ይህን የውቃሉ?
ታሪክ መግቢያ
ታሪካዊ አመጣጥ
የስልጤን ብሔረሰብ ታሪካዊ አመጣጥ በተመለከተ በብሔረሰቡ የዕድሜ ባለፀጋዎች የሚነገሩ የትውፊት እና አንዳንድ የተገኙ የጽሑፍ መረጃዎችን በሁለት መልኩ ከፍለን እንመለከታለን፡፡ የመጀመሪያው የትውፊት መረጃ እንደሚያመለክተው በጥንት ጊዜ ዛሬ የብሔረሰቡ አባላት በሚኖሩበት ሥፍራ "ዡራ" ወይንም "ሀርላ" በመባል የሚታወቁ ሕዝቦች ይኖሩ እንደነበር ይገልፃል፡፡ ሌላው መረጃ ደግሞ በ8ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ የተወሰኑ ቀደምት የብሔረሰቡ አባላት ከምድረ ሣውዲ አረቢያ ተነስተው የኤደን ባህረ ሰላጤን አቋርጠው በስተምስራቅ አቅጣጫ በዘይላ ደሴት በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ያመለክታል፡፡ እነዚ
ህ ሕዝቦች በፀሐይ መውጫ አቅጣጫ ወደ አገሪቱ ክፍል ከገቡ በኋላ በሐረር ጀበርቲ ዛሬ “አደሬ” ወይንም "ሐረሪ" በሚባለው አካባቢ ቆይታ አድርገው ወደ ዛሬው መገኛ ሥፍራ በመምጣት ከነባሩ ሕዝብ ጋር ተቀላቅለው መኖር እንደጀመሩ ይነገራል፡፡
የእነዚህ ክፍሎች አመጣጥ በአብዛኛው እስልምናን ከማስተማር ጋር የተያያዘ እንደነበር የተገኙ የትውፊት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
የተወሰኑ የብሔረሰቡ አባላት ደግሞ የግራኝ መሀመድ ወረራ ካበቃ በ1ዐኛው ዓመት ገደማ ከ1553/63 በሀጂ አልዬ መሪነት የተለያዩ ቦታ እየሠፈሩ አሁን በዋናነት ወደ ሚኖሩበት አካባቢ እንደደረሱ ይነገራል፡፡ ሀጂ አልዬ በአባታቸው ኢትዮጵያዊ በእናታቸው የአረብ ዝርያ እንዳላቸው የሚነገር ሲሆን በስፍራው ሲደርሱ በመጀመሪያ መቀመጫቸውን ያደረጉት አልቾ ወሬሮ ላይ እንደነበር በታሪክ ይነገራል፡፡ በዚያን ወቅት የነበረው የስልጤ ሕዝብ ወደአሁኑ ስፍራ ከመድረሱ በፊት ገደብ ዝዋይ / ላቂ ደንበል/፣ ሲዳማ፣ አሊቶ ዳገት /ቡልቡላ አጠገብ/ በሚባሉ አካባቢዎች ቆይታ እንዳደረገ የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በወቅቱ ለሕዝቡ እንቅስቃሴ እንደምክንያት የሚገለፀው በግራኝ መሀመድ የተነሣ ጥሩ የመኖሪያ አካባቢ ለመፈለግ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በአጠቃላይ በአሁኑ ጊዜ ያለው የስልጤ ብሔረሰብ ከላይ በቀረቡትና በተለያዩ ጊዜያት የመጡ እና የነባር ሕዝቦች የረጅም ዘመን ውህደት ውጤት እንደሆነ ይታመናል፡፡
