Ermiyas Girma

Ermiyas Girma "እኔ ታናሽና የተናቅሁ ነኝ ትእዛዛትህን ግን አልረሳሁም"
መዝ:- 118 - 141
(5)

06/03/2026

አሳራጁ እራሱ ከተማ ቁጭ ብሎ ንጹሃን እያለ ሙድ ሲይዝ አትገረምም ወይ .. ወገኔ አንተ ኦርቶዶክሳዊ ታቦቱን ያዝ እንደ አባቶችኽ መክት አንክት💪🏾

06/03/2026

"መሆን ያለበት 'አዝነናል' ብለን መልእክት ማስተላለፍ አይደለም!"
-መምህር ዘበነ ለማ

17 የአፍሪካ ሃገራት ከፍተኛ የኢንዱስትሪ ዕድገት ሲያሳዩ የኛ ኢትዮጵያ ደግሞ በኦርቶዶክሳዊያን ደም ትጫወታለች
06/02/2026

17 የአፍሪካ ሃገራት ከፍተኛ የኢንዱስትሪ ዕድገት ሲያሳዩ የኛ ኢትዮጵያ ደግሞ በኦርቶዶክሳዊያን ደም ትጫወታለች

06/02/2026

አርሲ ኦርቶዶክሳዊያንን በመጨፍጨፍ የተለያዩ መንግሥታዊ አጀንዳዎች ማስቀየሻ የማድረግ ሴራው ቀጥሏል 😡

አርሲ ሀገረ ስብከት ከ10 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉየ101 ዓመት እድሜ ያለው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።   የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የ...
06/02/2026

አርሲ ሀገረ ስብከት ከ10 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ
የ101 ዓመት እድሜ ያለው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።


የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።

የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝርም

1. አቶ ደምረው አበራ የ70 ዓመት
2. ከፈለኝ ልክየለው የ56ዓመት
3. ሐይሉ ንጉሴ የ70 ዓመት
4. እሸቴ ዳመና የ42 ዓመት
5. አበባየሁ ዳኜ የ42 ዓመት
6. ሰሙ አባይነህ የ70 ዓመት
7. 2ሪፒ ወይንም ሚሊሻ አንዱ ክርቲያን አንዱ ሙስሊም በ24
8. አማረ በላይነህ የ80 ዓመት
9. ተሬ ደሴ የ25 ዓመት በአጠቃላይ የ10 ህይወት አልፈዋል።
በተጨማሪ 280 ሰው በላይ ተፈናቅለዋል

ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት፣ አሰኮ ወረዳ፣ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ እና ካራ ኩፍቴና በሚባሉ አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሟል።

በአሰኮ ወረዳ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ ብቻ በታጣቂ ኃይሎች በተፈጸመ ሰብአዊነት በጎደለው ጥቃት ከ10 በላይ ንጹሃን ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል።

ይህ አሰቃቂ ጥቃት በሰዎች ሕይወት ላይ ብቻ አላበቃም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የሚፈተትበትን መቅደስም ጭምር ኢላማ ያደረገ ነበር። በአካባቢው 101 ዓመታትን ዕድሜ ያስቆጠረው፣ ታላቁ የዕድሜ ባለጸጋ የጠላታ ጨፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወውደሙን ገልጸውናል።

በተመሳሳይ ጥቃት በካራ ኩፍቴና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት የተሰነዘረ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያኑ ንብረት የሆኑ ቤቶች በመቃጠላቸው ምእመናን የመድኃኔዓለምን ቅዱስ ጽላት ይዘው በእግራቸው ወደሌላ አካባቢ መሸሻቸው ታውቋል።

ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል። ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎችም ይዘውት የሸሹት እምነታቸውንና ማንነታቸውን ብቻ በመሆኑ አሁን ላይ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ ሲሉ ነበር በሃዘን ተውጠው የነገሩን።

ስለዝህ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ይህንን ችግር በማየትና በመረዳት የክርስቲያኖች መብት እንዲያስከብርና ዘላቂ መብቴ እንዲያመጣ በጥብቅ እንጠይቃለን።

Biyya Lallaba Arsii Aanaa Asakootti Kiristaanonni 10 ol Yoo Ajjeefaman Manni Kiristaanaa Qulqulluu Gabri'eelii Umurii Dheeraa Waggaa 101 lakkoofsise Guutumatti Gubate.

