ኑርሁሴን አህመድ - Nurhussen Ahmed

ኑርሁሴን አህመድ - Nurhussen Ahmed Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኑርሁሴን አህመድ - Nurhussen Ahmed, Market Research Consultant, Awash.

✩▃▂▁ታሪክን የኋሊት፤ መስከረም 𝟐/𝟏𝟗𝟔𝟕▁▂▃✩(ያለ ምንም ደም ዘውዳዊው ስርዓት የተገረሰሰበትና ሰለሞናዊው ስርወ-መንግስት የወደቀበት አብዮታዊ እለት) ==========መስከረም 2 የአዲሱ...
12/09/2024

✩▃▂▁ታሪክን የኋሊት፤ መስከረም 𝟐/𝟏𝟗𝟔𝟕▁▂▃✩
(ያለ ምንም ደም ዘውዳዊው ስርዓት የተገረሰሰበትና ሰለሞናዊው ስርወ-መንግስት የወደቀበት አብዮታዊ እለት)
==========
መስከረም 2 የአዲሱ ዓመት ሁለተኛ ቀን ከመሆኑም ባሻገር፤ ከመስከረም 1 ቀጥሎ የምትገኝ ከመሆኑም አልፎ በተለየ ታሪካዊ ክስተት በኢትዮጵያውያን ዘንድ የምትታወስ ታሪካዊ እለት ነች። ታሪካችንን ታክከን ግማሽ ክፍለ ዘመን በታሪክ የኋሊት ተጉዘን ልክ የዛሬ 50 ዓመት መስከረም 2 ቀን 1967 ላይ ስንደርስ የዚች ታሪካዊ እለት እንቆቅልሽ ሁነኛ ፍቺን እናገኘዋለን።

ከዛሬ ተነስተን በርረን መስከረም 2/1967 ዓ.ም. ላይ ለማረፍ ታድያ ሠኔ 21 ቀን 1966 ዓ.ም. ላይ መሬት ይዘን ለመንደርደር የታሪካዊ ክስተቱ እውነታ ያስገድደናል።
✩✩✩

ሠኔ 21 ቀን 1966 ዓ.ም. በአዲስ አበባ 4ተኛ ክፍለ-ጦር ግቢ በተካሄደ ስብሰባ "የጦር ኃይሎች፣ የክብር ዘበኛ፣ የፖሊስ ሠራዊትና የብሔራዊ ጦር አስተባባሪ ኮሚቴ" በኋላም “ደርግ” በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ኮሚቴ በ107 አባላት ተመሠረተ።

"ኢትዮጽያ ትቅደም፣ አቆርቋዧ ይውደም" በሚል መርህ የተነሳው ይህ ኮሚቴም ንጉሱን ለማውረድ የፈጀበት ጊዜ ሶስት ወራት እንኳን የሚሞላ አልነበረም። ሌ/ኮሎኔል ፍስሐ ደስታ በአብዮቱና ትዝታዬ መጽሐፋቸው እንደገለጹት "ደርግ ንጉሱን ለማውረድ ከሰኔ 21፣ 1966 እስከ መስከረም 1፣ 1967 ድረስ 56 ቀናት ያህል ወስዶበታል።"
✩✩✩

መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሠዓት ንጉሰ ነገስቱ በልዑል ራስ እምሩ ኃይለስላሴ እና በልዕልት ተናኘወርቅ ልጅ ኮሞዶር እስክንድር ደስታ ታጅበው በዙፋናቸው ላይ ተቀምጠዋል። በሻለቃ ደበላ ዲንሳ የተመራው 9 አባላት ያለው የደርግ ልዑካን ቡድንም ግራና ቀኝ በሰልፍ ቆመዋል።

ሻለቃ ደበላ ዲንሳ ደርግ ያዘጋጀውን ንጉሱን ከስልጣን የሚያወርደውን አዋጅ በንጉሱ ፊት ለፊት ቆመው አነበቡላቸው … ‹‹ … ለሀገርና ለህዝብ ደህንነት ሲባል በዛሬው ዕለት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከስልጣን ወርደዋል፤ …›› የሚል ይዘት ያለው ነበረ።

