YIDU Advert and Stage Organization

YIDU Advert and Stage Organization ይዱ የማስታወቂያ ስራዎች
ለማንኛውም የማስታወቂያ ስራዎች 0904827621

ዋል ደን ሜካፒ (Walden Makeup and Nail)💅ሜካፕ 💅ቅንድብ እና ሽፋሺፍት💅የእጅ እና የእግር ጥፍር 💅ሂና ለሰርግ ቀኖ ሙሽሮችን እና ሚዜዎችን ይመርብኝ ያለ አጃቢም ካላ ፣ለምሩቃን...
07/10/2023

ዋል ደን ሜካፒ (Walden Makeup and Nail)

💅ሜካፕ
💅ቅንድብ እና ሽፋሺፍት
💅የእጅ እና የእግር ጥፍር
💅ሂና

ለሰርግ ቀኖ ሙሽሮችን እና ሚዜዎችን ይመርብኝ ያለ አጃቢም ካላ ፣ለምሩቃን በደስታ ቀናቸው ፣ ለብራይድል እና ቀለል ላሉ ፕሮግራሞችም ቆንጆ ሜካፕ መስራት ጀምረናል
ይሄም ብቻ አይደለም ቤት ለቤት የማስዋብ የተመስገንበት ነዉ።

📍 አድራሻችን
ቁጥር 1, ሺንሺቾ ቁ.1.ቃ.ሕ.ቤ.ክያን ፊትለፊት
ቁጥር 2, አዲስአበባ ቦሌ
ቁጥር 3, ወላይታ ሶዶ
ቁጥር 4, ዱራሜ

ለበለጠ መረጃ:- ስልክ
📞0994938351
📞0940093344
ይደውሉ ያሉበት ቦታ ድረስ በምምጣት ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን!
YIDU AdYIDU Advert and Stage Organization YIDU Advert and Stage OrganizationaYIDU Advert and Stage OrganizationOYIDU Advert and Stage OrganizationzYIDU Advert and Stage Organizationp

YIDU Advertበበርካታ መንገዶች ልምድ እንዳገኝ ተሰጥኦን እንዳሳድግ እና በተለያዩ ነገሮች እየደገፈችሁኝ ስላላችሁ ስለምታበራታቱኝ በተሰጥኦኤ አምናችሁ ስለምታሰሩኝ ከልብ አመሰግናለሁ ።ተ...
05/10/2023

YIDU Advert
በበርካታ መንገዶች ልምድ እንዳገኝ ተሰጥኦን እንዳሳድግ እና በተለያዩ ነገሮች እየደገፈችሁኝ ስላላችሁ ስለምታበራታቱኝ በተሰጥኦኤ አምናችሁ ስለምታሰሩኝ ከልብ አመሰግናለሁ ።
ተካልኝ ኤልያስ
ገብርኤል GB
ፍፁም ብርሃኑ
ወርቁ ጉርማሞ
ስንሻው ገ/ማሪያም
ሙሉቀን ጸጋዬ
ይቻላል ኢንተርናሽናል ሆቴል
ዋቸሞ ዩንቨርስቲ ዱራሜ ካምፓስ (ሚኒ ሚድያ )
የሺንሺቾ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት
የቃጫ ቢራ ወረዳ አስተዳደር
YOM STUDIO
ሰርከስ ሺንሺቾ
ሾኦሊን ኩንጉፋ ሳንዳ እና ክክ ቦክስ ማሰልጠኛ ዱራሜ
ራዲ ዉሹ ማርሻል አርት አካዳሚ ሺንሺቾ

እንዲሁም ስማችሁን ያልገለፀነችሁ ሁላችሁም እግዚአብሔር ይስጥልኝ ! 🙏🙏🙏

በድርጅታችን ታሪክ ሁሌም በደማቅ ስማችሁ ይወሳል
@followersi@highlightDYIDU Advert and Stage OrganizationvYIDU Advert and Stage OrganizationdYIDU Advert and Stage OrganizationaYIDU Advert and Stage OrganizationgYIDU Advert and Stage Organizationinshicho Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የመውሊድ በዓል ረቡዕ ይከበራል!!የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1498ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዓወ) የመውሊድ በዓል የፊታችን ረቡዕ መስከረም 16/2016 በታላቁ አንዋር መስ...
25/09/2023