ዛሬም ይህ የስልጤ ብሔረሰብ በሀገራችን ከሚገኙ በርካታ ብሔረ-ብሔረሰቦችና ህዝቦች አንዱ ነው: ብሔረሰቡ በአዲስ አባባ-ሆሳዕና መንገድ በ172 ኪ.ሜ ርቀት ከመንገዱ ግራና ቀኝ 60 ኪ.ሜ ያህል ገባ ብሎ በሚገኘው በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን በስፋት ይኖራል። የዞኑ ጠቅላላ ስፋት 3ሺkm² ነው:: እኤአ 2004 በተደረገ ቆጠራ በዞኑ የሚኖረው 850ሺ በዞኑ መስተደደር ቢቻ የነበረ ሲሆን የዞኑ ተወላጆች የዞኑ ህዝብ በዞኑ መስተዳደር ስር ቢቻ የሚገኘት ከ1200,000 በለይ ይሆናል ተቢሎ ይታሰበል።
ከዞኑ በተጨማሪ ከ40% በለይ የሚሆኑ ከዞኑ ጎራቤት ካጉራጌ፣ካሀድያ ፣ካአለበና ካኦሮሞ ብሔረ-ቤሔራሰቦች ታቀለቅሎ ሳፍሮወል እናም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎችና የውጪ ሀገራትም በስፋት ተሰራጭተው ይኖራሉ። ከብሔረሰቡ 100% የሚሆነው የእስልምና ዕምነት ተከታይ ነው። 0.9 % የኣማራና የሌላ ብሔርሰብ ኦርቶዶክስ ክርስታን ይኖርበታል። ከዞኑ ውጭ የሉ ስልጤዎች 100% የስልምና ተካታይ ሲሆኑ በታጫር 99 % በለይ በከፍል ስልጤ ሙስልሞች ነቸው። ይህም መለት በአባት ወይም በእናት የስልጤ ዝርየነት የለቸው ነቸው። በስልጤ ብሔረሰብ ግብርና ዋነኛ የኢኮኖሚ መሠረት ሲሆን ከብት አርባታና ንግድም እንዲሁ የብሔረሰቡ የሀብት ምንጭ ናቸው።
የስልጤ ዞን አሁን በዛጠኝ ወረዳ የወቀረ ነው። ማለትም ምዕራብ አዘርነት:ምስራቅ አዘርነት:አልቾውሪሮ:ዳሎቻ:ላንፎሮ:ሳንኩራ :ሁልባረግ ስልጢና ወራቤ ወረዳዎች የተዋቀረ ነው።
የብሔረሰቡ ቋንቋ ስልጢኛ ሲሆን ከሴማዊያን ቤተሰቦች ይመደባል የቋንቋው ስፋት ከሀረሪኛና የዛይ ቋንቋ ጋር በጣም ሲመሳሰል በበርካታ የቃላት ትርጉዋሜ ደረጃ ከአረብኛ: አማርኛ ትግርኛ አርጎቢኛና ኦሮምኛ ጋርም ይገናኛል።
"ስልጤ" የሚለው ስም በዞኑ በሚገኙ በዋነኛነት አምስት ማኅበረሰቦች ማለትም ስልጢ መልጋ: ሁልባረግ :አዘርነት በርበሬና አልቾውሪሮ የጋራ መጠሪያ ሲሆን ማኅበረሰቦቹ በታሪክ: በማኅበራዊ ኑሮ :በባህል: በቋንቋና በሀይማኖት እንዲሁ ተመሳሳይ ናቸው። የስያሜውን መነሻ በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎች ያሉ ሲሆን ስያሜውን ያገኘው ከሀጂ አሊዬ 5ተኛ ልጅ ከሆኑት ገን-ስልጤ አልያም ሱልጣኔት ከሚለው አረብ ኢስላማዊ መንግስት ጥንታዊነት እንዲሁም ነባር ኢስላማዊ መንግስታትና ማኅበረሰቦች የታሪክ ወራሽነትን በማሰብ ነው የሚለው በስፋት ይገለፃል።:
ስልጤ የሚጣረበቸው ታጨመር ስሞች እስላም ታብሎ ስጣራ ፡ ቋንቋቸው` እስላምኛ `በመበል በደቡብ ክፍል እስከ ዘሬ ይታወቃል። ከሳሜን' ጉራጌ` ታብሎ የሚታዋቅ ብሆንም ስልጤ የራሱን ዞን ከመሰራተ ጀምሮ ስሙ ቀርቶዎል።
