Ethio Beteseb Media

Ethio Beteseb Media ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ እንዲሁም ወቅታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መረጃን የሚያደርስ ሚዲያ ነው ።
501(c)(3) Registered
(3)

💍 “ይህ ምስጢር ታላቅ ነው”          (ኤፌሶን 5፥32)👉በዛሬው ዕለት ሁለት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ ከሁለት የተለያዩ አገራት ሆነው፣  በቅድስት ቤተክርስቲያን ቅዱስ ጋብቻቸውን ...
09/20/2026

💍 “ይህ ምስጢር ታላቅ ነው”
(ኤፌሶን 5፥32)

👉በዛሬው ዕለት ሁለት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ ከሁለት የተለያዩ አገራት ሆነው፣ በቅድስት ቤተክርስቲያን ቅዱስ ጋብቻቸውን በሥርዓተ ተክሊል ፣ በሐዋርያዊት እምነትና በአንድ ቅዱስ ምስጢር ተዋሕደዋል፣በሥርዓተ ተክሊል ቅዱስ ጋብቻቸውን ፈጽመዋል።

🇪🇹 በኢትዮጵያ
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ እና ወ/ሮ ሳምራዊት

🇺🇸 በአሜሪካ
ዲያቆን ኢዮብ እና ወ/ሮ ማርያማዊት

👉ጋብቻ የሁለት ሰዎች ስምምነት ብቻ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚፈጸም ቅዱስ ቃል ኪዳን ነው። ሁለት ልቦች በአንድ ፍቅር፣ ሁለት ሕይወቶች በአንድ ተስፋ፣ ሁለት አገልግሎቶች በአንድ መንፈሳዊ ዓላማ የሚተሳሰሩበት ታላቅ ምስጢር ነው።

👉እግዚአብሔር አምላክ ትዳራቸውን ይባርክ፤ ቤታቸውን የፍቅር፣ የሰላም፣ የጸሎትና የአገልግሎት ቤት ያድርግላቸው። በሃይማኖት ጽኑ፣ በፍቅር የተሳሰሩ፣ በትዕግሥት የተደጋገፉና ለብዙዎች በረከት የሚሆኑ ያድርጋቸው።

🙏እንኳን ለቅዱስ ጋብቻችሁ ደስ አላችሁ!
“እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው።”
(ማቴዎስ 19፥6)

📍ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

09/17/2026

እንኳን ለአዲሱ ዓመት እና ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
Happy Ethiopian New Year & Meskel Celebration!

በቨርጂኒያ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተዘጋጀ የመስቀል በዓል የምሳ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

📍 ቦታ / Location:

6935 Columbia Pike, Annandale, VA 22003

🗓 ቀንና ሰዓት / Date & Time:

Saturday, September 19, 2026 at 2:00 PM

ቅዳሜ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ

ኑ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ!

09/15/2026

ይደመጥ

ለወላጆች መልእክት  ልጆቻችሁን ለማስተማር ዛሬ ምዝገባው የመጨረሻ ቀን  ነው
09/15/2026

ለወላጆች መልእክት ልጆቻችሁን ለማስተማር ዛሬ ምዝገባው የመጨረሻ ቀን ነው

An 8-week course in kindness, courage, and family for Ethiopian Orthodox students ages 9+, grounded in scripture from beginning to end.

📝እነዚህ እነማን ናቸው ...? 👉ልብሳቸው የተዋሕዶ ፣ከአንደበታቸው የሚወጣው ኑፋቄ  (የተሐድሶ እንቅስቃሴ )  እነዚህን የመሰሉ በውጭም በሀገር ውስጥም በየአጥቢያው የተሰገሰጉ  በርካታ ናቸ...
09/14/2026

📝እነዚህ እነማን ናቸው ...?

👉ልብሳቸው የተዋሕዶ ፣ከአንደበታቸው የሚወጣው ኑፋቄ (የተሐድሶ እንቅስቃሴ ) እነዚህን የመሰሉ በውጭም በሀገር ውስጥም በየአጥቢያው የተሰገሰጉ በርካታ ናቸው ። ወገን ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ነው ፣ የተሐድሶ እንቅስቃሴ መልኩን ቀይሮ በስፋት በየቦታው ተጀምሯል ።