የመውሊድ በዓል ረቡዕ ይከበራል!!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1498ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዓወ) የመውሊድ በዓል የፊታችን ረቡዕ መስከረም 16/2016 በታላቁ አንዋር መስጂድ እንደሚከበር አስታውቋል።

ለበዓሉ አከባበር ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከታላቁ አንዋር መስጂድ ጋር በቅንጅት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።

በዓሉ ረቡዕ ከጠዋት አንስቶ እስከ ቀን 7:00 ሰዓት ድረስ በታላቁ አንዋር መስጂድ እንደሚከበር ተመላክቷል። ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳት የተራቡትን በማብላት መሆን እንዳለበትም መልዕክት ተላልፏል።

YIDU Advert and Stage Organization

 በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች የእርቃን ምስሎች ስፔን ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠሩ ሲሆን ፖሊስ ምርመራ ላይ ነው።በደቡባዊ ስፔን ውስጥ የምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተ...
25/09/2023



በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች የእርቃን ምስሎች ስፔን ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠሩ ሲሆን ፖሊስ ምርመራ ላይ ነው።

በደቡባዊ ስፔን ውስጥ የምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተማ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች እርቃን ምስሎች ከእነርሱ እውቅና ውጭ በማኅበራዊ ሚዲያ ከተዘዋወሩ በኋላ ድንጋጤ ውስጥ ገብታለች ሲል ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

እርቃን ምስሎቹ የተሰሩት ሙሉ ልብስ ለብሰው የተነሱትን የታዳጊዎቹን ፎቶ በመጠቀም ነው።

በርካታ ምስሎቹ የተወሰዱትም ከታዳጊዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ነው።

ምስሎቹ ከተወሰዱ በኋላም አንድ ግለሰብ እርቃኑን ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ምናባዊ ምስል የሚፈጥር መተግበሪያ በመጠቀም የታዳጊዎቹ ምስል እርቃን እንዲቀር ተደርጓል።

እስካሁን ዕድሜያቸው በ11 እና በ17 ዓመት መካከል የሚገኙ 20 ታዳጊ ሴቶች፣ የዚህ ድርጊት ሰለባ መሆናቸውን በመግለጽ በደቡብ ምዕራብ ግዛቷ ባዳጆዝ ውስጥ በምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተማ እና አቅራቢያው ሪፖርት አድርገዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ የተጋሩት ሐሰተኛ የእርቃን ምስሎች በታዳጊ ሴቶቹ ላይ የተለያዩ ተፅዕኖዎችን አሳድረዋል።

የተወሰኑ ታዳጊዎች ከቤታቸው ለመውጣት እንደተሳቀቁ ተነግሯል።

ይህ ጉዳይ ወደ አደባባይ የወጣው ከታዳጊዎቹ ሴቶች መካከል የአንዷ እናት በሆነችው የማሕጸን ሐኪም ማሪያም አል አዲብ ምክንያት ነው።

አዲብ ማኅበራዊ ሚዲያዋን በመጠቀም ባወጣችው መልዕክት ምክንያት ጉዳዩ የስፔን ሕዝብ መነጋጋሪያ መሆን ችሏል።

አዲብ ታዳጊ ሴቶችንና ወላጆችን ለማረጋጋት ስትል በማኅበራዊ ሚዲያ ባጋራችው ቪዲዮ " የወጡት የAI ምስሎች የተፈጠሩት በበጋ ወቅት ቢሆንም ጉዳዩ ወደ አደባባይ የወጣው በቅርብ ቀናት ነው " ብላለች።

