በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Bu-I
  • በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ''አሰባሳቢ ገዢ ትርክት ለበለፀገች ኢትዮጵያ''!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ ከመስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አድርገው ሾመዋል።
28/09/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ ከመስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አድርገው ሾመዋል።

በቡኢ ከተማ አስተዳደር የተከበረው የደንጌሳት  በዓል አከባበር የሚያስቃኝ Arts Tv የተዘጋጀው ፕሮግራም
27/09/2026

በቡኢ ከተማ አስተዳደር የተከበረው የደንጌሳት በዓል አከባበር የሚያስቃኝ Arts Tv የተዘጋጀው ፕሮግራም

#ደንጌሳት #ቡዒ #...

27/09/2026

የፕሮግራም ጥቆማ!!!

መስከረም 17/2019 ዓ.ም

ልዩ የመስቀል በዓል አከባበር ፕሮግራም በቡኢ ከተማ አስተዳደር በArts Tv ዛሬ ምሽት 1:00 ሰዓት ላይ ይቀርባል።

በመሆኑም እናንተም ይህን ልዩ የመስቀል በዓል አከባበር ፕሮግራም እንድትከታተሉ ተጋብዛችኃል ።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከሰብለሰብ ህብረት ስራ ማህበር ጋር በመተባበር  ያዘጋጁት ሁለተኛው ዙር "የሰብለሰብ ራን" ታላቅ የጎዳናይ ሩጫ   በቡኢ ከተማ ተካሄደ።መስከ...
27/09/2026

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከሰብለሰብ ህብረት ስራ ማህበር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሁለተኛው ዙር "የሰብለሰብ ራን" ታላቅ የጎዳናይ ሩጫ በቡኢ ከተማ ተካሄደ።

መስከረም 17/2019 ዓ.ም

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከሰብለሰብ ህብረት ስራ ማህበር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሁለተኛው ዙር "የሰብለሰብ ራን" ታላቅ የጎዳናይ ሩጫ በዛሬው ዕለት በቡኢ ከተማ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዳነ ተሰማ መሰል የሩጫ ወድድሮች የማህበረሰብን ፍቅርና አንድነትን ከማጠናከር በተጨማሪ ታዳዎችን የሚያበረታታ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሰብለሰብ ህብረት ስራ ማህበር ከኢኮኖሚው ባሻገር በማህበረሰቡ ውስጥ እያደረገ ያለው ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ እጅግ የሚበረታታና የበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው ተግባር እንደሆነ አመላክተዋል።

የተጀመረው የጎዳና ላይ ሩጫ በቀጣይ ከፍ ባለደረጃ ተጠናክሮ መቀጠል መቻል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የቡኢ ከተማ አስተያደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳሻው አለማየው ጽ/ቤታቸው ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደው ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ "ሰብለሰብ ራን" ከሰብለሰብ ህብረት ስራ ማህበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል።

መሰል ስፖርታዊ ውድድሮች የማህበረሰቡን አንድነት በማጠናከርና ተተኪ ትውልዶችን በማነቃቃት ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን አመላክተዋል።

በቀጣይም ከፍ ባለደረጃ የበለጠ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነ ተናግረዋል።

ሰብለሰብ ህብረት ስራ ማህበር ማህበረሰቡን በኢኮኖሚ ከማነቃቃት ባሻገር በበርካታ በበጎ አድራጎት ስራዎች እየተሳተፈ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

ወድድሩ ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሲያስተባብሩ ለነበሩ የፀጥታ አካላት ፣ተቋማትና አዘጋጆች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የሰብለሰብ ህብረት ስራ ማህበር ሰብሳቢ አቶ ሲሳይ ዳጢ የህብረት ስራ ማህበሩ ዓላማ ከኢኮኖሚው ባሻገር ማህበረሰቡን በሁሉም ዘርፍ ማገዝና ማበረታታት እንደሆነ ተናግረዋል።

እሰከ አሁንም በበርካታ ዘርፎች ማህበረሰቡን ማገዙን ጠቁመዋል።

መሰል ስራዎች በቀጣይም የበለጠ ተጠናክረው እንደሚቀጥ ተናግረዋል።

ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

ለተጨማሪ መረጃ
የፌስቡክ ገፃችን 👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100068066105775

#የቴሌግራም ፔጃችን👇
https://t.me/BueeGovermentcomunication35

#የቲክቶክ-ፔጃችን👇
https://www.tiktok.com/?_t=8rUU1rZG5aS&

#ኢንስታግራም https://www.instagram.com/bueegovrncommunication35?igsh=YzljYTk1ODg3Zg==

#የዋትሳፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VayIqyN6mYPDqXJHKL3t

#ዩትዩብ
https://youtube.com/?si=ScPXI4i65LSi9V6p

#የቲዊተር (X)👇
https://x.com/BueeGovrnComm35?t=FvbB7Xk926nDj7_qXadSWg&s=35

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን

በጉራጌ ምድር በልዩ ባህላዊ ስነ-ስርዓት የሚከበረው የመስቀል በዓል *********************የመስቀል ደመራ ሲደመር ችቦው ሲበራ የመስቀል ዝማሬና እልልታ በየመንደሩ ሲሰማ የኢትዮጵያ...
27/09/2026

በጉራጌ ምድር በልዩ ባህላዊ ስነ-ስርዓት የሚከበረው የመስቀል በዓል
*********************

የመስቀል ደመራ ሲደመር ችቦው ሲበራ የመስቀል ዝማሬና እልልታ በየመንደሩ ሲሰማ የኢትዮጵያ መስከረም በልዩ ድምቀት ይጎላል። የመስቀል በአል የንግሥት እሌኒ ግማደ መስቀሉን የማግኘት ታሪክን መሰረት ያደረገ በዩኔስኮ የማይዳሰስ የሰው ልጅ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴት ቢሆንም በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ያለው ማህበራዊና ባህላዊ ፋይዳ ግን የጎላና ልዩ ገፅታ ያለው ነው።

በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ መስቀል ከአንድ ቀን የደስታ በአልነት በላይ የአመቱ ትልቅ መገናኛ የትውልድ ቀዬ መመለሻ የማስታወሻና የህይወት አዲስ ምእራፍ መክፈቻ ተደርጎ ይወሰዳል።

በዓሉ ሲቃረብ ከአዲስ አበባና ከልዩ ልዩ የሀገራችን ክልሎችና ከውጭ ሀገራት የሚኖሩ የብሄሩ ተወላጆች ወደ ትውልድ ቀያቸው በመጓዝ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይገናኛሉ።

የመስቀል ዝግጅት በአሉ ከወር አንስቶ ገንዘብና ቅቤ በማጠራቀም የሚጀመር ሲሆን አራት ወራት ሲቀሩትና በተለይም ከነሐሴ 12 (ከቡሄ) ጀምሮ ዝግጅቱ እየተጧጧፈ ይሄዳል።

በዚሁ መሰረት አባወራዎች ለእርድ የሚሆኑ ሰንጋዎችን ያደልባሉ የከብቶች ሳር ያዘጋጃሉ ፤እማወራዎችና ወጣት ሴቶች ደግሞ እንሰት በመፋቅና ቤቶችን በተለያዩ ባለቀለም አፈሮች በማሳመር ጅባ በመስራትና ለክትፎ የሚያስፈልጉ ቅቤና ሚጥሚጣዎችን ያዘጋጃሉ።

ወጣት ወንዶችና ልጆች ደግሞ ለደመራና ለበአሉ የሚሆን ፍልጥ እንጨት ከጫካ በመልቀምና በማዘጋጀት የስራ ክፍፍላቸውን ይወጣሉ።

የበዓሉ የእለት ተእለት አከባበርም የራሱ የሆነ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ስርዓት ያለው ነው። መስከረም 14 "ደንጌሳት" (የዴጚያ እሳት) በሚለው እለት ለሁሉም ቤተሰብ አባል በተዘጋጀለት የሸክላ ጣባት የጎመን ክትፎ የሚቀርብበትና በየደጃፉ የልጆች ደመራ "ጎረ ጎረ" እየተባለ የሚበራበት ነው።

ዋናው የመስቀል በዓልና የእርድ ቀን "ወኸመያ" መስከረም 15 እለት የሚከበር ሲሆን በእዚህ እለት የአባወራዎች ተግባር ጎልቶ የሚታይበት ሲሆን አባወራዎች የደለቡ ሰንጋዎችን በማረድ "ጨፉየ" (ጥሬ ስጋ በቅቤ መንከር) እና ባህላዊውን የጉራጌ ክትፎ ለቤተሰብ በማቅረብ የሚበላበት ዕለት ነው።

