐብቱ ጉልበት ያለው በጉልበቱ ሙያ ያለው በሙያው ይደርስላት ዘንድ በጠና ትማፀናለች።

01/12/2021

ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ ይተባበሩ!!!

አስር ጥያቄዎች ለፌዴራል መንግስት ***ወደፊት ለመዝለል ወደኋላ ማፈግፈግ ያስፈልጋል!በመሰሪዎችና ዕብሪተኞች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በዘር ተመርጦ በተኛበት ከታረደ በኋላ ኢትዮጵያ ተገዳ...
07/11/2021

አስር ጥያቄዎች ለፌዴራል መንግስት
***

ወደፊት ለመዝለል ወደኋላ ማፈግፈግ ያስፈልጋል!

በመሰሪዎችና ዕብሪተኞች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በዘር ተመርጦ በተኛበት ከታረደ በኋላ ኢትዮጵያ ተገዳ ወደ ጦርነቱ የገባችበትን አንደኛ ዝክር ዓመት ስናከብር አንድና ብቸኛ ህይወታቸውን ለሃገራቸው መስዋዕት ያደረጉ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆችን ስናስብ ጦርነቱ ከተጀመረ አሁን እስከደረስንበት ድረስ ያጋጠሙንን ድሎችና ፈተናዎች ወደኋላ ሄደን መገምገም አለብን። ሶስት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ አፈር ድሜ ማስበላት የተቻለው ህውሃት ከአፈርነት ተነስቶ እንዴት አሁን ላለበት ደረጃ ደረሰ የሚለው ጥያቄ መመለስ ይገባዋል ። ይህ በዚህ ወቅት መንግስትን ለመውቀስ ፣ ለማሳጣት ወይም ነገሮችን ዝም ብለን ለታሪክ መዝገብ ለመሰነድ ሳይሆን እስካሁን ከተሰሩ ስህተቶች ተምረን ዳግም እንዳይፈፀሙ ለማድረግ እንዲቻል ነው። ለምሳሌ በእኔ እይታ መንግስት ይህን ጦርነት በአግባቡ ለመጨረስና ኢትዮጵያን በማይነቃነቅ አለት ላይ በፅኑ ለማቆም የሚከተሉትን አስር ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ አለበት።

1) ህውሃት የሰሜን ዕዝን ለማጥቃት የወሰነው ጦርነቱ ከመጀመሩ ሶስት ቀን በፊት ''ማዕከላዊ ኮሚቴ ታላቅ የሚባል ታሪካዊ ውሳኔ አሳልፏል'' ብሎ ከነገረን በኋላ ነው። ይህ ውሳኔ እንደተወሰነ ወይም ከመወሰኑ ቀደም ብሎ በወቅቱ የነበረው የመከላከያ መረጃና ደህንነት ቢሮ የማጥቃት ሃሳቡ እንደነበረ ለምን አልደረሰበትም? ደርሶበት ከሆነ ለምን ቀድሞ ወታደሩን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል ስራ አልሰራም?

2) ለጦርነቱ ህውሃት ከ150 ሺ በላይ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አሰማርቶ እንደነበር ይገመታል። ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ግን መንግስት ከተሞችን ለመቆጣጠር ባደረገው ጥረት ይህ ሃይል ምንም ሳይነካ ከነመሳሪያው ወደገጠርና ማህበረሰቡ እንዲቀላቀል ሆኗል። ይህ የሆነበት አንዱ ምክንያት መንግስት ትንሽ ሽፍታና ወንበዴ የገጠመ ይመስል አንዴ 24 ሰዓት አንዴ 72 ሰዓት እጅ እንድትሰጡ ዕድል ሰጥቻችኋለሁ እያለ ራሱን ማዘናጋቱ ነበር። ይህ ለምን ሆነ? የህወሓት የትግል ታሪክ ከገጠርና ገጠር እንደሆነ እየታወቀ ለምን ገጠሩን ትቶ ከተማው ላይ ትኩረት ማድረግ አስፈለገ? የትጥቅ ማስፈታት ስራ ለምን በእያንዳንዱ የገጠር ቀበሌ ሳይቀር በወጥነት አልተሰራም ?

3) የትግራይን ዋና ዋና ከተሞች የኢትዮጵያ መከላከያ ወታደር ከያዘ በኋላ በጊዜያዊ አስተዳዳሪነት የተሾሙት ሰዎች አብዛኞቹ በአስተሳሰባቸው ከህውሃት ያልተሻሉ እንዲያውም የሚብሱና ከህውሃት ጋር አብረው የሚሰሩ ሆነው ሳለ የደህንነት መስሪያ ቤታችን ለምን በቅርበት ክትትል አላደረገባቸውም?

4) ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ በመጀመሪያ ሶስት ወራት የህውሃት ሰዎች እንኳንስ የሳተላይት ስልክ የሚጠጡት ውሃ እንኳ እንዳልነበራቸው ከራሳቸው አፍ ሰምተናል። ታዲያ አራቱም የትግራይ መግቢያና መውጫ በሮች ዝግ ሆነው እያለ የሳተላይት ስልኮች፣ ዘመናዊ ሬዲዮ መገናኛዎች፣ ተጨማሪ ዘመናዊ መሳሪያዎችና ''የሌላ ሃገር ተዋጊ ዜጎች'' (mercenaries) እንዴትና በየት ወደትግራይ ሊገቡ ቻሉ? ማንስ አስገባቸው?

5) መከላከያ ትግራይን ከተቆጣጠረ በኋላና በህይወት የተረፉ የህወሓት ሰዎች ተምቤን በርሃ ከከተሙ በኋላ በአስር ሺዎችና መቶ ሺዎች አዲስ ሃይል አሰልጥነው ሲያስመርቁ መንግስት ምን ሲሰራ ነበር? የአየር ሃይሉና የደህንነት መዋቅሩ ተምቤን ከኢትዮጵያ ግዛት ውጪ ያለ ይመስል እንዴት ቢያንስ እየተደገሰ ያለውን ችግር ለምን ማወቅ ተሳነው?

6) በሰኔ ወር መጀመሪያ አካባቢ መንግስት መከላከያ ሰራዊቱን ከትግራይ እንዲወጣ ሲወስን ህውሃት መረጃው ወዲያው እንደደረሰውና ለመውጣት የተዘጋጀውን መከላከያ ሰራዊት ማጥቃት እንደጀመረ ሰምተናል። የመንግስትን መከላከያ ሰራዊቱን የማስወጣት ውሳኔ ለህወሓት ሲያቀብል የነበረ ማን ነው? ጊዜያዊ አስተዳደሩ ወይስ በመከላከያ ውስጥ ያለ ባንዳ? ማንነቱ ተመርምሮ ለምን ህጋዊ እርምጃ አልተወሰደም ? አሁንም የመከላከያ መረጃና ስለላ ዲፓርትመንት ምን ሲሰራ ነበር?

7) የመንግስት ሰራዊት በህውሃት ለሁለተኛ ጊዜ በሰኔ ወር ውስጥ ሳይታሰብ ጥቃት ሲፈፀምበት መንግስት ለምን የአማራና የአፋር ክልሎች ወዲያውኑ እንደአማራጭ መከታ እንዲሆኑ እንዲዘጋጁ አላደረገም ? የችግሩን አሳሳቢነት ተረድቶ አንዴ ሞቅ አንዴ ቀዝቀዝ ለማድረግ ለምን ፈለገ? በተለይ የአማራ ክልል ካለበት ልዩ ስጋትና ተጋላጭነት አንፃር መደራጀቱና መዘጋጀቱ መደገፍ ሲገባው እንደስጋት ለምን ታየ?

8 ) ህውሃት ከትግራይ ክልል ወጥቶ አማራና አፋር ክልሎችን መውረር ሲጀምር ሁለቱ ክልሎች ምንም ሳይዘጋጁ ነበር የጠበቁት። ይህ በመንግሥት እንዝላልነት እንደሆነ ግልፅ ነው። ጥያቄው ግን ህውሃት ወረራ እንደጀመረ ለምን መንግስት ሃገርአቀፍ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቶሎ አላወጀም? ለምን ሁሌ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ አይነት አካሄድ ይሄዳል ? ነገሮችን 'አይሆኑም' ከማለት ቢያንስ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ አስቦ ለሁሉም ቢሆኖች ለመዘጋጀት አልቻለም ?

9) መንግስት የዓለም አቀፍ ጫናው እንዲበረታበት ካደረጉ ነገሮች ውስጥ ዋናው ጉዳይ የኤርትራ ወታደሮች በጦርነቱ መሳተፋቸውና የሰብዓዊ መብት ጥሰት አካሂደዋል መባሉ ነው። በመጀመሪያ መንግስት የኤርትራን መግባት ሲክድ ቆይቶ በኋላ እንደገና መግባታቸውን አምኗል። ይህ ትልቅ የሆነ ያለመታመን ችግር በአለም አቀፉ ማህበረሰብና በዲፕሎማሲያዊው መድረክ ፈጥሮበታል። ለምን የኤርትራን መግባት መንግስት መካድ ፈለገ? በዓለም አቀፍ ህግ መንግስታት በአስቸጋሪ ጊዜ የወዳጅ ሃገሮችን እርዳታ የመጠየቅ መብት አላቸው። አሜሪካ እንኳ በኢራቁና አፍጋኒስታን ጦርነት የ46 ሃገራትን ርዳታና ተሳትፎ በግሃድ ጠይቃ አግኝታለች። ኢትዮጵያም የኤርትራን እርዳታ መጠይቅና ማግኘቷ መብቷ ሆኖ ሳለ ለምን በሳተላይት ዘመን የተለያና የሚጋጭ መግለጫ መስጠት አስፈለገ? (በነገራችን ላይ የመንግሰት የተምታታ ትርክት ኤርትራን በተመለከተ ብቻ ሳይሆን በብዙ ነገሮች ላይ ነው። ይህም መንግስት እምነት የማይጣልበት እንዲባል አድርጎታል )