" ምን ያህል ሕጻናት ምስሎቹ እንደነበራቸው አናውቅም። ምስሎቹ የወሲብ ፊልም በሚጫንባቸው ገጾች ላይ ተጭነው እንደሆነም አናውቅም ነበር። ይህ ሁሉ ስጋት ነበረብን " ብላለች።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች እርቃን ምስሎችን ባማውጣት የተጠረጠሩ ታዳጊዎች ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 14 የሚደርስ ነው።

ፖሊስ ድርጊቱን እየመረመረ ሲሆን ምስሎቹን በመፍጠር ሒደት ውስጥ አሊያም በማኅበራዊ ሚዲያዎቹ #ዋትስአፕ እና #ቴሌግራም በማጋራት ተሳትፈዋል ያላቸውን ቢያንስ አስራ አንድ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ታዳጊ ወንዶችን መለየቱን አስታውቋል።

መርማሪዎች ታዳጊ ወንዶቹ ሐሰተኛ ምስሎችን በመጠቀም ታዳጊ ሴቶቹን #በማስፈራራት ማግኘት የፈለጉት ነገር ስለመኖሩ ለማወቅ ምርመራ እያካሄዱ ነው።

YIDU Advert and Stage Organizationአድራሻ ሺንሺቾ+251904827621EveryoneVisit KembataEthio telecom
24/09/2023

YIDU Advert and Stage Organization
አድራሻ ሺንሺቾ
+251904827621
Everyone

Visit Kembata
Ethio telecom

24/09/2023

✅ በዛሬው የ ኮምፒውተር ትሪክ የምናየው እንዴት በቀላሉ ዊንዶውስ ጄኒውን (እውተኛ) እንደምናደርግ ነው ::

ጄኒውን ማድረግ ማለት original የ window CD በምንገዛበት ጊዜ አብሮት የሚሰጠንን product key በምናስገባበት ጊዜ ጄኒውን ያደርገዋል። ኦርጅናል ካልሆነ ግን በተለያየ መንገድ ማድረግ ዘዴዎች አሉት።

የ Genuine አስፈላጊነት የ ፕሮግራሙ አምራች የሆነው ማይክሮሶፍት እንዲያቀው እና የፈለግነውን ሶፍትዌር እንድንጭን እንዲሁም የ ኮምፒዩተራችንን ደህንነት በ ማይክሮሶፍት እንዲጠበቅ ይረዳናል።

Genuine ወይም Activate ያልሆነ ኮምፒዩተር ከታች የ ሰአት ቦታው አከባቢ ምልክት ያሳየናል። አለበለዚያም setting ውስጥ ገብተን update and privacy የሚለው ውስጥ ስንገባ እናገኘዋለን።

ለዛሬ የ window እናያለን!

1. በመጀመሪያ (cmd) ብለን ሰርች ባር ላይ ትጸፋለችሁ በመቀጠል Right click the Command Prompt listing and select “Run as Administrator” ራይት ክሊክ አድርጋችሁ ራን ቱ አድሚንትሬተር የሚለውን ትጫናላችሁ።
2. ዊንዶው ላይ “SLMGR -REARM” ብላችሁ ትጽፋላችኁ ከዛ
ኢንተርን እንጫናለን command successfully executed. Restart now የሚቀጥለው ሜሴጅ ሲመጣ ኮምፒውተራችንን restart ok እናደረጋለን።

YIDU Advert and Stage Organization
Everyone

እጅግ ድንቅ በሆኑ ትላልቅ ሀገሪኛ ፊልሞች እና ቲያትሮች ታደሚያንን እና ተመልካቾቻቸውን ቁጭ ብድግ ያሰኙ ታላላቅ አርቲስቶች የጥበብ ሥራዎቻቸውን ለማቅረብ አነሆ ዱራሜ ከትመዋል 😍 ነገ ወደ ...
23/09/2023

እጅግ ድንቅ በሆኑ ትላልቅ ሀገሪኛ ፊልሞች እና ቲያትሮች ታደሚያንን እና ተመልካቾቻቸውን ቁጭ ብድግ ያሰኙ ታላላቅ አርቲስቶች የጥበብ ሥራዎቻቸውን ለማቅረብ አነሆ ዱራሜ ከትመዋል 😍
ነገ ወደ የከንባታ ዞን ባህል አዳራሽ ጎራ ብለው የጥበብ ድግሱን ይታደሙ

