Visit Wolaita

Visit Wolaita Promoting Culture, Investment Potential and Tourism diestination of Wolaita.

እንኳን ደስ አለን 🙌🌟 🎉🎉የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በዓለም ቅርስነት ተመዘገበበሕንድ፣ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የ...
10/12/2025

እንኳን ደስ አለን 🙌🌟 🎉🎉
የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ

በሕንድ፣ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ጥበቃ ኮሚቴ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ያቀረበችው የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በሰው ልጅ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ዝርዝር ስር ተመዝግቧል።

"ጊፋታ" በወላይታ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ በዓል ሲሆን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የሕዝቡ የማንነት መገለጫ የሆነ የአሮጌው ዓመት ማብቂያና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡

ጊፋታ እድሜ፣ ጾታ፣ ሃይማኖት ወይም ሌላ ማኅበራዊ ደረጃ ሳይለይ ለሁሉም ሠላም እና ማኅበራዊ ትሥሥር አስተዋጽኦ በማድረግ በዩኔስኮ የተለዩትን ዘርፎች ያካተተ ሁሉን አቀፍ ተግባራትን በማበረታታት የሚከበር በዓል መሆኑ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አስችሎታል።
ወላይታ ሚዲያ ኔትዎርክ
Following

ዮ ዮ ጊፋታ ❤💛🖤የ "ጊፋታ" በዓል መቃረቡን የሚያበስሩና በህዝቡ ዘንድ እጅግ የሚታወቁ በእንቅስቃሴያቸው ከወትሮ የተለዩ ገበያዎችም ያሉ ሲሆን እነሱም "ሃሬ ሀይቆ"፣ "ቦቦዶ"፣ "ጎሻ" በመ...
03/09/2025

ዮ ዮ ጊፋታ ❤💛🖤
የ "ጊፋታ" በዓል መቃረቡን የሚያበስሩና በህዝቡ ዘንድ እጅግ የሚታወቁ በእንቅስቃሴያቸው ከወትሮ የተለዩ ገበያዎችም ያሉ ሲሆን እነሱም "ሃሬ ሀይቆ"፣ "ቦቦዶ"፣ "ጎሻ" በመባል የሚታወቁ ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ "ቃኤ ጊያ" ይባላል::

ሃሬ ሀይቆ ገበያ (Hare hayiqo)፡- ቀጥተኛ ትርጉሙ የአህያ መሞቻ እንደ ማለት ሲሆን ይህም በወቅቱ አህያዎች ያለባቸውን ድካም ለማሳየት ነው፡፡ በዓሉ እየተቃረበ በመጣ ቁጥር ሁሉም ሰው ለበዓሉ ዝግጅት እህልና ሌሎችን ቁሳቁሶች ከአንዱ ቤት ወደ ሌላዉ ቤት እንዲሁም ከቤት ወደ ገበያ በአህዮች ስለሚወሰድ ይህንን ጊዜ ከሌላዉ የሚለየው አንድ አህያ በቀን ከሦስት ጊዜ በላይ እየጫነ ወደ ገበያ ሊመላለስ ይችላል፡፡

ቦቦዳ ገበያ (Bobooda)፡- ሁለተኛው በሃሬ ሀይቆ ሳምንት የሚውለው ገበያ ሲሆን ይህ ገበያ ከወትሮ ለየት ባለ መልኩ በተለየ ሁኔታ በአዳዲስ ክስተቶች የተሞላ ገበያ ነው፡፡ በዚህ ገበያ ገበያተኛው ከተለመደው ጊዜ ቀድሞ ወደ ገበያ የሚመጣበትና በአብዛኛው ሴቶች የሚበዙበት ነው፡፡ ሴቶች ለበዓሉ የሚያስፈልጉትን የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች የሚሸምቱበት ሆኖ በዚህ ገበያ የሸክላ ዕቃዎች ሽያጭና ግዢ በእጅጉ ይደራል፡፡ ከዚህም ሌላ በዓሉ እየተቃረበ ከመምጣት ጋር ተያይዞ ሰዎች ፍርሃት ፍርሃት የሚላቸው ጊዜ እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ የፍርሀቱ ምንጭም ከበዓሉ ትልቅነትና ስፋት አንጻር ምን ይጎልብኝ ይሁን በማለት ቤተሰቡ በሙሉ በፍርሃትና በጭንቀት የሚያሳልፍበት ወቅት ነው፡፡