የስልጤ ብሔረሰብ ብሔረሰቡ በዋናነት በክልሉ በስልጤ ዞን ውስጥ በሚገኙ ስምንት ወረዳዎች በሀገር ውስጥ ፣ በዎላይታ፣ በሲዳማ እና ጌዲኦ ዞኖች፣ በሀዋሣ ከተማ እና በአላባ ልዩ ወረዳ እንዲሁም ከክልሉ ውጪ በጂማ፣ በወለጋ፣ በናዝሬት /አዳማ/ ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በአደስ አበባ በባርካታ የትዮጵያ ከተሞች ከሌሎች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ጋር በስብጥር ይኖራሉ፡፡
ብሔረሰቡ በዋናነት የሚኖርበት ሥፍራ በሰሜን እና በሰሜን ምዕራብ የጉራጌ ዞን፣ በደቡብ የሀዲያ ዞን እና የሀላባ ልዩ ወረዳ፣ በምዕራብ የሀዲያ ዞን ፣ በምስራቅ የኦሮሚያ ክልል ያዋሰኑታል፡፡
የብሔረሰቡ ዋነኛ መገኛ ሥፍራ መልክዐ ምድራዊ አቀማመጥ በአብዛኛው ሜዳማ ሲሆን የተወሰነው በተለይም ምዕራባዊው ክፍል ተራራማነት ያለው ነው፡፡ የአየር ንብረቱ በተለያዩ ደረጃ ደጋማ፣ ወይናደጋማ እና ቆላማ ሲሆን አብዛኛው ክፍል ወይናደጋማ ነው፡፡ የሕዝቡ ኢኮኖሚ የተመሰረተው በዋናነት በእርሻ ሲሆን ከዚሁ ጐን ለጐን የተወሰነው ክፍል የከብት እርባታን፣ ንግድን፣ እና አንዳንድ የእደ ጥበብ ውጤታችን በማምረት ኑሮአቸውን ይመራሉ፡፡ በዋናነት ከሚመረቱ የእርሻ ምርቶች መካከል በርበሬ ፣እንሰት፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ ፣ ገብስ፣ አተር፣ ባቄላ፣ ቦሎቄ፣ አደንጓሬ፣ ቡና፣ ጫት፣ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ቋንቋ
የስልጤ ብሔረሰብ አፍ መፍቻ ቋንቋ ስልጢኛ ሲሆን ከሴማዊ የቋንቋ ቤተሰብ ይመደባል፡፡ ቋንቋው ከአረብኛ፣ ከጉራጊኛ ፣ ከሐረሪ፣ ቋንቋዎች ጋር ይመሳሰላል፡፡ የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ በከተሞች አካባቢ ያሉ አማርኛን እንዲሁም እንደ አጐራባችነታቸውና ቅርበታቸው የሀድይኛ፣ የማረቆኛ፣ የጉራግኛ፣ የኦሮምኛ እና የሀላብኛን ቋንቋዎች በሁለተኛ ደረጃ ይናገራሉ፡፡ ሌሎችም አጐራባች ብሔረሰቦች እንዲሁ የስልጢኛን ቋንቋ እንደየቅርበታቸው ለመግባቢያነት ይጠቀማሉ፡፡
ስልጢኛ ከ6ዐ ዓመት በፊት የአረብኛ ፊደልን በመጠቀም ለጽሑፍ የዋለ ቋንቋ ቢሆንም ከ1967 ዓ/ም ጀምሮ ልዩ ልዩ አዋጆች እና የመሰረተ ትምህርት ማስተማሪያ መጽሐፍት የሳባ ፊደልን በመጠቀም በቋንቋው ተተርጉመዋል፡፡ ከ1987 ዓ/ም ጀምሮ የ1ኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሣይክል የመማሪያ መጽሐፍት በቋንቋው ተዘጋጅተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የትምህርት ቋንቋ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ እንደዚሁም የሣባ ፊደልን በመጠቀም የመማሪያ መጽሐፍት፣ የስልጢኛ መዝገበ ቃላት፣ የስልጤ ሕዝብ ታሪክ እና ሌሎች መጽሀፍቶች በቋንቋው ተጽፈው አገልግሎት እየሠጡ መሆናቸው ቋንቋው በማደግ ላይ ያለ ስለሚሆኑ የሚገልፁ እውነታዎች ናቸው፡፡