ንጉሱም በሻለቃ ደበላ ላይ ያተኮረ አይናቸውን ሳይነቅሉ ‹‹… የእኛ አስተዳዳሪነት መወገድ ለሀረርና ለሕዝብ ይጠቅማል ከተባለ የተነብበውን ተቀብለናል …›› በማለት በለሆሳስ ተናገሩ። ደርግ የላከው ቡድንም ንጉሰ ነገስቱን ከስልጣን መውረዳቸውን አሳውቆ በአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ ተዘጋጀላቸው ማሪፊያ በቮልስ ዋገን ጭኖ ወሰዷቸው።

በቅርቡ ለገበያ በበቃው የይታገሱ ጌትነት መንግስቱ ኃ/ማርያም የስደተኛው መሪ ትረካዎች በተሰኘው መጽሀፍ እንደገለጹት ... ‹‹ … 1967 ንጉሱን ከዙፋናቸው ለማውረድ መስከረም 1 ወስነን መስከረም 2 ቀን አነሳናቸው። እውነቱን ለመናገር ምንም መከታ አልነበራቸውም፤ ምንም ሕዝባዊ ወገን አልነበራቸውም። ... እንደዚያ አንበሳ የነበሩት አጼ ኃይለስላሴ ምንም ነገር በማያደርጉበት ሁኔታ ነበር ቤተ መንግስታቸው ተቀምጠው ያሉት። እኛም ምንም ነገር ለማድረግ የተሳነን ነገር የለም። … የገጠመን ተገዳዳሪ የለም።›› (ከገጽ 55-56)

በመጨረሻም መስከረም 2 ቀን 1967 ደርግ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴን ከስልጣናቸው በማውረድ ‘ጊዜያዊ አስተዳደር ደርግ’ በሚል ስያሜ መንበረ ስልጣኑን ጨበጠ። ኢትዮጵያን ለሦስት ሺ ዘመናት እየተፈራረቀ ይመራት የነበረው ሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትም ያለ ምንም ደም ውድቀቱ እውን ሆነ።
✩✩✩መልካም አዲስ ዓመት✩✩✩

ኑርሁሴን አህመድ - Nurhussen Ahmed
መስከረም 2 ቀን 2017
✩✩✩
ዋቢ መጽሀፍት፦
ይታገሱ ጌትነት ገበየሁ፤ የስደተኛው መሪ ትረካዎች፣ ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም፤ ትግላችን ቅፅ አንድ፣ ገስጥ ተጫኔ (ዘነበ ፈለቀ)፣ ነበር ክፍል አንድ፣ እና የሌ/ኮሎኔል ፍስሐ ደስታ፤ አብዮቱና ትዝታዬ

24/03/2023
የአፋር ክልል LLRP ስትሪንግ ኮሚቴ የ2015 የፕሮጀክቱን እቅድና በጀት አጽድቋል፤የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP) ስትሪንግ ኮሚ...
01/10/2022

የአፋር ክልል LLRP ስትሪንግ ኮሚቴ የ2015 የፕሮጀክቱን እቅድና በጀት አጽድቋል፤

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP) ስትሪንግ ኮሚቴ መስከረም 19/2015 በሠመራ ከተማ ባካሄደው ስብሰባ የአፋር ክልል የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP) የ2015 በጀት ዓመት የስራ እቅድና በጀት ላይ በስፋት ተወያይቶ አጽድቋል።

በተጨማሪም የአፋር ክልል የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP) መዋቅር ቀደም ሲል ከነበረበት የእንሰሳት እርሻና ተፈጥሮ ኃብት ልማት ቢሮ ወደ አፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በመዘዋወር በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ስር ሆኖ እንዲቀጥል ስትሪንግ ኮሚቴው አጽድቋል።