10) ሃገሪቱ ለህልውናዋ ከሚያሰጋ ሃይል ጋር ጦርነት እያካሄደች መንግስት ለምን ሁሉ ነገርን እንደአዘቦት ለማየት ምንም እንዳልተፈጠረ ለማድረግ ሞከረ? ህዝብንና ሃገሪቱ ያላቸውን ሙሉ ሃይልና አቅም በአግባቡ ለጦርነቱ ማዘጋጀት ሲገባው ለምን ነገሮችን 'ሁሉም ሰላም ነው' አይነት መንገድ ለማየትና ሁሉም 'ከልኩ አያልፍም' አካሄድን መረጠ?!

መንግስት እኝህንና መሰል ጥያቄዎች በአግባቡ መልሶ ውስጡን አጥርቶ ከተንቀሳቀሰ እንደምንለው ኢትዮጵያ ታሸንፋለች። ያኔ (ኢትዮጵያ ስታሸንፍ ደግሞ) አላግባብ በግፍና በክህደት ለተጨፈጨፉት መከላከያ ሰራዊት አባላትና በጦርነቱ ለተሰው ሁሉም ዕንቁ የኢትዮጵያ ልጆች ትክክለኛና መስዋእትነታቸውን የሚመጥን መታሰቢያ እንደተደረገላቸው መቁጠር እንችላለን።

ድል ለኢትዮጵያ! ዘላለማዊ እረፍት እርሷን ለማቆየት አንድያ ነፍሳቸውን ለሰጡ ብርቅ ልጇቿ ይሁን !

ሸዋ ሸዋ አሸዋ የምትሆኝበት ቀኑ ደርሷል  ከበርሽ ላይ ነው፡፡የአዲስ አበባ መከራና ሰቆቃ ከ---- በኀላ ይጀመራል፡፡(መቼ እንደሆነ አልናገርም) ያኔ ምድር ትንቀጠቀጣለች፡፡እንደ ምጻት ትገለ...
04/11/2021

ሸዋ ሸዋ አሸዋ የምትሆኝበት ቀኑ ደርሷል ከበርሽ ላይ ነው፡፡የአዲስ አበባ መከራና ሰቆቃ ከ---- በኀላ ይጀመራል፡፡(መቼ እንደሆነ አልናገርም) ያኔ ምድር ትንቀጠቀጣለች፡፡እንደ ምጻት ትገለባበጣለች፡፡የሸዋ ምድር ኡኡታ የመከራ ቀንበር ፤ሰቆቃ ይወርዳል በማን አቅም ይቻል ይሆን? እንጃ!! አምላከ ቅዱሳን አንተ እወቀው በምንም ቃል መግለጽ አይቻልም መከራው ከባድ ነው፡፡ ሚያዝያ 7/8/2013 ዓም ከተጻፈው
ከአባ አምሃ ኢየሱስ ገ/ዮሐንስ ድንገተኛ የማስጠንቀቂያ መልእክት አምስት ገጽ
💚💛❤️💚💛❤️💚❤️💚💛❤️
ከአባ አምሃ ኢየሱስ ገ/ ዮሐንስ መደበኛም ሆነ ድንገተኛ መልእክት እንደ ተረዳነው ፡፡ መከራው የሚጀምርበትና የሚያበቃበት ወሩም ሆነ ቀኑ ሰአቱም ሆነ ሴኮንዱ ፡፡በእግዚአብሔር እና በቅዱሳን ልጆቹ ዘንድ የታወቀ እና የተወሰነ፡መሆኑን ነው፡፡እግዚአብሔር ከወሰነው ደግሞ ምንም ፈቀቅ የሚል ነገር የለም፡፡የመከራው ጊዜ መድረሱን ደግሞ መረዳት ያለብን በእውነተኞች እና በሐሰተኞቹ ወይም በእግዚአብሔር ልጆችና በዲያብሎስ ልጆች መካከል ያለው ውጊያ እና ፍልሚያ በተለይ በተለይ ከሐምሌ አምስት በኀላ የበለጠ እየጠነከረ መምጣቱ አንድ ምስክር ነው እና ሁላችንም በጥቃቄ በማስዋል እግዚአብሔር በመፍራት የበለጠ እውነትን በልባችን ውስጥ በማንገስ እምነትን ጋሻ በማድረግ በንስሐ ሕይወት በመላለስ በጾም በጸሎት በአጠቃላይ በበጎ ስራ በመትጋት፡፡የልዑልና የድንግል ወታደሮች በመሆን፡፡መልእክታቱን ፤ ደብዳቤዎችን ፤ ተምህርቶችን ፤መግለጫዎችን እና ማሳሰቢያዎችን እንዲሁም ምክሮችን ዘወትር በማዳመጥ ማስረጽ ጠላት በሐሰት ሲከሰን በመልእክቱ ያልተባለውን ተባለ ሲል የቱ ላይ በማለት ጠላትን በብቃት እንድንዋጋ የጦር መሳሪያዎችቻን ናቸውና
እንጠቀምባቸው፡፡እግዚአብሔር አምላክ ሁላችንንም በእናቱና በቅዱሳኑ ጸሎትና ምልጃ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን፡፡

