በጉራጌ ዞን የምሁር አክሊል ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Wolkite
  • በጉራጌ ዞን የምሁር አክሊል ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን የምሁር አክሊል ወረዳ  የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች  ጽ/ቤት ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለዜጎች!
(1)

በጉራጌ ዞን በምሁር አክሊል ወረዳ  የሐዋሪያት ከተማ የእሁድ ገበያ  የመስቀል በዓል ድባብ በፎቶ፦መስከረም 10/2019 ዓ.ም (ሐዋርያት)በገበያው የእርድ  ከብቶች፣ እንዲሁም ለመስቀል በዓል...
20/09/2026

በጉራጌ ዞን በምሁር አክሊል ወረዳ የሐዋሪያት ከተማ የእሁድ ገበያ የመስቀል በዓል ድባብ በፎቶ፦

መስከረም 10/2019 ዓ.ም (ሐዋርያት)

በገበያው የእርድ ከብቶች፣ እንዲሁም ለመስቀል በዓል አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች ቀርበው በዛሬው ቀን በደማቅ ሁኔታ ግብይት እየተከናወነ ይገኛል።

ለተጨማሪ መረጃ ምስሎችን ይመልከቱ!

የሳምንቱ አበይት ዜናዎችመስከረም 10/2019 ዓ.ም (ሐዋርያት)የ2019 የትምህርት ዘመንን ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን የምሁር አክሊል ...
20/09/2026

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች

መስከረም 10/2019 ዓ.ም (ሐዋርያት)

የ2019 የትምህርት ዘመንን ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን የምሁር አክሊል ወረዳ ትምህርት ጽ/ት ቤት አስታወቀ።

በምሁር አክሊል ወረዳ በሚገኘው ተ/ሃይማኖት አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2019 የትምህርት ዘመን በደመቀ ሥነ-ሥርዓት ወረዳዊ ት/ት የማስጀመር ስነ ስርዓት ተከናውኗል።

‎የሙህር እና አክሊል ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በዞናችን ካሉ መዋቅሮች በ2018 በጀት አመት አፈፃፀም 3ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ።

የምሁርና አክሊል ወረዳ የሐዋሪያት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 አዲሱ የትምህርት ዘመን ከ350 በላይ አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል የሚያስችለውን አስፈላጊ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ።

"ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ሀሳብ የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፓርት በመገምገም አመታዊ የጤና የጉባኤ መድረክ አካሄደ።

የ15 ኪሎሜትር የኬር ኦድ የጎዳና ላይ ሩጫ በወንዶች አትሌት አባይነህ አየን በሴቶች ደግሞ ማርታ ገ/ሚካኤል አንደኛ በመውጣት አሸናፊ ሆኑ።የ15 ኪሎ ሜትር የኬር ኦድ የጎዳና ላይ ሩጫ በአት...
20/09/2026

የ15 ኪሎሜትር የኬር ኦድ የጎዳና ላይ ሩጫ በወንዶች አትሌት አባይነህ አየን በሴቶች ደግሞ ማርታ ገ/ሚካኤል አንደኛ በመውጣት አሸናፊ ሆኑ።

የ15 ኪሎ ሜትር የኬር ኦድ የጎዳና ላይ ሩጫ በአትሌት አባይነህ አየን ከወላንዶ አትሌቲክስ ክለብ አሸናፊነ ሆኗል።

2ኛ በመሆን ያጠናቀቀው አትሌት አሰፋ ብርሀኑ ከአራዳ እንዲሁም 3ኛ በቀለ ሺፈራው ከኤልሞ ክለብ በአሸናፊነት ውድድራቸው አጠናቅቀዋል።

በሴቶች ደግሞ
1ኛ ማርታ ገ/ሚካኤል ከሀጎስ ክለብ
2ኛ ገላኒ በይሳ ከኦሮሚያ ፓሊስ
3ኛ መቅደስ ዋሌ ከግሎባል ስፖርት ኮሚኒኬሽን በመሆን አሸንፈዋል።

የ15 ኪሎ ሜትር የኬርኦድ የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ንቅየ ኬር ኦድ የጀፎረ ኑጫ በዊልቸር ዋትውዳድር ቋነሺም።መስከሮብ10/2019 ዘበር በጉራጔ ዞን በወርቅጥየ ከተማ ቲያሟሪ ያነዌ 6ተነ ማራ ንቅየ “ኬር ኦድ” የጀፎረ ኑጫ ውድድር በዊልቸር ቢ...
20/09/2026

