Henok Tibebu

Henok Tibebu no more

18/08/2026

በፊንፊኔ /አዲሳ'ባ በ1928 ዓ/ም በፋሽስት ጣሊያን ሰራዊት ብቻ ሳይሆን በመቶ ሽህ ባንዳ ጦር ጭምር የተወረረች ዘመን ነበር ፣ ለምሳሌ በዚህ ቪዲዬ የሚታየው 18 ሽህ የራስ ኃይሉ ባንዳ ጦር ሲሆን ይህን ወራሪ ባንዳ ወደ ፊንፊኔ ሲገባ በትራምፔት በማሲንቆ ጨዋታ በፊከራ ታጅቦ በፋሽስቱ ጀኔራል ጋሪቦልዲ የእንኳን ደህና መጣህ አቀባበል እንዲህ ተደርጎለት ነበር።

የኢትዮጵያ አርበኞች በተለይ ከ50 ሽ በላይ አርበኛ ሰራዊት ይመሩ የነበሩት ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ( አባቦራ) በፊንፊኔ የነበረው ከ100 ሽ በላይ በራስ ኃይሉ : በደጃዝማች ከበደ : በራስ ሙልጌታ : በደጃዝማች አያሌው ብሩ : በራስ ጌታቸው አባተ የሚመራው የባንዳ ጦር ከጣሊያን እኩል ጠራርገው እንደ ቃሪ አራግፈው ከፊንፊኔ ቢያባርሯቸው ኑሮ የባንዳ ሰፋሪ ጦር ፊንፊኔ ሰላሟን አይነሷትም ነበር ። በነገራች ላይ የሚያሳዝነው ታሪክ ሁሉም የእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎች ጀግኖች ሃገር ወዳድ አርበኞች ነፃ በአወጡት ሃገር ከነፃነት ማግስት ከፍተኛ ሹመት ተሰጥቷቸዋል።

የአዲስ አበባ (ፊንፊኔ) የአካባቢ ስሞች አመጣጥ የታሪክ፣ የባህል እና የከተማዋ ዕድገት ሂደት መግለጫ ነው። የቀደምት አካባቢዎች መጠሪያ ስሞች ከጊዜ በኋላ በአዳዲስ ስያሜዎች መተካታቸው ታሪ...
18/08/2026

የአዲስ አበባ (ፊንፊኔ) የአካባቢ ስሞች አመጣጥ የታሪክ፣ የባህል እና የከተማዋ ዕድገት ሂደት መግለጫ ነው። የቀደምት አካባቢዎች መጠሪያ ስሞች ከጊዜ በኋላ በአዳዲስ ስያሜዎች መተካታቸው ታሪካዊ እውነታና መሬት ላይ ያለ ሀቅ በመሆኑ ሊታመን እና ሊቀበሉት የሚገባ እውነታ ነው። እነዚህን መጠሪያዎች በተለያዩ መደቦች ከፋፍሎ በስርዓት ማየት ይቻላል፡

✅ የአዲስ አበባ የአካባቢ ስሞች አመጣጥ በምድብ

👉 ከባላባቶችና ታዋቂ ሰዎች ጋር በተያያዘ የተሰየሙ፡-
ራስ መኮንን
ራስ ብሩ
ራስ ሥዩም
ፊት አውራሪ ሀብተጊዮርጊስ
ደጃች ውቤ
ነጋድራስ ኃይለጊዮርጊስ
ደጃዝማች ዘውዱ
አባ ኮራን
ሸጎሌ (ሸኽ ሆጀሌ)

👉 ከብሔር ብሔረሰቦች ጋር በተያያዘ የተሰየሙ፡
ወሎ ሰፈር
አደሬ ሰፈር
ጎፋ
መንዝ
ሱማሌ ተራ

👉 ከሙያና ከሥራ ባልደረቦች ጋር በተያያዘ የተሰየሙ፡
ሠራተኛ ሰፈር
ዘበኛ ሰፈር
ኩባንያ ሰፈር
ጠብመንጃ ያዥ ሰፈር
ገዳም ሰፈር
ገባር ሰፈር
ሰረገላ ሰፈር
ሳቢ
ውኃ ስንቁ ሰፈር