መስከረም 16 "ያባንዳ እሳት" (የጉርዝ እሳት) ደግሞ ትልቁና አባቶች የሚመሩት ደመራ የሚበራበት ወጣቶች ባህላዊውን «አዳብና» ጨዋታ የሚጫወቱበትና ሃይማኖታዊ ስርዓቱ የሚፈፀምበት እለት ነው።

ከበአሉ እለታት በኋላም ማህበራዊ ትስስሩ ይበልጥ ይጠናከራል። መስከረም 17 "ንቅ ባር" (የከሰል ማይ) እለት እድርተኞች ደመራው በተቃጠለበት ስፍራ ተሰብስበው አዲስ የአካባቢ ዳኛ የሚሾሙበት አዳዲስ አባላትን የሚመዘግቡበትና የአካባቢ ልማትና ስራዎችን የሚያቅዱበት ነው።

መስከረም 18 "የፊቃቆማይ" ልጃገረዶች የተለያዩ ለስፌት ጌጣ ጌጦች የሚሆን ሰንደዶ የሚለቅሙበት ሲሆን ከመስከረም 17 እስከ 23 "የጀወጀ" (የጀወቸ) ባልና ሚስት አማችና አማቶቻቸውን ሙክትና ስጦታ ይዘው በመጠየቅ መርቃትና ክብር የሚያገኙበት ጊዜ ነው።

በተጨማሪም በሚካሄዱ ባህላዊ የአዳብና ጨዋታዎችና የዘፈን ትእይንቶች ወቅት ወጣቶች ሎሚ፣ ብርቱካንና የሸንኮራ አገዳ በመለዋወጥ የህይወት አጋራቸውን የሚመርጡበት አጋጣሚ ይፈጠራል።

የመስቀል በአል በጉራጌ ምድር የተራራቁ ቤተሰቦችና ዘመዶች የሚገናኙበት፣ በጥል ላይ ያሉ ባልና ሚስቶችና ጎረቤቶች የሚታረቁበት፣ እዳ የሚሰረዝበት፣ ወላጆች ለትውልዱና ለሀገር ሰላም የሚፀልዩበት ታላቅ የማህበራዊ ውህደትና የሰላም መድረክ ነው።

የደመራው እሳት በሌሊት ሰማዩን ሲያበራ በጉራጌ ቤቶች ውስጥ ደግሞ የፍቅር የእርቅና የአብሮነት ብርሃን ይበራል ይህም መስቀልን ከበአልነት በላይ ሰዎችን ከስራቸው፣ ከቤተሰባቸውና ከጋራ ትውፊታቸው የሚያገናኝ የፍቅር ድልድይ ያደርገዋል።

በብሌን ደምበሎ

"የመስቀል ደመራ በዓል ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶችን አቀናጅቶ የያዘ የኢትዮጵያዊያን ልዩ መገለጫ ነው።" አቶ በለጠ ጫካ መስከረም 16/2019 ዓ.ምመስቀል ደመራ በዓል በቡኢ ከተማ በተለያዩ...
26/09/2026

"የመስቀል ደመራ በዓል ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶችን አቀናጅቶ የያዘ የኢትዮጵያዊያን ልዩ መገለጫ ነው።" አቶ በለጠ ጫካ

መስከረም 16/2019 ዓ.ም

መስቀል ደመራ በዓል በቡኢ ከተማ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በደመቀ መልኩ ተከብሮ በሰላም ተጠናቋል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ የመስቀል ደመራ በዓል ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶችን አቀናጅቶ የያዘ የኢትዮጵያ ልዩ መገለጫ ነው ብለዋል።

በሀይማኖታዊ እሴቱ ክርስቶስ የተሰቀበለበት እውነተኛው መስቀል የተገኘበት ለማስታወስ እንደሆነ በባልላዊ ደግሞ የክረምት ወቅት ማብቂtያና የፀደይ መግባቱን ምልክት ተደርጎ እንደሚከበር ጠቁመዋል።

በማህበራዊ እሴቱ ደግሞ ፍቅርን ፣መቻቻልን እና አብሮነትን የሚያጠናከርበት ታላቅ በዓል እንደሆነ ተናግረዋል።

በዓሉ በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ዓመቱን በሙሉ ተለያይተው የነበሩ ቤተሰቦች የሚሰባሰቡበት ፣የተጣሉ የሚታረቁበትማህበራዊ ትስስር የሚጠናከርበት ልዩ ትርጉም የሚሰጠው እንደሆነም አንስተዋል።