ንቅየ ኬር ኦድ የጀፎረ ኑጫ በዊልቸር ዋትውዳድር ቋነሺም።

መስከሮብ10/2019 ዘበር

በጉራጔ ዞን በወርቅጥየ ከተማ ቲያሟሪ ያነዌ 6ተነ ማራ ንቅየ “ኬር ኦድ” የጀፎረ ኑጫ ውድድር በዊልቸር ቢያሮሰብ ዋትውዳድር ቋነሺም።

“ኔሁ ለኢትዮጵያ ሰላም ንሮጥነ” ቢብር ቃር ቲያሟሪ ያነዌ ንቅየ የጀፎረ ኑጫ ተትለያዮ የገነንዳ ክፍር የቸነዎ አትሌተንዳም የስፖርት ንማጀ ናነኖ ሰብ ባትሳትፎት ነረዊ ።

የዊልቸር ተወዳዳሪየንዳ ውድድር ወትቀረሰታ ተዀተሮምታ በሳና ይቅረዊ የ15 ኪሎ ሜትር የግሬድም የዴንጛ ዋና የጀፎረ ኑጫ ውድድር ቀሪዳር አክሽተዊ ይቋርሺቴ።

የ15 ኪሎ ሜትርዌ ውድድር ይትረሼ ከወርቅጥየ ዩኒቨርሲቲ ኸረምታነ ይጀፑርፗ ባሮክ ሆቴል ባምሮት ያሟሪቲኸር በውድድርዌ ይትሳተፎ አትሌት ሜናህኖ ጀፐሮም ይትረሶፗ ምልክት በቀረቦት ነረዎ።

በዝ ግዝየ የወርቅጥየ ከተማ ኸልቅም ተትልያየ መደር የቸነዎ የስፖርት ናማጂ ውድድርዌ ቲያደምቆ ያነዎ ቲኸር ኬር ኦድ የስፖርት ውድድር ብቻ ቴኸር የሰላም፣ የአትነት፣ የኸልቅ ትስስርም የከተማንዳ ባዘራ ተቀፐሮት ያትየዥ ንቅየኸረ ኤማኸረም ተረከበም።

በምሁር አክሊል ወረዳ የሚገኘው የ"ቃያ ገበያ" የመስቀል በዓል ድባብ በምስል፡-መስከረም 09/2019 ዓ.ም (ምሁር አክሊል ሐዋርያት)በገበያው የእርድ ከብቶች እና ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብ...
19/09/2026

በምሁር አክሊል ወረዳ የሚገኘው የ"ቃያ ገበያ" የመስቀል በዓል ድባብ በምስል፡-

መስከረም 09/2019 ዓ.ም (ምሁር አክሊል ሐዋርያት)

በገበያው የእርድ ከብቶች እና ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች ቀርበው በደማቅ ሁኔታ ግብይት እየተከናወነ ይገኛል።

ዘገባው የምሁር አክሊል ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በክልሉ ሁለንተናዊ ሰላምና እድገት ላይ የሚኖራቸው አበርክቶ የጎላ ነው-:ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መስከረም 8/2019 (ወልቂጤ)በ...
18/09/2026

የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በክልሉ ሁለንተናዊ ሰላምና እድገት ላይ የሚኖራቸው አበርክቶ የጎላ ነው-:ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

መስከረም 8/2019 (ወልቂጤ)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች የጋራ ፎረም ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ጉባኤው በክልሉ ሰላም እና ልማት ላይ የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ የጋራ ተግባቦት መፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል።

የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በክልሉ ሁለንተናዊ ሰላምና እድገት ላይ የሚኖራቸው አበርክቶ የጎላ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

በክልሉ በድህነት ውስጥ ያሉ የቤተሰብ አባላት እራሳቸውን እንዲችሉ መረዳጃ እየተቋቋመ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

በክልሉ በክረምት ወራት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት 2ሺ 7 ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ 2ሺ 6 ቤቶችን መገንባት መቻሉን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ከዚህ ውስጥ 1ሺ 885 ቤቶችን ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ማስረከብ ተችሏል፣
የተቀሩትን ደግሞ በዚህ ሳምንት ርክክብ እንደሚደረግ ጠቅሰዋል።

