የእንሴኖ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ዩኒት Enseno City Government Communication Unit

  • Home
  • Ethiopia
  • Butajira
  • የእንሴኖ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ዩኒት Enseno City Government Communication Unit

የእንሴኖ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ዩኒት Enseno City Government Communication Unit public and government service
(2)

02/10/2026
የከሸፈው የከበባ ስልት እና የማይገታው የኢትዮጵያ  ***************የአፍሪካ ቀንድ ውስብስብ የጂኦፖለቲካዊ ሽኩቻ ማዕከል በሆነበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ክብሯን እና ብሔራዊ ...
02/10/2026

የከሸፈው የከበባ ስልት እና የማይገታው የኢትዮጵያ
***************

የአፍሪካ ቀንድ ውስብስብ የጂኦፖለቲካዊ ሽኩቻ ማዕከል በሆነበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ክብሯን እና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር የማያዳግም ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ መውሰድ ጀምራለች።

የኢትዮጵያ መንግሥት በአሥመራ የሚገኘውን ኤምባሲውን ለመዝጋት መወሰኑና በአዲስ አበባ የሚገኙ አስር የኤርትራ እንዲሁም አንድ የግብፅ ዲፕሎማቶችን በ48 ሰዓታት ውስጥ ሀገር ለቀው እንዲወጡ ማዘዙ፣ የኢትዮጵያ ትዕግስት ገደብ እንዳለው የሚያሳይ ግልጽ የሉዓላዊነት ማረጋገጫ ፖለቲካዊ እርምጃ ማሳያ ነው።

ይህ ውሳኔ የመጣው የኤርትራን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የጠብ አጫሪነት ድርጊቶችን እንዲሁም የግብፅን በቀጣናው እግር ለመትከል የምታደርገውን አፍራሽ ሩጫ ተከትሎ ነው።

ካይሮ በሶማሊያ የጀመረችውን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ወደ ኤርትራ በማስፋት በአሰብ እና በጅቡቲ ዱራሌ ወደቦች አካባቢ ለማንዣበብ የምታደርገው ጥረት ኢትዮጵያን የማፈን ያረጀ ስልቷ አካል ነው።

ይሁንና የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ባለሙያዎች አበክረው እንደሚሞግቱት አሰብ ያለ ኢትዮጵያ ገበያ ከጥቅም ውጪ የሆነች ባዶ ምድር ናት።

ግብፅም ሆነች ሌሎች ሀገራት በአሰብ ላይ የሚያፈሱት መዋዕለ ንዋይ ኤርትራን ለማልማት ሳይሆን ኢትዮጵያ የጀመረችውን የባሕር በር አጀንዳ ለማደናቀፍ የተጠነሰሰ የፖለቲካ ሴራ ነው።

ይህ የግብፅና የኤርትራ የጥፋት ጥምረት ኢኮኖሚያዊ ትርፍን ያማከለ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ ለማደናቀፍ ያለመ ነው።

ግብፅ የታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውን መሆን ማስቆም እንደማትችል በተግባር ስታረጋግጥ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ለማፈን ቀጣናውን በማተራመስ ላይ ትገኛለች።

ነገር ግን ያላት ኢትዮጵያ በእንደዚህ ዓይነት የጠላቶች ጊዜያዊ የከበባ ስልት ከጉዞዋ እንደማትገታ ግልጽ ነው።

ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ የንግድና የፀጥታ ፍላጎቷን ማረጋገጧ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ በመሆኑ፣ ታላቁ ሕዳሴ ግድብን በራሷ አቅም ገድባ ለዓለም እንዳሳየችው ሁሉ የባሕር በር ጥያቄዋንም እውን ማድረጓ የማይቀር ታሪካዊ እርምጃ ነው።



በበረከት ሽመልስ

የፓርቲ አሠራርና አደረጃጀትን በማጠናከር የፓርቲውን ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፦ አቶ መሰለ ጫካ #ቡታጅራ መስከረም 22/2019የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓር...
02/10/2026

