Gurumo Ladisa Kebele Chief Administration

Gurumo Ladisa Kebele Chief Administration Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gurumo Ladisa Kebele Chief Administration, Social Media Agency, North Jakarta.
(1)

በወላይታ ሶዶ ከተማ ለሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲን የይምረጡ ቅስቀሳ በአራዳ ክፍለ ከተማ፥ጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ ተካሂዷል ‎ወላይታ ሶዶ፦‎ ግንቦት 4/2018 ዓ.ም ‎በወላይታ ሶዶ ከ...
12/05/2026

በወላይታ ሶዶ ከተማ ለሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲን የይምረጡ ቅስቀሳ በአራዳ ክፍለ ከተማ፥ጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ ተካሂዷል

ወላይታ ሶዶ፦‎ ግንቦት 4/2018 ዓ.ም ‎በወላይታ ሶዶ ከተማ ለሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲን የይምረጡ ቅስቀሳ በአራዳ ክፍለ ከተማ፥ጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ ተካሂዷል ።

‎በመርሃግብር ላይ የተገኙት ዶክተር ፍሬዉ ሞገስ የሶዶ ዙሪያ 1 ምርጫ ክልል ዕጩ ተወዳዳሪ እንደተናገሩት ብልጽግና ፓርቲ ትላንትናንና ዛሬን ያስተሳሰረ ፣ የኢትዮጵያ ተስፋን በማይናወጥ ጽኑ መሠረት የጣለ ፣የሴት እህቶቻችን የዉሳኔ ሰጭነት አድማስን ያሰፋ፣ለወጣቱ ትዉልድ ብሩህና በሁሉም ዘርፍ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ቀን ከሌት አየሰራ የሚገኝ ፓርቲ ነዉ ብለዋል።

‎በሃሳብ ልዩነት ሀገርን ማፍረስ አይቻልም ያሉት ኃላፊ ችግሮችን በውይይትና በመግባባት በመፍታት በፓርቲው መሪነትና በህዝቡ የነቃ ተሳትፎ የብልጽግና ጉዞአችንን አዉን እናደርጋለን ስሉ ተናግረዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የህዝብን ችግር በቅርበት እየፈታ ያለና የተጠየቁትንም ሆነ ያልተጠየቁትን ምላሽ የሚሰጥ ፓርቲ መሆኑ በመድረኩ ገልጸዉ በቅስቀሳ ፕሮግራሙ ላይ በነቅስ የተሳተፉ አባላትንም ሆነ ደጋፊዎችን አመስግነዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ እና የሶዶ ዙሪያ 1 ምርጫ ክልል ዕጩ ተወዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ዘገየ ጳዉሎስ በበኩላቸው እንደተናገሩት ‎ብልጽግና መንግስታችን በአለም አቀፍ ደረጃ የታወቀ፣በአፍሪካ ግዙፍ የሆነና በኢትዮጵያ እንደ ሀገር የተመሰከረለት በአጭር ግዜ ዉስጥ አለምን እያስደመመ የሚገኝ ተጨባጭ ለዉጦችን እያስመዘገበ ያለ ፓርቲ ነዉ ብለዋል

‎“እንደ አከባቢያችን የተለያዩ የዘመናት የህዝባችን ጥያቀዎች ምላሽ እያገኙ ያሉት በብልጽግና ፓርቲ ነዉ ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር ቀሪዎቹ የመልማት ጥያቄዎቻችን ምላሽ የሚያገኙትም በዚሁ በብልጽግና ፓርቲ ነዉ እኛ ለፓርቲያችን ታማኝ እንሁን ስሉ አሳስበዋል።

‎ብልጽግና ፓርቲ በተግባር የተፈተሸና ውጤታማ ፖሊሲ ያለው ፓርቲ ነዉ ካሉ በኋላ ፓርቲያችን ከየትኛውም ጊዜ በላይ ለሴቶችና ለወጣት ትኩረት የሰጠ፣ የኢትዮጵያን ታርክ እየቀየረ ያለ፣በአጭር ግዜ ዉስጥ የኢትዮጵያን ከፊታ ለማረጋገጥ እየተጋ ያለ ፓርቲ ግንቦት 24 እንዲመርጡ ጥሪውን አስተላልፏል ።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዝናቡ ተክሌ በበኩላቸው ፓርቲያችን ብልጽግና ጠይቀን የሚመልስ፣ በክፉም በደጉም ከጎናችን ያልተለየ አለኝታነቱን እያሳየና ዘርፈብዙ የሆኑ ልማቶችን በአካባቢያችን እየሰራ ያለ ፓርቲ ነዉ ካሉ በኋላ ‎የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንድጠናቀቁ፣የተሻሉ መሰረተ ልማቶች እንድስፋፉና በሁሉም መስክ የበለጸገች ኢትዮጵያን እዉን ለማድረግ ምርጫችን ብልጽግና ይሁን ብለዋል።