ጎሻ (Gooshsha)፡- ሶስተኛው ሳምንት ገበያ ጎሻ ሲሆን ጥሬ ትርጉሙ እብደት እንደ ማለት ነው፡፡ ሰዎች ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ወደ ገበያ ይሰበሰባሉ፡፡ በገበያ ውስጥ እርስ በርስ የሚገፋፉበት፣ የሚገጫጩበት፣ እንደ እብድ የሚይዙትን የሚጨብጡትን የሚያጡበት ነገር ግን የማይቀያየሙበት የገበያ ውሎ ነው፡፡

ከጊፋታ የእርድ ቀን በኋላ ለሚቀጥሉት 15 ቀናት በየትኛውም አካባቢ ገበያ ስለማይኖር ለበዓሉና ለእነዚህ ጊዜያት የሚበቃ ቁሳቁስና እህል ተሟጦ የሚሸመትበት ነው፡፡ ስለሆነም ሁሉም ሰው በዚህ ሳምንት መረጋጋት የማይታይበት በጥድፊያና በችኮላ የተሞላበት ሳምንት በመሆኑ የዕብድ ገበያ ወይም የዕብደት ሳምንት ይባላል፡፡

ቃኤ ጊያ (Qa’’e Giyaa)፡- ሌላው የመጨረሻው ማሳረጊያ ቃኤ ጊያ የሚባል ሲሆን ይህም በእርድ እሁድ ዕለት ማለትም ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ከሌሊቱ 10:00 እስከ ከጧቱ 2:00 የሚቆም ሲሆን በዚህም ለበአሉ የሚያስፈልግ ሆኖ ድንገት የተረሳ ነገር ካለ የሚሸመትበት ገበያ "ቃኤ ጊያ" ተብሎ ይጠራል::

የጎሻ ሳምንት እየተገባደደ ሲመጣ የሚውለው ሐሙስ “ኮሴታ ሐሙሳ” (ሻጋ ጋላሳ) ይባላል; ትርጉሙ:- በአማርኛ የእንኩሮ ሐሙስ እንደማለት::

ዕለተ አርብ "ሱልኦ አርባ" ቢዛ ጋላሳ ሲሆን ይህም በየቤቱ ለቦርዴ የሚሆን እህል የሚያዘጋጅበት፣ ለሆድ ማሟሻ ጎዳሬ (Boynaa Cadhdhiyaa) እና ከቦዬ የሚዘጋጅ (Boyyinaa Piccatta) የሚበላበት ዕለት ነው::

ዕለተ ቅዳሜ "ባጭራ ቄራ" ተብሎ የተሰየመ ሲሆን፣ አዲሱ አመት "ሹዋ ዎጋ" የእርድ እሁድ ተብሎ ይጠራል::
ወላይታ ሚዲያ ኔትዎርክ

19/02/2024


  ...አንድ ባለ ባጃጅ ኮንትራት ብለነው ተሳፈርን በመንገዳችን ላይ እቃ ፈልገን ብዙ ሰኣት አቁመነው አንዴም ሳይሰላች ቦታ ሲያሳየን ቆይቶ በስተመጨረሻም የምንፈልግበት ካደረስን በኃላ  ሂሳ...
19/02/2024

...

አንድ ባለ ባጃጅ ኮንትራት ብለነው ተሳፈርን በመንገዳችን ላይ እቃ ፈልገን ብዙ ሰኣት አቁመነው አንዴም ሳይሰላች ቦታ ሲያሳየን ቆይቶ በስተመጨረሻም የምንፈልግበት ካደረስን በኃላ ሂሳብ ስንለው 20 ብር ክፈሉ አለን

ምነው ስንለው 'እንግዳን በታሪፉ ነው የምንወስደው '!