የፓርቲ አሠራርና አደረጃጀትን በማጠናከር የፓርቲውን ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፦ አቶ መሰለ ጫካ

#ቡታጅራ መስከረም 22/2019
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ቅ/ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት ለመዋቅሮች ያደረገውን የኢንስፔክሽንና የሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ግብረ መልስ ለዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤቱ ግብረ መልስ ሰጠ።

የኢንስፔክሽኑንና የሱፐርቪዥኑን ቡድን ማጠቃለያ ሪፖርት አቶ አሰፋ ፈይሳ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ም/ኃላፊ አቅርበዋል።

በመድረኩ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ጫካ ጠንካራ የፓርቲ ሥርዓትና አደረጃጀት በመዘርጋት የፓርቲውን አጠቃላይ ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ኃላፊው ይህን የገለጹት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ቅ/ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት ለመዋቅሮች ያደረገው የሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን ማጠቃለያ ግብረ መልስ በተሰጠበት መድረክ ነው።

በዞኑ የፓርቲ አደረጃጀት በተቀመጠው መመሪያና አሠራር መሠረት እንዲመራ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች እየተጠናከሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ተከታታይ የሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን ሥራዎች የፓርቲውን ጥንካሬ ለማስቀጠልና የታዩ ጉድለቶችን በፍጥነት ለማረም የሚያግዙ መሆናቸውን ገልጸው በተገኙ ውጤቶች ላይ በመመርኮዝ ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና ክፍተቶችን ማረም በቀጣይ ትኩረት የሚሰጠው ሥራ መሆኑን ተናግረዋል።

የታችኛውን የፓርቲ አደረጃጀት ማጠናከር፣ ሌብነትና ብልሹ አሠራርን መታገል እንዲሁም መመሪያና አሠራርን ማስፈን የቀጣይ ሥራዎች ትኩረት መሆናቸውንም አቶ መሰለ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ጥራት ያላቸው ዕቅዶችን በማዘጋጀት ለተፈጻሚነታቸው በቂ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

የዞኑ ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሙንተሃ ሸሁር በሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽኑ በቡድኑ የተለዩ ዝርዝር ጉዳዮችን በመያዝ ተገቢውን የማስተካከያ ሥራ እንዲሰራ አሳስብዋል።

የውስጥ አሠራርና የተቀመጡ የሥራ አቅጣጫዎች በተግባር መተርጎማቸውን በማጣራት የተገኙ ጥንካሬዎችና ክፍተቶች በቀጣይ የሥራ ሂደት የሚመሩበት ግብዓት እንደሚሆኑም ተመላክቷል።

በመድረኩ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሰረት ሽፋ፣ የዞኑ ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዳነ ተሰማ፣ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ ፈይሳ እና የፓርቲ አመራሮች ተገኝተዋል።

የሀገር ሕልውና እና የሉዓላዊነት መስመርአዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በትናንትናው ዕለት መንግሥት ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ኢትዮጵያ የሕልውናዋ እና የሉዓላዊነቷን ቀይ መስ...
02/10/2026

የሀገር ሕልውና እና የሉዓላዊነት መስመር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በትናንትናው ዕለት መንግሥት ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ኢትዮጵያ የሕልውናዋ እና የሉዓላዊነቷን ቀይ መስመር በግልጽ ያሰመረችበት ታሪካዊ ክስተት ነው።

ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘው ኤምባሲዋ እንዲዘጋ የወሰነች ሲሆን÷ 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶችም በ48 ሰዓታት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥታለች፡፡

ይህ የመንግሥት ውሳኔም የሀገርን ሉዓላዊነት እና የሕዝብን ደህንነት ለማስከበር የተወሰደ ወሳኝ እንዲሁም የማይናወጥ ቁርጠኝነት ማሳያ ነው።

ኢትዮጵያ ሁልጊዜም ቢሆን ከጎረቤት ሀገራት ጋር ላላት ሰላማዊ አብሮ የመኖር መርሕ፣ ለጋራ እድገት እና ለቀጣናዊ መረጋጋት በስፋት ስትሰራ ቆይታለች፡፡