እኛም በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት በፍቅርና በአንድነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በዓሉ የሰላም የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የሶዶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ በቴ በበኩላቸው የመስቀል በዓል በልዩ ድምቀት ከሚከበሩ የዓደባባይ በዓል አንዱ እና የአገር ገፅታን ለዓለም በማስተዋወቅ ጉልህ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ በዓል እንደሆነ ተናግረዋል።

በዓሉ ሀይማኖታዊ ፣ባህላዊና ማህበራዊ
ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በመሆኑም በዓሉ ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ለሀገራችን መሆን ይገባዋል ብለዋል።

በዓሉ የሰላም የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የምስራቅ ጉራጌና የማረቆ ልዩ ወረዳ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ቀሲስ ሰሎሞን ዓባይነህ እንኳን ለታላቁ የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የመስቀለ ትርጉም ፍቅርንና አንድነት መሆኑን በመግለፅ እኛም በዓሉን ስናከብር እውነተኛውን የመስቀሉን ትርጉም በሚገልፅ መልኩ በፍቅር ፣በአብሮነትና በመቻቻል ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

ለተጨማሪ መረጃ
የፌስቡክ ገፃችን 👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100068066105775

#የቴሌግራም ፔጃችን👇
https://t.me/BueeGovermentcomunication35

#የቲክቶክ-ፔጃችን👇
https://www.tiktok.com/?_t=8rUU1rZG5aS&

#ኢንስታግራም https://www.instagram.com/bueegovrncommunication35?igsh=YzljYTk1ODg3Zg==

#የዋትሳፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VayIqyN6mYPDqXJHKL3t

#ዩትዩብ
https://youtube.com/?si=ScPXI4i65LSi9V6p

#የቲዊተር (X)👇
https://x.com/BueeGovrnComm35?t=FvbB7Xk926nDj7_qXadSWg&s=35

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን

አዳብና ባህላዊ  ይዘቱን በጠብቀ መልኩ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ  ተገለፀ።                    መስከረም 16/2019 ዓ.ም                       =========...
26/09/2026

አዳብና ባህላዊ ይዘቱን በጠብቀ መልኩ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ተገለፀ።

መስከረም 16/2019 ዓ.ም
================
በምስራቅ ጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ በአናቲ ኪዳነ ምህረት ላይ የአዳብና ጨዋታ የማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሂዷል፡፡

የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የባህልና ቋንቋ ቡድን መሪ አቶ ሐብታሙ ከበደ በቅድሚያ እንኳን ለ2019 ዓ/ም እጅግ በጉጉትና በናፍቆት የሚጠበቀው የወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች የመተያየት፣ የመገናኘት፣ የመተጫጨት፣ የመፈቃቀርና የአብሮነት ቱባ ባህል የሚንፀባረቅበት የመጀመሪያ የአዳብና በዓል ማስጀመሪያ ቀን በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

የሶዶ ክስታኔ ማህበረሰብ የበርካታ ባህላዊ፣ታሪካዊ እንዲሁም ተፈጥሯዊ እሴት ባለቤት እንደሆነና ባህልና ቋንቋ የአንድ ማህበረሰብ የማንነት መገለጫ በመሆናቸው በተገቢው ሁኔታ ጥበቃና እንክብካቤ ከተደረገላቸው ለማህበረሰቡ የሚሰጡት ፋይዳ የላቀ እንደሆነ አብራርተዋል።

የሶዶ ክስታኔ ማህበረሰብ መገለጫ ከሆኑት ባህሎች መካከልም አንዱ የአዳብና ባህል እንደሆነና ይህ ቱባ ባህል ከማልማትና ከማስተዋወቅ ጋር በተያያዘ ከሶስቱ መዋቅር በጋራ በመሆን ከመስከረም 16 ጀምሮ እስከ ጥቅምት አምስት ድረስ በተመረጡ ቦታዎች እንደሚከበር ገልጸዋል።

አቶ ሐብታሙ አክለውም የአዳብና በዓል በሶዶ ክስታኔ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠውና ከመስከረም 16 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 5 ድረስ ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች በቤተሰባቸው ሙሉ ፈቃድ ተሰጥቷቸው በየገበያውና በየአብያተክርስቲያናቱ ተሰባስበው የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታ ከማካሄድም ባሻገር የሚተያዩበትና የሚተጫጩበት የሚደሰቱበት አዲስ ሴት ሙሽሮች ለመስቀል ወደ ቤተሰባቸው ተመልሰው እስከጥቅምት 5 በየአዳብናው እየሄዱ የሚዝናኑበት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የአዳብና በዓል ወጣት ወንዶች፣ ሴት ልጃገረዶች፣ ሙሽሮችና ሌላውም ማህበረሰብ የሚሳተፍበት ትልቅ የአደባባይ በዓል ነው ያሉ ሲሆን ይህን የማይዳሰስ ውብ ቅርስ አባቶች በቃል፣ በትውፊትና በክዋኔ ለአሁኑ ትውልድ አድርሰውለታል ብለዋል።