Mana Kiristaanaa Fayyisaa Addunyaa irrattis Saamichi kan taasifame yommuu ta'u Amantoonni Taabota qabatanii baqataniiru. Manni Jireenyaa fi qabeenyi Kiristaanotaas gubateera.

Namoonni Ajjeefamanis
1. Obbo Dammiroo Abarraa Umuriin 70
2. Kaffaalanyi Likkeelawu Umuriin 56
3. Hayiluu Nugusee Umuriin 70
4. Isheetuu Daammanaa Umuriin 42
5. Ababaayyoo Daanyee Umuriin 42
6. Sammuu Abbaayinee Umuriin 70
7. Milishoota 2
8. Obbo Amaraa Balaayinee Umuriin 80
9. Taree Dassee Umuriin 25 kan ta'an yoo ta'u walumaa galatti Namoonni 10 ajjeefamaniiru. Namoonni 280 ol immoo qa'ee isaanirraa buqqaafamanii baqataniiru.

Caamsaa 23 Bara 2018 irraa eegalee Biyya Lallaba Arsii Aanaa Asakoo Ganda Xalataa Caffaatti fi Naannoowwan Kaarraa Kufaateenaa jedhamanitti ajjeechaan Suukanneessaa Ortodoksoota irratti xiyyeeffate taasifamaa jira.

Ajjeechaa suukanneessaan kunis du'a Kiristaanotaa irratti qofa kan xiyyeeffate ooso hin taane Qulqulluu Dhiigni fi Foon Waaqayyoos kan itti amantootaf laatamu Mana Kiristaanaa irrattis kan xiyyeeffateedha. Kanaanis Manni Kiristaanaa Qulqulluu Gabri'eelii Xalataa Caffaa kan umurii Waggaa 101 ol lakkoofsisee guutumaan guututti gubateera. Badii wal fakkaatuun Mana Kiristaanaa Fayyisaa Addunyaa Kaarraa Kufaateenaa irratti saamichi qabeenya Mana Kiristaanaa irrattis taasifameera. Uummannis Taabota qabatee gara iddoo biraatti baqachaa jira.

Sababa rakkoo nageenyaa hamaa kanaafis Uummanni bakka itti dhalatee guddate, qe'ee godhatee qabeenya horaterraa dirqamaan buqqaafamaa jiraachuun ibsamaa jira. Kanaanis gadda guddaa keessa seenanii jiru.
Kanaafuu Mootummaa fi qaamni dhimmi ilaalu rakkoo kana hatattamaan ilaalee fi hubatee furmaataa Fulla'aa akka kennuu fi mirga Uummataa fi Amantoota Ortodoksii akka eegsisu cimsinee gaafanna.

ምንጭ:- የአርሲ ሀገረ ስብከት ሚድያ Miidiyaa Biyya Lallaba Arsii ...✍️

ዘማሪት ማኅሌት ወልደ ዮሐንስ እንኳን ደስ አለሽ በአሜሪካ ተወልደው አድገው ለቤተ ክርስቲያን ፍቅር ካላቸው ልጆች አንዷ ናት ቤተሰቦቿ ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉ በቤተ መቅደስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ...
06/02/2026

ዘማሪት ማኅሌት ወልደ ዮሐንስ እንኳን ደስ አለሽ በአሜሪካ ተወልደው አድገው ለቤተ ክርስቲያን ፍቅር ካላቸው ልጆች አንዷ ናት ቤተሰቦቿ ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉ በቤተ መቅደስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ደጅ ከማይለዩ እናት አባት እጅ ያደገች ናት ቸሩ መድኃኔ ዓለም አገልግሎትሽን ይባርክ እመ አምላክ አትለይሽ የቅዱሳን መላእክት ምልጃ የጻድቃን የሰማዕታት ጸሎት ከአንቺ ጋር ይሁን ..🙏

"እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ትንንሾችንና ትልልቆችን ይባርካል"
መዝሙር. 113 - 21

መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልሽ..!