ይሁን እንጂ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት እና የሰላም እጅ መዘርጋት የሚኖረው ዋጋ የሀገር ሕልውና፣ ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ውስጥ እስከማይገባበት ድረስ ብቻ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳመላከተው÷ ይህን ጠንካራ ርምጃ የተወሰደው ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመችው ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ የጠብ አጫሪነት እንዲሁም የትንኮሳ ድርጊቶች ምላሽ ለመስጠት ነው።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ መንግሥት ዲፕሎማሲያዊ ጥሰት የፈጸሙ አሕመድ ሞሐራን አሕመድ ሶሊማን የተባሉ የግብጽ ዲፕሎማት በ48 ሰዓታት ውስጥ ከሀገር ለቅቀው እንዲወጡ አሳስቧል፡፡

የሀገርን ደህንነት የማስከበር ሕገ መንግሥታዊ እና ታሪካዊ ኃላፊነት የተጣለበት የመንግሥት አካል የሀገሪቱን ሰላም የሚፈታተኑ ድርጊቶች ሲፈጸሙ ዝም ብሎ አይመለከትም፡፡

የቪዬና የዲፕሎማሲ ስምምነትን በመጣስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሆኑ ዲፕሎማቶችን ሀገር እንዲለቁ መደረጉ ሕግን እና ዓለም አቀፍ አሰራርን ተከትሎ የተወሰደ ሕጋዊ ርምጃ ነው።

ዲፕሎማሲ የሀገርን ጥቅም የማስከበሪያ መሳሪያ እንጂ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ሴራዎች የሚሸሸጉበት ሽፋን ሊሆን አይችልም። የዲፕሎማሲያዊ መብት እና አሰራርን ተገን በማድረግ በሀገር የውስጥ ጉዳይ እና ደህንነት ላይ አደጋ መፍጠር ዓለም አቀፍ ህጎችን የሚጥስ ተግባር ነው።

በመሆኑም የመንግሥት ውሳኔ የኢትዮጵያን ክብር የሚያስጠብቅ፣ የሕዝብን ደህንነት የሚያረጋግጥ እና የማንኛውንም ወገን ትንኮሳ በጽናት የሚመክት ወቅታዊና አስፈላጊ ርምጃ ነው።

የኢትዮጵያ መንግሥት አለመግባባቶች በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ ያለው ጽኑ ፍላጎት ኢትዮጵያ ለሰላም ያላትን ዝግጁነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡

የተላለፉት ውሳኔዎችም ኢትዮጵያ በሉዓላዊነቷ እና በብሔራዊ ደህንነቷ ላይ ምንም ዓይነት ድርድር እንደማታደርግ ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እና ለቀጣናው ሀገራት ግልጽ መልዕክት ያስተላለፈ ሆኗል፡፡

የሀገርን ሉዓላዊነት ማስከበር የሁልጊዜም ቅድመ ሁኔታ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት በሀገር ሕልውና ጉዳይ ላይ ያላቸው አንድነት እና ጽናት ምንጊዜም የማይነቃነቅ የሀገራችን መደገፊያ ምሰሶ ሆኖ ይቀጥላል።

በዮናስ ጌትነት

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት የክልሉን አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በ7ኛ ዙር የመጀመሪያ...
02/10/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት የክልሉን አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በ7ኛ ዙር የመጀመሪያ ታሪካዊ መስራች ጉባዔው ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ያቀረቧቸውን የክልሉ አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፡-

1. ዶ/ር ደምሴ አድማሱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

‎ 2. ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ

3. አቶ ንጋቱ ዳንሳ - በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ

4. ዶ/ር ካርታ ካስኬ - የግብርና ቢሮ ኃላፊ

5. አቶ ዳዊት ዳሳለኝ - የጤና ቢሮ ኃላፊ

6. ወ/ሮ ወይኒቱ መልኩ- የባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ

7. ዶ/ር መስፍን መንዛ- የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

8. አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ - የመንግስት ኮምንኬሽን ጽ/ቤት አገልግሎት ኃላፊ