27/10/2021

ደባርቅ ያችን ሰዓት...
🔥
....ማንም ሰው ከተማውን ለቆ መሄድ ይችላል! እኛ ግን በደምና በአጥንታችን ከተማችንን በአሸባሪው ትህነግ ሳናስደፍር እንደምናተርፋት አንጠራጠርም! የአሰላለፍ ስምሪት እንደሚከተለው ነው...የወጣቱን አሰላለፍ በዝርዝር አቀረቡ!.... እ... እ... እ... ማንም ሰው ልብ አድርጉ ማንም ሰው ባለሥልጣንን ጨምሮ ከከተማዋ እንዳይወጣ እነ እከሌ ጎንደር በር ላይ ኬላ ጥላችሁ ጥብቅ ፍተሻ አድርጉ....

ከፊቱ እልኸ ይታያል! አይኑ ድልዝ በርበሬ መስሏል... እ...እ.. እና የመጨረሻ የምነግራችሁ አባቶቻችን በትውልድ ቅብብሎሽ እዚህ ያደረሷትን ከተማ ጥላችሁ ወደ ዬትም አትሂዱ... እዚሁ በጋራ እንሙት (ድምጹ ሞቀ!!) ሰማችሁ ወይ? አለ አሁንም አይኑን አጉረጥርጦ... ሰምተናል አለ የሀገሬው ኮበሌ... ጦሩን፣ ገጀራውን፣ ፈራዱን፣ አንካሴውን፣ እያጋጨ... ሰምተናል!! አለን... አለን... አለን... በእውነት እኔ እንደዚች ቀን ሰውነቴ በሐሴት ሲርድ አላስታውስም!!

ተናጋሪው ቀጥሏል... የደም ስሩ በግምባሩ ላይ ተረተር ሰርቷል! የጦር ሜዳ መነጽሩ ደረቱ ላይ ይታያል... ሙሉ ትጥቅ በወገቡ ላይ አስሯል... ክላሽንኮቩን ሻጥ አድርጓል! በሙሉ ወታደራዊ ልብሱ ቁመናው ይማርካል! እውነት እውነት እላችኋለሁ ግርማው ያስፈራል... እና ከተማችሁን ለቃችሁ አትሂዱ! ግን አለ... ድምጹ ጨመረ.... ግን ዛሬ ከተማው ስትሻው ጥሏት የሄደ ሰው ነገ እኛ ልጆቿ በደምና በአጥንታችን ከተማችንን በአሸባሪው ትህነግ ሳናስደፍር ካተረፍናት በኋላ ሀብት ንብረት አለኝ ብሎ ተመልሶ አይመጣም.... ቅልጥ ያለ ጩኸት... ጭብጨባ... እልልታ... የመሳሪያ ሁካታ... የራስ ውብነህ አሞራው ልጆች ፉከራ... ሽለላ.... ኦህህህህ....

ይህ ሰው ይህ ጀግና የደባርቅ ከተማ ከንቲባ የወንዶች ቁና ሰለሞን ተዘራ ነው!! ያልተዘመረለት እንዲወመርለትም የማይሻ ልበ ሙሉው ጀግና ግንባረ ኮስታራው ግንባራ መራራው ሰለሞን ተዘራ...

ሰሌ እኛ ጀግንነትህን በአካል ያየን ወንድሞችህ በዘመናችን ሙሉ እናከብርሃለን‼️

Address

Asella

Telephone

+251901539393

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amater TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amater TV:

Share