08/05/2026
በወላይታ ሶዶ ከተማ፥ በአራዳ ክፍለ ከተማ የጉሩሞ ላዲሳ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አዘጋጅነት የብልጽግና ፓርቲ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶን የማስተዋወቅ እና የቅስቀሳ ፕሮግራም በደማቅ ...
08/05/2026

በወላይታ ሶዶ ከተማ፥ በአራዳ ክፍለ ከተማ የጉሩሞ ላዲሳ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አዘጋጅነት የብልጽግና ፓርቲ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶን የማስተዋወቅ እና የቅስቀሳ ፕሮግራም በደማቅ መልክ ተካሂዷል ።





08/05/2026

በአራዳ ክፍለ ከተማ፥ ጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ደማቅ ሁኔታ የምርጫ ቅስቀሳ ዛሬ በቀን 29/08/2018 ዓ.ም አካሄደዋል።
ጉሩሞ ላዲሳ

07/05/2026

በወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ-2 ምርጫ ክልል ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ለክልል ምክር ቤት የቀረቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች፦




ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!በወላይታ ሶዶ ከተማ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፍ!ከወላይታ ዞንና ሶዶ ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ ወጣቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች በወላይታ ሶዶ ከተማ ...
06/05/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!

በወላይታ ሶዶ ከተማ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፍ!

ከወላይታ ዞንና ሶዶ ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ ወጣቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች በወላይታ ሶዶ ከተማ ደማቅ ምርጫ ቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፍ እያደረጉ ናቸው።

"ወጣቱ ብልፅግናን ይመርጣል፤ ሀገርን ያፀናል" በሚል መሪ ቃል ወጣቶች ብልፅግና ፓርቲን የ"ይምረጡ" ደማቅ ምርጫ ቅስቀሳ በወላይታ ሶዶ ጎዳናዎች በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ወጣቶች የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ እግር ጉዞ በማድረግ የብልፅግና ፓርቲ ምርጫ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶን ህዝቡ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲመርጥ ቅስቀሳ እያካሄዱ ነው።

ብልጽግና ፓርቲ የተጀመረውን ሀገራዊ የለውጥ ጉዞና በሚያካሂደው በሁሉም እንቅስቃሴዎች ከፓርቲው ጎን እንደሚሆኑ ወጣቶች በድጋፍ ሰልፉ ገልፀዋል።

የወጣቱን ችግሮች ለመፍታት ብቃትና ቁርጠኝነት የተጎናፀፈ ፓርቲ ብልፅግና እንደሆነ ብልጽግና በወጣቱ፤ ከወጣቱ እና ለወጣቱ መሆኑን በመጥቀስ ብልፅግናን ለምን እንደሚመርጡ ጭምር እግር ጉዞ በማድረግ ሌሎች እየገለፁ ናቸው።

7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒ ሆኖ በብልጽግና ፓርቲ አሸናፊነት እንዲጠናቀቅና ድምጻቸዉን ለብልጽግና ፓርቲ ለመስጠት በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውንና መዘጋጀታቸውንም በድጋፉ አረጋግጠዋል፡፡

የሚዲያ እና ኮሚዩንኬሽን አካላት በቅንጅት በመስራት የመንግስትን ውጤታማ ተሞክሮዎችን ማስፋት ይገባቸዋል-አቶ አገኘሁ ጴጥሮስ  የወላይታ ሶዶ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የ9 ወር ሴ...
05/05/2026

የሚዲያ እና ኮሚዩንኬሽን አካላት በቅንጅት በመስራት የመንግስትን ውጤታማ ተሞክሮዎችን ማስፋት ይገባቸዋል-አቶ አገኘሁ ጴጥሮስ


የወላይታ ሶዶ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የ9 ወር ሴክቶሪያል ጉባኤ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።

የወላይታ ሶዶ ከተማ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አገኘሁ ጴጥሮስ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት የለውጡ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ ለኮሙኒኬሽን ሴክተር ትኩረት ሰጥቶ እየደገፈ ይገኛል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን መምሪያ የህዝቡን የመረጃ ፍላጎት ለማርካት ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረገውን ቅንጅታዊ አሰራር ሊያጠናከር እንደሚገባ አቶ አገኘሁ አሳስበዋል፡፡