9. አቶ ብርሃኑ ዘውዴ- የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮምሽን ኮምሽነር

10. አቶ ተፈሪ አባተ- የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

11. አቶ ታደለ ወልደሚካኤል- የንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

12. ዶ/ር ዝናቡ ወልዴ- የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

13. አቶ መንግስቱ በየነ- ኢኖቬሽንና ቴክኖሎ ቢሮ ኃላፊ

14. አቶ ኤካል ኔትር- መስኖና ቆላማ ቢሮ ኃላፊ

15.ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ- የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ

16. አቶ ሙሉቀን ታደሰ- የፍትህ ቢሮ ኃላፊ

17. ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ- የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ

18. አቶ አቤነዜር ተረፈ - የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ

19/ አቶ ተወልደ ተስፋዬ - የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ

20. ዶ/ር አልማዝ ባልታ - ፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ

21. ዶ/ር ሰለሞን ቡኬ - የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ

22. አቶ ወንድማገኝ ደግፊ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሾመዋል።

የካቢኔ አባላቱ በምክር ቤቱ ቃለ መሃላ በመፈፀም ስራቸውን በይፋ ጀምረዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  የህዝብን ድምጽ፣ ጥቅም እና ፍላጎት የሚያስተጋባ ቁልፍ ተቋም ነው:- ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር ) (መስከረም 22/2019)ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል  ህዝብ ተወካዮች...
02/10/2026

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህዝብን ድምጽ፣ ጥቅም እና ፍላጎት የሚያስተጋባ ቁልፍ ተቋም ነው:- ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር )

(መስከረም 22/2019)
ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለብልጽግና ፓርቲ አባላት በአሰራር እና በስነ-ምግባር ደንብ ላይ ያተኮረ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ እየተሰጠ ነው

በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር )በስልጠና መድረኩ ላይ እንደገለጹት በክልሉ የተሰጠንን የህዝብ አደራ በብቃት መወጣት ይኖርብናል ብለዋል።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊ እንድንሆን ህዝቡ ለሰጠን ይሁንታ ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህዝብን ድምጽ፣ ጥቅም እና ፍላጎት የሚያስተጋባ ቁልፍ ተቋም መሆኑን ዶ/ር ዲላሞ አብራርተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ አባላት የህዝብ ተወካይነት ኃላፊነታቸውን መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱን ህጋዊ እና ተቋማዊ ሚና መረዳት እንደሚጠበቅባቸው ዶ/ር ዲላሞ አመላክተዋል።

የህዝብ ተወካይነት እና የፓርቲ ዲሲፕሊን አክብሮ መስራት አብይ ጉዳይ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

የምክር ቤት አባላት ስራ ከመጀመራቸው በፊት ህጋዊ፣ተቋማዊ እና የህዝብ ተወካይነት ሚናቸውን በብቃት እንዲወጡ ለማስቻል የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ ስለመሆኑም ዶ/ር ዲላሞ ጠቁመዋል።

በምክር ቤቱ ስራ የተሳትፎ፣የዲሲፕሊን እና የተጠያቂነት ባህል እንዲጠናከሩ ማገዝ እንደሚገባም ዶ/ር ዲላሞ ጠቅሰዋል።

አቶ አሻድሊ ሀሰን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሰየሙአዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አቶ አሻድሊ ሀሰንን በድጋ...
02/10/2026

አቶ አሻድሊ ሀሰን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሰየሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አቶ አሻድሊ ሀሰንን በድጋሚ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በማድረግ ሰይሟል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በጉባዔው ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈፅመዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅራዕይ

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢሬቻ መልዕክት የተወሰዱ ነጥቦች፦********************✅ “ኢሬቻ ሰላም ነው! ገዳ ስልጣኔ ነው! የኢትዮጵያ ስልጣኔ አይቀሬ ነው!” የክ...
02/10/2026

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢሬቻ መልዕክት የተወሰዱ ነጥቦች፦
********************