👉በዚህ ጉዳይ በጋራ ቆመን በማር የተለወሰ የሚመስል መርዛቸውን እየረጩ ያሉ ወገኖችን እናጋልጥ ...📍

📍 ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

📝"ዘመንን ያሻገረ ዕድሜ" ዘመነ ሉቃስ     "እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ለአዲሱ ዓመት "👉በአዲስ ዓመት ዋዜማ በመወለዴ መልካም ምኞታችሁን ለገለጻችሁልኝ ፣ ወዳጄቼ ክብር ይስጥልኝ ፣ በዕ...
09/10/2026

📝"ዘመንን ያሻገረ ዕድሜ" ዘመነ ሉቃስ

"እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ለአዲሱ ዓመት "

👉በአዲስ ዓመት ዋዜማ በመወለዴ መልካም ምኞታችሁን ለገለጻችሁልኝ ፣ ወዳጄቼ ክብር ይስጥልኝ ፣ በዕድሜ በጤና ይጠብቅልኝ ፣ ተባረኩ🙏

👉የሰው ልጅ ባለሥልጣን ፣ ታወቂና ዝነኛ ፣ ባለሀብት ፣ ቆንጆ መልከመልካም ፣ ሁሉ ያለው ስለሆነ የማያገኘው ግን እግዚአብሔር ብቻ በቸርነቱ የሚያድለው ሀብት ዕድሜ ነው ።

👉 ዕድሜ ያለው ሰው ዘመንን ይሻገራል ክፉውንም ደጉንም ያያል ታዲያ ዕድሜ ይገድበናል ሳይሉ በዘመናቸው እኩይ ተግባር የፈፀሙ በአንፃሩም መልካምን ሥራ የሰሩ ዛሬ የሉም እንነሱ እንደሌሉ ያወቅነው ፈጣሪ ዕድሜ ስለሰጠን ብቻ ነው ። ይህንን እንድናውቅ የረዳንን አምላክ ማመስገን ሳይሆን ባወቅንበት መጠንና ልክ ዛሬ በማይሰሙንና በማያዩን ሙታን ላይ እንፈርዳለን፤ እጃችንን እንቀስራለን የዕድሜው ሚስጢር ግን ዕድሜ ለንስሀ እንደሆነ ብዙዎች ዘንግተናል።

👉ይችን ምድር ለመርገጥ የሚጠየፉ የነበሩ ዛሬ ከምድር በታች አፈር ተጭኖአቸዋል ፤ በደግ ሥራቸው ስምና ዝናን ያተረፋ በመልካም አርአያነታቸው በቁማቸው መልካሙን የትህትና ልብስ ለብሰው የነበሩ ዛሬ ይህንን ዘመን እንዲያዩ የምንመኝላቸው ከመቃብር በታች ናቸው።

👉በሚያልፍ ቀን ውስጥ የማያልፈው ጌታ በቸርነቱ ዘመንን የምንሻገርበት ዛሬ ዕድሜ የሰጠን ምን የተለየ ሥራ ሰርተን ይሆን?????

👉ዘመንን በቸርነቱ የሚያሻግር ፈጣሪ በአዲስ ዘመን አዲስ ልብ እንዲኖረን ይሻል ፤ አሮጌውን ልብስ አውልቀን አዲሱን እንድንለብስ፤ ከካራን ወጥተን ወደ ከንአን እንድንገባ ፤ በሞት ሳይሆን በሕይወት እንድንመላለስ ፤ በሐጥያት ሳይሆን በጽድቅ እንድንኖር ፤ እርስበርስ በመገፋፋት ሳይሆን በመቻቻል ፤ በጠብ ሳይሆን በፍቅር ፤ ልዩነትን በማጥበብ አንድነትን እያሰፋን እንድንኖር ዘመንን የሚያሻግር ዕድሜ የሰጠንን አምላክ እያመሰገንን በፍቅር ፤ በይቅርታ እየተሳሰብን መንፈሳዊ ሕይወታችንን በንስሀ እያደስን የምንኖርበት ዘመን እንዲሆን ዕድሜ ሰጥቷናልና እያመሰገነው በንስሀ እንኑር📍 ይህ ዕድሜ መቼ እንደሚገታ አናውቅምናም በሞት ሳይሆን በሕይወት ለመኖር እግዚአብሔር ይርዳን !!!

👉የኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ወዳጆች( ቤተሰቦች ) ሁላችሁንም እንኳን አደረሳችሁ መልካም አዲስ ዓመት ዘመነ ሉቃስ የሰላም ፤ የፍቅር ና የደስታ
ይሁንላችሁ!!!

Address

Maryland City, MD
20876

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Beteseb Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Beteseb Media:

Shortcuts

Share