Bonga FM 97.4

Bonga FM 97.4 SRTA-Bonga Branch FM 97.4 is Government Owned Media.

በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጣቢያ ባልደረባ የጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ ህልፈትን ተከትሎ በርካታ አድማጮችና የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቻችን ሀዘናቸውን እየገለጹ ነው።በጣቢያችን...
25/05/2026

በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጣቢያ ባልደረባ የጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ ህልፈትን ተከትሎ በርካታ አድማጮችና የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቻችን ሀዘናቸውን እየገለጹ ነው።

በጣቢያችን የፌስቡክ ገጽ ላይ ከሰፈሩ የተከታዮቻችን የሀዘን መግለጫ መልዕክቶች መካከል ከብዙ በጥቂት ሀብታሙ ታደሰ አዘጋጅቶታል ማርታ ታምሩ እንደሚከተለው ታቀርበዋለች።

በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጣቢያ ባልደረባ የጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ ህልፈትን ተከትሎ በርካታ አድማጮችና የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቻችን ሀዘናቸውን እየገለጹ ነው....

25/05/2026

ሰኞ ፤ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ/ም የጠዋት ስርጭታችን

አርሰናል ከ22 ዓመት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አነሳክለቡ ይህንን ታላቅ ዋንጫ ማሳካት የቻለው ታዋቂው አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ቡድኑን ሳይሸነፍ (Invincibles) ስም ዋን...
24/05/2026

አርሰናል ከ22 ዓመት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አነሳ

ክለቡ ይህንን ታላቅ ዋንጫ ማሳካት የቻለው ታዋቂው አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ቡድኑን ሳይሸነፍ (Invincibles) ስም ዋንጫ ካነሱበት የ2003/2004 የውድድር ዘመን በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የአርሰናል ድል ሳይዋዥቁ መታመንን እና ጸንቶ መታገልን ያስተማረ ነው፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
24/05/2026

የአርሰናል ድል ሳይዋዥቁ መታመንን እና ጸንቶ መታገልን ያስተማረ ነው፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጣቢያ ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ ህልፈትን ተከትሎ በርካታ አድማጮችና የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቻችን ሀዘናቸውን እየገለጹ ነው።በ...
24/05/2026

በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጣቢያ ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ ህልፈትን ተከትሎ በርካታ አድማጮችና የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቻችን ሀዘናቸውን እየገለጹ ነው።

በጣቢያችን የፌስቡክ ገጽ ላይ ከሰፈሩ የተከታዮቻችን የሀዘን መግለጫ መልዕክቶች መካከል ከብዙ በጥቂት እንደሚከተለው ተሰናድቷል።

ከቢጣ ወረዳ ኦካ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጋዜጠኛው አድናቅ ነኝ በማለት በአስተያየት መስጫችን ላይ መልዕክታቸውን ያስቀመጡት መምህር ዘላለም መኮንን የጋዜጠኛው ሞት ልቤን ሰብሮታል ብለዋል።

አክለውም ዛሬ ጧት ተወዳጁን ጣቢያ ከፍቼ እጅግ በጣም የምወደውን ጋዜጠኛ ሞት ስሰማ በእውነት አዝኛለሁ። ነፍስህ በሠላም ትረፍ በማለት ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

ይህች ናት ሞት? በሚሉ ቃላት የሀዘን መግለጫ መልዕክቱን በፌስቡክ ገጻችን የሀሳብ መስጫ ላይ ያስቀመጠው የቀድሞ የስራ ባልደረባው ጋዜጠኛ ታጋይ ገ/ሚካኤል ነው።

ፍቄ ልባችንን ሰብሯል ውድ የቀድሞ ባልደረቦቼ ይበልጥ የሀዘን መግለጫ ክላስካሉን ስሰማ ራሴን መቆጣጠር ከብዶኛል ብሏል።

መጽናናቱን ይስጠን፤ ዛሬ የሬዲዮ መስተንግዶ መምራት አለመታደል ነው ያለው ጋዜጠኛ ታጋይ ህልም ቢሆን ከሚያሰኙ አሳዛኝ ቀናቶች ውስጥ አንዱ ይሄው ነው። ፍቆ ሁሌም ከልቤ ነህ እወድዳለሁ በማለት ሀዘኑን ገልጿል።

በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጣቢያ የራዲዮ ዜናና ፕሮግራሞች ክፍል አስተባባሪና የስራ ባልደረባው አሰግድ ሳህሌ በግል የፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው የሀዘን መግለጫው "ሞት አረመኔው። ሞት ቀማኛው። ሞት ነጣቂው። ሞት ቀፋፊው። በነፍሳት መታጨቅ ማትጠረቃ ኦና። መስረቅ የማይደክምህ መንታፊ። ሰቀቀን ማስታቀፍ ማይሰለችህ አውሬ። ርኀራሄ ማያውቅህ ጽልመት። የፍቅሩን ሳቅ ቀማኸኝ። ፍልቅልቁን ወንድሜን በድን ኾኗል አልከኝ። ክፉ ደግ አብሮኝ ያሳለፈን ባልደረባዬን ከእይታዬ ሰውርክ።

ስሙ በክፉ ተነስቶ ማያውቀውን ገራገሩን መነተፍከኝ።

በአቅመ ቢስነትህ በመድሃኒቱ እቅፍ ኾኖ እየተሳለቀብህ እንደኾነ ማን ባረዳህ! ወደ ሙሉ ሕይወት መሻገሪያችን እንደኾንክ ማን በነገርህ! ፍቄ ወደ አባቶቹ ተከማቸ። ወደ እረፍቱ ገባ! የነፍሱን ቤዛ ተገናኘ። ፍቄ ከእንግዲህ አትከፋም! የአባታችን እቅፍ ይመችሃል። የፊቱም ብርሃን ያጠግብሃል። ጌታህን ናፍቀህ ፈጥነህ የተለየኸን እኛም በትንሣኤው ቀን እናይሃለን። ደህና ሁን ፍቄ" በማለት ሳያስበው በድንገት በተለየው ባልደረባ ጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

"ምስጉን፤ ታታሪና ክፉ የማይወጣው" በማለት ስለ ጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ መልካም ስነ-ምግባር የገለጹት ደግሞ የቦንጋ ኤፍ ኤም 97.4 ሬዲዮ ጣቢያ ተርጓሚ አቶ ፀጋዬ ገብረማርያም ናቸው።

የቀድሞ ባልደረባውና አሁን ላይ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሚሰሩ አቶ ወጋየሁ በላቸው ፍቅሩን ማጣት ለእኛም ብቻ ሳይሆን ለጣቢያውም ጉድለት ነው በማለት ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

በጣም የምንወደውና ድምጽን ለመስማት የምንጓጓው ጋዜጠኛ ህይወት በማለፉ ልባችን ተሰብሯል፤ ፈጣሪ ለባልደረቦቹና ለቤተሰቦቹ፤ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለካፋ ህዝብ መጽናናትን ይስጥ በማለት ሀዘኑን የገለጸው ደግሞ ከአዲስ አበባ ግርማ ቆጭቶ የተባሉ የፌስቡክ ገጻችን ተከታይ ናቸው።

አገኘሁ አበበ የተባለ ተከታያችን ደግሞ አድማጮችን በቅንነት የምያስተናግድ ታማኝ ጋዜጠኛ ህልፍቱ በጣም ያሳዝናል ነብሱን ይማር በማለት በጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

"በድምጽህ በምታቀርባቸው የተለያዩ ዝግጅቶች የሚያውቁህ አድማጮችህ በጣም አዝነዋል" በማለት ጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ ተወዳጅና በአድማጭ ዘንድ የማይረሱ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት የሚታወቅ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ ሀዘናቸውን የገለጹት ደግሞ በፌስቡክ ስማቸው "ካመቶ ከተማ ወልደጊዮርጊስ" የተባሉ የገጻችን ተከታይ ናቸው።

ከገዋታ ወረዳ ዶማ ቀበሌ ኢያሱ እሸቱ የተባሉ ተከታያችን ደግሞ የምንወደው ጋዜጠኛ ፍቅሩ ህይወቱ በማለፉ በጣም አዝነናል። አይናችንን ነው ያጣነው። ፈጣሪ ነፍሱን ይማርልን። ለመላው የካፋ ህዝብም መጽናናትን እመኛለሁ በማለት ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

ፍቅሩ አንተ ሰው አክባሪ ትልቅ ሰው ነበርክ፤ ሞት ላንተ አይገባም ነበር። የምወድህ ልዩ ጓደኛዬ ዳግም አንተን እንዳላይህ ጨክነህ ተለየሄኝ። እኔ ምን ማለት እችላለሁ? ነፍስህ በገነት ትረፍ በማለት ጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ በሰው ዘንድ ያለውን መወደድ በሚጠቁም መልኩ ሀዘናቸውን የገለፁት ደግሞ አክሊሉ አለሙ የተባሉ ተከታያችን ናቸው።