በመሆኑም የአሁኑ ትውልድ የአባቶቹ መገለጫ የሆነውን እሴት ሳይበረዝ ሳይከለስ ቱባ ባህሉን ጠብቆ ለዓለም በመሸጥ ቀጣይ ይህን ውብ በዓል በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አዳብና ፍቅርን አንድነትን አጉልቶ የሚያሳይ ዲሞክራሲን የሚሰብክ ነው ያሉት አቶ ሀብታሙ የቆዩ እድሜ ጠገብ የሆኑ ነገር ግን ትርጉማቸው የሰፋ ባህላዊ ጨዋታዎች የሚከወንበት መሆኑንም አንስተዋል።

በቦታው ተገኝተው በበዓሉ የተሳተፉት አቶ ወንድሙ እሼቱ እና አቶ ታደሰ ፈይሳ የተባሉ አባቶች የሶዶ ክስታኔ ማህበረሰብ አንዱ መገለጫው የሆነው ቱባው የአዳብና በዓል ሳይበረዝና ሳይከለስ ለትውል ለማስተላለፍ ይረዳ ዘንድ ልጆቻችንን ይዘን መጥተን እያሳየንና እያስተማርን እንደኛለን ብለዋል።

ይህ ቱባ ባህልን ለማበላሸት ጠለፋና የተለያዩ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን የሚፈፅሙ አካላት ከድርጊታቸው ተቆጥበው የመተጫጫ፣ የመዝናኛ፣ የአንድነትና የአብሮነት አልፎም ተርፎም የሰላም እሴት መገንቢያ የሆነው የአዳብና በዓል በጋራ አልምቶና ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በስፍራው ተገኝተው ሲጫወቱ የነበሩ ያነጋገርናቸው አንዳንድ ወጣቶች እንደገለፁትም የሶዶ ክስታኔ ማህበረሰብ መገለጫ ከሆኑት ባህሎች መካከል አንዱ የአዳብና ባህል እንደሆነና ይህ ቱባ ባህል ከማልማትና ከማስተዋወቅ ጋር በተያያዘ የእኛ የወጣቶች ሚናችን የጎላ በመሆኑ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል ብለዋል።

#ዘገባው የሶዶ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው፡፡

የጉራጌ ማህበረሰብ የመስቀል በዓልን ሀይማኖታዊ ትውፊቱን እና ባህላዊ እሴቱን ሳይለቅ ለረጅም ዘመናት በድምቀት ሲያከብር ቆይቷል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) (ሆሳዕና፣መስከረም...
26/09/2026

የጉራጌ ማህበረሰብ የመስቀል በዓልን ሀይማኖታዊ ትውፊቱን እና ባህላዊ እሴቱን ሳይለቅ ለረጅም ዘመናት በድምቀት ሲያከብር ቆይቷል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

(ሆሳዕና፣መስከረም 16/2019 )በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስቀል በጉራጌ ልዩ የበአል ዝግጅት በደቡብ ሶዶ ወረዳ ተከብሯል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት መስቀል ለጉራጌ ማህበረሰብ ልዩ በዓል ነው ብለዋል።

ጉራጌም ለመስቀል ልዩ መሆኑን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ያስታወቁት።

የጉራጌ ማህበረሰብ የመስቀል በዓልን ሀይማኖታዊ ትውፊቱን እና ባህላዊ እሴቱን ሳይለቅ ለረጅም ዘመናት በድምቀት ሲያከብር መቆየቱን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

ለበዓሉ የ11 ወራት ዝግጅት በማድረግ መከበሩ በህብረተሰቡ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ መስተጋብር በማጠናከር ረገድ የጎላ አበርክቶ እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው አስታውቀዋል።

መስቀል መላው የጉራጌ ልጆች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ተሰባስበው ቤተሰቦቻቸውን የሚጠይቁበት እና እርስ በእርስ የሚደጋገፉበትን እድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።