በዕለቱ ከ ቲያትር፣ ግጥሞች፣ ጭውወቶች ና ወጎች ጥቂቶቹ ናቸው።

📅 ነገ እሁድ 8:00 ስዓት

አዘጋጅ :- ሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር ከፕሮሞተር ቤቲ ጋር በመተባበር

ሄኖሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር/ Henon Charity Associationጎሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር/ Henon Charity Associationድሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር/ Henon Charity Associationህሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር/ Henon Charity Associationሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር/ Henon Charity Associationeሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር/ Henon Charity Associationhሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር/ Henon Charity Associationsሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር/ Henon Charity AssociationYIYIDU Advert and Stage OrganizationdYIDU Advert and Stage OrganizationnYIDU Advert and Stage OrganizationtYIDU Advert and Stage OrganizationrYIDU Advert and Stage Organization

በጤና እና በህይወት ዘመን አገልግሎት ዘርፍ የመሳላ አዋርድ ያሸነፉት ፕሮፌሰር Biruk Lambisso Wamisho  ፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ እና ያስሸለሟቸው  ዋና ዋና አገልግሎቶቻቸው፦-25...
23/09/2023

በጤና እና በህይወት ዘመን አገልግሎት ዘርፍ የመሳላ አዋርድ ያሸነፉት ፕሮፌሰር Biruk Lambisso Wamisho

ፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ እና ያስሸለሟቸው ዋና ዋና አገልግሎቶቻቸው፦

-25 ዓመት(ከ1998ዓ.ም ጀምሮ)የሕክምና፣የምርምር፣ ሀኪሞችን የማስተማርና የመምራት አገልግሎት

-በነዚህ አመታት ሀገራችን ባለፈችባቸው በሁሉም ጦርነቶችና ግጭቶች የጉዳት ሰለባ የሆኑትን በኦፕራሲዮን በማከም፣በየግንባሩ በመዝመት፣በማስተባበር፣ውድ የአጥንት ሕክምና ዕቃዎችን ባላቸው ስምና መልካም ግንኙነት ውጭ ሀገር ካሉ ወዳጆቻቸውና ኩባንያዎች በነፃ ወደሀገራችን የተለያዮ ሆስፒታሎች አስመጥቶ በነፃ ማከፋፈል
(የዱራሜ ሆስፒታልን ጨምሮ 15 የአጥንት ህክምና ማዕከላት አቋቁመዋል)

-በሀገሪቱ ትልቁንና ብቸኛውን የአጥንት የሰብ-እስፔሻሊስትና የስፔሻሊስቶች ማሰልጠኛ ተቋም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚገኘውን በከፍተኛ ውጤታማነት ከበርካታ አመታት ጀምሮ አሁንም መምራት
-ከ20 ሺህ በላይ ከባባድ በኦፕራሲዮኖች ማድረግ

-ከ250 በላይ የአጥንት ቀዶ ሕክምና እስፔሻሊስት ሐኪሞችን በአመራር ዘመናቸው አሰልጥነው አስመርቀው ዕቃ አስታጥቀው ወደ መላ የሀገራችን ክፍሎች በማሰማራት በተለይ በነዚህ የግጭትና የጦርነት ዓመታት በከፍተኛ ብቃት እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ሀላፊነታቸውን መወጣት ላይ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰር እጁን ይዞ ያላስተማረው እውቅ የአጥንት ሐኪም የለም።

*የባድመ ጦርነት የሰኔ 16ን የቦንብ አደጋን የመሰሉ በርካታ ፍንዳታ ሰለባዎችን ማከም በቅርቡ የሰሜኑ ግጭቶች ሁሉም ላይ በህክምና መሳተፍ የዘወትር ስራቸው ነው።