ሞሐመድ አባቡልጉ የተባሉ ተከታያችን "አቦ የእኛ ጋዜጠኛ ፍቅሩ፤ መቼም ሀዘንህ ከውስጤ አይወጣም እንግዲህ ምን እንላለን ፈጣሪ ነፍስህን ይማር በማለት ጋዜጠኛ ፍቅሩ ከሰው ልብ የማይጠፋ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ድምጹን በጣም ወድጄ የማዳምጠው ፍቅሩ ህይወት በማለፉ ልቤ በጣም አዝኗል። ፈጣሪ ነፍሱን ይማርልን በማለት ሀዘናቸውን የገልጹት ደግሞ አደመ ከበደ የተባሉ የፌስቡክ ገጻችን ተከታይ ናቸው።

እኛ ለአብነት እነዚህን ቀነጫጭበን ለእናንተ አቀረብን እንጂ በተወዳጁና ትጉ ጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ ህልፈት ልባቸው እጅግ በጣም ማዘኑን የገለጹት የስራው አድናቂዎችና አድማጭ ተከታዮቻችን በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው።

በሀብታሙ ታደሰ

"373 መምህራን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ወስደዋል" :- የካፋ ዞን መምህራን ማህበርግንቦት 16/2018 ዓ.ም (ቦንጋ ኤፍ ኤም 97.4) የካፋ ዞን መምህራን ማህበር የመምህራንን መብት እ...
24/05/2026

"373 መምህራን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ወስደዋል" :- የካፋ ዞን መምህራን ማህበር

ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (ቦንጋ ኤፍ ኤም 97.4) የካፋ ዞን መምህራን ማህበር የመምህራንን መብት እና ጥቅማ-ጥቅም የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡

የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ወንድሙ፣ ማህበሩ ከ13 ሺህ በላይ አባላትን ያቀፈ አንጋፋ ማህበር ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ማህበሩ ከተቋቋመለት አላማ አንፃር የመምህራንን መብት እና ጥቅማ-ጥቅም የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ሥራዎች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡

የመምህራን የደረጃ ዕድገት፣ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ እንዲሁም ሌሎች የትምህርት ማሻሻያ ላይ ማህበሩ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በዞኑ 373 መምህራን ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እየተሰጣቸው እንደሆነም ገልፀዋል።

በቀጣይ ተደራጅተው እየጠበቁ ያሉ መምህራን የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ ማህበሩ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

ከማዘጋጃ ከተሞች ውጭ ያሉ መምህራንን በሚመለከትም የአከባቢው አስተዳደር እና ህዝብ ምቹ መኖሪያ እንዲያዘጋጁላቸው ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ማህበሩ ከዞኑ አስተዳደር ጋር ባለው መልካም ግኑኝነት ችግሮችን በውይይት የመፍታት ልምድ እየዳበረ መጥቷል ብለዋል፡፡

የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ የበርካታ አካላትን ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው ያሉት አቶ ተመስገን "የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው መምህር ነው" ብለዋል፡፡

በዚህም መሠረት መምህራን የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙም ነው የገለጹት፡፡

በቀጣይ ቀናት ለክልላዊና ብሔራዊ ፈተናዎች ተማሪዎችን የማዘጋጀት ሥራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዳንኤል መኩሪያ

የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ!

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/share/181X2irsqB/

ቴሌግራም፡ https://t.me/bongafm974radiostatio

ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/.4?_t=ZM-90PCjvnnVBz&_r=1

ከ44 ሚልዬን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተሰሩ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ ቦንጋ፡ ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (ቦንጋ ኤፍ ኤም 97.4)በሺሾ-እንዴ ወረዳ ከ44 ሚልዬን ብር በላ...
24/05/2026

ከ44 ሚልዬን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተሰሩ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ

ቦንጋ፡ ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (ቦንጋ ኤፍ ኤም 97.4)

በሺሾ-እንዴ ወረዳ ከ44 ሚልዬን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተሰሩ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ።