👉 ከአጋጣሚዎች፣ ከክስተቶችና ከመሬት ምልክቶች ጋር በተያያዘ የተሰየሙ፡-
ሰባራ ባቡር
ዶሮ ማነቂያ
እሪ በከንቱ
አፍንጮ በር
አራት ኪሎ
አምስት ኪሎ
ስድስት ኪሎ
ጣሊያን ሰፈር
22 ማዞሪያ
ንፋስ ስልክ

👉 ከጣሊያን ወረራ ጋር በተያያዘ የወጡ የፋሺስት ስያሜዎች፡
መርካቶ
ፒያሳ
ፖፖላሬ
ካምቦሎጆ
ካዛንቺስ

👉 ከአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት ግንባታ ጋር በተያያዘ የተሰየሙ፡-
አራዳ ጊዮርጊስ
ዮሴፍ
ኪዳነ ምህረት
ቀራኒዮ መድኃኔዓለም
ቀጨኔ መድኃኔዓለም
የካ ሚካኤል
የረር ሥላሴ
ኡራኤል
ቦሌ መድኃኔዓለም

✅ የፊንፊኔ ቀደምት ስሟ ሲሆን በስሯ የነበሩት ቀደምት የአካባቢ ስያሜዎች እና አሁን ላይ የሚጠሩበት አዳዲስ ስሞች ከታች ማየት ትችላላችሁ በምስሉም ላይ ተመልከቱ።

~ መርካቶ . . . . . . . . . .አጋምሳ
~ ራስ ካሳ ሰፈር . . . . . . በዳ ኤጄርሳ
~ ጥቁር አንበሳ. . . . . . . .ባሮ ኮርማ
~ ፒያሳ. . . . . . .. . . . . .. .ቢርቢርሳ ጎሮ
~ ስድስት ኪሎ . . . . . .. . .ጨፌ አራራ
~ ሜክሲኮ . . . . . . .. . . . .ጨፌ አነኒ
~ ሳር ቤት. . . . .. . . . . .. . ጨልጨሊ
~ አራት ኪሎ . . .. . . . . .. . ዳለቲ
~ እንጦጦ . . .. . . . . .. . ዲልድላ አዱሬ
~ ሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ. . . .ለጋ ቀመሌ
~ ትልቁ ቤተመንግስት. . . . ቱሉ ዳለቲ
~ አስኮ . . . . . . . . .. . . . . ቂሌ
~ ተክለሃይማኖት. . . . . .. . ሱሉላ ጋርቢ
~ አዋሬ . . . . . .. . . . . .. . አዋሮ
~ ሩፋኤል. . . . . . . . .. . . . .አዳሚ
~ ቸርቸር ጎዳና . . .. . . . . .. . ወዴሳ

~ ሀና ማርያም . . .. . . . . .. ቱሉ ኤጄርሳ
~ ቅዱስ ዮሴፍ/አዲስ ሰፈር . .... ሉሜ
~ ቡና ቦርድ ላፍቶ . . . ...... .ቱም ቱም
~ ጎፋ . . . .. . . .... . ...... . ቱሉ Dheርቱ
~ ፈረንሳይ ለጋሲዎን . . . . . . . . .ቡርቃ ኤጄርሳ
~ ልደታ . . . . . . . . . . . . .ጫፌ ሙዳ
~ ዉጭ ጉዳይ . . . . . . . . . Dhaካ አራራ
~ ጎተራ/ወሎ ሰፈር. . . . .ዶሎ ቡዴና
~ ግንፍሌ . . . . . . . .. . . . Dhuሙጋ
~ አዲስ ከተማ . . . . . . . . . ጎልባ
~ ቃጫ ፋብሪካ . . . . . . . . . .ሀረዋ
~ ጉርድ ሾላ . . . . . . . . . . . . .ሀርቡ
~ እስጢፋኖስ . . . . . . . . . ሁሉቃ ኮርማ
~ ብሄረ ፅጌ. . . . . . . . . . . . .ጃጃ