✅ “ኢሬቻ ሰላም ነው! ገዳ ስልጣኔ ነው! የኢትዮጵያ ስልጣኔ አይቀሬ ነው!” የክረምቱ ጨለማ አልፎ የብራዋ ጀንበር ስትወጣ ኦሮሞ በአንድነት ወጥቶ የክረምቱን ጨለማ ያሳለፈውን ፈጣሪውን ያመሰግናል፤ ለሚመጣውም ጊዜ ተስፋን ይሰንቃል።

✅ ለኢትዮጵያ የሰነቅነው የብራ ራዕይ ጠንካራ አንድነት ላይ የተመሠረተች፣ ሉዓላዊነቷ የተከበረ፣ በስፋት የምታመርትና ማንኛውንም ዓይነት ፈተና የምትቋቋም ለአፍሪካ ግንባር ቀደም ተምሳሌት የሆነች ሀገር መገንባት ነው።

✅ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ፣ ሀገራዊ ምክክር በተሳካ ሁኔታ መከናወኑ፣ እንደ ማዳበሪያ ፋብሪካና የነዳጅ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መጀመራቸው የስልጣኔ ጀንበር ለኢትዮጵያ ብቅ እያለች ለመሆኗ ጥቂት ማሳያዎች ናቸው።

✅ የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ ወደ መልካው ተመልሶ ስርዓት ውስጥ መግባቱ፤ የሆራ ሀርሰዴ ኢሬቻ ደግሞ በቢሾፍቱ ውበት ደምቆ ከፍ ብሎ መከበሩ የኦሮሞ ህዝብ ባህሉንና እሴቱን ለማሳደግ ላነሳው ጥያቄ ምላሽ ናቸው።

✅ አሁን የምንገነባው ስልጣኔ በጥንታዊ እሴቶቻችን ላይ የተመሠረተ እንዲሆን በመደመር ፍልስፍና አቅደን ለጋራ እውቀት፣ ለጋራ ፍትህ፣ ለጋራ ልማትና ለጋራ ደህንነት ስርዓት እየገነባን እንገኛለን።

✅ መንገድ ስተው ከሀገራቸው በተቃራኒ ለቆሙ ወንድሞቻችን “ከሚያመሹበት የሚያድሩበት ቤት ይሻላል”፤ አሁንም ፊታቸውን ወደ ሰላም ከመለሱ የሰላም በር የተከፈተ ነው።

✅ ኦሮሞ በትግሉ ነፃ ወጥቷል፤ ከዚህ በኋላ በጠብመንጃ አፈሙዝና ከጠላት ጋራ በመወገን የሚመለስ የኦሮሞ ጥያቄ ፈፅሞ አይኖርም።

✅ ልክ ትናንት ኦሮሞ በአባቶቹ ደምና አጥንት ኢትዮጵያን እንደገነባ፣ ዛሬም የኢትዮጵያን ስልጣኔ ዕውን ለማድረግ ባለን ዕውቀት፣ አቅምና ሀብት ሁሉ ከሌሎች ወንድም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን በግንባር ቀደምነት ኢትዮጵያን እንድናፀና ጥሪዬን አቀርባለሁ።



አቶ አብዱላሂ አደን ዩሱፍ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሰየሙ አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ አብዱላሂ አደን ዩሱፍን የአስተ...
02/10/2026

አቶ አብዱላሂ አደን ዩሱፍ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሰየሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ አብዱላሂ አደን ዩሱፍን የአስተዳደሩ ከንቲባ አድርጎ መርጧል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መስራች ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችንም ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅራዕይ

ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሰየሙ አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 7ኛው የሥራ ዘመን 1...
02/10/2026

ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሰየሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 7ኛው የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት 1ኛ መስራች ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በጉባዔው ተስፋዬ በልጅጌን (ዶ/ር) በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መርጧል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅራዕይ

Address

Butajira

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የእንሴኖ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ዩኒት Enseno City Government Communication Unit posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የእንሴኖ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ዩኒት Enseno City Government Communication Unit:

Shortcuts

Share