የተመረቁ መሠረተ-ልማቶች የለውጡ መንግስት የማህበረሰቡን ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ያደረገውን ትኩረት የሚያሳዩ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በምረቃው መርሃግብር መልዕክት ያስተላለፉት የወረዳው ዋና አስተዳደሪ አቶ ደምሴ ገ/ማርያም በአካባቢው ከዚህ ቀደም የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆነው የቆዩ የመንገድና ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት በመሆናቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

የለውጡ መንግስት ከገባ ወዲህ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ ቆይቷል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ፤ በተለይም በሚሰሩ ልማቶች ላይ ህዝብን በማሳተፍ የተደረጉ እንቅስቃሴዎች ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዋናነት በአዲስ መልክ በስራ ዕድል ፈጠራ ወደ ሰፈራ የገቡ ወጣቶችን የመሰረተ-ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ቅድሚያ እንደተሰጠው ጠቁመዋል።

በወረዳው በሁሉም አካባቢዎች የሚስተዋሉ የመንገድ መሠረተ ልማት ችግሮችን ለመፍታት ከተለያዩ ቦታዎች ማሽኖችን በማስመጣት ኮረት በማምረት የጥገና እና የጥርግያ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

ወሺ ጊዳ፣ ኖባ ህሪዮ፣ ከዲኩራ ወሺ እስከ ጊዳ 18 ኪሎ ሜትር ከግሪን ኮፊ ሀላፊነቱ የተወሰደ የግል ድርጅትና የግል ባለ ሀብቶች ባደረጉት ድጋፍን ጨምሮ በ16 ሚሊዮን ብር ወጭ መሰራቱን ተገልጿል።

በሌላ በኩል ከኖባ ሽመሮ 10 ኪ.ሜትር መሰራቱን ጠቁመው የሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር 3 ኪሎሜትር ድርሻውን በመውሰድ ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ከሾራ ጠቃ ቀበሌ ከማህበረሰብ 2.5 ሚሊዮን ብር ከመንግስት 10.7 ሚልዮን ብር በድምሩ 12.9 ሚሊዮን ብር ለመንገዱ ግንባታ ወጭ መደረጉን ገልጸዋል።

በዲንብራ የተገነባው ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የኢንሼቲቭ ስራ ቀደም ሲል በሆራ ከተማ በተመሳሳይ ተገንብተቶ ስራ መጀመሩን አስታውሰዋል።

በመርሃ ግብሩ ህሪዮ ቀበሌ የተገነባው ሞደል ጤና ጣቢያ የእናቶችን ጤና እና የህፃናትን ክትባት በቀላሉ እንዲያገኙ የህበረተሰብ ጤና ለማስጠበቅ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

የካፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ አንዳሻው ከበደ በመረግብሩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የሺሾ እንደ ወረዳ የብልፅግና ትሩፋት መሆኑን ገልጸዋል።

የወረዳው አስተዳደር የህዝብ ጥያቄ ለይቶ ምላሽ ለመሰጠት ያደረገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ተናግረው ፤ የተመረቀው የወሺ ጊዳ እና ከኩታ ሾራ- ሽመሮ መንገድ ማህበረሰቡን በሁሉም መስክ ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

ዞኑ ከ1 መቶ 60 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ በሁሉም ወረዳዎች የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ተደራሽ በማድረግ በዘርፉ የሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

መንግስት በቀጣይም የህዝብ የመልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ምላሽ በመስጠት የህብረተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

በመረሐግብሩ የክልል፣ የዞንና ወረዳ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግለዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

በመረሃ ግብሩ ማጠቃለያ ለፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና እና ዕውቅና ስነ-ስረዓት ተከናውኗል።

በምኞት ወ/ሚካኤል

የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ!

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/share/181X2irsqB/

ቴሌግራም፡ https://t.me/bongafm974radiostatio

ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/.4?_t=ZM-90PCjvnnVBz&_r=1
ዩቲዩብ፡
https://www.youtube.com/.4

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሀገሪቱ ህገ-መንግስት እና ሀገሪቱ ተቀብላ ባጸደቀቻቸው የዓለም-አቀፍ ህጎች መሠረት መከናወን አለበት፦ የክልሉ ፍትህ ቢሮግንቦት 16/09/2018 ዓ.ም (ቦንጋ ኤፍ ኤም...
24/05/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሀገሪቱ ህገ-መንግስት እና ሀገሪቱ ተቀብላ ባጸደቀቻቸው የዓለም-አቀፍ ህጎች መሠረት መከናወን አለበት፦ የክልሉ ፍትህ ቢሮ

