Amhara Satellite Media Network ASAMN

Amhara Satellite Media Network ASAMN Amhara satellite Media Network
Focus on the social , economic & political
issues of Amhara and Ethiopia at large የ YouTube ቻናላችን >> bit.ly/3nhGJe3

ዳውንት የተ ማ-ረ-ከ 😁😁😁
09/09/2026

ዳውንት የተ ማ-ረ-ከ 😁😁😁

የምኒልክ ዕዝ  አዛዥ  💪💪💪💪የድሉ ፊት አዉራሪ  እንደ አስማረ ዳኜ ሲሻዉ ወሎ ሲሻዉ ጎጃም ሲሻዉ ጎንደር ሲሻዉ ወሎ እያለ የጁላን ጦር የሚያነጋግረዉ ጀግና  ድርሳን ብርሀኔ
09/09/2026

የምኒልክ ዕዝ አዛዥ 💪💪💪💪

የድሉ ፊት አዉራሪ እንደ አስማረ ዳኜ ሲሻዉ ወሎ ሲሻዉ ጎጃም ሲሻዉ ጎንደር ሲሻዉ ወሎ እያለ የጁላን ጦር የሚያነጋግረዉ ጀግና ድርሳን ብርሀኔ

ታሪክ ሰሪው ዋርካው ምሬ ወዳጆ (አለቃ)
09/09/2026

ታሪክ ሰሪው ዋርካው ምሬ ወዳጆ (አለቃ)

ከአፋብን 1ኛ ምኒልክ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ የተላለፈ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት!!ለጀብደኛው የምኒልክ ዕዝ ሁሉም ኮሮች፣ ለመላው ሰራዊታችን እና ለምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ...
09/09/2026

ከአፋብን 1ኛ ምኒልክ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ የተላለፈ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት!!

ለጀብደኛው የምኒልክ ዕዝ ሁሉም ኮሮች፣ ለመላው ሰራዊታችን እና ለምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በሙሉ፣ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ ያለን!

መራራው የአማራ ህዝብ ትግል በድል እስከሚጠናቀቅ ድረስ ህዝባችን እና ድርጅታችን የጣሉብንን አደራ በቁርጠኝነት ለመወጣት ዛሬም እንደ ትላንቱ በትጋት እንታገላለን።

ዕዛችን አፋብን 1ኛ ምኒልክ ዕዝ እያደረገ ያለው ተጋድሎ በታሪክና በትውልድ ሲዘከር ይኖራል። በህልውና ትግሉ ውስጥ አንጸባራቂ ድሎች እየተመዘገቡ ነው። በተለይም «ዘመ*ቻ አደም አሊ»፣ «ዘመቻ ራንቦ» እና የአሁኑ «ዘመ*ቻ መሐመድ ቢሆነኝ» በአማራ ተጋድ*ሎ ዘመን ከፍተኛ ታሪካዊ ጀብ*ዱ የፈጸምንባቸውና የጠላ*ትን ቅስም የሰበርን*ባቸው አኩሪ ታሪኮቻችን ናቸው።

ይህ ድል እንዲጻፍና ወታደ*ራዊ ገድ*ል እንዲፈጸም ላደረጋችሁ የሰራዊ*ታችን አባሎችና በየደረጃው የምትገኙ አመራሮች ልፋታችሁ ትጋታችሁ ፍሬ አፍርቶ በማየታችሁ ልትኮሩ ይገባል።
የተመዘገቡትን ወታደ*ራዊ ድሎች ጠብቀን አዳዲስ ድሎችን እናመጣ ዘንድ በተሻለ መደማመጥና የሌት ተቀን ትጋት የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሁላችንም ጠላትን በመምታትና የወገን ሃይልን በማጠናከር ላይ ልናተኩር ይገባናል!

«ስንከባበርና ስንደማመጥ ከባ*ዱ ይቀላል» እንደሚባለው፤ በጶጉሜ 03 2018 ዓ.ም. በዕዛችን ልዩ ዘመ*ቻ እና በ16ኛ ኮር (የደጋው መብረቅ) የተሰራው አንጸባራቂ ወታደ*ራዊ ድል በጣም የሚያኮራ ነው። በተለይም በአውደ ው*ጊያ ያሳያችሁት አሸናፊነት፣ ወደር የሌለው ፅናትና ከፍተኛ ቁጭት ጠላትን ደምስሳችሁ ድልን የተቀዳጃችሁ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!

በውጊያው ወቅት ያሳያችሁት አስደናቂ ወታደራዊ የትግል ብቃት፣ የትዕዛዝ አፈጻጸም ጥራት እና እርስ በእርስ የመደጋገፍ የጓዳዊነት መንፈስ አንጸባራቂ ድሎችን አስመዝግቧል።

በ«ዘመ*ቻ መሐመድ ቢሆነኝ» የታወጀው ይህ ዘመቻ በርካታ ሁነቶችና ወታደ*ራዊ ብልጫዎች የታዩበት ሲሆን፣ በተለይም የወገን ሃይልን የመፈጸም ብቃት ያረጋገጠ ነበር።
በአውደ ውጊያውም
፩. የውጊ*ያ የበላይነትን በማረጋገጥ የጠላትን ወታደራዊ ስትራቴጂ እና የመከላከል ምሽግ በጥበብና በወሳኝ ደፋር እርምጃ ሙሉ በሙሉ መደምሰስ ተችሏል!
፪.በጽናትና ቁርጠኝነት አስቸጋሪ የአየር ጠባይና የመሬት አቀማመጥን በመቋቋም የተሰጣችሁን የውጊያ ግብ በላቀ ሁኔታ ማሳካት ተችሏል!