የስልጤ ባህል
ባህላዊ አስተዳደር
በስልጤ ብሔረሰብ ውስጥ በርካታ ማህበራዊ ቡድኖች / ጐሣዎች/ ያሉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ስልጤ፣ መልጋ፣ ችሮ ፣ ዲላባ/ጳ/፣ ኑግሶ /ኦግሶ/፣ አሊቶ፣ አባሮ፣ ኡራጎ፣ ጉምቢ፣ ጊዳዋሁሴንና አለቂሮ ለአብነት ይጠቀሳሉ፡፡ እያንዳንዳቸው በንዑሣን ጐሣዎች የተከፋፈሉ ናቸው፡፡ ከላይ የተገለኒትንም ሆነ ሌሎችንም ጐሣዎች በአንድ ላይ የሚያስተሳስርና የሚያስተዳድር "ጐጐት" የሚባል ባህላዊ አስተዳደር ሥርዓት ያላቸው ሲሆን የሥርዐቱ አፈፃፀም "ሴራ" ወይንም "ዳምቡስ" በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሥርዓት የሚመራው በጐሣ መሪዎች ሲሆን እያንዳንዳቸው የራሳቸው የሆነ የሥልጣን ተዋረድ እና ህጋዊ መተዳደሪያ ደንብ አላቸው፡፡
የብሐረሰቡ ባህላዊ አስተዳደር የተለያዩ የስልጣን ሀላፊነትና የሥራ ድርሻ ያላቸውን አካላት ያቀፈ ሲሆን በዚህ የስልጣን ተዋረድ መሰረት "ገራድ" ዋና ዳኛ ሲሆን ከዚህ በታች ሙሉ ገራድ፣ ወላብግራድ፣ ሣረ ገራድ በመባል የሚታወቁ ረዳቶች አሉት፡፡ ከነዚህ ባህላዊ አስተዳደር አካላት በተጨማሪ የበታች አስተዳደር የሚባሉ "ሞሮ" የጐሣ ተጠሪ፣ ሙራ" የአካባቢ ተጠሪና ተላላኪ፣ እና በቤተሰብ ደረጃ የቤተሰብ ሸንጐ የሚባሉ አሉ፡፡ እያንዳንዱ ጐሣ "ሜልቾ" የሚባል ጉባኤ አለው፡፡ ከዚህም ባሻገር በብሔረሰቡ ዘንድ አራት ደረጃ ያሉት ባህላዊ የፍትህ ሥርዓት ያለ ሲሆን እነዚህም እንደየቅደም ተከተላቸው እና የሥራ ተግባራቸው "ማገ" ፣ “ራጋ" /ህግ ተርጓሚ/፣ ፈርዛገኝ /ይግባኝ ሰጪ ክፍል/ እና "ወገጋገኜ" በመባል ይጠራሉ፡፡ ይህ ሥርዓት በብሔረሰቡ ውስጥ የሚከሠቱ ግጭቶችንና ወንጀሎችን እንደየክብደታቸው እና ጥፋታቸው መጠን በመመዘን ተገቢውን ቅጣት በመስጠት በባህላዊ መንገድ ግጭት የሚፈታበት አካሄድ አለው፡፡
አንድ የማህበረሰቡ አባል የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ቢፈጸም ወንጀሉን አውቆና አስቦበት አሊያም በድንገት የፈፀመ መሆን እለመሆኑን በማጣራትና በመመርመር በባህላዊ መንገድ ፍርድ ይሠጣል፡፡ ይህም በብሔረሰቡ አጋርሳ፣ ተተጋ፣ ሰበባ፣ ተልካና ተልማ በማለት እንደወንጀሎቹ ዓይነት ቅጣት ይቀጣሉ፡፡ በሥርዓቱ "ሙሊ" በሚባል የመሐላ እና የወንጀል ምርመራ ጥበብ ድብቅ ወንጀሎች ይወጣጣሉ፡፡ የተጠርጣሪው ወንጀለኛ የወንድና የሴት አያት ወገኖች አብረው መሀላ እንደፈጽሙ ይደረጋል፡፡ ይህን ለመፈፀም ፈቃደኛ ካልሆነ ተጠርጣሪው በወንጀለኛነት ይፈረጃል፡፡