መስከረም 21/2015
https://www.facebook.com/AfarLLRP/

ማዴንጎ አፈወርቅ መንግስቱ (ከ1970 - 2015)--------------------------------------------ሙዚቃ የአፍ መፍቻ ያክል ለእሱ ህይወት ቅርብ እንደሆነች ይነገርለታል። ...
29/09/2022

ማዴንጎ አፈወርቅ መንግስቱ (ከ1970 - 2015)
--------------------------------------------
ሙዚቃ የአፍ መፍቻ ያክል ለእሱ ህይወት ቅርብ እንደሆነች ይነገርለታል። ገና በልጅነቱ ነበር የሙዚቃ ፍቅር በውስጡ ያደረበት። በ1982 የ12 ዓመት ህጻን እያለ የ4ኛ ሜካናይዝድ ባህል ቡድን ሲቪል ሙዚቀኛ በመሆን ተቀጥሮ ስራ እንደጀመረ ይናገራል። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ሙዚቃ የእሱ የመንፈስ ምግብ ብቻ ሳትሆን እንጀራውም ጭምር ሆናለች።

በልጅነቱ በተለያዩ መድረኮች የኤፍሬም ታምሩን፣ አረጋኸኝ ወራሽ፣ ጸጋዬ እሸቱ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ፣ ይሁኔ በላይና የመሳሰሉ ድምጻዊያኖች ስራዎችንና የሴት ድምጻዊያኖችን ሙዚቃ ሳይቀር አስመስሎ ያዜም እንደ ነበር በአንድ ወቅት በሰይፉ ሾው ላይ ቀርቦ ተናግሯል።

በ1983 መጨረሻ አካባቢ በባህርዳር መብራት ሆቴል በነበረ አንድ የሠርግ ፕሮግራም የይሁኔ በላይና የኤፍሬም ታምሩን ሙዚቃ በተከታታይ ሲጫወት የተመለከቱት ሁሉ ይህ ህጻን ነገ የት እንደሚደርስ መገመት አላዳገታቸውም ነበር።

ማዴንጎ አፈወርቅ በ1990ዎቹ በአገራችን የሙዚቃ ኢንደትሪ ክስተት ከሆኑ ተወዳጅ ወጣት ድምጻዊያን በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ነው።

ማዴንጎ አፈወርቅ መንግስቱ ከአባቱ አቶ አፈወርቅ መንግስቱ እና ከእናቱ ወ/ሮ ሀገርነሽ ዋሴ ሚያዚያ 10 ቀን 1970 በጎንደር ክ/ሀገር አዘዞ ከተማ ተወለደ። በኋላም ላይ ከቤተሰቡ ጋር ወደ ደብረታቦር ከተማ ተዛውሮ እዛው ማደጉን ግለ-ታሪኩ ያስረዳል።

ማንዴንጎ በ1989 ከሁለት ጓደኞቹ ጋራ በአንድ በመሆን በኮሌክሽን አልበም ያውጣ ቢሆንም ብዙም ተደማጭ አልነበረም። በህዝብ ዘንድ ተደማጭነት ያተፈበትን የመጀመሪያ አልበሙን በ1991 ለህዝብ ጆሮ ማብቃት ችሏል። በዚህ አልበም ውስጥ ከተካተቱ ሙዚቃዎች መካከልም 'ስያሜ አጣሁላት' እና 'አማን ነው ወይ ጎራው' የተሰኙት ሙዚቃዎቹ ይበልጥ ከህዝቡ ጋር አንዲተዋወቅ አድርገውታል።

ቴዲ አፍሮን ጨምሮ ይልማ ገ/አብና የመሳሰሉ የግጥምና ዜማ ደራሲዎች የተሳተፉበት "አይደረግም" የተሰኘው በ1997 የተለቀቀው ሁለተኛ የሙዚቃ አልበሙ 'ማዴንጎ አፈወርቅ' የሚለው ስም በአገራችን የሙዚቃ ኢንደስትሪ በደማቅ ብዕር እንዲጻፍ ያስቻለ ነበር።