-65 ከፍተኛ የምርምር ስራዎችን ጨርሰው አሳትመዋል።ሁለት መፅሐፍ ፅፈዋል።

-በነፃ ማገልገሉ ሁለት ጊዜ የከምባታን ሕዝብ በፌደራል ፓርላማ መወከልን፣የኢትዮጵያን ሕክምና ማህበርን ሁለት ተርም መምራትን፣የኢትዮጵያ የአጥንት ሕክምና ማህበርን ሁለት ተርም መምራትን፣በኢትዮጵያ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስቶች ማህበርን ሁለት ጊዜ መምራትን፣የፌደራል የሕክምና ስህተት አጣሪ ኮሚቴን ለ10 ዓመት መምራትንና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል

-በኮቪድ አስቸኳይ ጊዜ ወቅትና በተለያዮ State of Emergency ወቅት ዘመቻዎችን በቦርድ አባልነት በመምራት በፈተናዎች ወቅት በቁርጠኝነት አገልግለዋል።

-የመጀመሪያውና ብቸኛው ኢትዮጵያዊ የአጥንት ሕክምና ፕሮፌሰር ናቸው።

-በኢትዮጵያ ፓርላማ ከባድና ውስብስብ ኦፕራሲዮን በማድረግ ብሔራዊ ተሸላሚ።

-በዓለም መድረክ በምርምር ስራቸውና በህክምና አገልግሎታቸው በርካታ ሽልማቶችን ለሀገራችን አስገኝተዋል።

-በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ የሀገሪቱን መሪዎች በፓሊሲ ላይ ማማከር ማማከርና አቅጣጫ ማሳየት የዘወትር ስራቸው ነው።

-ባላቸው የውጭ ሀገር መልካም ግንኙነት በብዙ ሚሊየኖች የሚገመቱ የአጥንት ሕክምና ዕቃዎች በነፃ ለሀገራችን አስገኝተዋል

-በነፃ ማገልገል ምርጫቸው ሲሆን ለዚህም ማሳያና ምሳሌ ለመሆን ከፓርላማ የሕዝብ ውክልና ምንም ደሞዝ/ክፍያ አይቀበሉም፣መኪና ነዳጅ ጥቅማጥቅም አይቀበሉም፣ከየትም ምንም አበል አይቀበሉም አይወዱም(የደሀ በጀት በዓበል አይነካ ይላሉ)፣ቤትና መሬት ስጦታ ምናምን አይቀበሉም።ጤናና ብቃት ፈጣሪ ሠጥቶኛል ሠርቼ ማግኘት ብሎም ማካፈል እችላለሁ ብለው በዞናችን ወይም ስለጥሩ ጉዳይ የትም ቦታ መዋጮ ካለ ያዋጣሉ። ሁሉም ሳይሆን ፌስቡክ ላይ የሚለጠፈውን በአመት ለተለያየ ያዋጡትን ብንደምር አሀዙን ማየት ይቻላል።

ከላይ በተዘረዘሩት እና በርካታ መልካም ስራዎች በጤና እና በህይወት ዘመን አገልግሎት ዘርፍ የመሳላ አዋርድ አሸናፊ ሆነዋል።

እንኳን ደስ አሎት!

ሳይንቲስት ኢንጂነር Getahun Heramo  ተመራማሪ፣ ደራሲ፣ የፈጠራ ባለቤት፣ ምሁር ባለ ሐብትና ኬሚካል ኢንጅነር ናቸው። ኢንጅነር ጌታሁን ሄራሞ ለአንድ መቶ ዓመታት ያህል ሀገራችን  ከ...
23/09/2023

ሳይንቲስት ኢንጂነር Getahun Heramo ተመራማሪ፣ ደራሲ፣ የፈጠራ ባለቤት፣ ምሁር ባለ ሐብትና ኬሚካል ኢንጅነር ናቸው። ኢንጅነር ጌታሁን ሄራሞ ለአንድ መቶ ዓመታት ያህል ሀገራችን ከውጭ ሀገር ስታስገባ የነበረውን የሕትመትና የሠዓሊ ቀለሞችን ቀመር በብቸኝነት በሀገር ውስጥ በመቀመር ኢትዮጵያ ውስጥእንዲመረት ያደረጉና ለነዚሁ ምርቶች የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ያስቀሩ የቀለም ፎርሙሌሽን የፈጠራ ስራ ባለቤት ናቸው።

በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተለይም የሕትመትና የሠዓሊ ቀለማት የሚያመርቱ እጅግ በጣም ጥቂት ኩባንያዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ሆኖም ሁሉም በሚባል ደረጃ በውጭ ሀገር በተለይም በአውሮፓና በሕንድ ባለሙያዎች የተቀመሩ ናቸው፤ ስለዚህም አሁን ባለው መረጃ በምሥራቅ አፍሪካም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ደረጃ አኳያ ኢንጅነር ጌታሁን ሄራሞ ብቸኛው ሀገር-በቀል የሕትመትና የሠዓሊ ቀለሞች ኢትዮጵያዊ ፎርሙለተርና አምራች መሆናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል።

ከመደበኛ ሙያቸው ባሻገር ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች ሀሳብን በሀሳብ በመሞገት ይታወቃሉ። የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸውን በመጠቀምም የአዲስአበባ ከተማ ታሪካዊ ሕንፃዎች የቀለም ዕድሳትና የከተማው የቀለም ዲዛይን ሙያውን በተከተለ መንገድ እንዲከወን በመሞገት በከተማው ከንቲባ ፅ/ቤት ተቀባይነትን ያገኘ ውጤታማ ሥራ ሰርተዋል።
ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ የከምባታ እናት ፍሬ የሆነ ኩሩ ኢትዮጵያዊም ናቸው። ሳይንቲስት ጌታሁን ሄራሞ በሳይንሱ ዘርፍ ባደረጉት የፈጠራ ሥራ ቀደም ሲልም የተለያዩ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ሽልማቶችን ተጎናፅፈዋል።

1. ከኢትዮጵያ ኬሚካል መሐንዲሶች ማሕበር "Industrial Innovation Award" በሚል ሽልማት አግኝተዋል።
2. ከዓለም ባንክ (World Bank) Best Business Idea Award for the Successful Import Substitution በሚል ከፍተኛና አለም አቀፋዊ ሽልማት ተጎናፅፈዋል።

3. ጄኔቫ ከሚገኘው ከዓለም አቀፍ የአዕምሮ ንብረት ጥበቃ ፅ/ቤት (WIPO....World Intellectual Property Office) ቢሮ "Best Ethiopian Inventor for Successful Import Substitution Research on Local Manufacturing" በሚል ከፍተኛ ሽልማትም ተጎናፅፈዋል። ይህን ከጄኔቫ የተላከውን ሽልማትም ኢንጂነሩ የተቀበሉት ከወቅቱ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ከክቡር ግርማ ወ/ጊዮርዮስ እጅ ነበር።

4. ከተባባሩት የዓለም መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም. የወቅቱ ጠ/ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በተገኙበት የኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ የቀለም ፋብሪካ ምርጥ የዓመቱ መካከለኛ እንዱስትሪ በመባል ተሸልሟል።

ባለ ምጡቅ አእምሮ ሳይንቲስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ካሏትና ማህፀን ለምላሟ የከምባታ እናት አምጣ ከወለደቻቸው ምርጥ የሀገር ውስጥ ምሁሮች አንዱና ዋነኛው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥም የቀለም ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ሥነ ልቦናዊ ተፅዕኖዎች ዘመናዊ በሆነ መልኩ እንዲጠኑ መሠረት የጣሉ የኬሚካል መሐንዲስም ናቸው።

ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ የጠቅላይ ሚኒስትር የዶ/ር አብይ አህመድ ቢሮን ጨምሮ ለሚኒስትሮችና ለከፍተኛ ባለስልጣናት በተለያዩ ጊዜዎች ከሙያቸው ጋር በተገናኘ በቢሮ አደረጃጀትና የቀለም ሥነ ልቦናዊ ተፅዕኖዎች ዙሪያ ሥልጠናዎች ሰጥተዋል።

