10/05/2020
“ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።” ማቴዎስ 6፥34
“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።” ፊልጵስዩስ 4፥6
ትናንት አልፏል። ዛሬ ላይ ትኩረት እናድርግ። እግዚአብሔር አዲስ ነገር ያደርጋል።
ነገ ምን ሊከሰት እና ሊመጣ ስላለው ነገር በማሰብ ተስፋ አንቁርጥ። በሚመጣው በማንኛውም አስቸጋሪ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይረዳናል ፡፡
መጨነቃችንን እናቁም። ወደ ፊት መራመዳችንን እንቀጥል። ችግሩ ሊኖር ይችላል። እግዚአብሔር ሁልጊዜም ለእኛ ታማኝ መሆኑንም ማስታወስ አለብን፡፡
ሁላችንም በእግዚአብሄር ጥበቃ ስር መሆናችን የሚታወቅና የተረጋገጠ እውነት ነው ፡፡ የእኛ እርዳታ የሚመጣው ከእርሱ ነው።
"እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው፥ እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው። ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና።" (መዝሙር 9 9-10)
አትጨነቅ፣ ሁሉም ነገሮች በእግዚአብሔር እጅ ናቸው!