በዚህ አልበሙ ውስጥ ከተካተቱ ሙዚቃዎች መካከልም የአልበሙ መጠሪያ የሆነው 'አይደረግም' ጨምሮ ከተለያየን፣ ነይ የአፋሯ ወጣት፣ ሞኙ ልቤ እና ትዝታ ዜማዎቹ ይበልጥ የአድማጭን ቀልብ በመግዛት አድናቆትን እንዲያገኝ አስችለውታል።

የማዴንጎ ሶስተኛና የመጨረሻ አልበም የወጣው ከዛሬ 7 ዓመት በፊት በ2007 መጨረሻ ላይ ነበር። 'ስወድላት' የተሰኘው ይህ አልበሙ ማዴንጎን የእውቅና ማማ እንዲቆናጠጥ አድርጎታል።

ማዴንጎ በዚች አጭር እድሜው በሙዚቃው ስለ አገር አድነት አቀንቅኗል፤ በተለያዩ ግንባሮችም በመሄድ የአገር መከላከያ ሠራዊትን የማነቃቃት ስራዎችን ሰርቷል። በወታደር ቤት ከማደጉ ጋር ተያይዞ በዲሲፕሊን የታነጸ መሆኑን የሚናገረው ማዴንጎ በማይታዩት በበጎ ስራዎቹ ለበርካታ ዜጎች ድጋፍ በማድረግ ደርሷል። በርካታ ጀማሪ ሙዚቀኞች መድረክ እንዲያገኙ ብዙ ድጋፍ ያደርግ እንደነበርም ይነገርለታል።

ማዴንጎ አራተኛ አልበሙን በማዘጋጀት ላይ እያለ ለሁላችንም የማይቀረው ሞት ቀድሞታል። መስከረም 17/2015 ማዴንጎ አፈወርቅ በ44 ዓመቱ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ማዴንጎ የ17 ዓመት እድሜ ያላት የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበር።

ለማዴንጎ ቤተሰቦች፣ የስራ ባልደረባዎች፣ ወዳጆችና አድናቂዎች መጽናናትን እመኛለሁ።

ኑርሁሴን አህመድ - Nurhussen Ahmed
መስከረም 18/2015

13/09/2022

የአንተ ድክመት ለሌላ ሠው ድክመት መሙያና ማካካሻ ሲሆን ከማየት በላይ ህመም የለም። የአንተን ህመም ለእሱ ዝንተ-ዓለም አይሽሬ በሽታው ማስታገሻና ፈውስ እየተጠቀመበት የአንተንም የፈውስ ዘመን በዛው ልክ ያርቅበሃል።

ከሚያፈሰው ሽንቁር በርሜልህ ላይ የእሱን ባዶ ጀሪካን ደቅኖ ሊሞላ ቀን ከሌት ይባዝናል። በአንተ ሽንቁር ጀሪካኑን መሙላቱስ ይሁን በምጽዋት ይያዝልኝ ብለህ ታልፈው ይሆናል። ሽንቁሩን አይተህ እንዳትደፍነው ከእይታ እንዲሰወር ማድረጉን ግን አንተ ችለህ ብታልፈው እንኳን ፈጣሪ አይምረውም።

ለማንኛውም ወንድሜ ያንተ በሽታ የራስህ እንጂ በሌላው ህመም የሚፈወስ አይደለም። ከቻልክ ቻለው፤ ካልቻልክ ግን የአንተ በሽታ ላይድን፤ የሌሎች ህመም ከአንተ ውቅያኖስ በሽታህ የጠብታ ያክል እንኳን ላይቀንስልህና ላይካፈልህ በከንቱ ኃጥያትህን በማብዛት አትድከም።

አህያውን እንዲህ ያንደላቀቀው አንበሳው ያለበት ሁኔታ ነው። የአንበሳው ያለበት ሁኔታ የተቀየረ ቀን ግን አህያውን አያርገኝ።

(ይህን ጽሁፍ ያነበበ ሁሉ በተሰማው መንገድ ትርጉም የመስጠት መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ማንኛውም አንባቢ ግን የፀሀፊውን ትርጉም የመንካት መብት የለውም።)

የፌስቡክ ፔጄን ላይክ ያድርጉ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063918061583