፫.የህይወት መስዋ*ዕትነትና ጀግንነት ለአማራ ህዝብ ህልውና፣ ለህዝብ ደህንነት እና ለክብራችን ሲባል ያሳያችሁት ወታደራዊ ወኔና ተጋድሎ ለትውልድ የሚሻገር የታሪክ ድርሳን ነው።

ይህ የተመዘገበው አስደናቂ ድል ለህል*ውና ትግላችን የተስፋ ብርሃን፣ ለቀሪው ሰራዊት የመንፈስ ጥንካሬ፣ ለጠላት ደግሞ የቁም ቅዠት ሆኗል።

ድርጅታችን አፋብን እና የአማራ ህዝብ በጀግንነታችሁ፣ በዲሲፕሊናችሁና በከፈላችሁት መስዋዕትነት ላቅ ያለ ኩራትና ክብር አለው። የጀግንነት ገድላችሁ በወታደራዊ ታሪካችን ውስጥ በወርቅ ቀለም ተጽፎ ይኖራል!

ክብርና ሞገስ በአውደ ውጊ*ያ ታሪክ ለሰሩት ጀግኖቹ አሃዶቻችን!

ፊት አውራሪ ድርሳን ብርሃኔ የአፋብን 1ኛ ምኒልክ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ

ዳግም ገደሉን አይደል?? በጠበቃ መንግስቱ ዘገየ    የወለጋው እልቂት ከትላንትና ይልቅ ዛሬ ደጋግሞ አመመኝ። ከገደ*ሉን ይልቅ ዓዒሻ የፈጠራ ትርክት ናት ብለው የቀለዱብን ደጋግመው ገድለውና...
09/09/2026

ዳግም ገደሉን አይደል?? በጠበቃ መንግስቱ ዘገየ

የወለጋው እልቂት ከትላንትና ይልቅ ዛሬ ደጋግሞ አመመኝ። ከገደ*ሉን ይልቅ ዓዒሻ የፈጠራ ትርክት ናት ብለው የቀለዱብን ደጋግመው ገድለውናል።በዚያ ጭፍ*ጨፋ ደማ*ቸው እንደ ጅረት የፈሰሰው የወሎ ዘመዶቼ አማራን ጥረገው ወደመጣበት መልሰው ግደ*ለው እየተባሉ ወደሞ*ት የተሸኙበት ደማ*ቸው ከረፋኝ። እሽ ግዴለም፤ ዐዒሻ የእውነት አይደለችም "የፈጠራ" ገፀ ባህሪ ናት ብለን እንኳ ብናስብ በህዝባችን ላይ የተከሰተው ጭፍ*ጨፋ ዐዒሻ ተናገረችው ከዚያ በላይ እጥፍ ድርብ ነገር አያናግርም ነበር ወይ!! ችግር የለውም። እኛ ግን ከገዳዮቻችን በላይ በጨም*ላቃ ጎልዳፋ ብዕራቸው ዳግም የገደ*ሉንን የጠላ*ቶቻችን ተላላኪዎችን ስምና ግብር በደማቁ ጥቁር ቀለም እየከተብን ነው። Time for Justice will come!!

ኪነተኛው ባጫ ደበሌ በትብብሩ ደንግ*ጦ ባለፈው ጊዜ ቢቢሲ አማርኛ ዝግጅት ላይ ቀርቦ አንድ ነገር ተናግሮ ነበር፤ የአሁኑ ጦ*ርነት "ግንባርም ደጀንም የለውም እንተላለቃለን" የሚል ነበር:: ...
09/09/2026

ኪነተኛው ባጫ ደበሌ በትብብሩ ደንግ*ጦ ባለፈው ጊዜ ቢቢሲ አማርኛ ዝግጅት ላይ ቀርቦ አንድ ነገር ተናግሮ ነበር፤ የአሁኑ ጦ*ርነት "ግንባርም ደጀንም የለውም እንተላለቃለን" የሚል ነበር::

እና እኛም እንላለን ግንባርም ደጀንም የሌላችሁ እናንተ ብልፅግናዎች እንጂ ፋኖ እና በሂደት ላይ ያለው ትብብር ግንባርም ደጀንም አለው:: ግንባርም ደጀንም የሌለው ሰራዊ*ታችሁ መሄጃ ጠፍቶት ሙሉ ክፍለ ጦ*ር ከነ ትጥ*ቁ ተማ*ርኳል:: ይቀጥላል!

