07/09/2026
#ጳጉሜን 2 - የማንሰራራት ቀን!
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ - የቀጣናዊ የኃይል ትስስርና የዲፕሎማሲ ማዕከል! 🌍⚡️
ኤሌክትሪክን ለጎረቤት ሀገራት ማስተላለፍ ከውጭ ምንዛሬ ግኝት ባሻገር በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ውስጥ ዘላቂ የኢኮኖሚ ትስስርንና የወንድማማችነት የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው። ኢትዮጵያን የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ማዕከል በማድረግ በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቅና ወደ አገልግሎት መግባት የማይተካ ታሪካዊ ሚና ተጫውቷል!
የሕዳሴ ግድብ ለቀጣናዊ የኃይል ትስስር ያለው አበርክቶ፦
🔹 የቀጣናው የኢነርጂ ማዕከል መሆን
ሀገራችን ኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራትን በንጹህና ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል በማገናኘት ቀጣናዊ የአህጉራዊ የኢኮኖሚ ውህደትን በግንባር ቀደምትነት እየመራች ትገኛለች።
🔹 የውጭ ምንዛሬ ገቢ እመርታ
ከኃይል ሽያጭ የተገኘው ገቢ ከዓመት ወደ ዓመት እያደገ የመጣ ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት ከኃይል ሽያጭ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ብቻ የ27 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።
በበጀት ዓመቱ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ኦፕሬሽን መግባቱ ለአጠቃላይ የኃይል ኤክስፖርት ማደግና ለውጭ ምንዛሬ ግኝቱ ከፍ ማለት ዋናውን ድርሻ ወስዷል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን እና ሌሎች ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን በስፋት በመገንባት ሀገራችንን የቀጣናው የኃይል ምንጭ የማድረግ ተልዕኮውን አጠናክሮ ይቀጥላል!
💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”