ETHIO BEST ኢትዮ ቤሲት

ETHIO BEST  ኢትዮ ቤሲት ➥ ✍️ፀሐይዋ ስትጠፋ አትፍራ ምክንያቱም ከዋክብት ይወጣሉና‼️

27/09/2024
ኢትዮጵያ ኮከብ ተጨዋቿን አጣች!አዲሱ ሙሽራ ማረፉ ተሰምቷል !በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።በቅርቡ የጋብ...
27/03/2024

ኢትዮጵያ ኮከብ ተጨዋቿን አጣች!

አዲሱ ሙሽራ ማረፉ ተሰምቷል !

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን የፈፀመው አዲሱ ሙሽራ ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ።

ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው፤ ለሀዋሳ ከተማና አሁን ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎት ሰጥቷል።

አመለ ሸጋው ተጨዋች አለልኝ አዘነ ላለፉት ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት ክለቡንና ሀገሩን እያገለገለ የሚገኝ ወጣት ተጨዋች ነበር።

(ባላገሩ ቴሌቪዥን)

2 የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወንዝ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አለፈ።በዎላይታ ዞን " ሁምቦ " እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ዳርቻ ፎቶግራፍ በመነሳት ላይ የነበሩ ሁለት ተ...
10/12/2023

2 የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወንዝ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አለፈ።

በዎላይታ ዞን " ሁምቦ " እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ዳርቻ ፎቶግራፍ በመነሳት ላይ የነበሩ ሁለት ተማሪዎች ተንሸራተዉ ወደወንዙ በመግባታቸዉ ህይወታቸው አልፈዋል።

ሁለቱም ህይወታቸው ያለፈው የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች መሆናቸው ተነግሯል።

የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ለአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በጠየቀዉ ድጋፍ መሰረት የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች የወጣቶቹን አስከሬን ዛሬ ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም አዉጥተዉ አስረክበዋል።

ተማሪዎችና ወጣቶች ፎቶ ግራፍ ለመነሳትና ለመዝናናት በሚል ወንዝ አካባቢ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ መሰል አደጋዎች የሚያጋጥሙ በመሆኑ ወንዝ አካባቢና የመዋኛ ስፍራዎች አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው ያገኘው።

26/11/2023

Address

Sodo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ETHIO BEST ኢትዮ ቤሲት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share