~ በላይ ዘለቀ መንገድ . . . . . . .ካራ ቆርጢ
~ የካ ሚካኤል . . . . . . . . . . .ቡርቃ ቆሪቻ
~ አየር ጤና . . . . . . . .. . . . . . ማደሮ
~ ባምቢስ . . . . . . . . . . . . . . .መልካ አቦሼ
~ አጣና ተራ . . . . . . . . . . . . . . .ጣሮ
~ ጨርቆስ ቤተክርስቲያ . . . . . . . . . .ሃዳ አማ(ጎልቦ)
~ ቄራ . . . . . . . . . . .. . . . . . . .ጉለሌ በdhaሶ
~ ጃን ሜዳ . . . . . . . . . . . . . . .ሁሩፋ ቦንቢ
~ ካሳንቺስ . . . . . . .. . . . . . . . . . ቃርሳ
~ ንፋስ ስልክ. . . . . . . . . . . . . . . ሮባ

~ 22 ማዞሪያ . . . . . . .. . . . . .. . ዶቃ ቦራ
~ ቀጨኔ. . . . . . . . . . . . . . . . . ዶቢ
~ ለገሀር . . . . . . . . . . . . . . . . . ለገሀሬ
~ መካኒሳ . . . . . .. . . . . .. . ባከኒሳ
~ ቤተል . . . . .. . . . . .. . . . .ቦኬ
~ አቃቂ . . . . . .. . . . . .. . ሀቃቂ
~ ፍልውሃ . . . . . .. . . . . .. ሆራ ፊንፊኔ
~ ቃሊቲ . . . . . . . .. . . . . .. . ቃሉ

14/08/2026

ዛሬም የተለየ ነገር አልተፈጠረም፤ የ35 ዓመቱ ጤናማ አብሮነት ይቀጥላል!
"አዲስ አበባን በተመለከተ አዲስ አጀንዳ መጣ" እያሉ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሞክሩ አካላት አንድ መካድ የማይችሉት ሀቅ አለ። ይኸውም አዲስ አበባ ላለፉት 35 ዓመታት የኦሮሚያ ክልል መንግስት መቀመጫ ሆና ቆይታለች የሚለው እውነታ ነው። ታዲያ ዛሬ የተለየ ነገር ምን ተፈጠረ?
ሕገ-መንግስቱ "ልዩ ጥቅም ያገኛል" ብሎ ደንግጎ በነበረባቸው በእነዚህ ረጅም ዓመታት ውስጥ እንኳ፣ ክልሉ የሌላውን ኢትዮጵያዊ መብት የሚጋፋ የተለየ ጥቅም ይገባኛል ብሎ የጠየቀውም ሆነ ያገኘው ነገር የለም። አዲስ አበባ ሁሌም የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መዲና፣ የፌዴራል ማዕከል፣ እንዲሁም የውበትና የልማት ተምሳሌት ሆና ነው የኖረችው።
የአሁኑ የሕግ ማዕቀፍ ምክረ-ሐሳብ የሚያደርገው ይህንኑ በተግባር ሲሰራበት የነበረውን ተፈጥሯዊ ቁርኝት፣ ይበልጥ ግልጽ በሆነ የ"ጋራ ተጠቃሚነት" መርህ ማጠናከር ብቻ ነው። የመኖሪያ ቤት፣ የውሃ፣ የመንገድና የጸጥታ ጉዳዮችን በጋራ ማስተዳደር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽ ለሆኑት ለከተማዋና ለክልሉ የጋራ ብልጽግና ወሳኝ ነው። የ35 ዓመቱ አብሮነታችን ዛሬም በማይነጣጠል የጋራ ተጠቃሚነት ይቀጥላል እንጂ አዲስ የተፈጠረ ስጋት የለም!