የሚዲያ አውታሮች የገፅታ ገንቢ መሳሪያ በመሆን በተለይም 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሀዊ ሰላማዊ እና ከፍተኛ ዲሞክራሲ የሚንፀባረቅበት ማድረግ እንደሚገባም አቶ አገኘሁ ገልፀዋል፡፡

ሀሰተኛ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚነዙትን የጥላቻ ትርክት በመመከት እና አንድነትን የሚያጎሉ ዘገባዎችን በማጠናከር የሚዲያ ሰራዊቱ የብልጽግና ሞተር ስለመሆኑ አቶ አገኘሁ አስረድተዋል፡፡

ተቋሙ የመረጃ ቋት መሆኑን በተግባር አሳይቷል ያሉት አቶ አገኘው የህዝብ አስተያየት በማጠናከር በመንግስት እና በህዝብ መሀከል ድልድይ ሆኖ ማገልገል እንደሚገባ መክረዋል፡፡

የወላይታ ሶዶ ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሀላፊ ወ/ሪት ብሩክ ጴጥሮስ መድረኩ በታቀደው ልክ መሳካቱን ገልፀዋል፡፡

ከባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር ሰፊ ስራዎችን እየሰራን እንቀጥላለን ያሉት ሀላፊዋ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ሕዝብ ግንኙነት ፎካል ፐርሰኖችን የማብቃት ተግባር ሎዩ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑም አብራርተዋል፡፡

የየሴክተር ሕዝብ ግንኙነት ፎካል ባለሙያዎች የተደራጀ መረጃዎችን በማቅረብ ስልጠናውን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከወዲሁ እንቅስቀሴ እንዲጀምሩም መክረዋል፡፡

ወቅቱ የምርጫ በመሆኑ ተደራሽ ሊሆኑ የሚገቡ መረጃዎችን ሚዛናዊነትን ጠብቆ ማሰራጨት እንደሚገባ ወ/ሪት ብሩክ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

ከባለድርሻዎች ጋር በትብብር እና በቅንጅት በመስራት ለውጡን ለማስቀጠል ያለቸውን ቁርጠኝነት ሀላፊዋ ገልፀዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፈዎች በሰጡት አስተያየት በሚዲያ እና ስትራቴጂካዊ ኮሙዩኒኬሽን አሁናዊ እውነታዎች ላይ ወቅታዊ ግንዛቤዎችን መጨበጣቸውን ተናግረዋል፡፡

ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት ተግባራዊ በማድረግ ሚዛናዊ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን ለማሻሻል እንደሚሰሩም አመልክተዋል፡፡

30/04/2026
በወላይታ ሶዶ ከተማ በአራዳ ክ/ከተማ በጉሩሞ ላዲሣ ቀበሌ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ የቅስቀሳ መርሃ ግብር ተካሂዷል። በጉሩሞ ላዲሣ ቀበሌ ነዋሪዎች በላዲሣ  ከተማ በተካሄደው የይም...
29/04/2026

በወላይታ ሶዶ ከተማ በአራዳ ክ/ከተማ በጉሩሞ ላዲሣ ቀበሌ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ የቅስቀሳ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በጉሩሞ ላዲሣ ቀበሌ ነዋሪዎች በላዲሣ ከተማ በተካሄደው የይምርጡኝ ቅስቀሳ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ በተግባር አሳይተዋል።

ብልፅግና እውነተኛ ብዝሃነት የተረጋገጠባትንና የወንድማማችነት እሴት የዳበረባትን ሀገር እውን በማድረግ፣ አካታች የፖለቲካ ባህልና የወል ትርክት በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲበቅል አድርጓል።

በሀገራችንን ዉስጥ ስር የሰደደዉን እርስ በርስ የመጠላለፍ እና አግላይነት የሰፈነበትን የፖለቲካ ባህል በመለወጥ፣ ሁሉም ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ወሳኝ ሚና እንዲኖራቸውና ከማግለል ወደ ዉሳኔ ሰጪነት እንዲሸጋገሩ ማድረግ ታሪክ የቀየረ ፓርቲ ነዉ።

ሀገራችን በብልፅግና መሪነት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በአፍሪካ የሁለንተናዊ እድገት አርአያ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ አዲስ ኃይል በመሆን የሚገባትን ቦታ የምትይዝ ይሆናል።

ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ!
ብልፅግናን መምረጥ ሀገራዊ መግባባት እንዲሰፍን፣ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እና ሀገራዊ አንድነት እንዲጠነክር መፍቀድ ነው!

ብልፅግናን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!

ወደ ተምሳሌት ሀገር ከብልፅግና ጋር!

Address

North Jakarta

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurumo Ladisa Kebele Chief Administration posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share