Market Research Consultant

"ኢትዮጽያ ትቅደም፣ አቆርቋዧ ይውደም" ደርግ"አሁን ተራው የእኛ ነው ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ" ቀዳማዊ ዐፄ ኃ/ስላሴ (መስከረም 2 ቀን1967)*********መስከረም 2 በአገራችን አበይት ...
12/09/2022

"ኢትዮጽያ ትቅደም፣ አቆርቋዧ ይውደም" ደርግ
"አሁን ተራው የእኛ ነው ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ" ቀዳማዊ ዐፄ ኃ/ስላሴ (መስከረም 2 ቀን1967)
*********
መስከረም 2 በአገራችን አበይት የታሪክ ክስተቶችን ካስተናገዱ ቀናት በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች። የዛሬ 48 ዓመት መስከረም 2 ቀን 1967 የደርግ መንግስት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴን ከስልጣናቸው በማውረድ የአገሪቱን የመሪነት ምርኩዝ የጨበጠባትና የ17 ዓመት የስልጣን ጉዞ ችቦ የለኮሰባት ታሪካዊ እለት ነች። የደርግ መንግስት 'ሀ' የሠለሞናዊው ስርወ-መንግስት ደግሞ 'ፖ' ሆና በአገራችን የታሪክ መዝገብ ሰፍራለች - መስከረም 2።

ሠኔ 21 ቀን 1966
***
የመስከረም 2 ታሪካዊነት ጥንስስ ከእለቱ ሶስት ወራት አካባቢ ቀደም ብሎ በሠኔ ወር 1966 ይጀምራል። በአገሪቱ አራቱም አቅጣጫዎች የሚገኙ ከተራ ወታደር እስከ ሻለቃ ማእረግ ድረስ ያላቸው የጦር ኃይሎች፣ የፖሊስ ሠራዊትና የብሔራዊ ጦር አባላት የተወከሉ 107 አባላት ሠኔ 21 ቀን 1966 በአዲስአበባ 4ተኛ ክፍለ ጦር ባካሄዱት ስብሰባ "የጦር ኃይሎች፣የክብር ዘበኛ፣ የፖሊስ ሠራዊትና የብሔራዊ ጦር አስተባባሪ ኮሚቴ"ን መሠረቱ።

በወቅቱም ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማርያምን ሊቀመንበር፣ ለኮሚቴው ምስረታ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳበረከቱ የሚነገርላቸው ሻለቃ አጥናፉ አባተን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር እንደሁም ሻለቃ ገ/የስ ወ/ሀናን ጸሐፊ በማድረግ መረጡ።

መስከረም 2 ቀን 1967
***
"ኢትዮጽያ ትቅደም፣ አቆርቋዧ ይውደም" በሚል መርህ የተነሳው ኮሚቴም ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያደርገው ንቅናቄ ውጤት አፍርቶ ሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መስከረም 2 ቀን 1967 ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴን ከስልጣናቸው በማውረድ ጊዜያዊ አስተዳደር ደርግ በሚል ስያሜ አገሪቱን ማስተዳደር ጀመረ።

በመጨረሻም በእለቱ ቀዳማዊ ዐፄ ኃ/ስላሴ በቀጥታ ስርጭት በተላለፈ የመጨረሻ ንግግራቸው "አሁን ተራው የእኛ ነው ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ" በማለት መዕክታቸውን በማስተላለፍ ስልጣናቸውን ለተረኛው ደርግ አስረከቡ። ኢትዮጵያን ለሦስት ሺ ዘመናት እየተፈራረቀ ይመራት የነበረው ሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የስልጣን ጉዞም በዚሁ እለት አከተመ።

ግንቦት 20 ቀን 1983
***
ደርግ ከመስከረም 2 ቀን 1967 ጀምሮ በወያኔ መራሹ የኢህአዴግ ሠራዊት ስልጣኑን እስከተቀማበት ግንቦት 20 ቀን 1983 ድረስም ሀገሪቱን ለ17 ዓመታት ሲመራ ቆይቷል።
***
የአገራችንን ሠላም ያርግልን! መልካም አዲስ ዓመት በድጋሚ!
መስከረም 2/2015
Nurhussen Ahmed Mohammed (NAM)