እኔስ ምን አልኩ እናመሰግናችኃለን::

COME TO THE CITY OF JOYVISIT LAND OF 50+ KINGS
10/02/2024

COME TO THE CITY OF JOY
VISIT LAND OF 50+ KINGS

በ“07 ቅምሻ ኮንሰርት” ዮዮ ጊፋታ ብለን በአብሮነት ደምቀን… ከጓደኞቻችን ጋር ጨፍረን… አሮጌውን ዓመት ሸኝተን አዲሱን ዓመት ከM-PESA ሳፋሪኮም ጋር እንቀበላለን። ሳፋሪኮም እና ሚዶ ሬ...
27/09/2023

በ“07 ቅምሻ ኮንሰርት” ዮዮ ጊፋታ ብለን በአብሮነት ደምቀን… ከጓደኞቻችን ጋር ጨፍረን… አሮጌውን ዓመት ሸኝተን አዲሱን ዓመት ከM-PESA ሳፋሪኮም ጋር እንቀበላለን። ሳፋሪኮም እና ሚዶ ሬከርድስ ያዘጋጁት መስከረም 19 በወላይታ ሶዶ ስቴዲየም የM-PESA ሳፋሪኮም ድግስ አይቀርም

በ250 ብር የመግቢያ ትኬቱን በM-PESA Safaricom ሲገዙ ትኬቱን ከነጻ የ100 GB ሳፋሪኮም ዳታ ጋር ያገኛሉ፤

እንዲሁም የመግቢያ ትኬቱን በወላይታ ሶዶ ከሚገኙ የM-PESA ሳፋሪኮም አከፋፋይ ሱቆች ማግኘት ይችላሉ

በተጨማሪ በር ላይ ትኬቱን በ500 ብር ያገኙታል ከ100GB የሳፋሪኮም ዳታ ጉርሻ ጋር።

 !በድጋሚ   እያልን መስከረም 18/1/2016 ዓ/ም በካዎ ኮይሻ ወረዳ የተዘጋጀውን   ለመሄድና ለመጫወት ከወዲሁ ዝግጅታችንን አጠናቀናል። የሚቀረን የእናንተው ተሳትፎ ብቻ ነው።   ❤❤❤ ...
25/09/2023

!
በድጋሚ እያልን መስከረም 18/1/2016 ዓ/ም በካዎ ኮይሻ ወረዳ የተዘጋጀውን ለመሄድና ለመጫወት ከወዲሁ ዝግጅታችንን አጠናቀናል። የሚቀረን የእናንተው ተሳትፎ ብቻ ነው።
❤❤❤

🖋መኪና ወይም ትራንስፖርት በነፃ
🖋ውሃና ምግብ በአቅማችን ልክ ሆኖ በነፃ
🖋ፎቶና Video በነፃ ስሆን
🖋 ቲ_ሼርት 400 ብር ብቻ መሆኑን እያሳወቅን ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ መመዝገብ የሚቻለው እስከ እሮብ 16/1/2016 ድረስ ብቻ መሆኑን እንገልፃለን።
ቲ_ሼርት የሚትፈልጉ ወጣቶች Size ከ400 ብር ጋር ከዚህ በታች ባለው በባንክ አካውንት አስገብታችሁ Screenshot ወይም የባንክ ደረሰኝ በinbox እንዲታስቀምጡልን እናሳስባለን።
👉 1000499386088 CBE
Buzayehu Buche
ለበለጠ መረጃ
ስልክ 0912496222
0916138849

የጉዞው አስተባባሪ

የባህልና ስፖርት ሚኒሰቴር ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ የተለያዩ የክልልና የዞን የመንግስት የሰራ አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶችና ከደቡብ ኢትዮጵያ  ክልል ከሁሉም ዞኖች የተወጣጡ የ...
24/09/2023

የባህልና ስፖርት ሚኒሰቴር ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ የተለያዩ የክልልና የዞን የመንግስት የሰራ አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶችና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሁሉም ዞኖች የተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ሶዶ ስታድየም ገብተው የጊፋታ በዓል መከበር ጀምሯል።

Address

S**o

Telephone

+251928660454

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Wolaita posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share