በተለይ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል የፈፀመ መሆኑ ከተረጋገጠ የወንጀለኛው ወገኖች ካሣ ይከፍላሉ፡፡
ሴቶች በባህላዊ ሥርዓቱ የመሰብሰብ መብት የላቸውም፡፡ በቤተሰብ እና ከአካባቢው ሕዝብ ጋር አለመስማማት ወይም አለመግባባት ሲፈጠር ግን ሴቶች ለሸንጎው "አቤት" ይላሉ፡፡ አቤቱታቸው ተሰሚነት ስላለው ፈጣን ምላሽ ያገኛሉ፡፡ በብሔረሰቡ ዘንድ የጎሣ መሪው ሚስት “ኢቲኮ” የሚል የማዕረግ ስም ይሠጣታል፡፡ እሱ ሥልጣኑን ሲረከብ ቤተሰቧቿ ከ50-60 ከብቶች በማምጣት ድግስ ደግሠው እሷንም ለማዕረጓ ተስማሚ የሆነ ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ ሴቶች በኢኮኖሚው እና በሌሎችም ሥራዎች የጎላ ሚና አላቸው፡፡ አብዛኛው ስራ በብሔረሰቡ በሴቶች ጉልበት ይከናወናል፡፡
ባህላዊ እሴቶች
የጋብቻ ሥርዓት
በብሔረሰቡ ዘንድ ብዙ የጋብቻ ሥርዓት አይነቶች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል የመጀመሪያው በስፋት የተለመደው የስምምነት ጋብቻ ነው፡፡ ይህ የጋብቻ አይነት የአግቢው ቤተሰብ ሽማግሌ ወደ ልጅቷ ቤተሰቦች በመላክ በተገቢዎች ቤተሰብ ሥምምነት የሚፈፀም ነው፡፡ ሁለተኛው የጋብቻ ዓይነት "ኩል" ይባላል፡፡ በዚህ የጋብቻ ሥርዓት ልጅቱም ሆነች ቤተሰቦቿ ሣያውቁ አግቢው ፈረስ ላይ ተቀምጦ ከነፈረሱ ወደ ልጅቱ ቤት በመግባት አለንጋውን በቤቱ ምሰሶ ላይ አስሮ ልጅቱ እንድትሰጠው ቤተሰቧን የሚያስገድድበት ነው፡፡
ሶስተኛው የጋብቻ ዓይነት “ጠለፋ”፡- ሲሆን ወላጅ ከላይ የተጠቀሰውን የኩል የጋብቻን ካልተቀበለ ልጅቱ ወይም ቤተሰቦቿ ልጅን ካልፈለጉ ወይም አግቢው ወጪና ጋጋታን በመፍራት የሚወስደው ሌላ አማራጭ ነው፡፡ በዚህም ልጅቱን ይዞ በመኮብለል በመጨረሻም ሽማግሌ ልኮ ጋብቻው የሚፈፀምበት ሥርዓት ነው፡፡ አራተኛው የጋብቻ ዓይነት “ኦጋ” የሚባል ሲሆን በዚህ የጋብቻ ሥርዓት ሴቷ የመረጠችው ልጅ አባት ቤት ሰተት ብላ በመግባት ምሰሶ ላይ ቅቤ ቀብታ እንዲያገባት የምትጠይቅበት ሥርዓት ነው፡፡ አምስተኛው የጋብቻ ዓይነት የውርስ ጋብቻ የሚባል ሲሆን በዚህ የጋብቻ ሥርዓት ባል ሲሞት የሟች ታላቅ ወይም ታናሽ ወንድም አለያም የቅርብ ዘመድ የሟችን ሚስት የሚያገባበት ወይም የሚወርስበት ሥርዓት ነው፡፡