በቀጣይ ከህዳር አንድ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2019 ተመሳሳይ ቤቶች ለመገንባት መታቀዱን ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።

በሚቀጥሉት 5 እና ስድስት ዓመታት ከ20 እስከ 25 ሺ ቤቶች ይገነባሉ ሲሉም ጠቁመዋል።

ህዝባችንን ነጻ የማውጣት እና ሰላሙን የማረጋገጥ ስራ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው የምክክር ኮሚሽን ለአራት ዓመታት 4ሺ የሚጠጉ የኢትዮጵያ ልጆች ለ46 ቀናት ሲመክሩ መቆየታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰዋል።

በምክክሩ የኢትዮጵያ ዋና ዋና በሚባሉ 8 አጀንዳዎች ውስጥ 400 ንኡሳን አጀንዳዎች ተለይተው 99 በመቶ መግባባት መቻሉን አመላክተዋል።

ተጨማሪ ማብራሪያ በሚፈልጉ ጥቂት አጀንዳዎች ላይ ምክረ ሀሳብ ሆነው ለመንግስት ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቅሰዋል።

2019 ለክልሉ ብሎም ለኢትዮጵያም የማንሰራራት አመት እንደሚሆን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች የተዛቡ አመለካከቶችን በማረም ረገድ ጉልህ ሚና እንዳላቸውም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ባለ ብዙ ጸጋ የተቸራት ሀገር ናት ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በሚቀጥለው ዓመት 80ሺ ሰዎች ከውጭ ሀገር መጥተው በአዲስ አበባ ስብሰባ እንደሚያካሄዱ አብራርተዋል።

ሀገራችን በኮንፈረንስ ቱሪዝም ላይ ያላትን አቅም እያሳደገች እንደምትሄድ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

በጉባኤው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳድሩ የህግ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ኑሪዬ ሱሌ የሀገር ሽማግሌዎች የጋራ ፎረም መመስረቻ እና የግንኙነት አሰራር ስርዓት ዉስጠ ደንብ አቅርበዋል።በቀረበው ውስጠ ደንብ ላይ ዝርዝር ውይይት እንደሚካሄድበት ይጠበቃል።

የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን

የጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ ጥራትና ፍትሃዊነት በማረጋገጥ የእናቶችና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የምሁር አክሊል ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አስታወቀ።መስከረም 7/20...
17/09/2026

የጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ ጥራትና ፍትሃዊነት በማረጋገጥ የእናቶችና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የምሁር አክሊል ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አስታወቀ።

መስከረም 7/2019 ዓ.ም

"ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ሀሳብ የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፓርት በመገምገም አመታዊ የጤና የጉባኤ መድረክ አካሄደ።

የማስፈፀም አቅም በመገንባት በየደረጃው ተለይተው የወጡትን ማነቆዎች በመፍታት የተመዘገቡ መልካም ተሞክሮችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተሰራ እንደሚገኝ የምሁር አክሊል ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ዋና ኃላፊ ይታገሱ መለስ ተናግረዋል።

ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ስራዎች በበጀት አመቱ በዋናነት ትኩረት ተሰጥቶ የተሰሩ መሆናቸው ገልፀዋል።

የእናቶች ጤና በማሻሻል የህፃናት ሞት መቀነስ እንዲሁም የማህበረሰቡ የማዐጤመ ተጠቃሚነት ሽፋን ለማሻሻል በትኩረት መሰራቱ ተናግረዋል።

የህክምናና የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሃዊ ተደራሽነትን ማሻሻል፣የእናቶች ፣ህፃናት እና ጤናና ስርዓት ምግብ ሁኔታን ማሻሻል ግብ ተጥሎ መሠራቱ ገልፀዋል።

በሁሉም እድሜ ክልል የሚገኙ ዜጎች ጤናና ደህንነት ማረጋግጥ ፣ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ማሳካት እንዲሁም የጤና አገልግሎት ጥራት በማሻሻል ጤና ላይ ያለውን እምነት እና መተማመን መገንባት የጤናው ዘርፍ ዋና አላማ በመሆኑ ለዚህ ደግም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል።