06/01/2026

"ስለሰማችሁ ብቻ አትጸድቁም"
-መምህር ዘላለም ወንድሙ

👉"በዓለ ኀምሳ" ሐዋ. 2፥1ስብሐት ለከእሰግድ ለርደትከ👉"የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።"ኢዮ. 33፥4👉"እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚ...
05/30/2026

👉"በዓለ ኀምሳ" ሐዋ. 2፥1

ስብሐት ለከ
እሰግድ ለርደትከ

👉"የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።"
ኢዮ. 33፥4

👉"እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ"
ማቴ. 3፥16

👉"አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል . . . ከሆነም በኋላ ታምኑ ዘንድ አሁን አስቀድሞ ሳይሆን ነግሬአችኋለሁ።"
ዮሐ. 14፥26-29

👉"ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤ እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋር ኖራችኋልና ትመሰክራላችሁ።"
ዮሐ. 15፥26-27

👉"ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ። ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ መንፈሴን አፈስሳለሁ፤ በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ"
ኢዩ. 2፥28-30

👉"በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር። ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤ ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ። እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን? የጳርቴና የሜድ የኢላሜጤም ሰዎች፥ በሁለት ወንዝም መካከል በይሁዳም በቀጰዶቅያም በጳንጦስም በእስያም፥ በፍርግያም በጵንፍልያም በግብፅም በቀሬናም በኩል ባሉት በሊቢያ ወረዳዎች የምንኖር፥ በሮሜም የምንቀመጥ፥ አይሁድም ወደ ይሁዲነትም የገባን፥ የቀርጤስና የዓረብ ሰዎች፥ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።"
ሐዋ. 2፥1-11

👉"በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ከአብ ተቀብሎ ይህን እናንተ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው"
ሐዋ. 2፥33

#ጰራቅሊጦስ ብሂል(ማለት) [በቀሲስ ታምራት ውቤ]

1. #መጽንዒ፦ የሚያጸና ማለት ነው፡፡

2. #መንጽሒ፦ የሚያነጻ ማለት ነው፡፡

3. #ናዛዚ፦ የሚያፅናና ማለት ነው፡፡

4. #አራኃዊ፦ የሚከፍት ማለት ነው፡፡

5. #መስተፍሥሒ፦ ደስ የሚያሰኝ ደስታን የሚመላ ማለት ነው፡፡

6. #ከሣቲ፡- ምሥጢርን የሚገልጥ ማለት ነው፡፡

7. #አለባዊ፦ ማስተዋልን የሚሰጥ ማለት ነው፡፡

8. #መስተናግር፦ ሃይማኖትን፣ የጥበብን ቃል፣ ምሥጢርን የሚያናግር የሚያስተረጉም ማለት ነው፡፡

9. #መስተሥርዪ፡- ኃጢአትን የሚያርቅ የሚያስወግድ የሚደመስስ ማለት ነው፡፡

10. ፡- የእውነት መንፈስ፣ #መንፈስ #ቅዱስ ማለት ነው።

ስብሐት ለከ ጰራቅሊጦስ በስብሐተ አብ ቅዱስ
ስብሐት ለከ ጰራቅሊጦስ በስብሐተ ወልድ ውዱስ
ስብሐት ለከ ጰራቅሊጦስ በስብሐተ ስምከ ዘይሤለስ
ስብሐት ለከ አምላኪየ በአፈ ኵሉ ዘነፍስ
በሰማይ ወበምድር በባሕር ወበየብስ፠

እሰግድ ለርደትከ
እሰግድ ለርደትከ
እሰግድ ለርደትከ

Address

Lancaster, PA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ermiyas Girma posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ermiyas Girma:

Share