በብሔረሰቡ ዘንድ ሠርግ እና የጥሎሽ ሥርዓት የሚፈፀመው እንደ ቤተሰቡ ኢኮኖሚ አቅም ነው፡፡ ብር ከሣር ጋር ተጨብጦ ለእናት፣ለአባትና ለቅርብ ዘመዷቿ ጉልበት እየተሳመ ይሰጣል፡፡ በስልጤ ብሔረሰብ ጋብቻ አፈፃፀም ብዙ ወጪ ያለባቸው የልጅቷ ወገኖች ናቸው፡፡ ለመተዳደሪያ እና ለመቋቋሚያ የሚሆን ቁሳቁስ እና ገንዘብ ቤተሰቦቿ ይደጉሟታል፡፡ በቅሎ መውረጃና የመቀነት መፍቻ ተብሎ የልጅቷ አባትና እህቶች ከብት ወይም ገንዘብ ለሙሽራዋ ይሸልማሉ፡፡ ሠርገኛዉ ወደ ሙሽሪት ቤት ከመሄዱ በፊት “አታካኖ” የሚባል ባህላዊ ምግብ ይመገባሉ፡፡ ልጅቱ ቤት ሠርገኞቹ ቅቤ እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡ በሠርጉ ዕለት የሩቅና የቅርብ ዘመድ አዝማድ ይሰበሰባል፤ ከበሮ እየተደለቀ ይዘፈናል፡፡ ሙሽሪትን በቀን ብርሃን ይዞ መውጣት በባህሉ የተከለከለ ነው፡፡ ከጋብቻ በፊት የሴትና የወንድ ልጆች ግርዛት የተለመደ ሲሆን ሴቶች በወሊድ ወቅት ልዩ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል፡፡
ባህላዊ በዓላት
በብሔሰቡ ባህላዊ እና መንፈሳዊ በአላት ይከበራሉ፡፡ አረፋ፣መውሊድ እና ረመዳን ፆም ፍቺ እንዲሁም “ሸዋል” በሚባሉ ወቅቶች ህዝቡ ከበሮ እየደለቀ በዓላቱን ያከብራቸዋል፡፡
ባህላዊ የቤት አሠራር
በስልጤ ብሀሄረሰብ ባህላዊ የቤት አሠራር ብሔረሰቡን የቤት አሠራር ስንመለከት በስልጤ የህብረተሰብ አጠረር " ገር " ማለት ቤት ስሆን በደጋው ‹‹ጉዬ›› የሚባል ትልቅ ቤትና ትንሹ" ዛገር'' ይበላል። ሁለቱ የሚሳሩት በጥድ፣በባህር ዛፍና በቀርቀሀ ይሠራል፡፡ ሌለኛው አንድ ሆኖ በትንሹ የሚሰራው ቤት ‹‹ጋር›› ሲባል መለስተኛ መጠን ያለው ሆኖ በቆላማው ክፍል ደግሞ ብዙ እንጨትና ሳር የማይፈልጉ የሣር ቤቶች ይሠራሉ፡፡ በነዚህ አካባቢዎች ሁሉም ቤቶች ግድግዳቸው በጭቃ ይለሰናል፡፡
ባህላዊ መሣሪያዎች
የሥልጤ ባህላዊ ቤትባህላዊ መሣሪያዎች በዕደ ጥበባት ሥራዎች በኩል ከሸክላ፣ከብረታ ብረት(ማረሻ)፣ከሻማ ስራ አልባሳት፣ከእንጨት ከቀርከሀ እና ከስንደዶ የተለያዩ የመገልገያ ዕቃዎች፣ መጠጫዎችና ጌጣጌጦች፣ ወለል ምጣፎችና የመኝታ ቁሳቁሶች በህዝቡ ዘንድ በግልና በህብረት ይመረታሉ፡፡ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ከሸንበቆ፣ከመቃ እንዲሁም ከብረት የትንፋሽ መሣሪያዎች ከቆዳ ደግሞ ከበሮን በመስራት ለሠርግ፣ ለአመታዊ ባህላዊ በዓላትና ለጭፈራ ይጠቀምባቸዋል፡፡ የጦር መሳሪያዎች እንደጋሻ፣ጦር፣ወስፈንጥርእንዲሁም አሽግሌ የተባሉትን በመጠቀም ምርቱን የሚያበላሹባቸውን አውሬዎች ለማጥመድና ለውጊያ ሲገለገልባቸው ኖሯል።
ባህላዊ ምግብና የአመጋገብ ሥርዓት