የድጋፍና ክትትሉን ሥርዓት በማጠናከር የነፍሰጡር እናቶች ማቆያ በሁሉም ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታል እንዲኖር በማድረግ ሁሉንም በመሰረታዊ ግብዓት ማሟላት ይገባል ሲሉ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

የጤና አገልግሎት ጥራት በማሻሻል ማህበረሰቡ በጤና ስርዓት ላይ ያለውን እምነት እና መተማመን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በጤና ተቋማት እየገጠመ ያለውን የመድሀኒት አቅርቦት ችግር በመቅረፍና ፅዱ መንደር በመፍጠር የማህበረሸባችን የበሽታን የመከላከል አቅሙን ማሳደግ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በሀገር ደረጃ በባለፈው አመት በጤናው ዘርፍ በርካታ ተግባራት በማከናወን የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የምሁር አክሊል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብስራት ገብሩ ተናግረዋል።

በወረዳም በበጀት ዓመቱ በጤናው ዘርፍ የማህበረሰቡ ተሳትፍ ከፍተኛ እንደነበር ገልፀው የጤና ተቋማት ሁሉ አቀፍ አገልግሎት ለመስጠት የህክምና ቁሳቁስ ለማሟላት የህዝቡ ተሳትፎ ጉልህ ሚና የነበረው በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አያይዘውም እንደተናገሩት በጤና ተቋማት እየገጠመ ያለውን የመድሀኒት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የማህበረሰቡ ሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋንን በትኩረት መሰራቱን ገልፀዋል።

የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት በማሻሻል በሁሉም ዕድሜ ክልል የሚገኙ ዜጎች ጤናና ደህንነቱ የተጠበቀ የማህበረሰብ ክፍል ለመፍጠር መሠራቱ አብራርተዋል።

በጤና ዘርፍ የህዝባችን ተሳትፎና ባለቤትነት በትልቅ ደረጃ ማሳደግ ያለብን መሆኑና በወረዳው የሚገኙ የጤና ተቋማቶች ሞዴል ለማድረግ እንደሚሰራ ገልፀው ለዚህ ደግሞ ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።

በመጨረሻም በ2018 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው ጤና ጣቢያዎች፣ጤና ኬላዎች፣የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣የሞዴል እማወራዎች፣በተቋሙ በጡረታ የተሠናበቱ ባለሙያዎችና በጤናው ዘርፍ ላይ እገዛ ያደረጉ አጋር አካላት እውቅና በመስጠት ጉባኤው ተጠናቋል።

የወረዳው የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት

የᎀሕር አክሊል ወረዳ የአፍያ ሸመነ የሁያም አስራ ስሙተኘ ዘበን የአመትዌ የአፍያ ሸመነ ወባጀ ወሰክት ቀረሰም።መስከሮብ 07/2019 ዘበን (ሐዋሪያት)በጉራጔ ዞን የሞህር አክሊል ወረዳ የአፍ...
17/09/2026

የᎀሕር አክሊል ወረዳ የአፍያ ሸመነ የሁያም አስራ ስሙተኘ ዘበን የአመትዌ የአፍያ ሸመነ ወባጀ ወሰክት ቀረሰም።

መስከሮብ 07/2019 ዘበን (ሐዋሪያት)

በጉራጔ ዞን የሞህር አክሊል ወረዳ የአፍያ ሸመነ የሁያም አስረስሙት ዘበን የቾተኖ ቡር ቡር ሜራ ይግመግሙᎄም በ2019 ዘበን የሸመነዌ ይቾትዮ ስኖዝ ያትቧጀቦ የወረዳዌ የአፍያ ሸመነ የአመትዌ ወባጀ በሐዋሪያት ከተማ ወሰክት ቀረሺም።

ዮረዳዌ የአፍያ ሸመነ ቡር ዳነ አበአጥ ይታገሱ መለሰ የሸመነዌ ወባጀ በዘንጎት ይገዎቦ ነሁቸር የቤሙኸማ ቦረ የ2018 ዘበር የወረዳንዳ ወሄ ወሄ ሜራ በሸመነዌ የቾቲኸማ በ2019 ዘበን የሸመነዌ ይቾትዮ ውጥን ተባለፈዌ የበለጠ ወቶት ያነብነኸማ አሳሰበሙም።