🌻የአዲስ ዓመት ወግ🌻የመስከረም ወር ሲጀምር በክረምት ደመና፣ ዝናብ፣ ጭጋግና ውርጭ የጠቆረው ሰማይ ጥርት ይላል። ጸሐይም ያለምን ከልካይ ሙሉ ሃይሏን በማድረስ ምድር ወደ ብርሃማነት ትቀየራለ...
11/09/2022

🌻የአዲስ ዓመት ወግ🌻

የመስከረም ወር ሲጀምር በክረምት ደመና፣ ዝናብ፣ ጭጋግና ውርጭ የጠቆረው ሰማይ ጥርት ይላል። ጸሐይም ያለምን ከልካይ ሙሉ ሃይሏን በማድረስ ምድር ወደ ብርሃማነት ትቀየራለች። ተራራው፣ ሜዳና ሸንተረሩ በአደይ አበባ ፍካትና ልምላሜ ይደምቃል። መስከረም ደመና የለበሠው ሠማይ ወደ ብርሃናማነት የሚቀየርበትና በሠዎችም ዘንድ የአዲስ ተስፋ ፍንጣቂ የሚታይበት ወር ነው።

ኢትዮጵያውያን መስከረም 1 አዲሱን ዓመት የምንጀምርበት ከሌሎቹ የአለም አገራት የተለየ የዘመን ቀመር አለን። የአገራችን መንግስት ግን ከህዝቡ/ከዜጎቹ የቀደመ መሆኑን ለማሳየት ይመስላል፤ አዲሱን አመት ሐምሌ 1 ነው የሚጀምረው። በሌሎቹ የአለም አገራት ግን የዜጎችም የመንግስትም የዘመን አቆጣጠር አንድ ነው። ጃንዋሪ 01 የሁሉም አዲሱን ዓመት አንድ ላይ ይጀምራሉ። ይሄም ሌላኛው ከሌሎቹ ለየት የሚያደርገን የዘመን አቆጣጠር ነው (ያው መለየት ከተባለ)።

አዲስ አመት በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች በተለያየ መልኩ ይከበራል። በአንዳንድ አካባቢዎች መስከረም 1 የአገሬው ሠው በአንድ ላይ በጠዋት በዙሪያው በሚገኝ ወንዝ ወርዶ ያለፈውን ዓመት አዳፋውን ገላውን በመታጠብ ያራግፋል። አዲስ ልብስ ለብሶ በነጭ የአገር ባህል ልብስ ደምቆ አዲሱን ዓመት የሚቀበለውም ብዙ ነው።

አዲስ ዓመት ሲመጣ አንድ የልጅነት ጓደኛዬ ትውስ ይለኛል። ይህ ጓደኛዬ 'አዲሱን አመት ተኝተን መቀበል የልብንም' የሚል ፍልስፍና አለው። በዚህም ምክንያት ሌሊቱን ሙሉ በቴሌቭዥን የሚተላለፉ የበዓል ዝግጅቶችን እያየን እንድናነጋ ያደርጋል።

ቀደም ባሉት ዓመታት ከሸራተን አዲስ፣ ከሂልተን፣ ከስቴድየም፣ ከሚሊኒየም አዳራሽና ከመሳሰሉት በወቅቱ አንድዬ በሆነው ETV በቀጥታ ስርጭት ይተላለፍ ነበር። በእነ ሠራዊትና ሙሉአለም፣ ጥላሁን እልፍነህና የመሳሰሉ የመድረክ አጋፋሪዎች የሚመሩ አስቴር፣ ሀመልማል፣ ኤፍሬም፣ ቴዲ አፍሮ፣ ጎሳዬ፣ ታምራት፣ የመሳሰሉ የ90ዎቹ እንቁዎች ሙዚቃ ታጅቦ በእነ ደረጀና ሀብቴ፣ ተስፋዬ ካሳና ዋነሶች የመሳሰሉ ኮሜዲያኖች ቀልድ እየተዋዙ የሚቀርበው የቀጥታ ስርጭት እንቅልፍ የሚባል በአይን እንዳይዞር ያደርግ ነበርና መምሸቱን ሳናስብ ይነጋ ነበር።

