09/30/2026
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሰየሙ
ላለፉት አመታት አዲስ አበባን በከንቲባነት ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በድጋሜ ከንቲባ ሆነው በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ተሰይመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንግስት ምስረታና 4ኛው ዙር የከተማው ምክር ቤት የመክፈቻ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመሩበት ሁሉ ውጤት የሚያስመዘግቡ ጠንካራ የህዝብ ልጅ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ያስመሰከሩ ናቸው።
በከተማው የስራ ባህል እንዲለወጥ የህዝብ ችግር የሚፈቱ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በማሰራት ከተማዋን በለውጥ ጎዳና መርተዋል።
ከተማዋ አዲስ አበባ በሰው ተኮር የልማት ስራዎች ተጠቃሽ እንዲትሆን አስችለዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፅናትን ብርታትን ለዓላማ ታምኖ መስራትን በከተማዋ የለውጥ ስራዎች ላይ አስመስክረዋል ሲሉ የምክር ቤት አባላትም ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኦሮሚያ ክልል ከመምህርነት ጀምሮ በበርካታ የሃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።
እንዲሁም በፌዴራል ደረጃም በበርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊነት አገልግለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ሆነው የተሰየሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።