በአሁኑ ወቅት ሳይንቲስት ኢ/ር ጌታሁን ሄራሞ በመጀመሪያ ሴት ልጁ ስም የተሰየመና በንግድና እንዱስትሪ ሚኒስትሪ ዕውቅና ተሰጥቶት የተመዘገበ የ"ኒታ የቀለም ፋብሪካ" ባለቤት ናቸው። ኒታ የሚለው ቃል በከምባቲሳ የኛ ማለት ነው። ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ የሁለት ሴቶችና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ሲሆኑ የሶስቱም ልጆቻቸው ስም የተሰየመው በከምባቲሳ ነው... እነሱም ኒታ ጌታሁን፣ ዊማ (መሉ) ጌታሁን እና ቤሃም (የማካፈል ሕይወት) ጌታሁን። ስለዚህም ኢንጂነሩ የእኛ የእነርሱ የሁሉም ዕንቁ ናቸው።

ከሥነ ፅሁፋዊ አስተዋፅኦ አኳያም ኢንጂነር ጌታሁን "የለማኙ ሎጂክ" የተሰኘ መንፈሳዊ መፅሐፍ ደራሲም ናቸው። አባል በሆኑበት የመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያንም ከልጅነታቸው ጀምሮ በዝማሬ፣ በስብከትና በሙዚቃ መሳሪያ አምላካቸውን እስከ ዛሬም ድረስ እያገለገሉ ይገኛሉ። በተለያዩ ሀገር አቀፍ ሚዲያዎች በሚቀርቡበትም ወቅት ለስኬታቸው ሁሌም በምክንያትነት የሚጠቅሱት የሚያገለግሉትን እግዚአብሔርን ነው።

ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ ከላይ በተዘረዘሩ እና በርካታ መልካም ስራዎች በሳይንስ ዘርፍ የራሳቸውን ታላቅ ሀገራዊና አህጉራዊ አስተዋጽኦ በማበርከታቸው የዘንድሮው የመሳላ አዋርድ አሸናፊ ሆነዋል።

Congratulations!

Via Visit kembataa

ታላቅ የበጎ አድራጎት ድግስ በሺንሺቾ ከተማ አናሲሞስ በጎ አድራጎት ማህበር  ዕለተ ቅዳሜ ከ ቀኑ 7:30 ጀምሮ ከ ብርሃን ባንክ ጎን በሚገኘው ሜዳ ላይ ።  በ ዕለቱ   ለአቅመ ደካማ ቤተሳ...
22/09/2023

ታላቅ የበጎ አድራጎት ድግስ በሺንሺቾ ከተማ
አናሲሞስ በጎ አድራጎት ማህበር ዕለተ ቅዳሜ ከ ቀኑ 7:30 ጀምሮ ከ ብርሃን ባንክ ጎን በሚገኘው ሜዳ ላይ ።
በ ዕለቱ
ለአቅመ ደካማ ቤተሳቦች የአስቤዛ ፣ የታረዙትን የመልበስ ፣ እና ለተማሪዎች የደብተር እና እስኪሪቢቶ
መቅረት አይቻልም!!!

YIDU ADVERTISING AND STAGE ORGANIZATION ለተለያዩ የማስታወቂያ ስራዎች እንዲሁም ላላችሁ ሃሳብ እና አስተያየት  ይደውሉልን +251904827621YIDU Advert and...
22/09/2023

YIDU ADVERTISING AND STAGE ORGANIZATION
ለተለያዩ የማስታወቂያ ስራዎች እንዲሁም ላላችሁ ሃሳብ እና አስተያየት
ይደውሉልን +251904827621
YIDU Advert and Stage Organization
https://t.me/Yidu_advert

https://t.me/Yidu_advertt

Share እና like በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ 🙏🙏🙏

Address

Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when YIDU Advert and Stage Organization posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to YIDU Advert and Stage Organization:

Share