አሁን ላይ ይሄ ጓደኛዬ በዚህ ፍስፍናው ጸንቶ ይቀጥል፣ ይተወው ባላውቅም እኔ ግን አዲስ አመት በመጣ ቁጥር በዋዜማው ሌሊቱን ሙሉ ቴሌቭዥን መስኮት ላይ ተተክዬ ማሳለፍ ልምድ ሆኖብኝ ቀጥሏል። አንድም የሚረባ ፕሮግራም እንኳን በሌለበት 20 እና 30 ቻናል በመቀያየር መቀበሉን አሁንም ቀጥዬበታለሁ።

ድሮ ድሮ ከአዲስ ዓመት ይልቅ የዋዜማው ሌሊት ዝግጅት ነበር የሚናፍቀን። የሸራተንን ርችት ከሌሊቱ 6 ሠዓት በቀጥታ ስርጭት መመልከት ልዩ ስሜት ነበረው። ከአስር እስከ አንድ ይቆጠርና አዲሱ አመት ገባ እንኳን አደረሳችሁ! የሚለው የመልካም ምኞት መግለጫ ከሀመልማል አባተ ዜማ ጋር ታጅቦ በቀጥታ ሲቀርብ ያለውን ስሜት አትጠይቁኝ። ዛሬ ግን ይሄ ሁሉ የለም። አይ ዘመን! እኛም በእኛ ዘመን ለማለት በቃን። አልሃምዱሊላህ።

ለማንኛውም ለሁላችሁም እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2015 በሠላም አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ። 2015 ለሁላችንም የከፍታ፣ የእድገት፣ የብልጽግና፣ የፍቅር፣ ሠላም፣ የአንድነትና የስኬት ይሁንልን።

አገራችንን ሠላም ያርግንል
ቸር ያሰማን!
🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ኑርሁሴን አህመድ - Nurhussen Ahmed (NAM)
መስከረም 01/2015

እንኳን ለ2015 አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ!አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የብልጽግና ይሁንልን!!!!!🌼🌼🌼🌻🌻🌻🌼🌼 🌼🌻🌻🌻🌼🌼🌼
11/09/2022

እንኳን ለ2015 አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ!
አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የብልጽግና ይሁንልን!!!!!
🌼🌼🌼🌻🌻🌻🌼🌼 🌼🌻🌻🌻🌼🌼🌼

"Why Nations Fail" የተሰኘው መጽሀፍ Daron Acemoglu እና James A. Robinson በሚባሉ ታዋቂና ዝነኛ ኢኮኖሚስቶች በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር በ2012 የተጻፈ ድንቅ መ...
09/09/2022

"Why Nations Fail" የተሰኘው መጽሀፍ Daron Acemoglu እና James A. Robinson በሚባሉ ታዋቂና ዝነኛ ኢኮኖሚስቶች በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር በ2012 የተጻፈ ድንቅ መጽሃፍ ነው።

ከቀናት በፊት ስለዚህ መጽሃፉ አንድ የፌስቡክ ጓደኛዬ ያሰፈረውን ጽሁፍ ከተመለከትኩ በኋላ ከዚህ ቀደም ጀምሬ ያስቀመጥኩን መጽሃፍ ከሼልፍ አውርጄ ድጋሚ ማንበብ ቀጠልኩ። መጽሃፉ የአገራትን የብልጽግና እና ድህነት ምንጮች ከአለም አገራት ነባራዊ ሁኔታና እውነታ ጋር በማዛመድ ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