ብሔረሰቡ በበዓላት ጊዜ የሚያዘጋጃቸው ባህላዊ ምግቦች ሉልሶ (ክትፎ)፣አይብና ጎመን፣የጎመን ክትፎ፣(ጨበሮ) ፣በቅቤ የታሸ ቆሎ (ሀና ቃላ) ይባላል፡፡ እንዲሁም ሻሜታ ይጠጣል፡፡ ቆጮ፣ጦሮሾና በቆላማ ክፍል ደግሞ እንጀራ በአዘቦት ቀናት ይበላሉ፡፡
ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት
ብሔረሰቡ የተለያዩ የለቅሶ ሥርአቶች አሉት፡፡ ትልቅ ሰው ወይም የሀገር ሽማግሌ ሲሞት መልዕክተኛ በተለያየ አቅጣጫ ይላካል፡፡ ፈረሰኛ ከጎረቤት ይመጣል፡፡ ሴቶች እንደየቅርበታቸው መሬት ላይ በመውደቅ ሀዘናቸውን ይገልፃሉ፡፡ የሟች ልብሶች ተይዘው ለቅሶ ይለቀሳል፡፡ ሟች የጎሣ መሪ ከሆነ ከቀብር በኋላ መሪነቱ ለልጅ ይሰጣል፡፡ ወራሹ ህፃን ከሆነ ሞግዚት ይመደብለታል፡፡ ትዳር ሳይመሰርት ለሞተ መሪር ሀዘን ይታዘናል፡፡
በዞኑ በርካታ ድንቅ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ቅርሶችና መስህቦች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል በኢትዮጵያ ጥናትና ቅርስ ጥበቃ የታወቀው የአሳኖ ተክል ድንጋይ ዋነኛው ሲሆን ሌሎችም የትክል ድንጋዩች በአልቾ ወረዳ ቃዋቆቶ ጣንዣ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የአይናጌ፣የኡርባ ዋሻዎችም እንዲሁ ታሪካዊ ናቸው ፡፡ ለሞሮ ፋፍፍሮ፣ወይራ የተባሉ ፏፏቴዎችና አሹቴ ሙቅ ውሃ፣ የቡራቆ፣ የሀሮ ሻይጣንና ትንሹ አባያ የተባሉ የተፈጥሮ ሃይቆች በዞኑ ሲገኙ ጋሮራ፣ዌራ፣ዲጆ፣ የተባሉ ወንዞችና ጋፋት፣ሙጎ፣ባልጨኩ ተራራዎችም እንዲሁ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ይገኛሉ፡፡ የሐጂ አሊዬ ኡምናን፣ አልኪ፣ጌስቴይ ጣሂራት፣ገንሠልጤ የተባሉ ጥንታዊ መስጊዶችም ከብሔረሰቡ ታሪካዊ ቅርሶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ለበላጣ መረጃ ቀጥሎ የላውን ኣንብቡ---
የስልጤ ብሄረሰብ በግሎባል አቀማማጥ
======================
Location: Southern Ethiopia, Ethiopia, East Africa, Africa
ለቲቱድ (Latitude) : 7° 49' 55.9" ሳሜን (7.8322°) በስታ ሳሜን(north)
(በሳበት ዲግሪ በአርበ ዛጠኝ ደቂቃ 55.ሳኮንድ 9 መይክሮ ሰካንድ በስታ ሳሜን ወይም (783 22) ዲግሪ ይህል ስሆን
ለንግቱድ (Longitude): 38° 16' 7.4" (38.2687°) በስታ ምስራቅ east
Elevation: 1,967 metres (6,453 feet)
ይቀጥለል
የስልጤ ድህራ ገፅ/silte page
like · · Share ቢላል መሐመድ !! የስልጤ በህልና አኗኗር ተማሪ !!