በአመትዌ አፍያ ሸመነ ቤትዌ የᎀሕር አክሊል ወረዳ ቡር አራባሪ አበቃጥ ብስራት ገብሩ ፣ የወረዳዌ ወባጀ ቤት ቡር የኸልቅ አፍ አበቃጥ ጅላሉ ሸምሱ፣የᎀሕር አክሊል ወረዳ የዝፓና ቤት አላፊ አበቃጥ ሰይፈ ይልማ ፣የጥፈት ቤት ዳነ፣የቀበሌዌ ቡር ዳነ፣የቀበሌ የአፍያ ሸመነ ቡር ዳነ፣ እንጎድ በቀበሌ ይትምለከትኖ ሰብ ቦባጀዌ ተረከቦም።

ዮባጀ ቤትዌ ዝርዝር አሳብ ኤዝነም ንዠበርኖ ቲቢ የጣፈን የሞህር አክሊል ወረዳ የመንግስት አትራህቦት ሸመነን።

በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ የሐዋሪያት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 አዲሱ የትምህርት ዘመን ከ350 በላይ አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል የሚያስችለውን አስፈላጊ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ...
17/09/2026

በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ የሐዋሪያት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 አዲሱ የትምህርት ዘመን ከ350 በላይ አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል የሚያስችለውን አስፈላጊ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ።
‎
መስከረም 07/2019 (ሐዋሪያት)‎ወላጆችም የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ያለውን ጥቅም በመገንዘብ ልጆቻቸው ገብተው እንዲሰለጥኑ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
‎
በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ የሃዋርያት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ትዛዙ ፍቃዱ እንደገለጹት ኮሌጁ በባለፈው የትምህርት ዘመን ከ110 በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አስመርቋል።

ይህንን ውጤት መነሻ በማድረግም በአዲሱ የትምህርት ዘመን የሰልጣኞችን ቁጥር ወደ 350 ለማሳደግ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
‎
ለስልጠናው መሳካት በቂ የወርክሾፕ ማሽነሪዎች፣ የመማሪያ ክፍሎችና አሰልጣኝ መምህራን መሟላታቸውን የጠቀሱት ዋና ዲኑ የኮሌጁን ግቢ ሳቢና ማራኪ ከማድረግ ባለፈ የመንገድ ርቀትና የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ሰልጣኞች የመኝታ ዶርምና የቁሳቁስ ድጋፍ መመቻቸቱን ገልጸዋል።
‎
ኮሌጁ በቅርቡ ከደረጃ እድገት ያገኘ መሆኑን ያወሱት አቶ ትዛዙ በአሁኑ ወቅት በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፣ በዳታቤዝ፣ በሃርድዌር፣ በኔትወርኪንግ እና በሌሎችም በርካታ የሙያ ዘርፎች እስከ ደረጃ አምስት ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኑን አብራርተዋል።
‎
በመጨረሻም በ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ውጤት ያላመጡና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት ያልቻሉ ወጣቶች ወደ ኮሌጁ በመምጣት እንዲመዘገቡ ጥሪ ያቀረቡት ዋና ዲኑ ወላጆችም የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ያለውን ጥቅም በመገንዘብ ልጆቻቸው ገብተው እንዲሰለጥኑ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
‎

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት;በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን! ‎‎ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆ...
16/09/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት;

በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን!
‎
‎ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ።
‎
‎ ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ ዕድል ተጠቃሚ እና ባለአደራ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የእናንተ ቁርጠኝነት መሠረት እንደሆነ ሙሉ እምነቴ ነው።
‎
‎ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራኖቻችን ትጋትና መሰጠት መሰረታዊ ምሰሶ ነው። ተማሪዎቻችንን ማነቃቃት፣ አቅማቸውን ማውጣት፣ እንዲሁም ነገ ተፎካካሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሏቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና እሴቶችን የማስታጠቅ አደራን ቀጥሉበት ስል በትህትና አሳስባለው።
‎
‎በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ ስኬታማ እና ፍሬያማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
‎

Address

Hawariyat
Wolkite

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በጉራጌ ዞን የምሁር አክሊል ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to በጉራጌ ዞን የምሁር አክሊል ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት:

Shortcuts

Share

Category