የመስከረም ወር በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ከዘመን መለወጫ ጀምሮ ወደየ አካባቢው በመምጣት ቤተሰቡን የሚያገለግልበት፣እርሻውን የሚያቃናበት፣ቤቶቹን የሚያድስበት፣ልጆቹን ለትዳር የሚያዘጋጅበት እንዲሁም ፈጣሪን የሚያመሰግንበት ወቅት ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

በዚህ ጊዜ ተሰባስበን ፈጣሪን እንድናመሰግን ለረዳን አምላክ ምስጋና ማቅረብ ተገቢ ነው ብለዋል።

የመስቀል በዓል በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሀይማኖታዊ እና በባህላዊ ይዘቱን ሳይለቅ በድምቀት የሚከበር በዓል ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

የመስከረም ወር ለኢትዮጵያውያኖች የብሩህ ተስፋ፣የይቅርታ፣የመገናኛ፣አዲስ ተስፋ እና ልምላሜ የሚስተዋልበት መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

ወርሀ መስከረም ተማሪዎች ወደ አዲስ የመማሪያ ክፍል የሚገቡበት፣ነጋዴዎች በአዲስ እቅድ ትርፋቸውን የሚያሰሉበት፣አርሶ አደሩ የላቡን ውጤት የሚያገኝበት፣በተለያየ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎች አዳዱስ እቅድ አዘጋጅተዉ የህይወታቸውን ምዕራፍ የሚጀምሩበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

በሁለቱም የጉራጌ ዞኖች አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙ የጸጥታ ችግሮች መኖራቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

ድንበር ተሻጋሪ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ከኦሮሚያ ክልል እና ከፌደራል የጸጥታ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

አሁን በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ችግሮች ከጥቂት ጊዜ በኋላ መልክ መልክ ይይዛሉ ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል።

2019 ዓ/ም የኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን የሚረጋገጥበት ዓመት እንደሚሆን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ለቀጣዩ የስራ ጊዜ ዝግጁ መሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው በጋራ እና በትብብር እየሰራን ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ እናሻግራለን ብለዋል።

በክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች ሉኡካን ቡድኖቻቸውን ይዘው በዓሉን ለማድመቅ ለተገኙ አካላት ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።

የሰላም፣የፍቅር፣የአንድነት እና የወዳጅነት በዓል እንዲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደሱ አበጋዝ በበኩላቸው የመስቀል በአል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት(ዩኒስኮ) ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ በቱሪዝም ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚ የላቀ ሚና እያበረከተ ነው ብለዋል።

መስቀል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የላቀ ትርጉም ያለው በዓል ስለመሆኑም አቶ ደሱ ጠቁመዋል።

አመቱን ሙሉ ተለያይተው ይኖሩ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚገናኙበት፣ማህበራዊ ችግሮቻቸውን የሚፈቱበት፣ወጣቶች ወደ ጋብቻ የሚያመሩበት፣በዳይና ተበዳይ ይቅር የሚባባሉበት እና ሌሎች አያሌ እሴቶቻችን በጉልህ የሚንጸባረቁበት በዓል ስለመሆኑም ምክትል አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።

በተስፋዬ መኮንን

የመስቀል የደመራ በዓል በቡኢ ከተማ  የሀይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በተለያየ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች  በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።መስከረም 16/2019 ዓ.ምየመስቀል ...
26/09/2026

የመስቀል የደመራ በዓል በቡኢ ከተማ የሀይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በተለያየ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

መስከረም 16/2019 ዓ.ም

የመስቀል የደመራ በዓል በቡኢ ከተማ የሀይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙቀት በተለያየ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን!!!

ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

ለተጨማሪ መረጃ
የፌስቡክ ገፃችን 👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100068066105775

#የቴሌግራም ፔጃችን👇
https://t.me/BueeGovermentcomunication35

#የቲክቶክ-ፔጃችን👇
https://www.tiktok.com/?_t=8rUU1rZG5aS&

#ኢንስታግራም https://www.instagram.com/bueegovrncommunication35?igsh=YzljYTk1ODg3Zg==

#የዋትሳፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VayIqyN6mYPDqXJHKL3t

#ዩትዩብ
https://youtube.com/?si=ScPXI4i65LSi9V6p

#የቲዊተር (X)👇
https://x.com/BueeGovrnComm35?t=FvbB7Xk926nDj7_qXadSWg&s=35

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን

24/09/2026

Address

Bu-I

Telephone

+251468830761

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share