ግንቦት 16/09/2018 ዓ.ም (ቦንጋ ኤፍ ኤም 97.4) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሀገሪቱ ህገ-መንግስት እና ሀገሪቱ ተቀብላ ባጸደቀቻቸው የዓለም-አቀፍ ህጎች መሠረት እንዲከናወን የፍትህ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፍትህ ቢሮ አስገነዘበ።

ቢሮው "የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ ማዕቀፍ እና ምርጫ ነክ ወንጄሎች" በሚል ርዕስ ለፍትህ አካላት በቦንጋ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፍትህ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ቤተልሔም ዳንኤል እንደገለጹት ምርጫ የአንድ ሀገር እጣ ፋንታ ለመወሰን ዜጎች በቀጥታ የሚሳተፉበት ታላቅ የታርክ ህደት ነው።

ይህ ህደት ከድምጽ መስጠት ባለፈ በርካታ ሀገራዊ ፋይዳዎችን ያነገበ ነው ያሉት ኃላፊዋ ለአንድ ሀገር ሰላም፤ ዕድገትና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የምርጫ ወሳኝ ሚና እንደሆነም ጠቁመዋል።

ምርጫ የመንግስትን የፖለቲካ ህጋዊነት የሚያረጋግጥ እንደሆነም ገልጸዋል።

በምርጫ ወደ ስልጣን የሚመጣ መንግስት የህግ ውክልና ስላለው የላቀ ስልጣን እንዲኖረው፤ ውሣኔዎቹ ተዓማንኒ እና ተቀባይነት ያላቸው እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል።

ምርጫ የተጠያቂነት ሥርዓትን ከማስፈን በተጨማሪ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖርና ሀገራዊ መረጋጋትን ይፈጥራል ብለዋል።

ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ያላቸውን የመወሰን መብት በተግባር የሚያሳዩበት ሂደት እንደሆነም ጠቁመዋል።

በአንድ ሀገር ወስጥ በየደረጃው የሚደረግ ምርጫ በሀገሪቱ ህገ-መንግስት እና ሀገሪቱ ተቀብላ ባጸደቀቻቸው የዓለም-አቀፍ ህጎች እንዲሁም በሀገርቱ የምርጫ ህግጋት መሠረት መከናወን እንዳለበትም አሳስበዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፤ ፍትሐዊ፤ ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የምርጫ አዋጁንና ደንቡን በአግባቡ ማወቅና መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል።

ስልጠናው የቀጣይ ሥራዎች ላይ ጉል አሰተዋጽኦ እንዳለው የገለጹት ደግሞ በክልሉ ፍትህ ቢሮ የልዩ ልዩ ወንጄሎች ዳይሬክቶሬት ዳይረክተር አቶ ይንገስ ታደለ ናቸው።

በስልጠናው ከተሳተፉት መካከል የኮንታ እና የዳውሮ ዞን ፍትህ መምሪያ ሃላፊዎች አቶ ሚልዮን ተፈራ እና ወይዘሮ የሺ አሰፋ በምርጫ ሥነ ምግባር እና በሌሎችም ህጎች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ያሳደገ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።

የምረጫ ህደቱ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ለማስቻል የሚረዳ እንደሆነም ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ ሀብታሙ ገብሬ
ፎቶ ኪዳኔ ተስፋዬ

የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ!

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/share/181X2irsqB/

ቴሌግራም፡ https://t.me/bongafm974radiostatio

ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/.4?_t=ZM-90PCjvnnVBz&_r=1

ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/.4

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ 8 ቀናት ብቻ ቀርተውታልድምፅዎ ወሳኝ ነው! ግንቦት 24 መሪዎን ለመምረጥ ዝግጁ ኖት? #ኢትዮጵያ   #ምርጫ   #ዴሞክራሲ   #በምርጫ  #ብቻ
24/05/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ 8 ቀናት ብቻ ቀርተውታል

ድምፅዎ ወሳኝ ነው! ግንቦት 24 መሪዎን ለመምረጥ ዝግጁ ኖት?

#ኢትዮጵያ #ምርጫ #ዴሞክራሲ #በምርጫ #ብቻ

23/05/2026
ጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ በስራ ባልደረቦቹ አንደበት
23/05/2026

ጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ በስራ ባልደረቦቹ አንደበት

Address

Bonga
138

Telephone

+251473311641

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bonga FM 97.4 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category