ሌላኛው ሃላፊነት ከብልፅግናዎች ባንጠብቅም የባጫ ደበሌ አደገኛና ሃላፊነት የጎደለው ንግግሩ "እንተ*ላለቃለን" የሚል ነበር:: እና መተ*ላለቅ ሃገርም ህዝብም ማሻገር አይችልም እንጂ መፍትሔ ቢሆን ኖሮ በዚህ አለም ለመተ*ላለቅ ከአማራ በላይ ምክንያት ያለው አልነበረም::

ህልውና*ችን በተባበረ ክን*ዳችን!
ከአፋብን ጋር ወደፊት!
ጳጉሜ 3/2018 ዓ.ም

አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ከጠ*ላት ነፃ ባወጣቸው ቀጠናዎች ሰፊ ሕዝባዊ መድረክ እና ጊዜያዊ የሲቨል አስተዳደር መዋቅር አዋቀረ!በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ 016 ደብረ ዘይት ታዳጊ ከተማ ...
08/09/2026

አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ከጠ*ላት ነፃ ባወጣቸው ቀጠናዎች ሰፊ ሕዝባዊ መድረክ እና ጊዜያዊ የሲቨል አስተዳደር መዋቅር አዋቀረ!

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ 016 ደብረ ዘይት ታዳጊ ከተማ ከህዝብ ጋር ሠፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን አብዘሃኛው የቀበሌው ማህበረሰብ በመድረኩ ላይ ተገኝቷል። በዚህ ደማቅ ህዝባዊ መድረክ ላይ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከነዚህም መካከል የአማራ ሕዝብ የት*ግል መነሻ ምክኒያት፣ ግብ እና መዳረሻ አላማ፣ የትግሉ ወቅታዊ ቁመና፣ ስለ ቀጠናዊ አሰላለፍ እንዲሁም ስለ ሲቨል መዋቅር ጥቅምና አስፈላጊነት ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ የምኒልክ 1ኛ ዕዝ የጤና መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ዶክተር ኡስማን ሰይድ፣ የምኒልክ 1ኛ ዕዝ ምክትል አደረጃጀት መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ሲሳይ ሳተናው፣ የምኒልክ 1ኛ ዕዝ ምክትል ሚዲያና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ዳሽን፣ የ141ኛ ክፍለጦር አስተዳደር አርበኛ ፍሰሃ እንዲሁም የወረዳው ሲቪል አስተዳደሮች ተገኝተዋል።

በመጨረሻም ከቀበሌው ማህበረሰብ በርካታ ጥያቄዎች ያነሳ ሲሆን በምኒልክ 1ኛ ዕዝ አመራሮች አጥጋቢ ምላሽ ተሰጥቷል። ሕዝቡም በትግሉ ደስተኛ እንደሆነና በቀጣይም አገዛዙን ለመቅበር ዝግጁ መሆናቸኑን አስረድተዋል። የቀበሌው ሕዝብን ሊመሩና ሊያስተባብሩ የሚችሉ የቀበሌ አመራሮችን በማዋቀር መድረኩ ተጠናቋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ህልው*ናችን በተባበረ ክን*ዳችን!

አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!

ጷግሜ:-03/ 2018 ዓ/ም

08/09/2026

የፋኖ ማርሸት ጉዳይ አድስ መረጃ ወጣ #ፋኖ #ማርሸት #አፋብን

ሰበር ዜና.  የጀብደኛዉ ምኒልክ 1ኛ ዕዝ አሃድ የሆኑት 16ኛ ኮር እና ልዩ ዘመ*ቻ የጠ*ላት ሠራዊ*ትን ዋጥ አድርገዉታል።አንድ ከፍተኛ ወታደ*ራዊ አዛ*ዥ ሲገ*ደል ወታደ*ራዊ ተሽከርካሪዎች...
08/09/2026

ሰበር ዜና. የጀብደኛዉ ምኒልክ 1ኛ ዕዝ አሃድ የሆኑት 16ኛ ኮር እና ልዩ ዘመ*ቻ የጠ*ላት ሠራዊ*ትን ዋጥ አድርገዉታል።

አንድ ከፍተኛ ወታደ*ራዊ አዛ*ዥ ሲገ*ደል ወታደ*ራዊ ተሽከርካሪዎች ወድመ*ዋል!

የምኒልክ 1ኛ ዕዝ አሃዶች ከትናንት ጳጉሜ 02/2018 ዓ/ም ጀምሮ በሦስት ግንባ*ሮች እያደረጉት በሚገኘው ከባድ ተጋ*ድሎ ለጊዜው ማዕረጉ በውል ያልተለየ አንድ ከፍተኛ ወታደ*ራዊ አዛዥ ሲገ*ደል በርካታ ተሽከርካሪዎች ወድ^መዋል።

ዝርዝሩን እንመለስበታለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳ*ችን!

አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!

ጷግሜ:-03/ 2018 ዓ/ም

Address

London

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Satellite Media Network ASAMN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amhara Satellite Media Network ASAMN:

Shortcuts

Share

Category