መጽሃፉ ከመነሻው እንደ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን እና ጃፓን የመሳሰሉ የምዕራብ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ አገራት ለምን የበለጸጉ አገራት ተባሉ? ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራት፣ የደቡብ አሜሪካና ደቡብ ኤዥያ አገራትስ ለምን ድሃ ሆኑ? ከሚል ጥያቄ ይነሳል። እነዚህ የአለም አገራት ልዩነቶች የተፈጠሩት እውነት ባላቸው የመልከዓ-ምድር፣ የአየር-ሁኔታ፣ ባህል፣ እምነት እና እውቀት ልዩነት ነውን? ሲል ጥያቄውን ይቀጥላል። በመቀጠልም ምዕራባውያን ደሃ ከሚባሉ አገራት የተሻለ የማሰብ ችሎታና እውቀት ስላላቸው ወይስ ብልህ /Intelligent ሰለሆኑ? ሲል ይጠይቃል።

ጥያቄዎቹን ተከትሎም ተመሳሳይ ጂኦግራፊ፣ ባህል፣ እምነትና ማሰብ ችሎታ ያላቸው አገራት በመካከላቸው ያለውን የእድገት፣ ብልጽግና እና ድህነት ልዩነቶችን እያነሳ ይሞግታል። ከመልከዓ-ምድር፣ ከአየር ሁኔታ፣ ባህል፣ እምነትና ማሰብ ችሎታ በተለየ የአገራት እድገትና ብልጽግና ጋሬጣ የሆኑ ጉዳዮችን በስፋት ይዳስሳል። መጽሃፉ ለዘመናት ምላሽ ለታጣለት በተመሳሳይ አገራት መካከል የሚታየውን የኢኮኖሚ እድገትና ብልጽግና ልዩቶች ሚስጥር ከንድፈ-ሃሳብ በዘለለ የአለም አገራት አሁን ካሉበት ነባራዊ ሁኔታዎች በተቀዱ እውነታዎችና ምሳሌዎች በማስደገፍ መፍታት አስችሏል።

አንድ በሆነችው ኖጋሌስ ያሉ ሁለት ከተሞች ልዩነቶች፤ በባለጸጋ በሆነችው የአሜሪካዋ አሪዞና እና በደሃዋ የሜክሲኮዋ ሶኖራ፣ በሀብታሟ ደቡብ ኮሪያና በደሃዋ ሰሜን ኮሪያ መካከል ያሉ ልዩነቶች ታሪካዊ ዳራ እንዲሁም የግብጽ አብዬት ፋይዳ ቢስነትና የመሳሰሉ አለም አቀፍ የታሪክ፣ ኢኮኖሚና ፓለቲካ ክስተቶች በስፋት በመጽሃፉ ተዳሰዋል።

አገራት ለምን በለጸጉ? ለምንስ ደሃ ሆኑ? በአለም ላይ በተለያዩ አገራት የተካሄዱ አብዮቶች ለምን ለአገራት ዜጎች ጠብ የሚል ፋይዳ ማምጣት አልቻሉም? መልሱን መጽሃፉ በደንብ አስቀምጦታል። ይህን መጽሃፍ እንድታነቡ እየጋበዝኩ፤ መጽሃፉን በሶፍት ኮፒ የምታገኙበትን ሊንክ ከስር አስቀምጫለሁ።

በቀጣይ ስለመጽሃፉ በስፋት የምለው ይኖረኛል። መልካም ቆይታ።

አገራችንን ሠላም ያርግልን።
NAM - ጳጉሜ 3/2014

https://ia800606.us.archive.org/15/items/WhyNationsFailTheOriginsODaronAcemoglu/Why-Nations-Fail_-The-Origins-o-Daron-Acemoglu.pdf

"War is a place where a young people who don't know each other and don't hate each other kill each other, by the decisio...
27/08/2022

"War is a place where a young people who don't know each other and don't hate each other kill each other, by the decision of old people who know each other and hate each other but don't kill each other and shake hands at the end of the war." Anonymous
•••
"War does not determine who is right - only who is left." Bertrand Russel
•••

Address

Awash

Telephone

+251911734148

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኑርሁሴን አህመድ - Nurhussen Ahmed posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ኑርሁሴን አህመድ - Nurhussen Ahmed:

Share