ኦነግ ህወሓትን አስጠነቀቀ፣ የህወሓት ተስፋ መነመነ፣ የቀራቸው አንድ ኢሕአፓ ብቻ ነው
22/07/2026

ኦነግ ህወሓትን አስጠነቀቀ፣ የህወሓት ተስፋ መነመነ፣ የቀራቸው አንድ ኢሕአፓ ብቻ ነው

ተሰናባቹ የፓርላማ አባል 5ዓመታትን የረባ ያልረባ ጥያቄዎችን በማንሳት የእለት ጭብጨባ ፈላጊውና የጽንፈኞች መጠቀሚያ ሆኖ የቆየው ደሳለኝ ጫኔ እነሆ በጩኸትና በለቅሶ አንዳች ለውጥ ማምጣት ሳ...
07/07/2026

ተሰናባቹ የፓርላማ አባል 5ዓመታትን የረባ ያልረባ ጥያቄዎችን በማንሳት የእለት ጭብጨባ ፈላጊውና የጽንፈኞች መጠቀሚያ ሆኖ የቆየው ደሳለኝ ጫኔ እነሆ በጩኸትና በለቅሶ አንዳች ለውጥ ማምጣት ሳይችል ቀርቶ 5ዓመታትን ካባከነ በኋላ በመጨረሻ የመሰናበቻ ግዜው ጸጉሩን አስተክሎ ለውጡ ጸጉር ማስተከል ብቻ መሆኑን አሳይቶናል! መክሸፍ እንደ ደሳለኝ ማለት ይህን ግዜ ነው! ሀገር የሚለውጥ ስራ ለመስራት እንጂ ፀጉር ለማስተከልኮ ፓርላማ መግባትም አያስፈልግም ነበር፡፡ ዮኒ ማኛም አስተክሏልና!😀🥹

05/07/2026

ፈጣሪ የሰጠንን ቀበና “ሰዉ “ አጠፋዉ ፤ ይህ የተፈጥሮ ስጦታ መጥፋት ቁጭት ያደረበት “ሰዉ “ ደግሞ ቀበናን ዳግም እንደ አዲስ እንዲወለድ አደረገዉ።

29/04/2026

የሀሳብ ፖለቲካ!

28/04/2026

አዲስ አበባ ውብ አበባ!

ለከተማነትት የማይመጥኑ የነበሩ አካባቢዎችን ወደ ዘመናዊነት ያሸጋገረች ከተማቀደም ሲል በአሳፋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩት እንደ ፒያሳ፣ ካዛንችስ፣ አዋሬ እና እሪ በከንቱ ያሉ ሰፈሮች ዛሬ ታሪካ...
27/04/2026

ለከተማነትት የማይመጥኑ የነበሩ አካባቢዎችን ወደ ዘመናዊነት ያሸጋገረች ከተማ

ቀደም ሲል በአሳፋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩት እንደ ፒያሳ፣ ካዛንችስ፣ አዋሬ እና እሪ በከንቱ ያሉ ሰፈሮች ዛሬ ታሪካቸውን አድሰው ለነዋሪዎቻቸው ምቹና ለዓይን ማራኪ ወደሆኑ የሥልጣኔ ማዕከላትነት ተቀይረዋል።

አሁን ደግሞ ይህ ታላቅ የለውጥ ማዕበል ወደ ቅጠል ተራ ደርሷል፤ በዚያም በሦስት ወራት አጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ 500 ቤቶች ተገንብተው ለነዋሪዎች ሊተላለፉ መሆኑን ስንሰማ ተግባሩ እጅግ የሚያስደንቅና የከተማዋን ብሩህ ተስፋ የሚያበስር ሆኖ እናገኘዋለን።

ይህ ተነሳሽነት ቅጠል ተራንም ከድሮው የተራ አኗኗር ታሪክ አውጥቶ የዘመናዊነት አካል እንደሚያደርገውና በታቀደለት ጊዜም ስኬታማ እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለን።

ፕሮጄክቱ ሲጠናቀቅ ከ20ሺ በላይ ወገኖቻችን የዘመናዊ መኖርያ ቤት ባለቤት ይሆናሉ።
26/04/2026

ፕሮጄክቱ ሲጠናቀቅ ከ20ሺ በላይ ወገኖቻችን የዘመናዊ መኖርያ ቤት ባለቤት ይሆናሉ።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Henok Tibebu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Henok Tibebu:

Shortcuts

Share